የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና ፡
የቤተ ፡ አይሁድ ፡
ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
ወንድሞች
፡ እህቶች ፡ እንደምን ፡ አላችሁልኝ?ሕይወት ፡ እንዴት ፡ ነው?ሁሉም ሠላም?አምላክ ፡ ይመሥገን ፡፡ የዛሬው ፡ መልእክቴ ፡ የሚያተኩረው ፡ በቅርቡ
፡ አንዳንድ ፡ ወንድሞች ፡ “እናንተ ፡ ቅብዐቶች ፡ ለመስቀልና ፡ ለጻድቃን ፡ ስግደት ፡ አይገባም ፡ ብላችሁ ፡ ጽፋችኋል ፡
በመጽሐፋችሁ” ፡ እያሉ ፡ ሲከሱን ፡ ሲወቅሱን ፡ አስተውያለሁ ፡፡ የቅብዐቱን ፡ ጣዕመ ፡ ምሥጢር ፡ ሳያውቁት ፡ በልካችን ፡
እያበዙ ፡ አንድ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ሲበዘብዙት ፡ ብንመለከትም ፡ የፍርዱ ፡ ባለቤት ፡ አምላክ ፡ እሱ ፍርዱን ፡ ያስቀምጣል
፡ ፡ ማቴ 12፡ 32 ፤ ብዙ ፡ ወንድሞችና ፡ እህቶችንም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ምክንያት ፡ ድጋሚ ፡ አጥምቀው ፡ እስላም ፡ አረሚ
፡ አድርገውበታል ፤ እያደረጉበትም ፡ ይገኛል ፡፡ ስለዚህ ፡ እውነታው ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ መጻፍ ፡ ስላለብኝ ፡ ከመጽሐፉ
፡ ያለውን ፡ ቃል ፡ ሳልጨምር ፡ ሳልቀንስ ፡ እንዲህ ፡ አርበዋሁ፡፡ አንብብዋ ፡ ለመልእት ፡ እምጥታ ፡ እስከ ተፍጻሜታ ፤
እንዲሉ ፤ ከመጀመሪያው ፡ እስከመጨረሻው ፡ ሳያነቡ ፡ የወደቁት ፡ ካሮች ፡ እኛን ፡ ማላመጥ ፡ አፋቸውን ፡ መፍቻ ፡ ስላደረጉት
፡ ነው ፡ እንጅ ፤ በወልደ ፡ አብ ፡ ላይ ፡ የተገለጠው ፡ ቃል ፡ ለቅዱሳንና ፡ ለመስቀል ፡ ስግደት ፡ አያስፈልግም ፡ የሚል
፡ አይደለም ፡፡ ስለሆነም ፡ የመጽሐፉን ፡ ሙሉ ፡ ኃይለ ፡ ቃል ፡ እንደሚከተለው ፡ ላስነብባሁ፡፡
የጌታችን
፡ የባሕርይ ፡ ልጅቱ ፡ እንዴት ፡ ነው? ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ተብሎ ፡ ይመረመራልን? ፡ ቢሉ ፡፡ የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡
ልደት ፡ ይቅርና ፡ የእኛ ፡ የፀጋ ፡ ልጅነት ፡ እንኳን ፡ አይነገርም ፡ አይመረምርም ፡፡ “ግሩም ፡ ቅድሳቲከ ፡ አቡሁ ፡
ለእግዚእነ ፡ ወመድኃኒነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ዘውእቱ ፡ ባሕቲቱ ፡ በእንተ ፡ ባሕቲትከ ፡ አቡሁ ፡ በጽድቅ ፡ አንተ ፡
ወኢይትረከብ ፡ ልደቱ ፡ ዘእምኔከ” ፡ እንዳለ ፡ ቄር ፡ ቅዳሴ ፡ t ፡ 10 ፡፡
የእኛ
፡ የጸጋ ፡ ልጅነታችን ፡ እንዳይመረመር ፡ የአይሁድ ፡ አለቃቸው ፡ ኒቆዲሞስ ፡ የሚባል ፡ የቤተ ፡ አይሑድ ፡ አለቃቸው ፡ ምሁረ ፡ ኦሪት ፡ ነበር ፡ እሱም ፡ የጌታችን ፡ የትምህርቱን
