በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡
ቅዱስ ፡ አሐዱ ፡ አምላክ
ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ ፡ ክፍል ፡
ዐራት
በቅብዓት ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ሆነ ፡
ማለት ፡ ምን ፡ ማለት ፡ ነው?
============================================
በቅብዓት ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ሆነ ፡ ማለት ፡ ምሥጢሩ ፡ ምንድን ፡ ነው? ፡
ቢሉ ፤ ወልድ ፡ በሰውነቱ ፡ የባሕርይ ፡ ሕይወቱን ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ በመላ(ካለ ልክ ) ፡ ተቀብሎ ፡ ከአብ ፡ የባሕርይ
፡ ልደትን ፡ ተወለደ ፡ ማለት ፡ ነው ፡፡ ምነው ፡ ይህስ ፡ ቢሆን ፡ በአብ ፡ ያልተወለደ ፣ በራሱ ፡ ያልተወለደ ፣ ስለምን
፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተወለደ? ፡ ቢሉ ፤ ይህስ ፡ ወላዲ ፡ በሚመስለው ፡ ሕይወት ፡ ይወልዳል ፡ እንጅ ፡ በማይመስለው ፡
ሕይወት ፡ አይወለድም ፡፡ ለዚህም ፡ ምሣሌ ፡ ያሥረዳል ፤ እንዴት ፡ ያሥረዳል? ፡ ቢሉ ፤ እነሆ ፡ ዛሬ ፡ በደመ ፡ ነፍስ
፡ ሕያዋን ፡ የሆኑ ፡ እንስሳት ፡ ከእንስሳት ፡ ይወለዳ ፤ በነባቢት
፡ ነፍስም ፡ ሕያው ፡ የሆነ ፡ ሰውም ፡ ከሰው ፡ ይወለዳል ፡፡ በደመ ፡ ነፍስ ፡ ሕያው ፡ ያልሆነ ፡ ከእንስሳ ፤ በነባቢት
፡ ነፍስ ፡ ሕያው ፡ ያልሆነ ፡ ከሰው ፡ እንዳይወለድ ፤ እንደዚህም ፡ ሁሉ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ለአብ ፡ ሕይወቱ ፡ ስለሆነ
፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሕያው ፡ ያልሆነ ፡ ከአብ ፡ አይወለድምና ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሕይወትነት ፡ ከአብ ፡ ተወለደ ፡፡
“ወበከመ ፡ ለአብ ፡ ቦቱ ፡ ሕይወት ፡ ኀቤሁ ፡ ከማሁ ፡ ለወልድኒ ፡ ወሀቦ ፡ ሕይወተ ፡ ከመ ፡ ይኩን ፡ ሕይወት ፡ ኀቤሁ(ለአብ
፡ በራሱ ፡ ሕይወት ፡ እንዳለው ፡ እንዲሁ ፡ ለወልድም ፡ ሕይወት ፡ ይኖረው ፡ ዘንድ ፡ ሕይወትን ፡ ሰጠው ፤ እስመ ፡ ወልደ
እግዚአብሔር ፡ ወልደ ፡ እጓለ ፡ እመሕያው ፡ ውእቱ ፡ (የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ነውና))” ፡ እንዳለ ፡
ወንጌለ ፡ ዮሐንስ(ምዕ ፡ 5
፡ t 26) ፡፡
ወልድ ፡ እምቅድመ ፡ ዓለም ፡ በመለኮቱ ፡ ከአብ ፡ ሲወለድ ፡ በባሕርየ ፡ መለኮት
፡ መቀበል ፡ የለበትምና ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ተቀብሎ ፡ ተወለደ ፡ ይሉት ፡ ዘንድ ፡ አይገባም ፤ ዛሬ ፡ ግን ፡ በሥጋ
፡ ርስት(በሥጋነቱ) ፡ መቀበል ፡ አለና ፡ የባሕርይ ፡ ሕይወቱ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ተቀብሎ ፡ ከአብ ተወለደ ፡ ይባላል
፡ እንጅ ፡፡ “መኑ ፡ ውእቱ ፡ ወልዱ ፡ ዘተወፈየ ፡ ኵነኔ ፡ አብ ፡ እንበለ ፡ ሥጋሁ ፡ ወአኮ ፡ መለኮቱ ፤ ወመለኮትሰ ፡
