በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹“ለሊሁ ቀባዒ ወተቀባዒ ወለሊሁ ቅብዕ…ራሱ አክባሪ ራሱ ከባሪ ራሱ ክብር ነዉ” የሚለዉን ቃል ከሚከተሉት ቃላት ጋር አስማምታችሁ ተርጉሙልን እስኪ?
[መላሽ ባይኖርም እኛ ጠያቂዎች ግን አለን]
ሀ‹‹‹‹‹‹ “ወበከመ ለአብ ቦቱ ሕይወት ኀቤሁ ለወልድኒ ወሀቦ ሕይወተ ከመ ይኩን ሕይወት ኀቤሁ….. ለአብ ከእርሱ ዘንድ ሕይወት እንዳለው ሕይወት ከእርሱ ይሆን ዘንድ ለወልድም ሰጠው፡፡” (ዮሐ.5፣26-27)፡፡
ለ‹‹‹‹‹‹ “ዘተሠርዐ ወልደ አግዚአብሔር ቅብዐ መንፈስ ቅዱስ…..በመንፈስ ቅዱስ ቅብዐት
የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ተባለ፡፡” (ተረፈ ቄርሎስ ምቅዋም 8 ገጽ 22)
ሐ‹‹‹‹‹‹‹ “ወለብዕለ ህላዌ መለኮት ንሕነ ንሬእዮ በልዕልና ስብሐቲሁ ዘውእቱ ላዕለ ኵሎሙ ፍጡራን ወአምጣነ ንዴተ ትስብእት ዘነሥአ ይትበሀል ከመ ውእቱ ተሰብሐ እምአብ፤ ወዝንቱ ዓዲ ይትሜሰል ዘተብህለ ከመ ውእቱ ነሥአ ስብሐተ ወመንግስተ ሥልጠነ ላዕለ ኵሉ ነሢእሰ ይትበሀል በእንተ ዐቅመ ትስብእቱ ወንሕነ ነአምር ከመ ውእቱ እግዚአ ስብሐት በመለኮቱ ወይነብር ምስለ አብ ወአልቦቱ ሕጸጽ በምንትኒ እምልዕልና ስብሐተ ወላዲሁ ወኢእምነ ግብሩ ዘስንዕው በህላዌ መለኮቱ ዝ ወእተ አምሳል ወበተአምኖቱ ንከውን ዕሩያነ…….
የባሕርየ መለኮትን ክብር ከፍጡራን ሁሉ በራቀ በልዑል ጌትነቱ እንዳለ እኛ እናውቀዋለን፤ የተዋሐደው ሥጋ ክብርን የሚሻ በመሆኑ መጠን ከአብ ክብርን ገንዘብ አደገ ይባላል፤ ይህም ጌትነትን መንግሥትን በሁሉ ላይ ሥልጣንን እርሱ ገንዘብ እንዳደረገ የተነገረውን ይመስላል፤ ክብርን ገንዘብ አደረገ መባሉ ሰው ስለመሆኑ ይነገራል፤ በመለኮቱ የክብር ባለቤት እንደሆነ፤ ከአብ ጋርም እኩል ትክክል እንደሆነ ከአባቱ ልዑል ጌትነት፤ በባሕርየ መለኮቱም አንድ ከሚሆንበት ግብሩ በምንም በምን ሕጸጽ እንደሌለበት እናውቃለን፤ አምነን አንድ የምንሆንበት ትምህርት ይህ ነው፡፡ (ዳን. 7፣ 13-255፤ ዮሐ. 12፣18፤17፣1፣-6)፣ (ሃአ ም. 79፣75)