ወመኑ ሐሳዊ ዘእንበለ ዘይክህል ወይብል ከመ ኢየሱስ ኢኮነ መሲሕ ፡ ኢየሱስ መሲሕ (የተቀባ) አይደለም ብሎ ከሚክድ በቀር ሐሠተኛ ማነው? ፩ዮሐ ፫፥፳፪ "መኑ ውእቱ ክርስቶስ - ክርስቶስ ማነው? "
✿አንብብዋ ለመልዕክት እምጥንታ እስከ ተፍፃሜታ ሃ.አዘአንፆኪያ (፻፰፥-፳)✿
በክርስቶስ ሰው መሆን አለምን በክህደት ውስጥ ምንኛ እንደገባ ይገርመኛል። ለመሆኑም ብዙ ሠዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ግንዛቤ ምንኛ ያውቁ ይሆን? እንግዲህ ከስሙ ትርጓሜ ስንነሳ
ክርስቶስ - በጽርዕ
መሲሕ - በአረብ
ቅቡዕ - በግእዝ
ቅቡዕ - በግእዝ
የተቀባ - በአማረኛ ተብሎ ይተረጎማል(ዮሐ ፩፥፵፩ ትርጓሜ)።
ክርስቶስ የሚለውን ስም የመሠከረለት የመጀመሪያ ሊቀ ጳጳስ ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደሆነ መጽሐፍ ይመሰክራል።ሉቃ.፱፥፳.......ለብቻው ሲፀልይ ደቀመዛሙርቱ ከርሱ ጋር ነበሩና እኔ ማን እንደሆንሁ ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው።............ጴጥሮስም መልሶ "አንተ ውእቱ መሲሑ ለእግዚአብሔር - አንተ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ " አለው። አንድም ስለመሠከረለት ጳጳስ ሾሞታል። የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ሠጥቶታል። የተቀባህ ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ መሠከረለት።አንድም ዘተሰምየ ክርስቶስሃ በእንተዝ ዘተቀብአ ምስሌነ ከመ ሰብእ - በስጋው ስለከበረ(ስለተቀባ) ክርስቶስ ተባለ ቄር.ቃለ ግዘ ፯፥፳፱ ። ወቅብዓቱሰ ዘተወክፈ በትስብእቱ፡መንፈሰ ቅዱስን ተቀበለ መባሉም በስጋው ነውአንድም ከበረ መባሉም በስጋው ነው።
እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ተቀብዓ ቃል በስጋሁ ወእም አመ ኮነ ቃል ስጋ አሜሃ አስተራየ በመንፈስ ቅዱስ ፡በእውነት የሚያመኑ ቃል በስጋው እንደተቀባ ያስተምሩ ፡ቃል ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ ታወቀ ፡ተገለጠ። እንዲ.ወጌ.ማቴ ፩፥፲፮ ክርስቶስ (ፅር ክርስቶስ ) የሹመት ስም የተቀባ ፡ቅቡዕ
ለምሳሌ በፀጋ ከተቀቡት እንደ ዳዊት፡ አሮን ተቀብቶ የተሾሙ ናቸው። መቀባትም ለ፫ሹመትነው።ካህንና ንጉስ ነብይ ለመሆን እነዚህ ሶስቱም የሚሾሙት መጀመሪያ በህዝብ ይመረጣሉ ።፪ከካህን ከነብይ በተቀደሠ ዘይት ይቀባል። በተቀባ ጊዜ የሹመትን ስራ የሚያስፈፅም ሀብት ስልጣንና ችሎታ ያድርበታል። ይህ ለኩሉ ነው ዘጸ፳፱፥፯,ዘሌ፬፥፫,፩ነ ገ.፲፯፥፲፩-፲፫

አንድም ክርስቶስ በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ ማለት ነው። ስለዚህ ነው እኮ መጽሐፍ እንዲህ የሚለው ወዘሰ ሐደረ ላዕሌሁ መንፈስ ቅዱስ በእንተ ስርዓተ ትስብእቱ ፡መንፈስቅዱስ ገንዘቡ ሆነ መባሉ ቃል ሰው ስለሆነ ነው ወእመ አኮስ እፎ ይትበሀል ከመዝ እስመ መንፈስ ቅዱስ ዚያሁ ውእቱ በህላዌ መለኮቱ ዘከመ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ሰውማ ባይሆንኖሮ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ህልው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ በባህርየ መለኮቱገንዘቡ ነውና።ሃ.አ ዘሳዊሮስ ፹፯፥ክ፱፥፲፰ በማለት አባቶቻችን አስተምረውናል።እንግዲህ አንዳንድ ሰዋች ክርስቶስ በሰውነቱ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል ከመፅሐፍ ሲያነቡ ይነስራቸዋል።ለምን ይሆን?
=>ዘኢትወለድ እማይ ወእመንፈስ ኢይክል በዊአ ውስተ መንግስተ እግዚአብሔር እስመ ዘተወልደ እምስጋ ስጋ ውእቱ ወዘተወልደእመንፈስ ቅዱስውእቱ፡ ይሕ ቅብዓት ምንድን ነው ቢሉ መንፈስ ቅዱስ ነው። ለሁሉ ፀጋ ክብር መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ሲያጠይቅ ጌታችን ከረቂቅ የተወለደ ረቂቅ ነው ከግዙፍ የተወለደ ግዙፍ ነው።ሲልከውሃ እናትነት ከመንፈስ ቅዱስ አባትነትን ልጅነትን ነስተው አሕዛብ አረማውያን ረቂቅ መንግስት ሰማያትን እነዲወርሱ ተፃፈ።አክሲማሮስ ዘስሉስ ክ.፪ ስለዚህም ቅብዓት ማለት መንፈስ ቅዱስ ነው ማለት ነዉ። ክርስቶስ ብሎ አምኖ ክርስቶሳዊያን ክርስቲያን እንዲባል ነገሩ የተገባ ነው።
በመንፈስ ቅዱስ መክበር መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ማድረግ ለፍጡር ስጋ የተገባ ነው።ቃልስ እንደ አባቱ በባህርየ መለኮቱ ፍጹም እንደሆነ ክብርን የማይሻ መንፈስ ቅዱስም እንደ አባቱ ሕይወቱ እንደሆነ እናውቃለን። ነገር ግን ይህ ከእመቤታችን የተከፈለ ስጋ እንኳንስ የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ለአካሉ ገንዘቡ ሊሆን በፀጋ እንኳን መንፈስ ቅዱስ ያላደረበት እንደሆነ መጽሐፍ ይመሰክራሉ። መንፈስ ቅዱስ ለአብናለቃል ሕይወትነቱ በአካልነቱ እንጅ ነፍስ ከስጋ ጋር ተዋህዳ ሕይወት እንደሆነቻት እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትነቱ ለአብና ለወልድ ከአካላቸውጋር ተዋህዶ አይደለም።
ስለ ቃልና ስጋ ተዋህዶ ስንናገርም ቃል በተለየ በብቻ አካሉ ከድንግል ከተከፈለ ስጋ ጋር በተዓቅቦ ሲዋሀድ ቃል የነፍስን ሕይወትነት በተዋህዶ ገንዘብ አደረገ። እንዲሁ ክብርን የመንፈስ ቅዱስን ሕይወትነት የሚሻ ባዕድ ስጋ ከቃል ጋር ሲዋሀድ ከእግዚአብሔር አብ አካል ዘእምአካል ባህሪ ዘእም ባህሪ ቢወለድየአባቱን ሕይወት መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ። በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለት ስለዚህ ነው። አንድም ወኩሉ ምግባረ መንፈስ ኅዱር ውስተ ስጋሁ =የመንፈስ ቅዱስ ስራ ሁሉ በለበሰው ስጋ ገንዘቡ ነው።
ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር ቅብዓመንፈስ ቅዱስ - በመንፈስ ቅዱስ ቅብዓት የእግዚአብሔር አብ የባሕሪ ልጅ ተባለ።ተረፈቄር.፰ገፅ፳፪ ቅድመ ተዋህዶ ቃል በአብ ልብነት ያስባል በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ህያው ይሆናሉ። ቃል የተወሀደው ስጋከአብ የባህሪልደት ሲወለድ የባሕሪ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ቢያደርግ (በመንፈስ ቅዱስ ቢከብር) ተቀባ ተባለ።አብ ለወልድ በስጋው መንፈስ ቅዱስንሊሠጠው ፈቃድ ቢሆን ቀባው ተባለ።አንድም ወአርዓየ ከመ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝውእቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ፡እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይሉምቀባው እንዲል.መፅ.ትርጓ.ግብ.ሐዋ.፲፥፴፰ ወበከመ ለአብ ቦቱ ሕይወትሃቤሁ ከማሁ ለወልድኒ ወሀቦ ሕይወተ ከመ ይኩን ሕይወት
ሃቤሁ እን.ወንጌ.ዮሐ.፭፥፳፯ አንድም አንተ ውእቱ ሊቀ ካህናቲነ ዘቅቡዕ እምኃበ አብ መንፈስ ቅዱስ - መንፈስ ቅዱስን ከአብ ዘንድ የተቀባህ ሊቀ ካሀናታችን አንተ ነህ።መ.ምስጥ ፪፥፳፫
መንፈስ ቅዱስ ለቃል በስጋ ርእስት የባህሪ ሕይወት ሲሆነው በመሠጠቱ ቅብዕ ተባለ። አንድም በእንተዝ ይትበሃል ከመ ነሥአ መንፈስ ዚአሁዘተነግረ በኢሳያስ ነቢይ እንዘ ይብል መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ ቀብዓኒ በእንተዝሰበከ እንዘ ይብል እስመ መንፈስ ዘዚአየ በሕላዌ ለሊሁ ኃደረ ላዕሌየ በእንተ ዝንቱ ወለምንትኑ ተሰመይኩ መሢሕ እንበለ ዳዕሙ ሶበ ኮንኩ ሰብአ እን.ሃአ.ሳዊ.ዘአንጾ.ክ፱፥፲፯ ዳግመኛም ከመ ዝንቱ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይነስእ እመንፈስ ቅዱስ ዘከመ ሥርዓተ ትስጉቱ በከማሁ ዓዲ ይሁብ ኪያሁ እስመ እግዚአብሔር ውእቱ በህላዌሁ ዘበአማን - እንዲ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደመሆኑ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ ወዲህ የባህሪ አምላክ ነውና መንፈስ ቅዱስን እንሠጥ ነገሩ የተገለጠ ነው።ሃ.አ.ክ.፶ ፥፺፪
አዎ እንአምላክነቱ ይሰጣል እንደ ሰውነቱ ይቀበላል ገንዘቡ ይሆናል ።
ዘይሁብ ወለሊሁ ይተወሀብ እን.አረ.መን.ድር ፲፩ - ይሠጣልም ይቀበላልም አለ ። በሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ያደርጋል። በመለኮቱ ይሰጣል።
