ከወደ ፡ ወልድያ ፡ የመጣችው ፡ የካሮቹ ፡ የምፍቅና ፡ ጥያቄ ፡ እና ፡ ኦርቶዶክሳዊ ፡ መልሷ ፡፡
===================================================
የተከበራችሁ ፡ ኦርቶዶክሳውያን ፡ ሁላችሁም ፡ በማስተዋል ፡ ተከታተሉኝ ፤ ይህች ፡ የካሮቹ ፡ የጨዋ ፡ ጥያቄአቸው ፡ ምንጫ ፡ የምዕራባዊት ፡ ጎጃም ፡ የሊቃውንት ፡ ጉባዔ ፡ ሰብሳቢና ፡ የዐራቱ ፡ ጉባዔ ፡ መምህር ፡ የሚባሉት ፡ የስምዐኮነ ፡ መልአክ ፡ ቃለ ፡ ጽድቁ ፡ ለአብ ፡ የተሰኘች ፡ መጽሐፍ ፡ ናት ፡፡ እኒህ ፡ ሳያላምጡ ፡ የሚውጡ ፡ አግበስብሶች ፡ መጽሐፏን ፡ ሳይመረምሩ ፡ እንዳለች ፡ውጠው ፡ እያነቀች ፡ ገደል ፡ እየለቀቀቻቸው ፡ ይገኛሉ ፡፡ እነሆም ፡ ይሕች ፡ ክሕደት ፡ ከምዕራብ ፡ ጎጃም ፡ ተነስታ ፡ ስሜን ፡ ወሎ ፡ ወልድያ ፡ ደርሳ ፡ ነጥራ ፡ ወደሸዋ ፡ ተመልሳለችና ፡ ክሕደቷን ፡ እንዳለች ፡ አስቀምጥ ፡ እና ፡ በብልት ፡ በብልቷ ፡ ክሽን ፡ ባለች ፡ የኦርቶዶክሳውያን ፡ ልሳን ፡ ለማበጠር ፡ አሐዱ ፡ ብያለሁ፡፡ ሙሉ ፡ ጥያቄው ፡ በቴሌ ፡ ግራም ፡ የደረሰኝ ፡ ሲሆን ፡ እንደሚከተለው ፡ እንደወረደ ፡ አቀርበዋለሁ፡፡ ሰውየው ፡ ሲልክልኝ ፡ “ህይወት” ፡ ያለውን ፡ “ሕይወት” ፡ “ህድረት” ፡ ያለውን ፡ “ኅድረት” ፡ ከማለት ፡ በስተቀር ፡ አልጨመርኩም ፡ አልቀነስኩም ፡፡
ሙሉ ፡ ጥያቄው‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቃል ፡ ለተዋሐደው ፡ ሥጋ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሕይወት ፡ ሆነው ፡ ሲባል ፤ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አካላዊ ፡ እስትንፋስ ፡ መሆኑ ፡ እርግጥ ፡ ነው ፤ ታዲያ ፡ ለሥጋ ፡ ሕይወት ፡ የሆነው ፡ በአካሉ ፡ ነው ፡ ወይስ ፡ በፀጋው? በፀጋው ፡ ነው ፡ ከተባለ ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡ ብለናልና ፡ በቃልና ፡ በሥጋ ፡ መካከል ፡ ልዩነት ፡ ወይም ፡ ሁለትነት ፡ የለምና ፡ የቃል ፡ ሕይወት ፡ የጸጋ ፡ ሕይወት ፡ መሆኑ ፡ ነው ፡፡ የጸጋ ፡ ሕይወት ፡ ያለው ፡ አምላክ ፡ ደግሞ ፡ የለንም ፡፡ እንዲህ ፡ ከሆነ ፡ እርሱ ፡ ፍጡር ፡ አምላክነቱም ፡ የጸጋ ፡ መሆኑ ፡ ስለሆነ ፡ እንዲህ ፡ ማለትንም ፡ አምላክ ፡ ከእኛ ፡ ያርቅልን ፡፡ እንዲሁም ፡ ሕይወት ፡ የሆነው ፡ በአካሉ ፡ ነው ፡ ከተባለ ፤ ደግሞ ፡ ሌላ ፡ ጥያቄ ፡ ያስነሳል ፡፡ ይኸውም ፡ ሥጋ ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ሕይወትነት ፡ የተቀበለው ፡ በተዋሕዶ ፡ ነው ፡ በኅድረት?