፩፦ በምስጢረ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ነስዓ ተወክፈ አለ የለም?
ከሌለ ነስአ ብሎ የባህሪ የሚል ወመንፈስ ቅዱስ ይነስእእምኔሆሙ በከመ ይቤ እግዚእነ እስመ እምዚአየ ይነስ - መንፈስ ቅዱስ ከአብ ልብነትን ከወልድ ቃልነትን ገንዘብ ያደርጋልና ሲል እርሱ ራሱ ወልድም ቃልነት ከእኔ አድርጓል ተናግራል ሃ.አ ፫:፷ ለምን አለ።
★ተወክፈ ብሎ የባህሪ እንዲሆን አመ ተወክፍየ አግዚአብሔር አብ መንግስቶ - እግዚአብሔር አብ መንግስቱን እጀ ባደረገ ጊዜ፩ቆሮ.፲፭፥፳፬
ዳግመኛም ዘይትወከፍ ፀሎተ ንፁሐን=የንጹሐንን ፀሎት የሚቀበል መፅ.ኪዳን
★ኃደረ የባህሪ የሚል ዘየኃድር ውስተ ብርሃን ሀበ አልቦ ዘይቀርቦ - የሚቀርበው ብርሃን በሌለ ውስጥ የሚኖር እርሱ ነው። ወዳ.ማ.ዘሰሉ.
ዳገመኛም አም ውስተ ዛቲ ደመና ብርሃን ኢትትረከብ ኃበ የኃድር እግዚአብሔር - ምንምብርሃን በሌለባትደመና እግዚአብሔር ድርባታል። አረ.መንፈ.ደር፮ ይህ ሁሉ ለምን ተፃፈ።
፪፦እግዚአብሔር አብ ወልድን በሰውነቱ አልወለድውም ለምትሉ ከሀዲዎች በሙሉ ፡-
✿የሐን.አፈወርቅ ድር ፱ወበእንተዝ ነገረ ቃል ትንቢት ዘሀለወ ይኩን - ስለዚህ ነገር ይደረግ ዘንድ ያለው ነብዩ የተናገረውን ነገር ወልድየ አንተ ወአነየም ወለድኩከ እንዲህ አለ :እመቦ ዘይብል ዝኑ ይትብሀል በእንተ ወልድየ - ወልድየ አንተ ያለውን አንሳው። ወአነዮም ወለድኩከ ያለው ለሹመቱ ይናገራልን የሚል ሰው ቢኖር ንብሎ እወ ይትብሀል አወ ለሹመቱ ይናገርለታል ብለን እንመልስለታለን። ሐተታ ወአነዮም ወለድኩከ መወለዱን ያስረዳል ያስረዳል እንጅ መሾሙን ያስረዳልን ፡የልጅነቱን ለሹመቱ ስለምን ምስክር አደረገው ቢሉ ቢወልደው እንጅ ሾመው። ወአነዮም ወለድኩከን አይሻውም። ወልድየ አንተ ያለው ስለ ባህሪ ልጅነቱ ይናገራል የሚል ሰው ቢኖር አውን ስለ ባህሪ ልጅነቱ ይናገራል ብለን እንመልስለታለን። አንድም ወአነዮምን ይሸዋል የባህሪ ልጁን እንደገና በስጋ የባህሪ ልጅ አድርጎታልና።
✿መጽሐፈ.ምስ.፫፥፵፮ ድንግልኒ ወለደት ዘኢዚአሃ መለኮት በዘዚአሃ ሥጋ ምስለ በዚአሃ ስጋዌ - ድንግልም በእርሷ በተገባ ስጋዌ የእርሷ በሆነ ስጋ የእርሷ ያልሆነውን መለኮት ወለደችው። አብኒ ወለደ ዘኢዚአሁ ሥጋ በዘዚአሁ መለኮት ምስለ ዘዚአሁ ኃይል ዘህሉና አምላክ - አብም የባህሪው ያልሆነውን ስጋ የባህሪው ከሆነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የርሱ በሆነ መለኮት ወለደ። ታዲያ አብ በሰወነቱ ወለደው አለ እንጅ አልወለደውም አለ?
