"በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሾልከው ያገባሉ" ፪ኛ ጴጥ ፪-፩ ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደተናገረው የዘመኑ ሊቃውንትና የቀድሞ ሊቃውንት ትርጓሜ ልዩነት እንደልቤ በተባለው የእስራኤል ንጉስ ቅዱስ ዳዊት “በእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ ቅብዓ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ -- ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳንተ ካሉት ይልቅ የደስታ ዘይትን ቀባህ” መዝ 44፥7....... ብሎ የተናገረው እኮ እግዚአብሔር ወልድ በኋለኛው ዘመን ሥጋ አዳምን ሲለብስ የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስን ግብር በግልጽ መናገሩ እንጅ የሦስቱንም ግብር ጠቅልሎ ለወልድ[ቃል] ብቻ መስጠቱ አይደለምና ልብ ልንል ይገባናል::
❌......በተዋሕዶ ከበረ ባዮች[ካሮች] “ቀብዓከ እግዚአብሔር አምላክከ -- እግዚአብሔርነትህ አምላክነትህ አከበረህ” ብለው እራሱ አክባሪና ክብር ሥጋ ደግሞ ከባሪ ነው ለሚለው ምንፍቅናቸው መሸፈኛ ይሆን ዘንድ ትርጓሜን እያጣመሙ ይገኛሉ::
ይህንንም በየተራ እንመልከተው:-
➕....፩ኛ.........የአብን ቀባዒነት ሲናገር ..........."ቀብዓከ እግዚአብሔር አምላክከ-- እግዚአብሔር አምላክህ ቀባህ" .......... ....... በማለት እግዚአብሔር አብ እንደቀባው፣ እንዳከበረው፣ እንዳነገሰው ተናገረ:: እግዚአብሔር የሚለው ስም የሦስቱ[አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ] መጠሪያ ስማቸው አይደለምን ቢሉ እውነት ነው የሦስቱ አካላት የአንድነት መጠሪያቸው ነው ነገር ግን እንደየ አገባባቸው ለእግዚአብሔር አብ፣ ለእግዚአብሔር ወልድ፣ ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚነገሩበትም አውድ እንዳለ መጽሐፍት ይናገራሉ::
ለዚህም ምስክር “እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩ” መዝ 2፥7...... ብሎ ሲናገር “እግዚአብሔር” የሚለው መጠሪያ እግዚአብሔር አብን ያመልክታል:: የወላዲነት ግብር የአብ ነውና:: በተወላዲነት ግብሩ ልጅ የተባለው ደግሞ ወልድ እንደሆነ ይናገራል::
እንዴት እግዚአብሔር አምላክህ ቀባህ አለው ወልድስ አምላክ አይደለምን የሚል ቢኖር ወልድ ሥጋ ሥለለበሰ እግዚአብሔር አብን አምላኩ ለወልድ ይለዋል:: ቅዱሳን አበውም ይህንን ምስጢር እንዲህ ያስቀምጡልናል::

“እግዚአብሔር አብ ውእቱ አቡሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በህላዌ መለኮቱ፤ እግዚአብሔር አብ አምላኩ ለወልድ ውእቱ በእንተ ትስብእቱ -- እግዚአብሔር አብ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርየ መለኮቱ አባቱ ነው፤ ሰው ስለሆነ ወልድ እግዚአብሔር አብ አምላኩ ነው” ሃይ/ አበው ዘኤጲፋንዮስ ምዕ 54፥9 በማለት ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሲናገር ዮሐንስ አቡቀለምሲስ ደግሞ በወንጌሉ “አዐርግ ኀበ አቡየ ወአቡክሙ ኀበ አምላክየ ወእምላክክሙ -- ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም ዐርጋለሁ” ዮሐንስ 20÷17 አንድምታ ...... አቡየ ብሎ የእሱን ልደት ተናገረ አቡየ ያለው የእርሱ የባሕርይ ነው አቡክሙ ያለው የእኛ የጸጋ ነው አምላኪየ አለ በሥጋ ይፈጥረዋል፤ አምላክክሙ አለ በጥንተ ተፈጥሮ በሐዲስ ተፈጥሮ ይፈጥረናልና በማለት አብ በሥጋው ለወልድ አምላኩ እንደሚባል አመስጥረው ተናግረዋል::