፠ ዳግመኛም ቄርሎስ እንዲህ አለ አሌ ሎለ ዘከመዝ እብድ =እንደዚህ ያለ እውቀት ክህደት ወዮለት። ወለመዝ ከመዝ ቁስለ ሕሊና ለእለ ከመዝ ይሄልዩ ህሊና ካለ እለ - ለእለ ካለ ሕሊናሆሙ ባለ በቀና ነበር። በሕፀ ክህደት ለተነደፈ እንዲህ ለሚል ፡ ወዘኢየአምር እፎ እፎ እንደምንም እንደሆነ ለማያምን ፡እንደዚህ ያለአላዋቂ ልቡና ወዮለት።አንድም አብድ እነንደዚህ ያለ አላዋቂ ልቡና ወዮለት። ወኢየአምር አለከመዝኒ ኢየአምር ይለዋል ፡እንደዚህ ለሚሉ ሠዎች ነገራቸው። እፎ እፎ እንደምንም እንደሆነ ምን እንደሆነ አላውቅም። ዘቅዱሳት መጽሐፍት ይሰብኩ ከመ ፩እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርሶቶስ ዘእምእግዚአብሔር አብ ገሀደ ቃል ዘተሰብአ ወተሰገወ ፡ከአብ ባህሪ የተወለደው ሰው የሆነው አንድም እንደሆነ ክቡራን መጽሐፍት ያስተማሩትን ፡እንዘ ይኮሲ ፡ሲነቅፍ አግኝተናልና። ኢየአምን አለማመን ብለህ እስር ወተወልደ በስጋ እምብዕሲ እምብዕሲት ከብዕሲት ተወልዷልና በዝላለው ፩ኬ ይእቲ ስጋ ከቃል ጋር አንድ ነውና።
ዘመለኮት ላለው ወዉእቱ መዘተዝለፍ ሃሎ ወይሄሉ፡ቃል ደግሞ ከስጋ ጋር ፩ነውና ወሰብእ ላለው ወበደኃሪ መዋዕል ተወልደ በስጋ ፡በሗላ ዘመን በስጋ ተወልዷልና። እንዘ ቅዱስ ውእቱ በህላዌሁ ከመ አምላክነ ፡አምላክ እንደመሆኑ በባህሪዮ ክብር ሲሆን ተቀደሰ ምስሌነ ፡በስጋ ከበረ ተባለ አንድም በስጋ ከበረ መባልን የሚስማማው ሰው ሆነ።በከመ ኮነ ሰብአ በዘይደሉ ተቀደሰ ፡መክበር የሚገባው ሰው እንደመሆኑ ፡ አንድምተቀደሰ በዘይደሉ ተቀድሰ በስጋ በከመ ኮነ ሰብእ ብሎ መግጠም ነው። ፡ሰው(እንደሆነ)ስለሆነ መክበር በሚገባው በስጋ ከበረ ተባለ።እንዘ እግዚእ ውእቱ
በመለኮቱ፡በአምላክነቱ የማይከብር ሲሆን በስጋ ከበረ ተባለ። ወእዘ እግዚአብሔር ሴሆን ፡ወአረአየ ገብረ ረሰዩ ዘዚአሁ፡የአዳምን ባህር ገንዘብ አደረገ፡
አንድም ገንዘብ አድርጎ ይሰምዮ ለአብ አምላክ፡አብን አምላኪየ ይለዋል። ወእንዘ ሕይወት ውእቱ ወማህይወት ሕይወት ወሀቤ ፡ሕይወት ሲሆን ፡ከመ አምላክ ፡አምላክ እንደመሆኑ ፡ይሠመይ ከመ አሕይዋ አብ ፡አብ እንደ አከበረው እንዳስነሳው ይናገራል የሐ.አፈወ.ድር፲፪ የተወሰደ
