በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
“ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ
መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”==ከፍል አንድ
===========================+=================================
ይድረት ለ “frehiwot aregie”
========+==========
መምሕር እንደሆንክ በጽሁፍህ መጨረሻ ላይ ባስቀመጥከው መልኩ ልከህልናል ፡፡
መነሻ ሀሳብህም “ቅብአተ ማለት ምን ማለት ነው?” በሚል ጥያቄ ላይ ተመርኩዘህ ብዙ ነገር ዘላብደሃል
ቀባጥረሃልም ፡፡ ቅብዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በእኔ ገጽ ቅብዓት ማለት ምን ማለት ነው በሚል ርእስ ጽፌልሃለሁና ያንን
ገብተህ ተመልከትልኝ እያልኩ በዚህ ዓምድ ስር ወዳጅህ “Hailemariam Mengstie” የተባለ ግለሰብ አሰባስቦ
በአንድ ላይ ለለቀቀው ፈጠራችሁ መልስን መስጠት እጀምራለሁ ፡፡ የምጀምረውም “ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ
መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም” በሚለው የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ይሆናል ፡፡
1ኛ‹‹‹‹‹‹
“ይህ ቃል ብዙ ሰዎች እንደፈለጉት ይተረጉሙታል ።በተለይ ቅብአት ነን ብለው ስለ ቅብአት የሚከራከሩ ፣የሚጽፉ ያለ ትርጉም ትርጉም፣ ያለ ፍችው ፍች ፣ያለ ምስጢሩ ምስጢር ተሰጥቶት እናያለን”››››ብለህ ጽፈሃል ፤ በአምላክ
ቸርነት ልለምንህና የት ላይ ያለ ፍችው ፍች ያለ ምሥጢሩ ምሥጢር እደሰጠነው ልትጽፍልኝ ይቻልህ ይሆን? ይህች በስማ በለው
እየተውተረተረች የምትነገረዋ ከንቱ ለፈፋችሁ ሊያበቃላት ጫፍ ላይ ደርሳለች ፡፡
2ኛ‹‹‹‹‹‹
“በእኛ ቤትም ቀብአ ወይም ቅብአት የሚል ገጸ ንባብ ሲያገኙ ይህ የቅብአቶች ነው እያሉ ያለ መልሱ መልስ የሚሰጡን እንሰማለን”›››››››ይህ ሀሳብ አንተን ጨምሮ ይመለከትሃልና ስሕተት
መሆናችሁን በደንብ መረዳት አለብህ፡፡
3ኛ‹‹‹‹‹‹“ቅብአትን ቅብአት
ነን ባዮች ሲተረጉሙ እንዲህ ይላሉ፦
1ቀብአ ማለት ቀባ ፣ለከከ፣ለቀለቀ፣ማለት ነው ፤ 2 ቀብአ ማለት አከበረ ማለት ነው ይሉና ከዚህ ውጭ ግን ቀብአን ተዋሐደ እያሉ ያለ ቋንቋው ያለ አገባቡ ያለ ስልቱ መተርጎም ስህተት ነው ብለው ተቀብአን ተዋሐደ ብሎ መተርጎም እንደማይገባ ይናገራሉ”››››››››ብለሃል ፤ በነገራችን
ላይ ቀብዓን ቀብዓ ለከከ ለቀለከ ብለው የተረጎሙት ኢትዮጵያውያን የልሳነ ግእዝ ሊቃውንት ናቸው እንጅ እኛ የተረጎምነው አይደለንም
፡፡ ለአብነትም የቀለም ቀንድ አለቃ ኪዳነ ወልድ ቅብዓት ማለትን “መቅባት መቀባት አቀባብ ቅብነት ቅባት” ይሉታል ፤ ቀቢዕ
የሚለውን ደግሞ መቅባት መቀባት መላከክ መለቅለቅ መሾም ለማክበር ለመፈወስ” ብለው ያብራሩታል (ገጽ 779-80) ፤ ሌላው ሊቅ
ደስታ ተክለ ወልድም እንዲሁ “ቀባ(ቀብዐ) ላከከ ለቀለቀ ደለሰ(ቅቤን) ፡፡ የሕጻንን ሕዋሳት ሜሮን አስነካ ፤ በራስ ላይ
ዘይት አፈሰሰ ፤ አከበረ ሾመ ሥልጣን ሀብት ሰጠ ችሎት አሳደረ ዐደለ ሰጠ ካህን ነቢይ ንጉሥ አደረገ” ብለው ትርጉመውታል
(ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ደስ ተክለወልድ) ፡፡ አስተውል እንግዲህ ይህንን ቀብዓ ወይም አከበረ የሚለው ቃል እንዴት እንደሚተረጎም
ከሰዋስው ምሁራን መረጃ ከጠቀስን ቀብዐን ተዋሐደ ብሎ መተርጎም ጽኑዕ ክሕደት መሆኑን አጥብቀን እንናገራለን ፡፡ “ተቀብዓን
ተዋሐደ” ብላችሁ ሰሙን ወርቅ አድርጋችሁ ያለ አገባቡ ብትተረጉሙት በክሕደት አረንቋ ውስጥ የሚዘፍቃችሁ ነው የሚሆነው ፡፡
ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳ 3 ላይ “መለኮቱሰ ኢይትቀባዕ(መለኮቱ ቅብዓትን አይሻም)” ይላልና ቅብዓት የሚለው
ተዋሕዶ ተብሎ ተለውጦ ቢተረጎም “መለኮት አልተዋሐደም ተዋሕዶን አይሻም)” የሚል ክሕደትን ያሽክማችኋል ፡፡ ቅዱስ ቄርሎስም
ድር 29 ላይ “ኢይጽሕቅ ቅብዓተ በህላዌሁ(በባሕርየ መለኮቱ ቅብዓትን አይሻም)” ብሏልና ቅብዓትን ያለ ምሥጢሩ ለውጦ ተዋሕዶ
ቢሉት “በባሕርየ መለኮቱ ተዋሕዶን አይሻም)” ያሰኛልና ጽኑዕ ክሕደትን ያመጣል ፡፡ በመሆኑም ቅብዓት ክብር ተብሎ ሲተረጎም
ተዋሕዶ ማለት ደግሞ አንድነት ተብሎ ይተረጎማል እንጅ ገልብጦ ቢተረጉሙት ገልብጦ ነው የሚጥል ፡፡