እውነት እላቹሀለው አብ በእርሱ በተገባ መለኮት የእርሱ ያልተገባ ስጋን ወለደው አለን አባጊዮርጊስ ዘጋስጫ። ስለዚህ በሰውነቱ ቢወልደው እንጅ ካልወለደው በስጋው ለምን ልጄ ብሎ ጠራው? ግዕዙን በደንብ ማንበብ ተገቢ ነው።
✿በእንተ ወልድ ዘተወልደ ሲል እምቅድመ አለም የተወለደውን ተናገረ። ወመፅአ እምዘርአ ዳዊት በስጋ ብሎ ደግሞ ከእመቤታችን የተወለደውን ተናገረ።ወአርአየ ከመ ወልደ እግዚአብሐሔር ውእቱ በኃይለ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ በስውነቱ የወለደውን ተናገረ።ጳው.ትርጓ.ዕብ፩፥፪
✿ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው።ማቴ ፫፥፲፫ይ እዚህ ለይ የምንረዳው ነገር ክርስቶስ ከእመቤታችን ያለ አባት ተወለደ፡ በ30 አመቱ "በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ"እንዲል መጽ. በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። ስለዚህ አብ በአባትነት ግብሩ በማህፀን ካልወለደው ልጄ ብሎ ለምን ጠራው? እውነት አላችኋለዉ ቃለ ለተዋሀደው ስጋ አብ በአባትነት ግብሩ በማህጸን ቢወልደው መንፈስ ቅዱስ በሕይወትነት ግብሩ እስትንፋስ(ሕይወት) ቢሆነው በመለኮቱ ያለ እናት የወለደውን ልጁ ዛሬ በማህጸን ስለወለደው የምወደዉ ልጄ ይህ ነው ብሎ ተናገረ። እንግዲህ በማህፀን ካልወለደው ለምን ልጄ ብለ ጠራው?
፫፦በሃይማኖት አበው ውስጥ ሁለት ቦታ ላይ አጣመው የተረጎሙት ሊቆች ተብየዎቾ እንይው።
ሀ፦ ወከማሁ ዓዲ አበዊነ ሐዋርያት ሶበ ሰገዱ ለስጋ ቅዱስ ሰገዱ ለእግዚአብሔር ቃል። ሃ.አበ.ዘአቡሊዲስ ፵፩ - ዳግመኛም አባቶቻችን ሐዋርያት በተዋህዶ ለከበረ ስጋ በሰገዱ ጊዜ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቃል ሰገዱ። በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ የታተመው ፲፱፻፺፩ እዚህ ላይ ዋናው ሀሳብ "ለስጋ ቅዱስ" የምትለዋን ሐረግ ነው። ይህች ቃል "በተዋህዶ ለከበረ ስጋ"በሚል ተተርጉሟል። በጣም የሚገርመው ነገር የሌለው ግስ ከየት አምጥተው እንዳስገቡት ነው። እስኪ ጎበዝ አይን ይፍረድ ስለእግዚአብሔር ብላችሁ"ተዋህዶ "የሚለውን ግስ አውጡልኝ።
"ወከማሁ ዓዲ አበዊነ ሐዋርያት ሶበ ሰገዱ ለስጋ ቅዱስ ሰገዱ ለእግዚአብሔር ቃል"። የኛ ሙህሮች "ለስጋ ቅዱስ" የምትለዋን ሐረግ "በተዋህዶ ለከበረ
ስጋ"ብለው ተረጉመውታል። መፅሐፍ ይፍረድ ነው እንጅ ሌላ ምን ይባላል ወገኖቸ። ሰው የሆነ ሁሉ ያስተውልመጽሐፍ እንዲህ አለ ለስጋ ፍቃዳቸው እንዲመች አድርገው ተረጎሙት እንዲ.ወንጌ.

