በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
[መላሽ ባይኖርም እኛ ጠያቂዎች ግን አለን]
ሀ‹‹‹‹‹‹ “ወበከመ ለአብ ቦቱ ሕይወት ኀቤሁ ለወልድኒ ወሀቦ ሕይወተ ከመ ይኩን ሕይወት ኀቤሁ….. ለአብ ከእርሱ ዘንድ ሕይወት እንዳለው ሕይወት ከእርሱ ይሆን ዘንድ ለወልድም ሰጠው፡፡” (ዮሐ.5፣26-27)፡፡
ለ‹‹‹‹‹‹ “ዘተሠርዐ ወልደ አግዚአብሔር ቅብዐ መንፈስ ቅዱስ…..በመንፈስ ቅዱስ ቅብዐት
የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ተባለ፡፡” (ተረፈ ቄርሎስ ምቅዋም 8 ገጽ 22)
ሐ‹‹‹‹‹‹‹ “ወለብዕለ ህላዌ መለኮት ንሕነ ንሬእዮ በልዕልና ስብሐቲሁ ዘውእቱ ላዕለ ኵሎሙ ፍጡራን ወአምጣነ ንዴተ ትስብእት ዘነሥአ ይትበሀል ከመ ውእቱ ተሰብሐ እምአብ፤ ወዝንቱ ዓዲ ይትሜሰል ዘተብህለ ከመ ውእቱ ነሥአ ስብሐተ ወመንግስተ ሥልጠነ ላዕለ ኵሉ ነሢእሰ ይትበሀል በእንተ ዐቅመ ትስብእቱ ወንሕነ ነአምር ከመ ውእቱ እግዚአ ስብሐት በመለኮቱ ወይነብር ምስለ አብ ወአልቦቱ ሕጸጽ በምንትኒ እምልዕልና ስብሐተ ወላዲሁ ወኢእምነ ግብሩ ዘስንዕው በህላዌ መለኮቱ ዝ ወእተ አምሳል ወበተአምኖቱ ንከውን ዕሩያነ…….
የባሕርየ መለኮትን ክብር ከፍጡራን ሁሉ በራቀ በልዑል ጌትነቱ እንዳለ እኛ እናውቀዋለን፤ የተዋሐደው ሥጋ ክብርን የሚሻ በመሆኑ መጠን ከአብ ክብርን ገንዘብ አደገ ይባላል፤ ይህም ጌትነትን መንግሥትን በሁሉ ላይ ሥልጣንን እርሱ ገንዘብ እንዳደረገ የተነገረውን ይመስላል፤ ክብርን ገንዘብ አደረገ መባሉ ሰው ስለመሆኑ ይነገራል፤ በመለኮቱ የክብር ባለቤት እንደሆነ፤ ከአብ ጋርም እኩል ትክክል እንደሆነ ከአባቱ ልዑል ጌትነት፤ በባሕርየ መለኮቱም አንድ ከሚሆንበት ግብሩ በምንም በምን ሕጸጽ እንደሌለበት እናውቃለን፤ አምነን አንድ የምንሆንበት ትምህርት ይህ ነው፡፡ (ዳን. 7፣ 13-255፤ ዮሐ. 12፣18፤17፣1፣-6)፣ (ሃአ ም. 79፣75)
መ‹‹‹‹‹‹‹ አማን አንገለጉ በዛቲ ሀገር ላዕለ ቅዱስ ወልድከ ኢየሱስ ዘቀባእካሁ…በዚህች አገር ወልድየ ፍቁርየ ዘኃረይኩ ባልከዉ በልጅህ ላይ ለምን ዶለቱ”ሐዋ4፡27
ሠ‹‹‹‹ “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባዉ”ሐዋ10፡38
ረ‹‹‹‹‹ “አብሰ ያፈቅር ወልዶ ወኩሎ ኩነኔሁ አወፈዮ ዉስተ እዴሁ….አብ ልጁን ይወደዋልና ሁሉን በእጁ ጭብጥ በእግሩ እርግጥ አድርጎ አስገዛለት”ዮሐ3፡35
ሰ‹‹‹‹‹ “ወእምዝ ተቀብዓ ቅብዓ ትፍስሕት ዘክርስቶስ ዘቦቱ ይነሥዑ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ ኩሎሙ አሕዛብ፡፡
ይህስ ቅብዓት ምንድን ነው? ቢሉ ቀድሞ ጌታችን ከባህርይ አባቱ በባህርይ ልጅነት ተወልዶ የባህርይ ልጅነት ያገኘበት መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ዛሬ ህዝቡ አሕዛቡ ከሥላሴ የፀጋ ልጅነትን የሚወለዱበት ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ይህ ነው፡፡”ቅዱስ ኢጲፋንዮስ ( ጽፈ አክሲማሮስ ዘሰሉስ ክፍል 2፡18)