ዳግመኛም ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ሲል ጻፈ “አማን አንገለጉ በዛቲ ሀገር ላዕለ ቅዱስ ወልድከ ኢየሱስ ዘቀባዕካሁ -- በዚህች አገር በቀባኸው በቅዱስ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ለምን ዶለቱ”ሐዋ4፡27........ “ላዕለ ቅዱስ ወልድከ ኢየሱስ ዘቀባዕካሁ -- በቀባኸው በቅዱስ ልጅህ በኢየሱስ ላይ”....... ከሚለው ላይ የቀባው፣ ያከበረው፣ ያነገሰው፣ አባት የሆነው እግዚአብሔር አብ እንደሆነ በግልጽ ይናገራል:: የተቀባው፣ የነገሰው፣ የከበረው፣ ልጅ የሆነው ክርስቶስ እንደሆነም በግልጽ ተናገረ::
➕....፪ኛ........ የወልድን በሥጋው መክበር[ተቀባዒነት] ሲናገር ......... ዳግመኛልም "በእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ ቅብዓ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ -- ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳንተ ካሉት ይልቅ የደስታ ዘይትን ቀባህ”.............. በማለቱ የተቀባ፣ የከበረ፣ እንዳንተ ካሉት ይልቅ ተብሎ ከነቢያት፣ ከካህናት፣ ከነገስታት ጋር ለንጽጽር የቀረበ እግዚአብሔር ወልድ እንደሆነ ተናገረ:: ለምን እግዚአብሔር ወልድስ አምላክ አይደለምን የተዋሐደውን ሥጋ እራሱ ማክበር አይችልምን ቢሉ በማክበር፣ በሥልጣን፣ በመለኮት፣ በአገዛዝ ከዚህም በሚበዛ ነገር ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ትክክል ነው:: አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይቄድሱ -- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያከብራሉ” ብሎ እንደተናገረ::
ነገር ግን በተለየ አካሉ፣ በተወላዲነት ግብሩ፣ በባሕርይ አንድነቱ እግዚአብሔር ወልድ[አካላዊ ቃል] ከንጽሂተ ንጹሐን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስን ነስቶ በተዋሐደ ጊዜ በአካሉ ግዙፍ፣ ጸቢብ፣ ውሱን የነበረ ፍጡር፣ መዋቲ፣ ደካማ፣ ከክብር በአፍአ የነበረ፣ የአብን ልብነትና የመንፈስ ቅዱስን ሕይወትነት ገንዘቡ ያላደረገ ነዳይ ሥጋ በአካሉ ስፉህ፣ ረቂቅ፣ ምልዑ ከነበረ ባሕርዩ ደግሞ ይኼ ነው ተብሎ ከማይመረመርና በአካል ሳይቀላቀል በሕልውና በመገናዘብ በአብ ልብነት ለባዊ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያው ወማሕየዊ ሆኖ የሚኖር መለኮታዊ አካል ጋር በተዋሐደ ጊዜ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ደግሞ ለቃል ገንዘቡ ሆነ:: ከዚህ ላይ ተዓቅቦን[በመጠባበቅ]፣ መገናዘብን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን:: “እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ዘእንበለ ኃጢአት ባሕቲታ -- ከኃጢአት በስተቀር የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብም ለቃል ሆነ” እንዳለ ቅዱስ ቄርሎስ::