ኢይትወፈይ ፡ ኵነኔ ፡ ወኢይነሥእ ፡ ሥልጣነ ፡ እመለኮት ፤ ወኢይሰይሞ ፡ መለኮት ፡ ለመለኮት (የፍትረትን ፡ ሁሉ ፡ ፍርድ
፡ የተቀበለ ፡ ልጁ ፡ ማን ፡ ነው? ፡ ከሥጋው ፡ መለኮትም ፡ አይደል ፡ መለኮትስ ፡ ፍርድን ፡ አይቀበልም ፡ ሥልጣንንም ፡
ከመለኮት ፡ አይወስድም ፡ መለኮትን ፡ መለኮት ፡ አይሾመውም)” ፡ እንዳሉ ፡ ሊቃውንት ፡ በመዝገበ ፡ ሃይማኖት(አንቀጽ ፡ 1 ፡ ቁ 35-36) ፡፡
እነሆ ፡ ዛሬ ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ልጅ ፡ እገሊት ፡ እናትህ ፤ እገሊት ፡ አባትህ
፡ ነው ፡ ካላሉት ፡ አባት ፡ እናቱን ፡ አየውቅም ፡፡ እንደዚህም ፡ ሁሉ ፡ ወልድ ፡ “እግዚአብሔር ፡ ይቤለኒ ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ( እግዚአብሔር
፡ አለኝ ፡ አንተ ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ዛሬ ፡ ወለድኩህ)” ፡ ማለቱ ፡ ወልድ ፡ ከአብ ፡ እንደተወለደ ፡ የማያውቅ ፡
ሁኖ ፡ አብ ፡ ነግሮት ፡ ነውን?ቢሉ ፤ እንደዚህስ ፡ አይደለም ፡ ይልቁንም ፡ ለሐዋርያት ፡ ያልጠየቁትን ፡ ምሥጢር ፡ ሲነግራቸው
፡ እንጅ ፡ ነው ፡፡ ማለትም ፡ አብ ፡ ለሐዋርያት ፡ ሲያስተምር ፡ ለወልድ ፡ የነገረ ፡ እየመሰለ ፡ ያስተምራቸዋል ፡፡ ሐዋርያት
፡ ግን ፡ ኋላ ፡ እየጠየቁ ፡ ይረዱታል ፤ ይህም ፡ ይታወቅ ፡ ዘንድ ፡ ዓርብ ፡ ሊሰቀል ፡ በምሴተ ፡ ሐሙስ ፡ “አባ ፡ ቅዱስ
፡ ዕቀቦሙ ፡ በስምከ” ፡ ብሎ ፡ ጸለየላቸው ፡፡ ሐዋርያት ፡ “ዕቀቦሙ” ፡ እየአለ ፡ የሚጸልይልን ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ በሞት
፡ ውሰዳቸው ፡ ሲል ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ጌታን ፡ ጠረጠሩት ፤ ጌታም ፡ ቢጠረጥሩት ፡ “ወኢይብለከ ፡ ከመ ፡ ትንሥኦሙ ፡ እምዓለም
፡ ዳዕሙ ፡ ከመ ፡ ትዕቀቦሙ ፡ እምእኩይ” ፡ ብሎ ፡ ጸለየላቸው ፡ እኩያን ፡ የተባሉ ፡ አጋንንት ፡ መናፍቃን ፡ ናቸው ፡
“ዕቀቦሙ” ፡ ማለቴም ፡ ከፍትወታተ ፡ እኩያት ፡ ከኃጣውእ ፡ ርኩሳት ፡ ጠብቃቸው ፡ ስልህ ፡ ነው ፡ እንጅ ፡ ከዚህ ፡ ዓለም
፡ በሞት ፡ ውሰዳቸው ፡ ስልህ ፡ አይደለም ፤ ብሎ ፡ ወልድ ፡ ለአብ ፡ የነገረው ፡ መሰለ ፤ ይህንን ፡ ጊዜ ፡ ወልድ ፡
“ዕቀቦሙ” ፡ ብሎ ፡ የጸለየውን ፡ ለሕይወት ፡ እንጅ ፡ ለሞት ፡ እንዳልሆነ ፡ አብ ፡ የማያውቅ ፡ ሆኖ ፡ ወልድ ፡ ነግሮት
፡ አይደለም ፡ ለሐዋርያት ፡ ለማስረዳት ፡ ነው ፡ እንጅ ፡፡ እንደዚህም ፡ ሁሉ ፤ “አንተ ፡ ልጄ ፡ ነህ ፤ ዛሬ ፡ ወድኩህ ፡ አለኝ” ፡ ማለቱ ፤ እምቅድመ ፡ ዓለም
፡ በመለኮቱ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያለው ፡ ሲሆን ፡ ልጅነትን ፡ ስለሚሻ ፡ ስለ ፡ ሥጋ ፡ እንግድነት ፡ ዛሬ(በጊዜ ፡
ተዋሕዶ) ፡ በሰውነቱ ፡ ከአብ ፡ የባሕርይ ፡ ልደት ፡ መወለዱን
፡ ሲያጠይቅ ፣ ለሐዋርያት ፡ ሲነግራቸው ፡ እንጅ ፡ የማያውቅ ፡ ሁኖ ፡ አብ ፡ ነግሮት ፡ አይደለም ፡፡
ምስጋና ፡ ለሥሉስ ፡ ቅዱስ
ክብር ፡ ለወለተ ፡ ዳዊት ፡ ወላዲተ ፡ አምላክ ፡ ቅድስት ፡ ድንግል ፡ ማርያም
ክብር ፡ ለመስቀለ ፡ ክርስቶስ ፡ እጸ ፡ መድኃኒት ፡ ኃይልነ ፡ ወጸወንነ፡፡
ይቀጥላል፡፡
No comments:
Post a Comment