፡ ስፋት ፣ የተአምራቱን ፡ ብዛት ፡ አይቶ ፡ ሌሊት ፡ ሂዶ ፡ ለጌታችን ፡ ሰገደለት ፤ ስለምን ፡ ሌሊት ፡ ሄደ? ፡ ቢሉ ፤
አይሁድ ፡ ክርስቶስ ፡ ካስተማረ ፡ ወዲህ ፡ እኛን ፡ ቆሎ ፡ በስልቻ ፣ ዳቦ ፡ በቅንብቻ ፡ ይዞ ፡ የሚጠይቀን ፡ አጣን ፤
አሁንም ፡ ለእሱ ፡ ሂዶ ፡ የሚሰግድለት ፡ ቤቱ ፡ ይተኮስ ፣ ንብረቱ ፡ ይወረስ ፡ ብለው ፡ ሕግ ፡ ሠርተው ፡ ስለነበር ፡
ስለዚህ ፡ ሌሊት ፤ ሂዶ ፡ ሰገደለት ፡ ሙሉ ፡ ታሪኩን ፡ ከዮሐ
፡ ወን ፡ ምዕ 3 t 1-8 ፡ ተመልከት
፡፡ “መንፈስ ፡ ኀበ ፡ ዘፈቀደ ፡ ይነፍሕ ፡ ወቃሎ ፡ ትሰምዕ ፡ ወኢተአምር ፡ እምኀበ ፡ ይመጽእ ፡ ወኀበሂ ፡ የሐውር ፡
ወከማሁኬ ፡ ውእቱ ፡ ኩሉ ፡ ዘይትወለድ ፡ እመንፈስ ፡ ቅዱስ”፡ ብሎ ፡ በምሳሌ ፡ ነገረው ፡፡ “መንፈስ ፡ ኀበ ፡ ዘፈቀደ
፡ ይነፍሕ” ፡ ማለቱ ፡ ነፋስ ፡ በፈቀደው ፡ ይነፍሳል ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡ ምነዋ ፡ የነፋስ ፡ ምን ፡ ፈቃድ ፡ አለውና ፡
በወደደው ፡ ይነፍሳል ፡ አለ?? ፡ ቢሉ ፤ ቀኝ ፡ ነፈሰ ፣ ግራ ፡ ነፈሰ ፡ ማለት፡ አለና ፡ ስለዚህ ፡ ወደ ፡ ወደደው ፡
ይነፍሳል ፡ አለ ፡፡ “ወቃሎ ፡ ትሰምዕ” ፡ ማለቱ ፡ የነፋስ ፡ ቃሉን ፡ ትሰማዋለህ ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡
የነፋስ ፡ ቃል ፡ ረቂቅ ፡ አይደለምን ፡ እንደምን ፡ ይሰማዋል? ፡ ቢሉ
፤ ዛፉን ፡ ሲአናውጥ ፣ ባሕሩን ፡ ሲገስጽ ፡ በግብሩ ፡ ይሰማልና ፡ ስለዚህ ፡ ቃሉን ፡ ትሰማለህ ፡ አለ ፡፡ “ወኢተአምር
፡ እምኀበ ፡ ይመጽእ ፡ ወኀበሂ ፡ የሐውር” ፡ ማለቱ ፡ ነፋስ ፡ ሲመጣ ፡ ሲሔድ ፡ አታይም ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡ ምነዋ ፡ ግራ
፡ ነፈሰ ፣ ቀኝ ፡ ነፈሰ ፡ ይባል ፡ የለምን?ስለምን ፡ አታይም ፡ አለ? ፡ ቢሉ ፤ የነፋሳትን ፡ መውጫ ፡ የነፋሳትን ፡ መግቢያ
፡ አታውቅም ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡ “ወከማሁኬ ፡ ውእቱ ፡ ኩሉ ፡ ዘይትወለድ ፡ እመንፈስ ፡ ቅዱስ “ ፡ ማለቱም ፡ ከመንፈስ ፡
ቅዱስ ፡ የሚወለድ ፡ ሰው ፡ እንደዚህ ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡ ይህ ፡ የሰም ፡ አነጋገር ፡ ነው ፡፡
ወርቁ
፡ ግን ፡ መንፈስ ፡ የተባለ ፡ እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡፡ “መንፈስ ፡ ኀበ ፡ ፈቀደ ፡ ይነፍሕ” ፡ ማለቱ
፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በወደደው ፡ ሕሊና ፡ ያድራል ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡ ምነዋ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አድልዎ ፡ ምርጫ ፡ አለበትን?