ለ፦ ወከመዝ ነአምሮ ተቀብአ ከመ ስርአተ ትስብእቱ ወለሊሁ ውእቱ ዘይቀብእ ርእሶ በመንፈሱ ባሕቲቱ ሃ.አ ፻፳፬፥፲፬=በአባ ጳውሎስ ጊዜ የታተመው፡ሰው እንደመሆኑ በተዋህዶ እንደከበረ እናውቃለን፡ግን በገዛ ስልጣኑራሱን የሚያከብር እርሱ ነው ብለው አይኑን አሳውረው ተርጉመውታል።ወገኖቼ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ"ከመለሊሁ ተቀብዓ ከመ ስርአተ ትስብእቱ"ከሚለው ተዋህዶ የሚል ግስ ፈልጉልኝ።
"ወለሊሁ ውእቱ ዘይቀብዕ ርእሶ በመንፈስ ባሕቲቱ"የሚለውን ደግሞ ግንበገዛ ስልጣኑራሱን የሚያከብር እርሱ ነው ብለው ተረጎሙት :የተቀባን አንቀጽ ለመሸሽ ሲሉ እንዲህ እያደረጉ ይተረጉሙታል። እስኪ በገዛ ስልጣኑ ሲሉ ይህ ስልጣን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ስልጣን ነውን?ወይስ እንዴት ነው? ስላሴ በስልጣን አንድ እንደሆኑ የምናምንባት ሀይማኖት ናት።ይህ ስልጣን አከላዊ ነው ዝረው? መልስ የሚሰጠኝ እፈልጋለሁ። አዎ ከዚህ ላይ በገንዛ ስልጣኑ ብለው የተረጎሙት "በመንፈሱ" የሚለውን ቃል ነው።
የሚገርመው ነገር ወንድሞቸ እውነት እላችሁኀለሁ "በመንፈሱ"የሚለው ቃል የአብ እና የወልድ ሕይወታቸው መንፈስ ቅዱስን ይወክላል። እንዲህ ካልሆነ ግን ለወልድ ብቻ"በገዛ ስልጣኑ"ተብሎ የተለየ ስልጣን አለው ብሎ ደፍሮ መናገር ከመናፍቁ አርጌስ ጋር መተባበር ይሆናል። በከመ ይቤ -እንዲህም እንዳለ ወልድ እምአብ ወኢይትኤረዩ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ- ወልድ ከአብ ያንሳል፡መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል ብሎ መካድ ማለትነው።ሎቱ ስብሐት።
✿የብርሐናው<የአስመራው እትም ግን እንድህ ብሎ ይተረጉመዋል።

ሐ፦ ተቀብዓ ፦ተወሐደ ብለው ተርጉመውታል ። ያሬ.ግስ እንደምሳሌ በዘተሰብዓ ተቀብአ ይገርማል የተቀብአን አንቀፅ ለመሸሽ ሲሉ የከፍ መንገድ ሰጠሙ። አንድም ተሰብአ ማለት ሰው ሆነ ማለት ነው። ሰውሆነ ማለት ደግሞ አካለ ቃልና ትስብእት አንድ ሆነው የተወሀዱበት ነው ማለት ነው። ስለዚህ ተሰብአም ተወሀደ ማለትነው።ስለዚህ ወገኖቸ "በዘተሰብአ ተቀብዓ" የሚለው "ስለተወሀደ ተወሀደ"ይባላል ጎበዝ አይን ያወጣ ክህደት
ይገርማል።
ቄር.ድ፫መለኮትሰ ኢተቀባ - በመለኮቱስ አይቀባም አለ። ስለዚህወገኖቸ እውትማ የተቀብአ ትርጉም ተወሐደ ከሆነ በመለኮቱ አልተወሀደም ብለው አረፋት።ሎቱ ስብሐት።የከፍ ክህደትውስጥ ገብተው አረፍ።
ስለዚህ በምንም ተአምር ተቀብአ-ተወሀደ ተብሎ አይተረጎምም።
መ፦ በተዋህዶ ከበረ ተዓቅቦን አየይዞ ተዋህዶ አገናዛቢ ነውና ምን ማለት ነው?




"መኑ ዘይክል ይትናገር ምስለ ኢየአምሩ ህገ እምነቶሙ ወይፈልጡ ከዊነ ስስት፡ የሐይማኖታቸውን ስራ ከማያወቁ ሰዋች ጋር መከራከር የሚቻለው ማን ነው ስስት ኃጢያት እንደሆነ የማያውቁ።እን.ዮሐ.አፈ.ድ ፱ ።"
መንፈስ ቅዱስን የምትሳደቡ ከአብ ከወልድ ስልጣን የለያችሁት ተመለሱ "ኢይፈቅድ ሞቶ ለኃጥዕ አላ ግብአቱ ኃበ ንስሃ እንዲ.ቅዱ.ያሬ የእናንተን በደል አያስብባቹህም ወደ ንስሃ ተመለሱ እንጅ ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመነአምልኮ ስብሐት ለማሪያም እመአምላክ እግዚትነ ወመድሐኒትነ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕጸ መድኃኒትነ ኃይልነ ወፀወንነ።
ምንት ንብል በዘኢይበጽሕ ሕሊናነ…..ሕሊናችን መርምሮ ለማይደርስበት ለዚህ ምሥጢር ምን እንላለን ፤ እጽብ ከማለት ዉጭ
ReplyDelete