፠ቄርሎስ ይቤ ነበብከ ርቱዓ በእንተ ቅብዓተ ክርስቶስሃ ይሠመየ በእንተ ዘተቀብዓ ምስሌነ ተቀባ ስለተባለ ክርስቶስ ተባለ እውነት ነገር ተናገርህ።አንድም ስለተቀባ ክርስቶስ ተባለ ዝውእቱ መሲህ ይኸውም መሲሕ ማለት ነው በከመ ይሰመይ በሐዊሮቱ ስለአስተማረ በቁሙ ስለሄደ ሐዋሪያ እንዲባል አንም በከመ ሐዋርያ ይላል ጌታ ወጥቶወርዶ ስለአስተማረ እንዲባል በዝንቱ አስማት ተሰምዩ ነቢያት ቅቡዓነ በዚህ ስም ነቢያት ተጠሩበት ዝውቱ መሲሐውያን ይኸውም ቅቡዓን ተትንቢት የሚያስተምሩ ማለት ነው ቄር.ድር ፴፫ በከመ ይቤ እንዲህ አለ ነህ ነሂ ነኃብር ስምየ አስማተ ክብር መለኮት ዘአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ - ክብር የሚሆን የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የጌትነታቸው ስም በመጥራት ዘወልደ ለዘተወልደ እምነሁ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ክልሎቱ ለዘተወልደ- ተወላዲውን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በማክበር ትምህርታችን ልማዳችን ነው
ምስለ አምጣነ ትዕስብእቱ ረከብኩ ለዋህድ - ሰው በሆነ ጊዜ ለቃል እንዲገባ እንናገራለን
ወገሀደ ይሰመይ ቅብዓተ ለእለ ይሌብውዎ - ሰው እንደሆነ ለሚያምኑ ሰዋች በጎላ በተረዳ ቃል ቅቡዕ ይባላል
እስመ ዘተሰብአ ተቀብዓ=ሰው በሆነ ገንዘብ ከብሯል። አንድም ሰው ስለሆነ ከብሯል። ና ወኪያሁ ይሰመይ ቅቡዕ ይባላል ።
ወይእዜ ሰብ ዘኢኮነ ዘትስብዕት ወዘትስጉት ነገር ዝንተ ነገር - አሁን የምንናገረው ነገር በማገናዘብ ካልሆነ ፡ አላ ወፅአ እምትስብዕቱ ወእምትስጉት ዝንተ ነገር በእንተ ዋህድ እግዚአብሔር ቃል- ስለ ዋህድ ቃል የምንናገረው በማገናዘብ ነው እንጅ ነገር በማገናዘብ ካልሆነ አማን እምንቤ ጥቀ ኢይደሉ ለዋህድ ክርስቶስ ስምየ ዘውእቱ ቅቡዕ ለዘኢተቀብዓ ለዋህድ - ክርስቶስ ና ለዘኢተቀብዓ አንድ ወገን ነው ላልከበረ ለቃል ክርስቶስ መባል
አይገባውም አይመቸውም ብለን በተናገርን ነበር። አንድም ቃል ከስጋ ቢዋሀዱ መንፈስ ቅዱስ ገንዘቡ ቢሆን በሰውነቱ ክርስቶስ ተባለ አንድም በዘተሰብዓ ተቀብዓ አን. እስመ መፅሐፍ ይነግር ከመ ቃል ስጋ ኮነ - ወንጌል ቃል ስጋ ኮነ ብሎ ተናግሯልና። አማንኬ ይደልዋ ክርስቶስ መባል ይገበዋል እንጅ ። መፅሐፍ ዘበኩሉ ጠቢብ ጳውሎስ በውስጥ በአፍ በኦሪት በወንጌል አዋቂ የሚሆን ጳውሎስ ተናገረ። ዘይቀድስ ወይቀድስ እም፩ያከብር - የከበረ ከአንድ አካል ይገኛል ብሎ ተናገረ።
በዘፍናኢ የሐፍር ስምዮቶሙ አኃው =ከበረ ስለተባለ አሐውየ እንዲህ ማለት አይፈር። ሊቁ እንዘ ይብል እነግሮሙ ስምከ ለአኃውየ እስመ ተቀደሰ ምስሌነ ሶበ ኮነ ከማነ - እንደኛ ሰው ስለሆነ አንድም ፍጹም ሰው በሆነ ጌዜ በሰውነቱ ከበረ ተብሏል።