በዚህም ተዋሕዶ ሁለትነትን አጥፍቶ አንድነትን ያፀናል እንጅ ክብርን አያስተላልፍም:: በጊዜ ተዋሕዶ የቃል ክብር ለሥጋ ተላልፏል የሚል ቢኖር የክብር አጸፋው ንዴት ነውና ቃልን ነዳይ ማድረግ ስለሚሆን ክርስቶስ በሥጋ የሞተው፣ የተራበው፣ የተጠማው፣ የተሰቀለው...... በግድ እንጅ በፍቃድ አይደለም ማለት ነውና አካለ ቃል አክባሪ አካለ ሥጋ ደግሞ ከባሪ አንድም አካለ ቃል ገዢ አካለ ሥጋ ተገዢ፣ አካለ ቃል ባለጸጋ አካለ ሥጋ ደሀ በማድረግ ግብርን መለየት ስለሚሆን ነው ቃል ሥጋን አከበረው የማይባለው::

ወልድ ሥጋን በመልበሱ ቅዱሳን አበው “ንሕነሰ ንረክቦ ለዝንቱ ወልድ ዋሕድ አምላክ ወውእቱ ሰብእ ለሊሁ እግዚእ ወለሊሁ ገብር፤ ለሊሁ በግዕ ወለሊሁ ሊቀ ካህናት፤ ወውእቱ ፍጡር ወፈጣሪ -- እኛስ ይህን አንድ ወልድን አምላክ ሰው፤ ገዥ ተገዥ፤ ሠዋዒ ተሠዋዒ፤ ፍጡር ፈጣሪ ሆኖ እናገኘዋለን” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥18 ብለው በአንድነት ስለ ሥግው ቃል፣ ክርስቶስ ተናገሩ እንጅ ቃልና ሥጋን ለይተው ቃል አምላክ ሥጋ ሰው፤ ቃል ገዥ ሥጋ ተገዥ፤ ቃል ሠዋዒ ሥጋ ተሠዋዒ፤ ሥጋ ፍጡር ቃል ፈጣሪ ብለው ተዋሕዶን ሽረው ምንታዌን አላስተማሩንም::
ስለዚህ ከበረ የተባለው ሥጋ ሳይሆን ሥግው ቃል[ቃል የተዋሐደው ሥጋ]፣ ክርስቶስ ስለሆነ አበው እንዲህ ይመሰክራሉ:-
ስለዚህ ከበረ የተባለው ሥጋ ሳይሆን ሥግው ቃል[ቃል የተዋሐደው ሥጋ]፣ ክርስቶስ ስለሆነ አበው እንዲህ ይመሰክራሉ:-
በእውነት ለሚያስተውል ሰውማ ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ወልድ ሥጋን በመልበሱ "ይቤ ዳዕሙ ለሊሁ አክበሮ ዘይቤሎ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ -- ዳግመኛም እንዲህ አለ እራሱ አክብሮ አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" ድር 8፥69 ብሎ የባሕርይ አባቱ አብ እንዳከበረው ተናገረ:: ዳግመኛም ካሮች የሚክዱትንም በሥጋ ከአብ መወለዱን ሊቁ “የባሕርይ ልጁን እንደገና በሥጋ የባሕርይ ልጅ አድርጎታልና” ድር 8፥74 ብሎ ቅዱስ ዳዊት “እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩ” መዝ 2፥7 ብሎ የተናገረውን ምስጢር አብራርቶ ተናገረ:: የክህደታቸው ጥግ የሌላቸው ክፋልያነ ክርስቶስ በተዋሕዶ ከበረ የሚሉ መናፍቃን ግን አብ ወልድን በሥጋ አልወለደውም ብለው ክደውታል የሃይማኖት አምድ ልሳነ ወርቅ ግን በድርሳኑ በጎላና በተረዳ ነገር አመስጥሮ ይናገራል::
ዳግመኛም ሊቁ ልሳነ ወርቅ እንዲህ አለ “ይቤ ወክርስቶስሰ አኮ ዘወደሰ ርእሶ በከዊነ ሊቀ ካህናት አላ ለሊሁ ሤሞ ወአክበሮ”ድር 8፥59 ክርስቶስ እንደ አሮን በቃሁ ነቃሁ ብሎ ራሱን የሾመ አይደለም ራሱ አብ ሾመዉ እንጅ ብሎ ተናገረ ሰሚ ግን ጠፋ አይ ካሮች በተዋሕዶ ራሱን በራሱ አከበረ እያላችሁ ስንት ትውልድ ገደላችሁ?