ቀ‹‹‹‹‹‹ “ወአዉሥአ ወይቤሎሙ አንትሙ መነ ትብሉኒ…እናንተ ማን ትሉኛላችሁ፡፡ ወተሰጠዎ ጴጥሮስ.. ጴጥሮስ መለሰ አንተ ዉእቱ መሢሑ ለእግዚአብሔር…አንተ ከእግዚአብሔር የተቀባሕ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ አለዉ”ዮሐ9፡20
በ‹‹‹‹‹‹ “ወይእዜኒ አባ ሰብሐኒ በሥብሐትየ ዘሀሎ ኀቤከ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም…አባት ሆይ አሁንም ዓለም ሳይፈጠር ካንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ አክብረኝ”ዮሐ17፡5
ተ‹‹‹‹‹‹“ነሥአ መንፈሰ በትስብእቱ ወሶጦ ላእለ ካልአን ወወሀቦሙ እምፍጻሜሁ…ሰዉ በመሆኑ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ በሌሎችም አሳደረዉ ከፍጹም ሀብቱም ሰጣቸዉ”ሃ.አበዉ ዘቅዱስ ቄርሎስ 80፡2
ነ‹‹‹‹‹‹‹‹ ““እስመ መንፈስ ዘዚአየ በህላዌ ለሊሁ ኃደረ ላእሌየ በእንተዝ ወለምንትኑ ተሰመይኩ መሲሐ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ኮንኩ ሰብአ…..በባሕሪዬ ገንዘቤ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በሕልዉናየ ጸና ሰዉ ብሆን ነዉ እንጅ ያለዚያ ስለምን ክርስቶስ ተባልኩ” ሃ. አበዉ ዘቅዱስ ሳዊሮስ 87፡17ይህንን ከኢሳይያስ 61፡1 እና ሉቃስ4፡18 ጋር አስማምታችሁ ብትተረጉሙልን?
ኀ‹‹‹‹‹‹ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ ቅዱስ ወረሠዮ ቅዱሰ ወማኅየዌ…በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት የአዳምን ባህርይ ያከበረዉ የባሕርይ አምላክ ያደረገዉ እርሱ ነዉ” ሃ.አበዉ ዘአልመስጦአግአያ 2፡5
2ኛ.‹‹‹‹‹‹ “አፍቀርከ ጽድቀ ወአመጻ ጸላእከ፤በእንተዝ ቀብዓከ ቅብዓ ትፍስሕት እምእለ ከማከ…ጽድቅን ወደድክ አመጻንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ የሚገኝ የደስታ ዘይትን ቀባህ”መዝ44፡7…..የሚለዉን ቃል
ሀ‹‹‹‹ ቀብዓከን አዋሐደህ ብላች ለመተርጎም መነሻችሁ ምንድንነዉ?አፈወርቅ ዮሐንስ ዘይተ ፍሥሐ፣ ቅዱስ ጳዉሎስ በእብ1፡9 ዘይሄይስ እም እሊአሆሙ ብሎ ሲወስደዉ ቅዱስ ቄርሎስ ደግሞ ቅብዓ ነከራ ብሎ ሲተረጉመዉ፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ደግሞ ይህ ቅብዓት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በእሁድ ክፍል 4፡1 እና በማክሰኞ2፡18 ላይ መሥክረዋል እናተ ግን ልዩ ተዋሕዶ ብላችሁ ስትተረጉሙት አባታችሁ ማን ነዉ?ማለት ማን አስተማራችሁ?
ለ‹‹‹‹‹‹ ሲቀጥል በዚሁ ኃይለቃል(በመዝ44፡7)አምላክነትህ ሰዉነትህን ቀባህ እላችሁ አምላክነትን ለቃል ብቻ ለይታችሁ ሰጥታችሁ ወልድን በአካለ ትስብዕት (በሥጋ) አምላክአይደለም በሚል ንግግራችሁ ለመነጣጠል እንደምን ደፈራችሁ?
