ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም (በ ፫፻፶፩ ዓ/ም ተመሰረተች)
![]() |
በደጉ ዮሐንስ የተሰራው ዕቃ ቤት |
![]() |
ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም [በ፫፻፶፩ ዓ.ም ተመሰረተች] |
![]() |
የአብነት ትምህርት ቤት መማርያ ጎጆዎች |
ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናዉጋ ወረዳ በወረዳዉ ዋና ከተማ ደብረወርቅ ለእይታ በሚማርክ ቦታ ላይ ትገኛለች፡፡ ቀደም ሲል "ምስካበ ቅዱሳን" የምትባለዉ ገዳሟ በ351 ዓ/ም እንደተመሰረተች ይነገራል፡፡በኋላም በዮዲት ጉዲት ተቃጥላለች፡፡በ1372 ዓ/ም በቀዳማዊ አጼ ዳዊት እንደገና ታንጻ በድጋሜ በ1553 በአጼ ገላዉድዮስ በኖራ ወብ ሆና ታድሳለች፡፡
በገዳሟ ከ711 በላይ ልዩ ልዩ ንዋየ ቅድሳት ይገኛሉ፡፡ለአብነት ሉቋስ የሳላት የወይኒቱ ማርያም ስዕል ፣ከአልማዝና ወርቅ የተሠሩ የአጼ ዮሃንስ ዘዉዶች፣የንግስት ዘዉዲቱ የወርቅ ካባ፣የከሳቴ ሰላማ ቀሚስ ፣በዓይነት በርካታ የሆኑ የብራና መጽሃፍትና ሌሎችም ቅርሶች በገዳሟ ይገኛሉ፡፡ገዳሟን ትልልቅና እድሜ ጠገብ የጽድ ዛፎች አስዉበዋታል፡፡ደ/ወርቅ ከተማን ከላይ ሆነዉ እንዲያዩዋት በሚያመች ከፍ ያለ ቦታ ላይም ታንጻለች፡፡በዚህ ገዳም የአምስቱ ጉባኤያት ትምህርት ማለትም የድጓ፣የአቋቋም፣የቅኔ፣የቅዳሴና፣የመጽሃፍት ትምህርቶች በበቁ አባቶች ይሰጣል፡፡
የአብነት ትምህርት ቤቱ ዉሉደ አርከስሉስ በመባል ይጠራል፡፡ድንቅና ሀገር በቀል እዉቀቶቻችን ነፍስ ከሚዘራባቸዉ ቅዱስ አድባራት መካከል ደብረ ወርቅ ማርያም አንዷ ናት፡፡ገዳሟ እጅግ በሚያምር የኪነ ህንጻ ጥበብ የተሠራ ጥንታዊ እቃ ቤት ያላት ሲሆን ዘመናዊ ሙዝየም በመገንባት በዞኑ ቀዳሚ ናት ፡፡ከምንም በላይ የሚደንቀዉ ንዋየ ቅድሳቱ የሚጠበቀዉ በንብና ቁጥራቸዉ በማይታወቅ ነብሮች መሆኑ ነዉ፡፡ንቦችን በማንኛዉም ጊዜ በአይን ማየት የሚቻል ሲሆን ነብሮች ጣራዉ ላይ እንደሚኖሩና ሰዉ እንደማይተናኮሉ አባቶች ይናራሉ፡፡
የገዳሟ አመታዊ ክብረ በዓል መስከረም 18 እና ጥር 21 /ቅዱስ ሉቋስ የሳላት ወይኑት ትወጣለች/ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ይከበራል፡፡ይምጡና ይህችን ባለብዙ ታሪክ የሆነችዉን ገዳም ይጎብኙ፡፡
የገዳሟ አመታዊ ክብረ በዓል መስከረም 18 እና ጥር 21 /ቅዱስ ሉቋስ የሳላት ወይኑት ትወጣለች/ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ይከበራል፡፡ይምጡና ይህችን ባለብዙ ታሪክ የሆነችዉን ገዳም ይጎብኙ፡፡
No comments:
Post a Comment