❌.......ካሮች ግን በተዋሕዶ ወለድኩህ ሲለው ነው ብለው ገደል ገብተዋል:: ለመሆኑ በተዋሕዶ ልጅነት ይገኛልን? በተዋሕዶ ከብሮ ልጅነት ያገኘ ማን ይሆን? በእውነት ወልድስ በተዋሕዶ ከበሮ የአብን ልጅነት አገኘ ካልን እኛስ በምን ከብረን የሥላሴን ልጅነት እናግኝ? ከማን ጋርስ እንዋሐድ?
ቅዱስ ቄርሎስስ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ፍጹም ሲሆን ሰው በመሆኑ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ" ሃይ/አበው 80፥1 ብሎ አልተናገረምን? ታዲያ መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ሥጋ ብቻ ከሆነ ለምን "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ ፍጹም ሲሆን" በማለት በመለኮቱ ክብርን፣ መቀበልን እንደማይሻ ሥጋ አዳምን ስለተዋሐደ ግን "ሰው በመሆኑ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ" ተብሎ የተነገረው ቃል ለተዋሐደው ሥጋ፣ ለክርስቶስ እንጅ ለሥጋ ብቻ ነው ብለው ከሚያስቡ ዝንጉዎች ጋር እንከራከር ዘንድ እንዴት ይቻለናል?

"እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ቃል ተቀብዓ በሥጋሁ -- በእውነት የሚያምኑ ቃል በሥጋው እንደተቀባ ያስተምሩ" ማቴ 1፥16 አንድምታ ...... ብለው አበው አስተማሩን እንጅ "ቃል ሥጋን እንደቀባው፣ ሥጋ በቃል እንደተቀባ" ያስተምህሩ ብለው ምንፍቅናን መቼ አስተማሩንና ነው ምንታዌን የምንቀበለው? ኧረ ወገኖቼ እናስተውል! በስም፣ በብዛት፣ በፖለቲካ እየደለሉ ርስታችንን፣ ሃብታችንን ሲወስዱብን ለምን ዝም ብለን እንመለከታለን?
ለመሆኑ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምስጢር ምዕ 1፥23 ላይ "የእውነት መንፈስ መጥቶ እርሱ በጽድቅ ሁሉ ይመራችኋል ከእርሱ የሆነውን ዐይነግራችሁምና የሰማውን ይናገራል እንጅ የሚመጣውን ፈጽሞ ይነግራችኋል እኔንም ያከብረኛል ከእኔ ተቀብሎ ይነግራችኋልና ሁሉንም ይገልጥላችኋል" ብለው ጽፈዋል::
❓ ............ ክርስቶስም "እኔንም ያከብረኛል" ብሎ እየመሰከረ እናንተ ደግሞ አያከብረውም እያላችሁ ለምን ትሞግታላችሁ?
ዳሩ ግን ከበረ ተባለ:: የከበረውም ክርስቶስ እንጅ ቃል ሥጋን እንዳላከበረው አበው ምስክሮቻችን ናቸው::
❓ታዲያ እራሱን በራሱ ያከበረ ከሆነማ ለምን:-
“እኔ እራሴን ባከብር ክብሬ ከንቱ ነው፤ የሚያከብረኝ አናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው” ዮሐ 8፥53-54 በማለት እና “ክርስቶስ ሊቀ ካህናት ሊሆን እራሱን ያከበረ አይደለም” ዕብ 5፥5 ተብሎ ተነገረ?
“ወድኅረ ተሰይመ አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ -- በኋለኛው ዘመን አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ተባለ” አባ ዝክሪ ወጳውሊ ዘደብረ ጽሞና ብለው ሲናገሩ ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ቅዱስ ቄርሎስ፣ ኪርያኮስም ይህንን ብሂል አስፍተው አምልተው ተናግረውታል ዳሩ ግን መቁረጥ መቀጠል ስራቸው ነውና ከእትሙ እየቆረጡ አስቀርተውታል:: በጥንታዊያን ገዳማት በብራናው ላይ ይገኛል::
ካሮች ደግሞ “ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ ቅብዓ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ -- እግዚአብሔርነትህ አምላክነትህ ልዩ ተዋሕዶን አዋሐደህ”......... በማለት ትርጓሜን ሲያጣምሙ ይስተዋላሉ:: ለመሆኑ “እግዚአብሔር አምላክከ -- እግዚአብሔር አምላክህ” ብሎ በቀጥታ መተርጎም ያሳፈራቸው ምን ይሆን? እኛ አምላክ አይደለም ያልን መሰላቸው እንዴ?