በኅድረት ፡ እንዳይባል ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡ ስላልን ፡ ምንታዌ ፡ ስለሌለ ፡ አንዱን ፡ አካል ፡ በአንዱ ፡ ማሳደር ፡ ይሆንብናል ፤ በሥላሴ ፡ ደግሞ ፡ ኃዳሪና ፡ ማኅደር ፡ የለም ፡ በተዋሕዶ ፡ ነው ፡ እንዳንል ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ ያሰኛል ፤ ቃልንም ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስንም ፡ ከሥጋ ፡ አዋሕዶ ፡ ሁለቱን ፡ አካላት ፡ አንድ ፡ ወደማድረግ ፡ ይወስዳል ፡፡ ስለዚህ ፡ ልንጠነቀቅና ፡ ልንፈራ ፡ የምንናገረውን ፡ ልናስተውል ፡ ይገባናል ፡፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ተቀባ ፡ (ሕይወት ፡ ሆነው) ፡ ሲባል ፡ በኅድረትም ፡ በተዋሕዶም ፡ ካልሆነ ፡ እንዴት ፡ ሊሆን ፡ ይችላል?”›››››››››››› የሚል ፡ ጥያቄ ፡ ነው
እንግዲህ ፡ ይህንን ፡ ጥያቄ ፡ በብልት ፡ በብልቱ ፡ ለመመልከት ፡ ይረዳን ፡ ዘንድ ፡ ቁጥር ፡ እየሰጠሁ ፡ ከሙሉ ፡ ማሥረጃ ፡ ጋር ፡ አብራራዋለሁ
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቃል ፡ ለተዋሐደው ፡ ሥጋ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሕይወት ፡ ሆነው ፡ ሲባል ፤ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አካላዊ ፡ እስትንፋስ ፡ መሆኑ ፡ እርግጥ ፡ ነው ፤ ታዲያ ፡ ለሥጋ ፡ ሕይወት ፡ የሆነው ፡ በአካሉ ፡ ነው ፡ ወይስ ፡ በፀጋው?”›››››››ብለሃል ፡ በመጀመሪያ ፡ ደረጃ ፡ ጥያቄው ፡ መሆን ፡ የነበረበት ፡ “በአካል ፡ ነው ፡ በፀጋ” ፡ ሳይሆን ፡ “በባሕርይ ፡ ነው ፡ በፀጋ” ፡ ተብሎ ፡ ነበር ፡፡ ይሁን ፡ እንጅ ፡ ካሮቹ ፡ ሁለመናችሁ ፡ ያልተገራ ፡ ያልተገዘረ ፡ በመሆኑ ፡ የምትጠይቁትን ፡ እንኳን ፡ አታውቁም ፡፡ ሆኖም ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ለወልድ ፡ በትስብእቱ ፡ ክብር ፡ ሆነው ፡ ሲባል ፤ በአካላዊ ፡ የባሕርይ ፡ ኅድረት ፡ እንደሆነ ፡ የአንጾኪያው ፡ ሊቀጳጳስ ፡ ቅዱስ ፡ ሳዊሮስ ፡ እንዲህ ፡ ሲል ፡ ተናግሯል ፤ “ወበእንተዝ ፡ ኵሉ ፡ ይትበሀል ፡ ከመ ፡ ውእቱ ፡ ነሥአ ፡ መንፈሰ ፡ ዚኣሁ ፡ ዘተነግረ ፡ በኢሳይያስ ፡ ነቢይ (ሰው ፡ ስለሆነ ፡ በኢሳይያስ ፡ እንዲህ ፡ ተብሎ ፡ የተነገረ ፡ የባሕርይ ፡ ሕይወቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ገንዘብ ፡ እንዳደረገ ፡ ይነገራል) ፤ እንዘ ፡ ይብል ፡ መንፈሰ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘላዕሌየ ፡ በእንተ ፡ ዝንቱ ፡ ቀብዓኒ (የእግዚአብሔር ፡ ሕይወቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አለ ፤ ሰው ፡ ስለሆንኩ ፡ ተሰጠኝ ፤ አከበረኝም ፤ ብሎ ፡ በኢሳይያስ ፡ የተነገረ ፡ ሕይወቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ገንዘብ ፡ እንዳደረገ ፡ ሊነገር ፡ ይገባል) ፤ ሰበከ ፡ በእንተ ፡ ዝንቱ ፡ እንዘ ፡ ይብል ፡ እስመ ፡ መንፈስ ፡ ዘዚኣየ ፡ በህላዌ ፡ ለሊሁ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌየ (ሰው ፡ ስለሆንኩ ፡ በህልውናዬ ፡ ያለመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተሰጠኝ ፡ ብሎ ፡ አስተማረ) ፤ ወለምንትኑ ፡ ተሰመይኩ ፡ መሲሐ (እንኪያ ፡ ስለምን ፡ መሲሕ ፡ ተባልኩ) ፤ ዘእንበለ ፡ ዳዕሙ ፡ ሶበ ፡ ኮንኩ ፡ ሰብአ (ነፍስን ፡ ሥጋን ፡ ብዋሐድ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ብሎ ፡ አስተማረ) ፤ ወዘሰ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእንተ ፡ ሥርዓተ ፡ ትስብእት ፡ ውእቱ (መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተሰጠው ፡ የተባለ ፡ ለሰውነቱ ፡ በሚገባ ፡ ነው ፡፡ አንድም ፡ ሰው ፡ ስለሆነ ፡ ስለከበረ ፡ ሥጋ ፡ ነው) ፤ ወእመ ፡ አኮሰ ፡ እስመ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘዚኣሁ ፡ ውእቱ ፡ በህላዌ ፡ መለኮት (ሰው ፡ ካልሆነማ ፡ በባሕርየ ፡ መለኮቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ገንዘቡ ፡ ነውና ፤ አንድም ፡ የባሕርይ ፡ ሕይወቱ ፡ ነውና ፡ እንደምንተሰጠው ፡ ይባላል) ፤ ዘከመ ፡ እግዚአብሔር ፡ በእግዚአብሔር ፡ በከመ ፡ ይቤ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፍጹም (አብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ህልው ፡ ሁኖ ፡ እንዲኖር ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስም ፡ በባሕርየ ፡ መለኮቱ ፡ ገንዘቡ ፡ ነውና ፡ ሰውማ ፡ ካልሆነ ፡ እንደምን ፡ ተሰጠው ፡ ይባላል) ፤ ወዝግብር ፡ ኢኮነ ፡ ክፉለ ፡ ዘከመ ፡ ፩ዱ ፡ እምነቢያት (ይህ ፡ ክብር ፡ ከነቢያት ፡ እንደአንዱ ፡ ሊያከብረው ፤ በተከፍሎም ፡ የተሰጠው ፡ አይደለም) ፤ ወኢበእንተዝ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ መንፈሰ ፡ እግዚአብሔር ፡ በእንተ ፡ ሥርዓት (በጸጋም ፡ ሊያከብረው ፡ በተከፍሎ ፡ የተሰጠው ፡ አይደለም) ፤ አላ ፡ በከመ ፡ ይቤ ፡ ኢሳይያስ ፡ ነቢይ ፡ ሶበ ፡ ፈቀደ ፡ ይምሀረነ ፡ ፍጻሜ ፡ ግብሩ ፡ ኈለቈ ፡ ዘንተ ፡ 7ተ ፡ ጊዚያተ ፡ ወይቤ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ መንፈሰ ፡ እግዚአብሔር ፡ መንፈሰ ፡ ጥበብ ፣ መንፈሰ ፡ አእምሮ ፣ መንፈሰ ፡ ምክር ፣ መንፈሰ ፡ ልቡና ፣ መንፈሰ ፡ ኃይል ፣ መንፈሰ ፡ ፈሪሃ ፡ እግዚአብሔር (ለምዕመናን ፡ የሚሰጠውን ፡ ፍጹም ፡ ክብሩን ፡ ያስረዳ ፡ ዘንድ ፡ በወደደ ፡ ጊዜ ፡ ኢሳይያስ ፡ እንዲህ ፡ ብሎ ፡ መላልሶ ፡ እንደተናገረ ፡ ገንዘቡ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ በጸጋ ፡ ሊያከብረው ፡ የተሰጠ ፡ አይደለም ፡፡ አንድም ፡ ለምዕመናን ፡ የሚሰጠውን ፡ ፍጹም ፡ ክብሩን ፡ ያስረዳ ፡ ዘንድ ፡ ኈለቈ ፡ ዘንተ ፡ 7ተ ፡ ጊዜያተ (ይህን ፡ ሰባት ፡ ጊዜ ፡ መላልሶ ፡ ተናገረ ፡ እንጂ) ፤ እስመ ፡ ኍልቈ ፡ ፯ ፡ በኀበ ፡ ዕብራውያን ፡ ፍጹም ፡ ውእቱ (፯ ፡ ማለት ፡ በዕብራውያን ፡ ዘንድ ፡ ፍጹም ፡ ነውና ፡ ለምዕመናን ፡ የሚሰጠውን ፡ ፍጹም ፡ ክብሩን ፡ ያስረዳ ፡ ዘንድ ፡ በወደደ ፡ ጊዜ ፡ ኢሳይያስ ፡ እንደተናገረ ፡ ገንዘቡ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ በጸጋ ፡ ሊያከብረው ፡ የተሰጠው ፡ አይደለም)” ፡ በማለት ፡ ቁልጭ ፡ አድርጎ ፡ ያስረዳል ፡፡ (ሃይ. አበው ፡ ዘሳዊሮስ ፡87 ፡ 17-19 ፡ አንድምታ ፡ በሊቀ ፡ ሊቃውንት ፡ ዕዝራ ፡ የተዘጋጀ) ፡፡ ቄርሎስም ፡ በድርሳኑ ፡ በአካል ፡ ተቀብሎታል ፡ የሚለውን ፡ አጽንቶታልና ፡ ይመልከቱት ፡፡
2ኛ‹‹‹‹‹“በፀጋው ፡ ነው ፡ ከተባለ ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡ ብለናልና ፡ በቃልና ፡ በሥጋ ፡ መካከል ፡ ልዩነት ፡ ወይም ፡ ሁለትነት ፡ የለምና ፡ የቃል ፡ ሕይወት ፡ የጸጋ ፡ ሕይወት ፡ መሆኑ ፡ ነው ፡፡ የጸጋ ፡ ሕይወት ፡ ያለው ፡ አምላክ ፡ ደግሞ ፡ የለንም ፡፡ እንዲህ ፡ ከሆነ ፡ እርሱ ፡ ፍጡር ፡ አምላክነቱም ፡ የጸጋ ፡ መሆኑ ፡ ስለሆነ ፡ እንዲህ ፡ ማለትንም ፡ አምላክ ፡ ከእኛ ፡ ያርቅልን”››››››››ብለህ ፡ ለጠየቅኸው ፡ ቃል ፡ ከላይ ፡ ቅዱስ ፡ ሳዊሮስ ፡ “ወዝግብር ፡ ኢኮነ ፡ ክፉለ ፡ ዘከመ ፡ ፩ዱ ፡ እምነቢያት (ይህ ፡ ክብር ፡ ከነቢያት ፡ እንደአንዱ ፡ ሊያከብረው ፤ በተከፍሎም ፡ የተሰጠው ፡ አይደለም) ፤ ወኢበእንተዝ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ መንፈሰ ፡ እግዚአብሔር ፡ በእንተ ፡ ሥርዓት (በጸጋም ፡ ሊያከብረው ፡ በተከፍሎ ፡ የተሰጠው ፡ አይደለም) ፤ አላ ፡ በከመ ፡ ይቤ ፡ ኢሳይያስ ፡ ነቢይ ፡ ሶበ ፡ ፈቀደ ፡ ይምሀረነ ፡ ፍጻሜ ፡ ግብሩ ፡ ኈለቈ ፡ ዘንተ ፡ 7ተ ፡ ጊዚያተ ፡ ወይቤ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ መንፈሰ ፡ እግዚአብሔር ፡ መንፈሰ ፡ ጥበብ ፣ መንፈሰ ፡ አእምሮ ፣ መንፈሰ ፡ ምክር ፣ መንፈሰ ፡ ልቡና ፣ መንፈሰ ፡ ኃይል ፣ መንፈሰ ፡ ፈሪሃ ፡ እግዚአብሔር (ለምዕመናን ፡ የሚሰጠውን ፡ ፍጹም ፡ ክብሩን ፡ ያስረዳ ፡ ዘንድ ፡ በወደደ ፡ ጊዜ ፡ ኢሳይያስ ፡ እንዲህ ፡ ብሎ ፡ መላልሶ ፡ እንደተናገረ ፡ ገንዘቡ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ በጸጋ ፡ ሊያከብረው ፡ የተሰጠ ፡ አይደለም”›››››በማለት ፡ አሥረግጦ ፡ ስለተናገረ ፡ በጸጋ ፡ አላልነውም ፡ ያልተጻፈ ፡ አታንብቡ፡፡
3ኛ‹‹‹‹‹‹ “እንዲሁም ፡ ሕይወት ፡ የሆነው ፡ በአካሉ ፡ ነው ፡ ከተባለ ፤ ደግሞ ፡ ሌላ ፡ ጥያቄ ፡ ያስነሳል ፡፡ ይኸውም ፡ ሥጋ ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ሕይወትነት ፡ የተቀበለው ፡ በተዋሕዶ ፡ ነው ፡ በኅድረት?በኅድረት ፡ እንዳይባል ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡ ስላልን ፡ ምንታዌ ፡ ስለሌለ ፡ አንዱን ፡ አካል ፡ በአንዱ ፡ ማሳደር ፡ ይሆንብናል ፤ በሥላሴ ፡ ደግሞ ፡ ኃዳሪና ፡ ማኅደር ፡ የለም ፤”›››››››ብለህ ፡ ተናግረሀል ፡፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ በአካል ፡ ገንዘቡ ፡ አደረገ ፡ ሥንል ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሥጋ ፡ ለበሰ ፡ ተዋሐደ ፡ ማለታችን ፡ እዳልሆነ ፡ በደንብ ፡ አድርገህ ፡ ልትረዳው ፡ ተገቢ ፡ ነውና ፡ ከላይ ፡ ሳዊሮስ ፡ እንደገለጠው ፡ “መንፈስ ፡ ዘዚአየ ፡ በህላዌ ፡ ለሊሁ ፡ ኃደረ ፡ ላዕሌየ (የባሕርይ ፡ ሕይወቴ ፡ የሚሆን ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ አደረ/ተሰጠኝ” ፡ አለን ፡ እንጅ ፤ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እኔን ፡ ተዋሐደ ፡ አላለም ፡፡ ይህ ፡ ማለት ፡ አካላዊ ፡ የባሕርይ ፡ ኅድረት ፡ ነው ፡ እንደ ፡ ምዕመናን ፡ የጸጋ ፡ አይደለም ፡፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ የተቀበለው ፡ በባሕርይ ፡ ኅድረት ፡ ነውና ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሥጋን ፡ ተዋሐደ ፡ ወደሚል ፡ ክሕደት ፡ የሚያስገባ ፡ አይደለም ፡ ልንልዎት ፡ እንወዳለን ፡፡ ለዚህም ፡ ነው ፡ ቅዱስ ፡ ሳዊሮስ ፡ “ወበዝ ፡ ግብር ፡ ኢኮነ ፡ ክፉለ ፡ ዘከመ ፡ ፩ዱ ፡ እምነቢያት (ይህ ፡ ክብር ፡ ከነቢያት ፡ እንደ ፡ አንዱ ፡ ሊያከብረው ፡ በተከፍሎ ፡ የተሰጠው ፡ አይደለም)” ፡ ብሎ ፡ ሐተታውን ፡ ልቡናን ፡ ደስ ፡ በሚያሰኝ ፡ ምሥጢር ፡ መናገሩ ፡፡ የምሥጢረ ፡ ቅብዐተ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ፆመኞቹ ፡ መለካውያን ፡ እናንተ ፡ ግን ፤ “ወበዝ ፡ ግብር ፡ ኢኮነ ፡ ክፉለ ፡ ዘከመ ፡ 1ዱ ፡ እምነቢያት” ፡ የሚለውን ፡ ግዕዝ ፡ ስትተረጕሙ ፡ “በዚህ ፡ ግብር ፡ ተዋሕዶ ፡ ጠፍቶ ፡ ከነቢያት ፡ እንደ ፡ አንዱ ፡ የሆነ ፡ አይደለም” ፡ ብላችሁ ፡ ግዕዝንም ፡ ምሥጢረ ፡ መጻሕፍትንም ፡ እንደምትጾሙ ፡ ይህ ፡ ትክክለኛ ፡ ማረጋገጫ ፡ ነው ፡፡
4ኛ‹‹‹‹‹‹‹በተዋሕዶ ፡ ነው ፡ እንዳንል ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ ያሰኛል ፤ ቃልንም ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስንም ፡ ከሥጋ ፡ አዋሕዶ ፡ ሁለቱን ፡ አካላት ፡ አንድ ፡ ወደማድረግ ፡ ይወስዳል ፡፡ ስለዚህ ፡ ልንጠነቀቅና ፡ ልንፈራ ፡ የምንናገረውን ፡ ልናስተውል ፡ ይገባናል ፡፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ተቀባ ፡ (ሕይወት ፡ ሆነው) ፡ ሲባል ፡ በኅድረትም ፡ በተዋሕዶም ፡ ካልሆነ ፡ እንዴት ፡ ሊሆን ፡ ይችላል?››››››››››ብለህ ፡ ተይቀሀል ፡ እኛ ፡ የምንለውና ፡ የምናምነው ፡ ወልደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሕያው ፡ ወልደ ፡ ማርያም ፡ ሥግው ፡ በሥግውነቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ በመላ ፡ በአካል ፡ ተቀብሎ ፡ የባሕርይ ፡ ክብርን ፡ ከበረ ፡ ብለን ፡ እንጅ ፤ በፀጋ ፡ ከበረ ፡ ብለን ፡ አይደለም ፡፡ ተቀበለ ፡ የተባለውም ፡ ስለሥጋ ፡ እንግድነት ፡ ነው ፡፡ በባሕርየ ፡ መለኮቱ ፡ በእርሱ ፡ ህልው ፡ ሆኖ ፡ የሚኖር ፡ የባሕርይ ፡ ሕይወቱ ፡ እንደሆነ ፡ መጻሕፍት ፡ ይመሠክሯል ፡ (ሃይ. አበው ፡ ዘሳዊሮስ ፡ '7 ፡ 07-09) ፡፡ ለጠየቁት ፡ ጥያቄዎት ፡ መልሱ ፡ በፀጋ ፡ ነቢያትን ፣ ሐዋርያትን ፣ ቅዱሳንን ፣ ምዕመናንን ፣ ካህናትን ፡ ያከብረናል ፡፡ የእርሱ ፡ መክበር ፡ ግን ፡ ከእኛ ፡ የተለየ ፡ የባሕርይ ፣ የማይወሰድ ፣ የማይነሣ ፣ ሲሆን ፤ ለሐዋርያት ፣ ለነቢያት ፡ አበው ፣ ለምዕመናን ፡ ለእኛ ፡ ደግሞ ፡ በልክ ፡ በመጠን ፣ በመሥፈርት ፡ የሚሰጥ ፣ የፀጋ ፣ ኃጢአትን ፡ በሠራን ፡ ጊዜ ፡ የሚነሣ ፡ (የሚወሰድብን) ፡ ነው ፡፡ በሐዋርያትና ፡ በክርስቶስ ፡ መካከል ፡ ያለው ፡ ልዩነትም ፡ ሐዋርያት ፡ በፀጋ ፡ ሲከብሩበት ፤ በልክ ፡ መስፈርት ፡ ሲቀበሉት ፤ ክርስቶስ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ክብርን ፡ ከብሮበታል ፤ አልቦ ፡ መሥፈርት ፡ ተቀብሎታል ፤ ልዩነቱ ፡ ይህ ፡ ነው ፡፡ ቅዱስ ፡ ዳዊትም ፡ የእርሱ(የክርስቶስ) ፡ መቀባት(መክበር) ፡ ልዩ ፡ መሆኑን ፡ ሲያጠይቅ ፡ “ቀብዓከ ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክከ ፡ ቅብዓ ፡ ትፍስሕት ፡ እምእለከማከ (እግዚአብሔር ፡ አምላክህ ፡ እንዳንተ ፡ ያሉ ፡ ካህናትና ፡ ነቢያት ፡ ከተቀቡት ፡ ይልቅ ፡ የደስታ ፡ ዘይትን ፡ ቀባህ)” ፡ መዝ ፡ #4 ፡ t ፡ 7) ፡ ብሏል ፡፡ ቅዱስ ፡ ጳውሎስም ፡ ክቡር ፡ ዳዊት ፡ እምእለ ፡ ከማከ ፡ ያለውን ፡ ዘይኄይስ ፡ እምእሊአሆሙ ፡ ብሎ ፡ አጉልቶ ፡ ተናግሯል (ዕብ ፡ ምዕ ፡ 1 ፡ t ፡ 9) ፤ አፈወርቅ ፡ ዮሐንስም ፡ “እስመ ፡ ለእግዚእ ፡ ክርስቶስ ፡ አኮ ፡ በመሥፈርት ፡ ዘተውህቦ ፡ መንፈስ ፡ ይቤ ፡ ቅብዓ ፡ ትፍስሕት ፡ እምእለከማ (መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ለክርስቶስ ፡ በልክ ፡ በመጠን ፡ የተሰጠው ፡ አይደለምና ፡ ቅብዓ ፡ ትፍስሕት ፡ እምእለከማከ ፡ አለ” ፡ ድር ፡ 3 ፡ ብሎ ፡ ዘአልቦ ፡ መሥፈርት ፡ ሲል ፡ ገልጦታል ፡፡ ቅዱስ ፡ ቄርሎስ ፡ ደግሞ ፡ “በቅብዓት ፡ ነከራ ፡ እምእለ ፡ ተሳተፎሙ ፡ ዘውእቶሙ ፡ ንሕነ ( እኛ ፡ ካገኘነው ፡ ክብር ፡ በበለጠ ፡ ክብር ፡ ከበረ ፤ እምእለ ፡ ተሳተፎሙ ፡ የተባልን ፡ እኛ ፡ ነን” ፡ (ጰላድ ፡ 05 ፡ t ፡ 1-9) ፡ በማለት ፡ አወሥጥሮ ፡ ተናግሮታል ፡፡ ቅዱሳን ፡ አባቶቻችን ፡ እንዲህ ፡ እንደነገሩን ፤ የክርስቶስ ፡ መክበር ፡ የባሕርይ ፡ ሲሆን ፤ የሐዋርያት ፡ መክበር ፡ ግን ፡ በጸጋ ፡ ነውና ፡ ልዩነቱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡፡
ይህ ፡ በእንዲህ ፡ እንዳለ ፡ መገልበጥ ፡ ልማዳችሁ ፡ የሆናችሁ ፡ በተዋሕዶ ፡ ከበረ ፡ ወልድ ፡ ቅብዕ ፡ ብላችሁ ፡ የምታምኑ ፡ ሁላችሁም ፡ ከላይ ፡ እርስዎ ፡ እንደጠቀሱት ፡ “በሦስት ፡ ከፍለን ፡ እንመለከታቸዋለን” ፡ ብለው ፡ የጠቀሷቸውን ፡ በአባ ፡ ጎርጎርዮስ ፡ አባባል ፡ “የቅብዓት ፡ ዘውጎች” ፡ የሚባሉ ፡ ተረት ፡ ተረቶችን ፡ ከኪዳነ ፡ ወልድ ፡ ገልብጣችሁ ፡ አስቀምጣችኋል ፡፡ እስኪ ፡ የሚጠቅም ፡ የሚረባ ፡ ከሆነ ፡ የሰሞንኞቹ ፡ የእናንተ ፡ ባህል ፡ ምን ፡ እንደሚባል ፡ እናስቀምጥላችሁ ፡፡
ጥያቄ ፡ ለዶማው ፡ ቢለዋ
1ኛ‹‹‹‹‹‹በተዋሕዶ ፡ ከበረ ፡ ብለህ ፡ ስታምነው ፡ ማን ፡ ነው ፡ በተዋሕዶ ፡ የከበረው?ማን ፡ አከበረው?ለምን ፡ ከበረ?