በተለምዶ ተዋሕዶዎች ተብለው የሚጠሩ ትክክለኛ ስማቸው ግን ካሮች መሲሕ በመንፈሰ አቡሁ ብለን የምናምነውንና መሲሐዊያን፣ ቅብዓን፣ ናዝራዊያን ተብለን የምንጠራውን እኛን ለማጭበርበር ሲፈልጉ ቅብዓትን እኮ ቅዱስ ቄርሎስ አውግዞታል ይሉናል:: እውነታውን ግን አብረን እንየው:-
ብዙዎቹ በተዋሕዶ ከበረ ብለው የሚያምኑ ሰዎች “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእርሱ አጋዥነት ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው ፤ ርኩሳን አጋንንትን በማውጣት ጊዜም ኃይልን ተአምራትን ከመንፈስ ቅዱስ ይቀበላል በሰውም የአምላክነትንም ሥራ እርሱ ራሱ ይሠራል የማይል ቢኖር ውጉዝ ይሁን ሃይ/ አበው ዘቄር 73÷49” በማለት አውግዟችኋል ይሉናል::
ሙሉ ቃሉ ግን ፠-----ሃይ/አበው ዘቄርሎስ ምዕ 73፥ 49 “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእርሱ አጋዥነት ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው፤ ርኩሳን አጋንንትን በማውጣት ጊዜም ኃይልን ተአምራትን ከመንፈስ ቅዱስ ይቀበላል በሰውም የአምላክነትን ሥራ ይሰራል የሚለው፤ መንፈስ ቅዱስ የባሕርዩ ነው የአምላክነትንም ሥራ እርሱ እራሱ ይሰራል የማይል ቢኖር ውጉዝ ይሁን ”------፠ ይላል::
እነሱ ግን ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ዋና ማሰሪያ ያደረገውን ኃይለ ቃል “መንፈስ ቅዱስ የባሕርዩ ነው” የሚለውን ነቅለው ያወጡታል አንዳንዴም ጨምረውት እናገኘዋለን:: ሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ ደግሞ ‘በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው’ የምትለዋን ሀረግ ‘በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚል ሰው’ ብለው ትርጓሜውን ለመጠምዘዝ ሞክረዋል:: ግን ለምን ይሆን መቁረጥ መቀጠል ልማድ ያደረጉት?

ለማንኛውም ግን ይህ ኃይለ ቃል የሚያወግዘው ለክርስቶስ የተሰጠው መንፈስ ቅዱስ እንደ ቅዱሳን “የባሕርዩ ሳይሆን የጸጋ ነው” የሚሉትንና የአምላክነትን ሥራ እሱ እራሱ አይሰራም ብለው የሚናገሩትን መናፍቃን መሆኑን ልብ ልንል ይገባል::
እንደእነሱ አባባልማ ከሆነ ‘መንፈስ ቅዱስ የባሕርዩ ነው’ የሚሉትን ፤ ‘በሰውም የአምላክነትን ሥራ ይሰራል’ የሚለውን ሁሉ ነው ቅዱስ ቄርሎስ ያወገዘው ሊሉ ነውን?