❌.......እንግዲያውስ “አምላኪየ አምላኪየ ለምንት ኀደከኒ -- አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” ብሎ በወንጌል የተናገረውንም “አምላኪየ አምላኪየ ለምንት ኀደከኒ -- አምላክነቴ አምላክነቴ ለምን ተውከኝ” በማለት አምላክነቱን ለቆ እንደነበረ አድርገው መናገራቸው ግድ ነው! አንዷን ክህደት እንሸፍናለን ሲሉ ከገደል ገደል እየተምታቱ ተሰባብረው ወደቁ::
➕....፫ኛ ........... መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ እንደሚባል ሲያስረዳ.......... "በእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ ቅብዓ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ -- ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳንተ ካሉት ይልቅ የደስታ ዘይትን ቀባህ” ......... ብሎ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት የተናገረውን ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ “ዘይኄይስ እምእሊአሆሙ -- ከእነሱ የሚልቅ [ከነገስታት፣ከከህናት፣ ከነቢያት]” ብሎ በዕብ1፥9 አንድማታ ላይ አብራርቶ ተረጎመዉ:: ይህንን አፈወርቅ ዮሐንስ በድርሳን 3 እና ድርሳን ስምንት ላይ “እምእሊአሆሙ-- ከእነርሳቸው” የተባሉ ምእመናን እኛ ነን በማለት “ዘይተ ፍስሐ -- የደስታ ዘይት” ብሎ አመስጥሮ ተናግሮታል፡፡ ይህም ማለት የምእመናኑ የካህናና ነቢያት የሚነሳ[የጸጋ በመሆኑ] የእርሱ ግን የባሕርይ መሆኑን መጻሕፍቱ አብራርተዉ ተናገረዉታል መስክረዉታልም፡፡ እነሆም ትርጓሜና ምሥጢር ተስማምተዉ ተቀምጠዋል፡፡

❌.......በተዋሕዶ ከበረ ብለው በሚያምኑ ካሮች ቤት ግን “ቅብዓ ትፍስሕት-- ልዩ ተዋሕዶ” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡በእዉኑ የደስታ ዘይት ብሎ ልዩ ተዋሕዶ ማለት አገባቡ ምንድን?
ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በአክሲማሮስ መጽሐፉ “ወእምዝ ተቀብዓ ቅብዓ ትስብዕት ዘክርስቶስ ዘቦቱ ይነሥዑ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ ኩሎሙ አሕዛብ-- ይህስ ቅብዓት ምንድን ነው ቢሉ ቀድሞ ጌታችን ከባሕርይ አባቱ በባሕርይ ልጅነት ተወልዶ የባሕርይ ልጅነት ያገኘበት መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ዛሬ ሕዝቡ አሕዛቡ ከሥላሴ የፀጋ ልጅነትን የሚወለዱበት ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ይህ ነው፡፡” መ.አክሲማሮስ ዘሠሉስ 2፥18 ብሎ ተናገረ እንጅ ይህስ ቅብዓት “ተዋሕዶ ነው፣ ልዩ ተዋሕዶ ነው” ብሎ አልተናገረምና እናንተ ከየት አመጣችሁት፣ ከነቢያት፣ ከሐዋርያት፣ ከሊቃውንት ያላገኛችሁትን ከምን አግኝታችሁ ታስተምራላችሁ? ወልድ ቅብዕ ብላችሁ ስታምኑስ ምስክራችሁ ምን ይሆን?
“ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም ወረሰዮ ቅዱሰ ወማሕየዌ -- በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት የአዳምን ባሕርይ ያከበረው የባሕርይ አምላክ ያደረገው እሱ ነው” ሃይ/አበው ዘእልመስጦአግያ 2፥5 ........ “በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት አከበረው” አለን እንጅ በተዋሕዶ አከበረው የሚል የለምና ካሮች ምስክራችሁ ምን ይሆን?

በወልድ ሕልውና ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው ሥጋን ያከበረው ትለኝ እንደሆነ:-
ቅዱስ ሳዊሮስ “ስለዚህ ለባሕርየ ገንዘቤ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በህልውናዬ ፀና ብሎ አስተማረ ፤ ሰው ብሆን ነው እንጅ ያለዚያ ለምን ክርስቶስ ተባልኩ? የምንድንበት ይህ ነው፤ የሚፈውሰን ይህ ነው፤ የጎበኘን ይህ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በኃላ ለድሆች የምስራች እነግራቸው ዘንድ፣ ያዘኑትን አረጋጋቸው ዘንድ፣ ለተማረኩት ነፃነታቸውን እሰብክላቸው ዘንድ እውሮች ያዩ ዘንድ ስለዚህ ላከኝ አለ፤ መንፈስ ቅዱስ ገንዘቡ ሆነ መባሉ ቃል ሰው ስለሆነ ነው፤ ሰውማ ባይሆን ኑሮ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ህልው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስም በባሕርይ መለኮት ገንዘቡ ነውና እንደምን ገንዘቡ ሆነ ይባላል? አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልው መሆኑ እንደተነገረ ” ሃይ/ አበው ዘሳዊሮስ ምዕ 87፥ክፍል 9፡ 17-18፣ ኢሳ 61፥1 ብሎ ብሎ የተናገረው ለምን ይመስልሃል?
❓........ “ሰውማ ባይሆን ኑሮ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ህልው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስም በባሕርይ መለኮት ገንዘቡ ነውና እንደምን ገንዘቡ ሆነ ይባላል?”........ ተብሎ የተነገረው ለክርስቶስ[ለሥግው ቃል፤ ቃል ለተዋሐደው ሥጋ] እንጅ ለሥጋ ብቻ ነውን?
❓.........ተቀባ፣ ከበረ፣ ሰው ሆነ ብለን የምንጠራው ክርስቶስን፣ ሥግው ቃልን እንጅ ሥጋን ብቻ ይመስላችኋልን?
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ “ስመ ብሂለ ክርስቶስ ወመሲሕ ወናዝራዊ አሐደ ይተረጎም ቅቡዕ -- ክርስቶስም መሲሕም ናዝራዊም ማለት በአንድነት የተቀባ ተብሎ ይተረጎማል” ...... ብለው የተናገሩት ለክርስቶስ እንጅ ለሥጋ ብቻ እንዳልሆነ ልታስተውሉ ይገባችኋል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ “ስመ ብሂለ ክርስቶስ ወመሲሕ ወናዝራዊ አሐደ ይተረጎም ቅቡዕ -- ክርስቶስም መሲሕም ናዝራዊም ማለት በአንድነት የተቀባ ተብሎ ይተረጎማል” ...... ብለው የተናገሩት ለክርስቶስ እንጅ ለሥጋ ብቻ እንዳልሆነ ልታስተውሉ ይገባችኋል::
በመቀጠልም በ2009 ዓ/ም እትም ላይ ቁምጥምጥ ያደረጋችኋት ኃይለ ቃል “ናሁኬ ነሥአ መንግስተ ተቀብዖ ኢየሱስ ናዝራዊ ተቀብዖ በቅብዕ ተሰብአ እንዘ አምላክ ዉእቱ ወተቀቢዖ በቅብዐ መለኮት በእንተ ሰብእናሁ -- እነሆ ናዝራዊ ኢየሱስ ቅብዓትን ተቀበቶ የመቀባትን መንግስት ተቀበለ፡፡አምላክ ሲሆን ስለ ሰዉነቱም የመለኮትን ቅባት ተቀብቶ ሰዉ ሆነ” መጽሐፈ ምስጢር 20፡40-41......... ብሎ ሲናገር ምስጢር ተሰውሮበት ይመስላችኋልን?
