ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሦስት
==================================
የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና
የቤተ ፡ አይሁድ ፡
ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
በባለፈው ፡ መልእክት ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡
ካሮች ፡ ለእመቤታችን ፡ የምንሰግደው ፡ ስግደት ፡ የወልደ ፡ እግዚአብሔር ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ በሚለው ፡
ሀሳብ ፡ ዙሪያ ፡ ላይ ፡ በሰፊዉ ፡ ተነነጋግረናል ፡፡ እኒህ ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ነጠላ ፡ ቃል ፡ እየመዘዙ ፡ ራሳቸውን
፡ ከጥልቅ ፡ ጉድጓድ ፡ ሲገቡ ፡ ይስተዋላሉ ፡፡ “ለመስቀል ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ እንዴት
፡ ቢሉ ፤ እንግዲያው ፡ የቅዱስ ፡ ጴጥሮስ ፡ የቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ መስቀል ፡ ይሰገድለታልን ፤ ስንኳንስ ፡ ለመስቀሉ ፡ ለርሳቸው
፡ አይሰገድላቸውም ፤መስቀል ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የሆነው ፡ ሥጋው ፡ ቢፈስበት ፤ ደሙ ፡ ቢፈስበት ፡ እሰግድ ፡ ለመስቀለ
፡ እግዚእነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርሰቶስ ፡ ዘተቀደሰ ፡ በደሙ ፡ ክቡር” ፡ ብለን ፡ እንሰግድለታለን›››››››ወልደ ፡ አብ ፡ ገፅ
፡ 251 ፤ ተብሎ ፡ የተቀመጠውን ፡ ቃል ፡ ሙሉውን ፡ ሳይቀበሉና ፡ ሳይመለከቱ ፡ “ስንኳንስ ፡ ለመስቀሉ ፡ ለርሳቸው ፡ አይሰገድላቸውም”
፡ የምትለዋን ፡ ቁንጽል ፡ ሀሳብ ፡ እያነሱ ፡ ለመስቀል ፡ አይሰገድም ፡ ለጻድቃንም ፡ አይሰገድም ፡ ብላችኋል ፡ እያሉ ፡
የጅል ፡ ንግግር ፡ ይናገራሉ ፤ ራሳቸው ፡ ቈናጽላን ፡ መሆናቸውን ፡ እንኳን ፡ አልተረዱም ፡፡ እነሱ ፡ እድሜ ፡ ልካቸውን
፡ እንደዚህ ፡ ይላሉ ፣ አከሌ ፡ ተሐድሶ ፡ ነው ፣ እሌ ፡ መናፍቅ ፡ ነው …..ሌላም ፡ ሌላም ፡ እያሉ ፡ የሰው ፡ ስም ፡
መስበር ፡ እንጅ ፡ የእነሱ ፡ ክሕደትና ፡ ውድቀት ፡ አይታያቸውም ፡፡ ሲያሻቸው ፡ ቅብዐት ፡ የሚለውን ፡ ተዋሕዶ ፡ እያሉ
፡ በነሲብ ፡ በመተርጐም ፣ ሲያሻቸው ፡ ተቀብዐ ፡ የሚሉ ፡ ቃላትን ፡ ከቅዱስ ፡ መጽሐፍ ፡ እየቆረጡ ፡ በማውጣት ፣ ሲያሻቸው
፡ ደግሞ ፡ የዋሁን ፡ ምእመን ፡ እንዲህ ፡ ቁንጽልጥል ፡ እያደረጉ ፡ እያወጡ ፣ ሲያሻቸው ፡ ደግሞ ምንጭ ፡ የሌለው ፡ አሉባልታና
ተረት ፡ ተረት ፡ አንዲት ፡ ጥቀትን ፡ ሁለተኛ ፡ እያጠመቅ ፡ እያደሱ ፡ ሌላውን ፡ ተሐድሶ ፡ እያሉ ፡ ይሳደባሉ ፤ ክርስቲያኖችንም
፡ እስላ ፡ አረሚ ፡ አይሁድ ፡ ከሐዲ ፡ ያደርጋሉ ፡፡ ልቡና ፡ ያላችሁ ፡ ሁላሁም ፡ እኔ ፡ ዘወትር ፡ የሚያንገበግበኝና ፡