ሊቃውንቱ ግን ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ እንዲህ ያስቀምጡታልና ኃይለ ቃሉን በደንብ ልንገነዘብ ይገባናል:-
ሀ.......... ሃይ/ አበው ቃለ ግዝት ምዕራፍ 121፥ 33 – 34
“ስለ አንዱ አምላክ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ ልዩ ሥልጣን በእሱ አድሮ እንደሚሰራ አድርጎ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ፤አጋንንትን የሚያወጣበትን ተአምራት የሚያደርግበትን ሥልጣን ተቀብሎ የአምላክነትን ሥራ በሰው ላይ ይሰራል፤ እሱ ገንዘቡ በሚሆን ሥልጣን የአምላክነትን ሥራ አይሰራም የሚል ሰው ቢኖር ውጉዝ ይሁን::
ትርጓሜ ዋሕድ ቃለ እግዚአብሔር እንደ እኛ ያለ ፍጹም ሰው ሆነ፤ ከአምላክነቱ አልተለወጠም፤ የአብ የመንፈስ ቅዱስ የሆነ ሁሉ ለወልድ ገንዘቡ ነው አብ መንፈስ ቅዱስ የሚሰሩትንም ወልድ ይሰራዋል፤ በስም አጠራር ብቻ ካልሆነ በቀር ከሥራ በማናቸውም ሥራ አይለይም ይህም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው:: ዮሐ 5፥17

ሰውም ቢሆን ከባሕርየ መለኮቱ ፈጽሞ አልተለወጠም ሥጋን ተዋሕዶ የአምላክነትን ሥራ ይሰራል እንጅ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልን ሥልጣንን ከሚቀበሉ ከቅዱሳን እንደ አንዱ አድርጎት፤ ከአባቱ ሥልጣንም ልዩ አድርጎት ሰው እንደመሆኑ እንደ እኛ ከበረ ወደ ሰማይም ይወጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ያደለውን ይቀበላል እንጅ የአምላክነትን ሥራ አይሰራም የሚል ሰው ቢኖር የዚች ግዝት ሥልጣን በእሱ አድራ ትለየዋለች::”
በማለት አብራርተው ተርጉመውታል:: ለዚያም ነው አበው “ንባብ ይገድላል ትርጓሜ ያድናል” የሚሉት::
ለ............ “ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ ቅዱስ ወረሰዮ ቅዱሰ ወማኅየዌ -- በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት የአዳምን ባሕርይ ያከበረው የባሕርይ አምላክ ያደረገው እሱ ነው” ሃይ/አበው ዘእልመስጦአግያ 2፥5 ብለው ሲናገሩ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት አከበረው አሉን እንጅ ቃል ሥጋን አከበረው አላሉንም::
ሐ........... “እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ተቀብዓ ቃል በሥጋሁ - በእውነት የሚያምኑ ቃል በሥጋው እንደተቀባ ያስተምሩ ” ማቴ 1፥16 አንድምታ ትርጓሜ አለን እንጅ ቃል ሥጋን እንደቀባው ያስተምሩ ብሎ አልተናገረምና በተዋሕዶ ከበረ [አካለ ቃል አካለ ሥጋን አከበረው፤ አካለ ሥጋ በአካለ ቃል ከበረ፤ አካለ ቃል ለአካለ ሥጋ ክብር ሆነው] ብለው ሲያምኑ ማስረጃ የላቸውም::
መ........... ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም በድርሳኑ እንዲህ ያስቀምጠዋል:-
ናሁኬ ዘለፎሙ በዝየ ለንፉቃን አይሁድ ወለሕዝበ ጳውሎስ ሳምሳጢ ለአርዮሳውያን ወለመርክላን ለሰባልዮስ ወለመንክዮን….እነሆ በዚህ አንቀጽ (በተቀብዐ) ተጠራጣሮች አይሁድን የጳውሎስ ሳምሳጢን ወገኖች አርዮሳውያንን መርክላንን ሰባልዮስን እለ መንክዮንን ረታቸው፡፡ወለመንክዮንሂ አግሀደ ሎቱ ከመ መለኮት ኢይትቀብዐ ዘእንበለ ዳእሙ ትስብእተ ሥጋሁ….ምትሐት የሚሉ እለ መንክዮንን በሰውነቱ እንጂ በመለኮቱ ከበረ እንዳይባል አስረዳቸው፡፡ ሐተታ ምትሐት ይላሉ እንጂ በመለኮቱ በባሕርይዉ ከበረ ይላሉን ቢሉ መጽሐፍ ቃልን በሥጋ ተቀባ ይለዋል፡፡ በሥጋ እንዳይሉ ምትሐት ይላሉ፡፡ መትሐት ካሉ በአምላክነቱ ከበረ ያሰኛልና፡፡ አንድም፤ ተቀብቶ ተዋሀደ ይላሉና በመለኮቱ ከበረ እንዳይባል አስረዳ በእንተዝ በማለቱ ነው፡፡

