![]() |
የአባ አስራተ ማርያም መድኃኒዓለም ገዳም |
አባአስራት ገዳም ከደብረ ማርቆስ ከተማ በስተደቡብ ከከተማዋ በግምት 8 ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል፡፡ ከከተማው ወደ አዲስ አባባ በሚወስደው አስፋልት መንገድ በስተቀኝ በኩል ገባ ብሎ ገዳሙ እስከሚገኝበት ስፍራ የ20 ደቂቃ እግር ጉዞ ይወስዳል ፡፡
አባ አስራት ገዳም በ1815 ዓመተ ምህረት አባ አስራት በተባሉ ሰው አማካኝነት የተቆረቆረ እንደሆነ አባቶች ያስረዳሉ፡፡በአመት ሁለት ጊዜ ማለትም በመጋቢት እና ጥቅምት 27 ቀን ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ በዓለ ንግሱ የሚከበር ሲሆን ገዳሙ በአሁኑ ሰዓት 57 ወንድና 20 ሴት ያህል መነኮሳት ይኖሩታል ፡፡ በገዳሙ የሴቶች ና የወንዶች ቤተ-ፀበል የተለየ ሲሆን ጫካውን ከሰሜን ወደ ደቡብ ለሁለት የሚከፍለው የጨሞጋ ወንዝ ለገዳሙ ትልቅ ድባብ አጎናፅፎታል፡፡
ከገዳሙ በታች የሚገኘው ደን ውስጥ የተለያዩ የዱር እንስሳት እንደ ጅብ፣ ቦሆር፣ፌቆ ፣ድኩላ፣ ከርከሮ፣ ዝንጀሮ የመሳሰሉት ይገኙበታል ከሀገር በቀል ዛፎች ደግሞ የሀበሻ ፅድ ፣ሰሳ፣ሾላ፣ዋርካ፣ዶግ፣ ጥቁር እንጨት እና ግራር የመሳሰሉት በዉስጡ ይዟል፡፡ ገዳሙ ለእይታ ከሚያምር ገደላማ መልክዓምድራዊ አቀማመጥና ከተፈጥሮ ደን ዉስጥ መገኘቱ ማራኪ እይታ አለው፡፡
ስለ አባ አስራት ገዳም ሰፋ ያለ ታሪክ ካለ ቢለቀቅ
ReplyDelete