3ኛ‹‹‹‹‹‹ቅድስት ሥላሴ በሥልጣን በመለኮት፣በአምላክነት ይህንን በመሳሰለዉ ሁሉ አንድ ናቸዉ፡፡ እንዲያዉም አንዱ ከአንዱ ተለይቶ እንዳይሰራ መጻህፍት ምስክራችን ናቸዉ፡፡
ሀ‹‹‹‹‹ “አብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ራሱ ብቻዉን የሚሠራ አይደለም፤እንዲሁ ወልድም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ለራሱ ብቻዉን የሚሠራ አይደለም፤እንዲሁም መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ ራሱ ብቻዉን የሚሰራ አይደለም፡፡” ሃይ.አበዉ ዘቅዱስ ኪራኮስ 91፡3 ይለናልና እናንተ ራሱ አክባሪ ራሱ ከባሪ ራሱ ክብር ነዉ ሥትሉ ይህንን ኃይለ ቃል ከምን አስቀምጣችሁት ነዉ?
ለ‹‹‹‹‹‹ከዚህ ከላይኛዉ ቃል ቅዱስ ኪራኮስ በተናገረዉ ማለት ነዉ እናንተ እንደምትሉት ወልድ ራሱ ቀባዒ ራሱ ተቀባዒ ራሱም ቅብዕ ነዉ ከተባለ፤ እነሆ በሥልጣን አንድ ናቸዉና አብ ለራሱ ቀባዒ ራሱ ተቀባዒ ራሱም ቅብዕ መሆኑን አትዘንጉት፤መንፈስ ቅዱስም በባህርይ አንድ ነዉና ራሱ ቀባዒ ራሱ ተቀባዒ ራሱ ቅብዕ መሆኑ አይቀሬ ነዉ፡፡ ይህ ነዉ ከተባለ ደግሞ እነሆ በሥላሴ ዘንድ ዝርዉነት የለምና መለኮት ሦስት አካላት ደግሞ ዘጠኝ ናቸዉ እያላችሁ በዋልድባ ገዳም ዉስጥ ካሉ ቤተ ሚናሶች ጋር አንድ ናችሁና ከእነሱ ጋር የምትቆጠሩ መሆናችሁ ነዉ፡፡
4ኛ‹‹‹‹‹አካለ ቃል አካለ ሥጋን በርስቱ አከበረዉ ብላችሁ ስታምኑ ተዋሕዶን እንደምን ረሳችሁት? አክባሪና ከባሪ ሁለት ግብር፣ አክባሪዉ አካላዊ ቃል ከባሪዉ ደግሞ አካላዊ ሥጋ ሁለት አካል፤እንዲሁም ባሕርይ ከአካል የተለየ አይደለምና ሁለት ባሕርይ እያደረጋችሁት መሆኑንስ ስለምን ዘነጋችሁት?
በመጀመሪያ ደረጃ----------አካለ ቃል በርስቱ አካለ ሥጋን አከበረዉ የሚለዉን ንግግራችሁን ከሚቀጥሉት ኃይለ ቃላት ጋር አስማምታችሁ ተርጉሙልን
ሀ‹‹‹‹‹‹‹ “በከመ ይቤሎሙ ክርስቶስ ለአይሁድ ወአኮ እምኀቤየ ዘመጻእኩ አላ አብ ዘፈነወኒ…ክርስቶስ አይሁድን እንዲህ አላቸዉ እኔ በራሴ የመጣሁ አይደለም አባቴ አብ ላከኝ እንጅ ” ዮሐንስ አፈወርቅድርሳን8፡56
ለ‹‹‹‹‹‹ “ይቤ ዳዕሙ ለሊሁ አክበሮ ዘይቤሎ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ ዳግመናም እንዲህ አለዉ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ ይህንን ማለቱ እራሱ ስላከበረዉና ስለ ሾመዉ ነዉ፡፡”ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን 8፡69
ሐ‹‹‹‹‹‹ “ይቤ ወክርስቶስሰ አኮ ዘወደሰ ርእሶ በከዊነ ሊቀ ካህናት አላ ለሊሁ ሴሞ ወአክበሮ”ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን 8፡59፡፡ ክርስቶስ እንደ አሮን በቃሁ ነቃሁ ብሎ ራሱን የሾመ አይደለም ራሱ አብ ሾመዉ እንጅ፡፡