ሥራየን ፡ ሁሉ ፡ ትቼ ፡ የምጽፍላችሁ ፡ ሥልጣን ፡ አስፈልጎኝ ፤ አልያም ፡ የምሠራው ፡ ሥራ ፡ ስለሌለኝ ፡ ተረ ፡ ረብ ፡
ጥቅም ፡ ማግኘት ፡ ፈልጌ ፡ ሳይሆን ፤ እውነትን ፡ እያየሁ ፡ ብዙዎች ፡ ሲቀብሯት ፡ ዝም ፡ ማለት ፡ ስለሌለብኝ ፡ ነው ፡፡
ለምድዊ ፡ ድሎትና ፡ ምቾት ፡ አምላክ ፡ በቸርነቱ ፡ ለደመወዝ ፡ የምትሆን ፡ ሥራ ፡ ሰጥቶኝ ፡ እኔንም ፡ ቤተሰቤንም ፡ በፈጣሪ
፡ ቸርነት ፡ እያኖርኩባት ፡ ነው ፡፡
ወደቀደመ ፡
ሀሳቤ ፡ ልመለስና ፡ ካሮቹ ፡ ቆምጠው ፡ የሚያነሱትና ፤ ምእመናንን ፡ ለክሕደት ፡ የሚያቁበት ፡ ቃል ፡ በደንብ ፡ ሲብራራ
፤ ለመስቀል ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ብየባሕርይ ፡ ልጅነቱን ፡ ያጠይቃል ፡ መባሉ ፡ ስለምን ፡ ነው? ፡ የቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ
፣ የቅዱስ ፡ ጴጥሮስ ፡ መስቀል ፡ ይሰገድለት ፡ የለምን? ፡ የሚል ፡ ሰው ፡ ቢኖር ፡ እንኳንስ ፡ ለመስቀላቸው ፡ ለእነሱ
፡ አይሰገድላቸውም ፡፡ ለመስቀላቸው ፡ አይሰገድም ፡ መባሉ ፤ ጌታችን ፡ ለተሰቀለበት ፡ መስቀል ፡ ስንሰግድ ፡፡ “እሰግድ ፡
ለመስቀለ ፡ እግዚእነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ዘተቀደሰ ፡ በደሙ ፡ ክቡር” ፡ ብለን ፡ እንደሆነ ፡ ሁሉ ፤ ለነ ፡ ቅዱስ
፡ ጴጥሮስ ፡ መስቀል ፡ “እሰግድ ፡ ለመስቀለ ፡ ጴጥሮስ ፡ (ጊዮርጊስ) ፡ ብለን ፡ የምንሰግድ ፡ አይደለም ፡ ማለት ፡ ነው
፡፡ ምክንያቱም ፡ የእነሱ ፡ ደም ፡ መስቀሉን ፡ የሚቀድስ ፡ ሳይሆን ፡ የክርስቶስ ፡ ደም ፡ የፈሰሰበት ፡ በመሆኑ ፡ መስቀሉ
፡ እነሱን ፡ የሚቀደሳቸው ፡ ነውና ፡፡
የጌታችን ፡ መስቀል ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡
ሥጋና ፡ ደም ፡ የፈሰሰበት ፡ ነውና ፡ “ዘተቀደሰ ፡ በደሙ ፡ ክቡር” ፡ ብለን ፡ መስገዳችን ፡ ክቡር ፡ ደም ፡ ያለው ፡
አምላካችን ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሥጋውን ፡ ቈርሶ ፡ ደሙን ፡ አፍሶ ፡ እኛን ፡ ያዳነ ፡ መሆኑን ፡ የምንሰብክበት ፡ መሆኑን
፡ ያጠይቃልና ፡ ለመስቀል ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ ማለት ፡ ስለዚህ ፡ ነው ፡፡ ለእሳቸው
፡ አይሰገድላውም ፡ መባሉ ፡ ደግሞ ፡ ለጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ስግደት ፡ እንድንሰግድ ፤ እንዲሁ ፡ ለጻድቃንም ፡ የባሕርይ
፡ ስግደት ፡ የምንሰግድ ፡ አይደለንም ፡ ማለት ፡ ነው ፡፡ ይልቁንም ፡ የጸጋ ፡ ስግደት ፡ እንሰግድላቸዋለን ፡ እንጅ ፡፡
ገና ፡ ለገና ፡ አይሰገድም ፡ ስለተባለ ፤ ለመስቀል ፡ እና ፡ ለቅዱሳን ፡ ስግደት ፡ አይገባቸውም ፡ ብሎ ፡ መደምደም ፡ ልክ
፡ ርጉም ፡ አርዮስ ፡ “ትቤ ፡ ጥበብ ፡ ፈጠረኒ” ፡ ያለውን ፡ ይዞ ፡ እንደካደ ፤ በዚህም ፡ ጫፍ ፡ ይዞ ፡ መነሳት ፡ ልማደ
