Saturday, September 22, 2018

ስለ እኛ

ምስጢረ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ
 ከብራና ወደ ወረቀት የተቀየሩ የቅዱሳን አበው መጽሐፍት [ስርዋጽም የተጨመረባቸውም ብዙዎች አሉ]

ቅዱሳን አበውን "የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው" ዕብ ፲፫፥፯  ብሎ ሐዋርያው  ቅዱስ ጳውሎስ  እንዳስተማረን  እኛም  እነርሱን አብነት አድርገን ትንቢታቸውን፣ ስብከታቸውን፣  ድርሳናቸው፣  ገድላቸውን ተቀብለን ለዘመናት  ኖረናል እየኖርንም  እንገኛለን ::

ነገር  ግን በቀደሙት ሐዋርያትና  በሊቃውንት እግር  የተተኩት የዘመናችን  መምህራን ቅዱሳን አበው  የተናገሩትን ትክክል አይደለም በማለት የራሳቸውን ሀሳብ እየጨመሩ [ስርዋጽ -አዲስ ነገር እያስገቡ]ና የነበረውን  ደግሞ እያስወጡ  በማር የተለወሰ መርዝ  በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ  ቤተ ክርስቲያን ላይ እየዘሩ ይገኛሉ::

 ነገርግን እኛ ይህንን በመረዳት ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ብለን ብንጠይቅም ምላሽ ስላልተገኘ እያንዳንዷን ጉዳቸውን ከቀደሙት አበው መጽሐፍት እያወጣን እንዴት እንዳወጡትና እንደጨመሩበት በግልጽ ለመወያየት ይህንን ጦማር መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ::

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። ገላ ፩፥፰ በማለት አውግዟቸዋል::


ለማንኛውም ያላችሁን አስተያየት new2zewdu16@gmail.com ብላችሁ ኢሜይል ብታደርጉልኝ ደስ ይለኛል::

1 comment:

  1. በጣም ደስ ይላል በርቱልን እግዚአብሔር አምላክ ያበርታቹህ እውቀትና ጥበብ ይጨምርላቹህ ትዕግስትና ማስተዋሉንም እንዲሁ ያብዛላችህ!!! ❤

    ReplyDelete