መ‹‹‹‹‹ “ይቤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅ ወምእመን በኀበ ዘገብሮ ይብል እስመ ንሕነ ነአምር ከመ ዉእቱ ይቀዉም ሠናየ ለህዝቡ ወኢየሐድጎሙ ይማስኑ….ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊቀ ካህናት ባደረገዉ በአብ ዘንድ የታመነ እዉነተኛ ነዉ አለ ለወገኖቹ በጎ ማገልገልን እንዲያገለግልይጎዱም ዘንድ ቸል እንደማይላቸዉ እኛ እንድናዉቅ መናገሩ
ነዉ፡፡”ሃ.አበዉ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ63፡27……ገብሮ ያለዉንም ሐዋርያ ሊቀ ካህናት አድርጎ እንደሾመዉ መናገሩ ነዉ፡፡(ቁ28)፡፡
ሠ‹‹‹‹‹‹ “ዘአንጽሖ አብ ወፈነወ ዉስተ አለም ወአኮ መጻሐፍ ዘይነግር ከመ መለኮት ይፈቅድ ንጽሐ አላ ይቤ በእንተ ሥጋ….አብ ወደዚህ አለም የላከዉ ያከበረዉ ከሰማይ የወረደ፤ሥጋዬ ይህ ነዉ እንዳለ መለኮት ክብርን እንዲሻ መጻሕፍት የሚናገሩ አይደሉም፡ሥለሥጋ ተናገረ እንጅ”ሃ.አበዉ ዘዮሐንስ(ኢጲስ ቆጶስ ዘኢየሩሳሌም)52ክ3፡10
ረ‹‹‹‹‹ “ለሥጋዉም ከመለኮቱ ወደ አንድ ወገን የተለየ ባሕርይ የለዉም ለመለኮቱም ወደ አንድ የሆነ ባሕርይ የለዉም” ሃ.አበዉ ዘአቡሊዲስ39፡8
በሁለተኛ ደረጃ---------ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካላዊ በተወላዲነት ግብሩ በባሕርይ አንድነቱ በተለየ አካሉ ሥጋን ሲለብስ፤አካላዊ ልብ በልብነት ግብሩ በባሕርይ አንድነቱ በተለየ አካሉ ለሥጋ ምን ሰራለት?አካላዊ እሥትንፋስ መንፈስ ቅዱስ በባሕርይ አንድነቱ በተለየ አካሉ በእስትንፋስነት ግብሩ ቃል ለለበሰዉ ሥጋ ምን ሰራለት ትላላችሁ? ምንም አልሰሩለትም የምትሉን ከሆነ ሥ፤ሴ በስልታን በሥራ በፈቃድ አንድ ናቸዉ እንጅ ይለያሉን ስንል እንጠይቃችኋለን?ሰርተዉለታል ካላችሁ ምን እንዴት?
ሲቀጥል አልሰሩለትም ከተባለ አካላዊ ሥጋ ከአካላዊ ቃል ጋር በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሲሆን የአብን ልብነትና የመንፈስ ቅዱስን ሕይወትነት እንዴት አገኘ ትላላችሁ? ወልድ በህልዉና ስለሚገናዝባቸዉ ወልድ ለለበሰዉ ሥጋ በርስቱ ሰጠዉ ትሉን ይሆናል፡፡እኛ ደግሞ እነሆ ቅድስት ሥላሴ በህልዉና ሲገናዘቡ አካላዉን እንጅ ዝርዉ አይደሉምና ሦስቱም አካላት ተዋሐዱ ልትሉን ነዉ?አይ! አንልም ካላችሁ እንዴት ተቀበላቸዉ ትሉናላችሁ?
5ኛ‹‹‹‹‹‹አብ ወልድን በአካለ ትስብእት ወልዶታል ብላችሁ ታምናላችሁ ወይንስ አታምኑም?አልወለደዉም የምትሉን ከሆነ በመዝ2 “እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ…እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህእኔ ዛሬ ወለድኩህ” የሚለዉን ቃል ዛሬ በተዋሕዶ የወለድኩህ ልጄ ነህ ብላችሁ ተርጉማችሁታልና አልወለደዉም ከሚለዉ ሀሳባችሁ ጋር አስማሙልን እስኪ?
6ኛ. አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ማለት ምን ማለት ነዉ?