እናንተ ግን ከዚች ኃይለ ቃል ላይ የተቀብዓን ግስ ተዋሐደ እያላችሁ መተርጎም ስላስቸገራችሁ ነቅላችሁ በመጣል “ናሁኬ ነሥአ መንግስተ ኢየሱስ ናዝራዊ ወዘተሰብአ እንዘ አምላክ ውእቱ -- እነሆ ናዝራዊ ኢየሱስ መንግስቱን ገለጠ አምላክ ሲሆን በፈቃዱ ሰው ሆነ” ....... በማለት የሊቁን ድርሰት ጠላት የዋለበት አዝመራ አስመስለውታል:: እንዲህም ሆኖ ግን የሚያስተውልና እውነታውን የሚያረጋግጥ አለመኖሩና ይህ ሁሉ ጽድቅ የሚመስለው ሰው ነው ያለው!
❓........ "ሰው ብሆን ነው እንጅ ያለዚያ ለምን ክርስቶስ ተባልኩ?"....... ብሎ ባለቤቱ የተናገረው ወልድ ዋሕድ ቢሆን እንጅ ቃል ሥጋን ስላከበረው ለሥጋ ወይንም ለቃል ብቻ የተነገረ ይመስላችኋልን?
❓........ ቃል በሥጋ ርስት ካልከበረ፣ የቀድሞ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስን ካልተቀበለ ቃልን መሲሕ ብሎ መጥራት እንዴት ይቻላል?
ሲጠቃለል "በመጨረሻ ዘመን እንደ እራሳቸው ፍላጎት የሚጋዙ ሐሰተኛ ነብያት ይመጣሉ። እነሱም ለእራሳቸው እና ሰዎችን ለማሳሳት ቅዱሳን መጽሐፍትን ያጣምማሉ ኑፋቄ ያስገባሉና ተጠንቀቁ " የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ግድ አለውና ካባ ደርበው ቆብ ደፍተው በሐዋርያት እግር የተተካን እኛ ነን በማለት ቅዱሳት መጽሐፍትን የሚቆራርጡና ኃይለ ቃል የሚለውጡ፣ በሥም የሚነግዱ ብዙዎቹ ስለሆኑ ልናስተውል ይገባናል::
እኛም “አንተ ግን ከልጅነትህ ጀምረህ ከማን እንደተማርክ ታውቃለህና ፀንተህ ኑር፤ እግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ቅዱሳን መጽሐፍ ሁሉ ለጽድቅ ምክር ይጠቅማል” እንዳለን መጽሐፍ ያለንን አጽንተን ልንይዝ ይገባናል::

~~~~~~~~~ ስብሐት ለሥሉስ ቅዱስ ~~~~~~~~~~~
ቃለ ሕይወትን ያስማልን…………የእኔ ጥያቄ የሚሆነ- ብዙ ጊዜ የቃልም የፅሑፍም መምህራን /// የእግዚአብሔር የባሕርይ ሰሙ አይታወቅም // በማለት ሲናገሩ እሰመለሁ ታዲያ የእግዚአብሔር የባሕርይ ስሙ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይደለምን በውኑ ይሄ ሥም ምንን ያመለክታል በውኑ በሶስቱ አካላት መካከል (ማለቴ፡- በስማቸው፣ በአካላቸውና በግብራቸው መካከል መቀዳደም ይኖራልን፤ በተጨማሪም እንዲብራራልኝ የምፈልገው (ተዋሕዶተ መለኮት በአካላተ ሥላሴና ተዋሕዶተ መለኮት ምስለ ሥጋ/ ምስጢረ ሥጋዌ ምን ይመስላል የሚለው እንዲብራራልኝ እፈልጋለሁ ፡፡ ይሔን ጥያቄ ለመጠየቅ የፈለኩት ብዙ ምክንያቶቸሀ ስላሉኝ ነው አመስግናለ...ሁ
ReplyDeleteEGIZABHAR YISTILN
ReplyDelete