፠ወከመሠ አማን ወልድ ውእቱ ዘተቀብዓ ፡የተቀባው የባህሪ ልጅ እንደ ሆነ ወኮነ ስጋ በፍጽም ትስብእት፡ነፍስን ስጋን ነስቶ ሰውም እንደሆነ፡ የአምን ክቡር ዳዊት ፡ክቡር ዳዊትም ያስረዳል አንድም ሰው እንደሆነ እንደተቀባ ያስረዳል።እንዘ ይብል በእንተ ወልድ መንበርከ አምላኪየ ለአለም ዓለም፡እንዲህ ብሎ የባህሪ እንደሆነ ያስረዳል። በትረ ፅድቅ ወበትረ መንግስትከ ፩ወገን ነው አፍቀርከ ጽድቅ ወአመፃ ፀላእከ ፡እንህ ብሎ ሠው እንሆነ፡
ወበእንተዝ ቀባዕቀ እግዚአብሔር አምላክከ አንድም አምላክከ ቅብዓ ትፍስእት እምለ ከማከ እንዱህ ብሎ ደግሞ እንደተቀባ ያስረዳል።
ለቡኬ ከመ አምላክ ስመዮ፡የባህሪ አምላክ ብሎት፡ ወበንበርሂ ወሂቦ ዘለዓለም ፡የዘላለም ዙፋንን ገንዘብ እንደሆነ ተናገረ።ስመዮ ከመ ተቀብዓእምእግዚአብሔር ፡ከእግዚአብሔር አብ በተገኘ ክብር ከበረ እንዳለዉ አስተውል ተረዳ።
ዘውእቱ ገሃድ እምእግዚአብሔር አብ፡ ከአብም ያገኘክብር አካለ መንፈስ ቅዱስ ነው። በቅብዓተ ነከረ እም ኢተሳትፎሙ ዘውእቶሙ ነህነ፡ ይኸውም ምዕመናን እኛነን እኛ ካገኘነው በበለጠ አንድም በሚበልጥ ክብር ከበረ እንዳለው እወቅ ተረዳ ። ወእመሂ ኮነ ሰብአ ምንም ሠው ቢሆን በአማን እግአብሔር ቃል ውእቱ ፡ በእውነት እግዚአብሔር ነው ። ወኢኮነ ኅቡአ ኂሩተ ህላዌሁ ኄር ባሕርዮ ፡ የተለወጠ አይደለም እለ ጥንቁቅ በርእሱ ፡ በባህሪው ፀነቶ ይኖራል እንጅ። ወፍፁም ፀጋ ወፅድቅ ፡ የባህሪ ክብር ገንዘቡ ነው በከመ ቃሉ ለዮሐንስ ለዮሐንስ እንደተናገረ ፡ ወሀሎ በኩሉ መለኮት ጌትነቱ በሁሉ አለ ፡አንድም በፍጽም ጌትነቱ አለ።
✿ ወእምተፍፃሜተ ዚአሁ ኩልነ ነሳእነ ፡ከፍጽም ጌትነቱ ከተፈፀመለት ሀብቱ ተቀበልን እንጅ አገኘንም ብትል ይሆናል። በከመ መፅሐፍ እስመ ተረፈዚአሁ ነሳዕነ ንህነ ኩልነ ፡ተብሎ እንደተፃፈ። ኅቡር ምስለ አምጣነ ትስብእቱዚአሁ፡ ሰው ቢሆን ሰው በሆነ ጊዜ ነሣዕነ አንድም ወደታች
ወዘትስብእቱ ለርሱ ረሰየ፡ የስጋን ገንዘብ ገንዘብ አደረገ። ይሰመይ ክርስቶስ ዘውእቱ ቅቡዕ ፡ ይኸውም ቅቡዕ ማለት ነው። ድር.ቄር.፴፪-፷
ሰው የሆነ ሁሉ ያስተውል፡ ቄር.በሰውነቱ ከበረ አለው አዋ በሰውነቱ ከበረ በአምላክነቱማ ያከብራል። ኢይጽቅ ቅብዓተ በህላዌ መለኮቱ አላ ተሰጊወዎ ነስአ ቅብዓት እም አብ በትስብእቱ ፡ በህላዌ መለኮቱማ መንፈስ ቅዱስን አይሻም ወዶ በለበሰው ስጋ ተቀባ እንጅ እን.ቄር ድር ፫
ስለዚህ መፅሐፍ ክርስቶስን በሰውነቱ ከበረ አለው እኛም በመጽሐፍ ነው የምንመራው እና በሰውነቱ ከበረ እንላለን።
ስብሐት ለሥሉስ ቅዱስ!
No comments:
Post a Comment