አብ ቀባዒ ነዉ ማለት በመጀመሪያ አካላዊ አብ ለአካላዊ ቃል የባሕርይ ልብ እንደሆነዉ እወቁ፣ በኋለኛዉ ዘመን በዘመነ ሥጋዌ በማኅጸነ ማርያም በሰዉነቱ ልብ ሆነዉ፡፡
ወልድ ተቀባዒ ማለት በመጀመሪያ ቃል ሕይወትን ከመንፈስ ቅዱስ እንደነሳ(አንድም የባህርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ) ዛሬ በጊዜ ተዋህዶ በአካለ ትስብእቱ ሕይወቱን እንደተቀበለ እመኑ፤መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ማለት በመጀመሪያ ለአካለ ቃል የባሕርይ ሕይወት እስተንፋስ እንደሆነዉ አሁንም ለቃል በአካለ ትሥብእቱ ሕይወት እስትንፋስ ሆነዉ ማለት እንደሆነ ልታዉቁ ይገባችኋል፡፡
ዳግመኛም አብ ቀባዒ ማለት በመጀመሪያ ከባሕርየ መለኮቱ አካላዊ ቃልን እንደወለደና አካላዊ መንፈስ ቅዱስን እንዳሠረጸ ሁሉ አሁንም በመለኮቱ ባሕርይ ቃል ከሥጋ ጋር በተዋሐደ ጊዜ ነፍሥ ያለዉን አካላዊ ሥጋ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ወለደዉ ማለት
ነዉ፡፡
ወልድ ተቀባዒ ማለት በመጀመሪያ አካላዊ ቃል በመለኮቱ ከአብ እንደተወለደ ሁሉ አሁንም ነፍሥ ያለችዉ አካላዊ ሥጋ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ተወለደ ማለት ነዉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ማለት አካለ ቃልን ነፍሥ ካለችዉ አካላዊ ሥጋ ጋር አዋሐደ፡ ሥጋንም ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም እኩል ትክክል አደረገዉ ማለት ነዉ፡፡
ከዚህ ላይ በክብር ማበላለጥ ሳሆን ግብራቸዉን መናገር ነዉ፡፡
አብ ቀባኢ ወልድ ተቀባኢ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ስትሉ አበላለጣችኋቸዉ የምትሉን ከሆነ ደግሞ አብ አባት ወልድ ልጅ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ነዉ እንላለን እና ስለተበላለጡ ነዉ ወይ ብለን አጥብቀን እንጠይቃለን?
በዚህ አጋጣሚ አፈወርቅ ዮሐንስ እንዲህ ብሏልና እንዴት ትተረጉሙታላችሁ
“ለአጽንዖተ ክልኤሆሙ….አብን መንፈስ ቅዱስን በጥንተ ስማቸዉ በጥንተ ግብራቸዉ ለማጽናት ቃል ሥጋን ተዋሐደ”ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን2፡155፡፡ ይለናልና የአብና መንፈስ ቅዱስ የቀድሞ ስማቸዉ አብ አባት መንፈስ ቅዱስ ሕይወት መሆኑንና የቀድሞ ግብራቸዉ አብ መዉለድ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ከአብ ሠርጾ ሕይወት መሆን አይደለምን?
7ኛ‹‹‹‹‹‹‹ እናንተ እንደትሉሥጋ በርስቱ ከአካለ ቃል ከበረ ከተባለ ቅዱስ ቄርሎስ እንደተናገረዉ እንቲአሁ ለቃል ኮነ
ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ብሎ እንደተናገረዉ ተዋሕዶ የቃልን ገንዘብ ለሥጋ አስተላልፎ የሥጋን ንዴት ወዴት
ጣለዉ ትላላችሁ?
8ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹“ወበእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ…እግዚአብሔር አምላክህ ቀባህ” የሚለው የዳዊት ቃል(መዝ44፡7) ከወንጌላዊው ዮሐንስ “አአርግ ኀበ አቡየ ወኀበ አቡክሙ ወኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ….እኔ ወደ አባቴ ወደአባታችሁ ወደ አምላኬ ወደአምላካችሁ አርጋለሁ”የሚለዉን እንዴት ትተረጉሙታላችሁ?
ከዚህ ጋር በተያያዘ አፈወርቅ ዮሐንስ እንዲህ ይለናል፡፡ “እነሆ እርሱ ጳዉሎስ አብን አምላኩ ለክርስቶስ አለዉ፡፡በእዉኑ ወልድ
ክርስቶስ በክብር ከአባቱ ያንሳልን?”ሃ.አበዉ ዘዮሀንስ አፈ ወርቅ 68፡11
ወልድ ወደ አምላኬ ወዳምላካችሁ ሲል በሥጋዉ መሆኑ የታወቀ ነዉና በሥጋዉ ምን ስላደረገለት ነዉ አምላኬ አባቴ ሊለዉ የቻለዉ ትሉናላችሁ?
9ኛ<<<< ክርስቶስ ማለት ምን ማለት ነዉ? እስኪ ከ1ኛ ዮሐ2፡22 እና ከማቴ 1፡16(አንድምታዉ ጋር አስምታችሁ
ተርጉሙልን?
ይቀጥላል.....
No comments:
Post a Comment