፡ መናፍቃን ፡ ነውና ፡ አንድን ፡ ኃይለ ፡ ቃል ፡ የተጠቀሰበት ፡ ምሥጢር ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ ሳያስተውሉ ፡ ድምዳሜ ፡
ላይ ፡ መድረስ ፡ ለስህተት ፡ የሚዳርግ ፡ ስለሆነ ፡ ልናስተውል ፡ ተገቢ ፡ ነው ፡፡
በዚያውም
፡ ላይ ፡ መናፍቃን ፡ በሰውነቱ ፡ ለተሰቀለው ፡ በአምላክነቱ ፡ ይሰገድለታል ፡ የሚሉ ፡ ከሆነ ፤ በአምላክነቱ ፡ እንጅ ፡
በሰውነቱ ፡ ተወግቶ ፡ ከጐኑ ፡ በፈሰሰው ፡ ውኃ ፡ አንጠመቅም ፣ በሰውነቱ ፡ ሥጋውን ፡ በልተን ፡ ደሙን ፡ ጠጥተን ፡ አንድንም
፡ የሚሉ ፡ ያሰኛቸዋል ፡፡ አንድም ፡ እንደ ፡ ንሰጥሮስ ፡ ሁለት ፡ አካል ፡ ሁለት ፡ ባሕርይ ፡ ያሰኝባቸዋል ፡፡ “እለሰ
፡ የአምኑ ፡ በክልኤቱ ፡ ህላዌያት ፡ ያጌብሮሙ ፡ ለአሐዱ ፡ ይስግዱ ፡ ወለካልዑ ፡ ኢይስግዱ ፡ ይጠመቁ ፡ በዘመለኮት ፡ ወኢይጠመቁ
፡ በዘትስብእት(ሁለት ፡ አካል ፤ ሁለት ፡ ባሕርይ ፡ ብለው ፡ የሚያምኑ ፡ ለአንዱ ፡ እንዲሰግዱ ፡ ለአንዱ ፡ እንዳይሰግዱ
፤ በመለኮት ፡ ባሕርይ ፡ እንዲጠመቁ ፡ በሥጋ ፡ ባሕርይም ፡ እንዳይጠመቁ ፡ ግድ ፡ ይሆንባቸዋል)” ፡ እንዳለ ፡ አቡሊዲስ(ሃይ.አበው
፡ ምዕ ፡ 39 ፡ ክ ፡ 1 ፡ t ፡ 16) ፡፡
ዮሐንስ
፡ ወንጌላዊ(ምዕ ፡ 1 ፡ t ፡ 14) ፡
ላይ ፡ “ወርኢነ ፡ ስብሐቲሁ ፡ ከመ ፡ ስብሐተ ፡ አሐዱ ፡
ዋሕድ ፡ ለአቡሁ(ለአባቱ ፡ እንደ ፡ አንድ ፡ ልጅ ፡ ክብር ፡ የሆነ ፡ ክብሩን ፡ አየን” ፡ ያለውን ፡ ሳዊሮስ ፡ ዘአንጾኪያ
፡ “አጠየቀነ ፡ ወንጌላዊ ፡ በመለኮቱ ፡ ወበትስብእቱ ፡ ከመ ፡ ወልድ ፡ ዋሕድ ፡ ለአቡሁ ፡ በብሂሎቱ ፡ ርኢነ ፡ ስብሐቲሁ
፡ ከመ ፡ ስብሐተ ፡ አሐዱ ፡ ዋሕድ ፡ ለአቡሁ (ወንጌላዊው ፡ ለአባቱ ፡ እንደ ፡ አንድ ፡ ልጅ ፡ ክብር ፡ የሆነ ፡ ክብሩን
፡ አየን ፡ ባለው በመለኮቱም ፡ በሰውነቱን ፡ ለአባቱ ፡ አንድ ፡ ልጅ ፡ እንደሆነ ፡ አስረዳን) ፡ ብሎ ፡ ተርጕሞታል ፡፡
እንዲህም ፡ ብሎ ፡ መተርጐሙ ፤ እምቅድመ ፡ ዓለም ፡ በመለኮቱ ፡ ድኅረ ፡ ዓለም ፡ በሰውነቱ ፡ ለአብ ፡ አንድ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡
ዮሐንስ ፡ ወንጌላዊ ፡ አስረዳን ፡ ሲል ፡ ነው ፡፡
ዛቲ
፡ ሃይማኖት ፡ መሲሐዊት ፡ ዘትትአመን ፡ ባቲ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ቅድስት
ምስጋና
፡ ለአንድ ፡ አምላክ ፡ ለቅድስት ፡ ሥላሴ
ክብር
፡ ለወላዲተ ፡ አምላክ ፡ ለድንግል ፡ ማርያም
ክብር
፡ ለመስቀለ ፡ ክርስቶስ ፡ እጸ ፡ መድኃኒት ፡ ኃይልነ ፡ ወጸወንነ
ወንድም
፡ እህቶች ፡ እኒህ ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ ጠፍተው ፡ እንዳያጠፉን ፡ እንጠንቀቅ ፡፡ በቀጣዩ ፡ ክፍል ፡ ደግሞ ፤ “ወንጌል ፡
በአሚን ፡ ብቻ ፡ ታድናለች” ፡ ትላላችሁ ፡ እያሉ ፡ የሚጃጃሉበትን ፡ ሉተራዊ ፡ አመለካከታቸውን ፡ በዝርዝር ፡ እንመለከታለሁ
፡፡ ምንም ፡ የማታውቁ ፡ ካሮች ፡ እባካችሁ ፡ ስለ ፡ አዛኝቱ ፡ ብላችሁ ፡ ስለማታውቁት ፡ ነገር ፡ አስተያየት ፡ አትስጡ
፡፡
No comments:
Post a Comment