፡ ቢሉ ፤ ሃይማኖት ፡ ተምሮ ፣ ምግባር ፡ ትሩፋት ፡ ሠርቶ ፡ ፣ ንስሐ ፡ ገብቶ ፡ ባገኘው ፡ ልቡና ፡ ያድራል ፡ ሲል ፡
እንጅ ፤ አድልዎ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘንድ ፡ የለም ፡፡ “ወቃሎ ፡ ትሰምዕ” ፡ ማለቱ ፡ ቃሉን ፡ ትሰማዋለህ ፡ ሲል ፡
ነው ፡፡ ምነዋ ፡ የመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ቃል ፡ ረቂቅ ፡ አይደለምን? ፡ ቢሉ ፤ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ያደረበት ፡ ሰው ፡ በደመና
፡ ሲበር ፣ ሕገ ፡ ወንጌልን ፡ ሲአስተምር ፡ ይሰማልና ፡ ስለዚህ ፡ “ወቃሎ ፡ ትሰምዕ” ፡ አለ ፡፡ “ወኢተአምር ፡ እምኀበ
፡ ይመጽእ ፡ ወኀበሂ ፡ የሐውር” ፡ ማለቱ ፡ በሙሴ ፡ የነበረ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በኢያሱ ፤ በኤልያስ ፡ የነበረ ፡ መንፈስ
፡ ቅዱስ ፡ በኤልሳዕ ፡ ሲአድር ፡ እንልታየ ፤ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ መጥቶ ፡ በሰው ፡ ላይ ፡ ሲአድር ፡ ፣ ከሰው ፡ ሲለይ
፡ አይታይም ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡ በዚህ ፡ ካልታወቀ ፡ በምን ፡ ይታወቃል? ፡ ቢሉ፤ ሃይማኖት ፡ በማጽናቱ ፣ ምግባር ፡ በማሠራቱ
፡ ፣ ንሥሐ ፡ በማስገባቱ ፡ ይታወቃል ፡፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተነሣው ፡ ሰው ፡ በምን ፡ ይታወቃል? ቢሉ ፤ ቃለ ፡ ሃይማኖት
፡ ሲነገር ፤ ሰይጣን ፡ በልቡናው ፡ ገብቶ ፡ ቃለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ያስንቀዋል ፣ የሥጋውን ፡ ሥራ ፡ ያሳስበዋል ፣ ነገር
፡ ዘርቅ ፡ ያናግረዋል : “የአትትዎ ፡ ለኃጥእ ፡ ከመ ፡ ኢይርአይ ፡ ስብሐተ ፡ እግዚአብሔር” ፡ እንዳለ ፡ ኢሳይያስ ፡ ምዕ
26 t9 ፡፡
የጌታ
፡ የባሕርይ ፡ ልጅነቱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ተብሎ ፡ ካልተነገረ ፡ የርሱ ፡ የባሕርይ ፡ የእኛ ፡ የጸጋ ፡ መሆኑ ፡ በምን ፡ ይታወቃል? ፡ ቢሉ ፤ በግብሩ ፡ ይታወቃል ፣ መጽሐፍም
፡ ይመሠክራል ፡፡
ሀ. በግብሩ ፡ ይታወቃል ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ነው?