ይቤ ቅብዐ ትፍሥሕት እምለ ከማከ፡፡ ይቤ ቅብዐ ትፍሥሕት እምለ ከማከ፡፡ አለ መኑ እሙንቱ እለ ከማሁ…..እምለ ከማከ የተባሉ እነማናቸው፣አኮኑ ውሉደ ሰብእ፡፡ ምእምናን አይደሉምን፡፡ እስመ ለእግዚእ ክርስቶስ አኮ በመስፈርት ዘተውህቦ መንፈስ……መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ በልክ በመጠን የተሰጠው አይደለምና፡፡ ቅብዐ ትፍስሕት እምለከማከ አለ ዘይኄይስ ያለበት ነው፡፡ አይቴኑ ይኄይሰ እምዘዝንቱ ተዐውቆ… …ከዚህ ምሥጢር የሚበልጥ ምን ምሥጢር አለ፡፡ አንድም፤ ከዚህ መረዳት የሚበልጥ ምን መረዳት አለ፡፡(ዮሐንስ አፈወርቅ ድረሳን 3:73-89፡፡
ወበዝንቱ ቃል ወግኦሙ ውስተ ልቦሙ ለአርዮስ ወለጳውሎስ ሳምሳጢ…. በዚህም ቃል (በተቀብዐ) አርዮስን ጳውሎስ ሳምሳጢን ረታቸው፡፡ እሰመ አኤርዮ ለወልድ ምስለ አቡሁ….ወልድን ከአብ ጋራ አሰተካክሎትልና፡ ወንእዶ ከመ ከማሁ፡፡ እንደ እርሱ አካል ባለ አካል አክብሮታልና፡፡ ( ዮሐንስ አፈወርቅ ድረሳን 3:98-100 )
በማለት ቃል በሥጋው እንደከበረ፤ ለክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ በልክ በመጠን የተሰጠው እንዳልሆነ፣ እንደ እርሱ አካል ባለ አካል እንዳከበረው አመስጥሮ ይናገራል እንጅ እንደ ሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ ቃል ሥጋን አከበረው ያለው አይደለምና ልናስተውል ይገባናል::
ረ............... “እኔ እራሴን ባከብር ክብሬ ከንቱ ነው፡፡ የሚያከብረኝ አናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው” ዮሐ 8፥53-54 በማለት አብ እንዳከበረው ይናገራል::
ሠ............... “ክርስቶስ ሊቀ ካህናት ሊሆን እራሱን ያከበረ አይደለም” ዕብ 5፥5 በማለት እራሱን በራሱ እንዳላከበረ በግልጽ ይናገራል::
ወንጌል ላይ “ዘበእንቲአሆሙ ለልየ እቄድስ ርእስየ ፤ ስለ እርሳቸው እኔ እራሴን አከብራለሁ” ዮሐ 17፡19 ይላልሳ ይህ እንዴት ነው ቢሉ ቅዱስ ቄርሎስና ዝክሪወጳውሊ እንደአምላክነቱ ያከብራል እንደ ሰውነቱ ደግሞ ይከብራል በማለት ሥጋ ከቃል ጋር በተዋሐደ ጊዜ ቃል በሥጋ ርስት ሲቀባ[ማቴ 1፥16 አንድምታ] ሥጋ ደግሞ በቃል ርስት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብሮ ይቀባልና ነው:: “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቄድሱ - አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ” እንዳለ አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ ደግሞ “ዘበእንቲአሆሙ ለልየ እቄድስ ርእስየ ፤ ስለ እርሳቸው እኔ እራሴን አከብራለሁ” ማለቱ እርሳቸውን ከኃጢያት ኃጢያትን ከእነሱ አርቃለሁ ማለቱ ነው እንደሆነ ይናገራል እንጅ ቃል ሥጋን ቀባው አላለንም ቃል በሥጋው ተቀባ አለን እንጅ ድርሳን 15 ላይ::
በመጨረሻም ለሆዳቸው ያደሩ፣ ለክብር ለዝና የሚጨነቁ የመጽሐፍትን ብሂል የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች ከላይ ያየነውን ኃይለ ቃል [ሃይ/ አበው ዘቄርሎስ 73፥49] በመጥቀስ ቅብዓትን [መንፈስ ቅዱስን] ቅዱስ ቄርሎስ አውግዞታል በማለት የዋሃንን ሲያታልሉ ይስተዋላልና እራሳችሁን ጠብቁ፤ ያልገባችሁን ጠይቁ ለማለት እወዳለሁ::

ስብሐት ለሥሉስ ቅዱስ!
No comments:
Post a Comment