እኛ
፡ ስንወለድ ፡ አፈማኅፀን ፡ ሳንፈታ ፣ ድንግልና ፡ ሳናፈርስ ፡ መወለድ ፡ አይቻለንም ፤ ጌታችን ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ
፡ ነውና ፡ አፈ ፡ ማኅፀን ፡ ሳይፈታ ፣ ድንግልና ፡ ሳያፈርስ ፡ በድንግልና ፡ ተፀንሶ ፡ በድንግልና ፡ ተፀንሶ ፡ በድንግልና
፡ ተወለደ ፡ ይህ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነቱን ፡ ያጠይቃና ፡ በግብሩ ፡ ይታወቃል ፡ ማለት ፡ ስለዚህ ፡ ነው ፡፡ “ወአማኑኤልሰ ፡ አንቀጸ ፡ ድንግልና ፡ ኢፈትሐ ፡ ከመ ፡ ሰብእ ፡ ወመዛግብተ ፡ ድንግልና ፡ ኢበተከ
፡ እስመ ፡ አምላክ ፡ ውእቱ ፡ ወበከመ ፡ ቦአ ፡ በማኅፀን ፡ ተወልደ ፡ ዘእንበለ ፡ ሙስና ፡ እስመ ፡ ከማሁ ፡ ተፀንሰ ፡
ዘእንበለ ፡ ሙስና ፡ ወመጽአ” ፡ እንዳለ ፡ ተረፈ ፡ ቄርሎስ ፡፡
ለ. መጽሐፍ ፡ እንዴት ፡ ይመሠክራል?
መጽሐፍ
፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ይመሰክራል? ፡ ቢሉ ፤ ቅዱስ ፡ ጳውሎስ ፡ በዕብ ፡ ምዕ 2 ፡ t 01 ፡
“ዘቀደሶሙ ፡ ለእሙንቱ ፡ ወእለሂ ፡ ተቀደሱ ፡ ኅቡረ ፡ እም1ዱ (እነሱን
፡ ያከበረና ፡ እሱና ፡ የከበሩ ፡ እነሱ ፡ ካንድ ፡ ከእግዚአብሔር ፣ ከአንድ ፡ ከአብርሃም ፡ ተገኝተዋልና) ፡ ወበእተዝ ፡
ኢየኃፍር ፡ አኃውየ ፡ ብሂሎቶሙ(ስለዚህ ፡ ወንድሞቼ ፡ ማለትን ፡ አያፍርም)” ፤ ብሎ ፡ የተናገረውን ፤ ቅዱስ ፡ ዮሐንስ ፡
አፈወርቅ ፡ “ነጽርኬ ፡ ከመ ፡ ሀሎ ፡ ርኅቀት ፡ ማዕከሌነ ፡ ወማዕከሌሁ ፡ ውእቱ ፡ ወልድ ፡ ዘበአማን ፡ ወንሕነ ፡ ውሉድ
፡ ዘበጸጋ ፡ ውእቱ ፡ ፈጣሪ ፡ ወንሕነ ፡ ፍጡራን ፡ ውእቱ ፡ መድኅን ፡ ወንሕነ ፡ ድኁናን” ፡ ብሎ ፡ ተርጕሞታል ፡፡ “ውእቱ
፡ ወልድ ፡ ዘበአማን” ፡ ማለቱ ፡ የርሱ ፡ ወልድ ፡ መባሉ ፡ የባሕርይ ፡ ነው ፤ እኛ ፡ ውሉድ ፡ መባላችን ፡ የጸጋ ፡ ነው
፡፡ እርሱ ፡ ፈጣሪ ፡ ነው ፤ እኛ ፡ ፍጡራን ፡ ነን ፤ እርሱ ፡ መድኅን ፡ መባሉ ፡ የባሕርይ ፡ እኛ ፡ ድኁናን ፡ መባላችን
፡ የጸጋ ፡ ነው ፡፡ በጸጋ ፡ ልጅነትና ፡ በባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ መካከል ፡ ያለውን ፡ ልዩነት ፡ ጠንቅቆ ፡ ማወቅ ፡ ይገባል
፡፡ መጽሐፍ ፡ ይመሰክራል ፡ ማለት ፡ ስለዚህ ፡ ነው ፡፡
ዳግመኛም
፡ እኛ ፡ የጸጋ ፡ ልጆች ፡ 3ት ፡ መዓልት ፡ 3ት ፡
ሌሊት ፡ በከርሠ ፡ መቃብር ፡ አድረን ፡ መነሣት ፡ አይቻለንም ፤ እሱ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ነውና ፡ 3ት ፡
መዓልት ፡
3ት
፡ ሌሊት ፡ በከርሠ ፡ መቃብር ፡ አድሮ ፡ መግነዝ ፡ ፍቱልኝ ፡ መቃብር ፡ ክፈቱልኝ ፡ ሳይል ፡ ተነሣ ፡ ፤ በግብሩ ፡ ይታወቃል
፡ ማለት ፡ ስለዚህ ፡ ነው ፡፡ “እፎ ፡ ኢኮነ ፡ ወልደ ፡ ዘበአማን ፡ እንዘ ፡ ሰማዕተ ፡ ይከውኖ ፡ ትንሣኤ ፡ ሙታን” ፡
እንዳለ ፡ ቄርሎስ ፡፡ እንዲህ ፡ ማለቱ ፡ ሙቶ ፡ መነሣቱ ፡ የባሕርይ ፡ ለጅነቱን ፡ ያጠይቃል ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ነው?
፡ አግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ አልተነሣችምን? ፡ ልጅነቷ ፡ የጸጋ ፡ አይደለምን? ፡ ቢሉ ፤ የእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ መነሣት
፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡፡ እንደምን ፡ ያጠይቃል? ፡ ቢሉ ፤ቅድስት ፡ ድንግል ፡ ማርያም ፡ የባሕርይ
፡ አምላክ ፡ የሆነውን ፡ ስለወለደች ፡ ተነሣች ፡ እንጅ ፤ በጸጋ ፡ ልጅነትማ ፡ የአቡነ ፡ ገብረ ፡ ሕይወት ፣ የአቡነ ፡
ተክለ ፡ ሃይማኖት ፡ እናቶችስ ፡ የጸጋ ፡ ልጆች ፡ አይደሉምን? ፡ ዳሩ ፡ ግን ፡ እነሱ ፡ የወለዱት ፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ ነውና
፡ አልተነሡም ፡ ገና ፡ ትንሣኤ ፡ ዘጉባዔን ፡ ይጠብቃሉ ፡፡ “እመሰ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ
፡ ቃል ፡ ዘከመ ፡ ኀደረ ፡ ላዕለ ፡ ኩሎሙ ፡ ቅዱሳን ፡ ወእሉ ፡ ኩሎሙ ፡ ቅዱሳን ፡ ሶበ ፡ ሞቱ ፡ ለምንት ፡ ኢተንሥኡ
፡ ዘእንበለ ፡ ዳዕሙ ፡ ዝንቱ ፡ ዘተወልደ ፡ እምእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ባሕቲቱ ፡ ተንሥአ ፡ እሙታን ፡ አመ ፡ ሣልስት ፡
እለት” ፡ እንዳለ ፡ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፡፡ እርሷ ፡ ግን ፡ ስለከዊነ ፡ ትስብእት ፡ በቅብዓተ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ
፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የሆነውን ፡ ወልዳለችና ፡ ሞታ ፡ ተነሣች ፡፡ እመቤታችን ፡ በልጅዋ ፡ ሥልጣን ፡ ተነሣች ፡ እንጅ ፡
በእርሷ ፡ ሥልጣን ፡ አልተነሣችም ፡ “ወአንሣእክዋ ፡ ለወላዲትየ” ፡ እንዳለ ፡፡ ጌታ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡ ነውና
፡ በገዛ ፡ ሥልጣኑ ፡ ተነሣ ፡፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ (በገዛ ፡ ሥልጣኔ ፡ ተነሣሁ)” ፡ እንዳለ ፡ ቄርሎስ
(ሃይ.አበው ፡ ምዕ ፡ 73 ፡ ክ
፡ 12፡ t ፡ 14) ፡፡
ይቀጥላል
ካሮቹ ፡ የወደቁት ፡ ይህንን ፡ ቃል ፡ ሳያዩ
፡ ቆርጠው ፡ በማንበባቸው ፡ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment