በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
“ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ
መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”==ከፍል አንድ
===========================+=================================
ይድረት ለ “frehiwot aregie”
========+==========
መምሕር እንደሆንክ በጽሁፍህ መጨረሻ ላይ ባስቀመጥከው መልኩ ልከህልናል ፡፡
መነሻ ሀሳብህም “ቅብአተ ማለት ምን ማለት ነው?” በሚል ጥያቄ ላይ ተመርኩዘህ ብዙ ነገር ዘላብደሃል
ቀባጥረሃልም ፡፡ ቅብዓት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በእኔ ገጽ ቅብዓት ማለት ምን ማለት ነው በሚል ርእስ ጽፌልሃለሁና ያንን
ገብተህ ተመልከትልኝ እያልኩ በዚህ ዓምድ ስር ወዳጅህ “Hailemariam Mengstie” የተባለ ግለሰብ አሰባስቦ
በአንድ ላይ ለለቀቀው ፈጠራችሁ መልስን መስጠት እጀምራለሁ ፡፡ የምጀምረውም “ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ
መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም” በሚለው የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ይሆናል ፡፡
1ኛ‹‹‹‹‹‹
“ይህ ቃል ብዙ ሰዎች እንደፈለጉት ይተረጉሙታል ።በተለይ ቅብአት ነን ብለው ስለ ቅብአት የሚከራከሩ ፣የሚጽፉ ያለ ትርጉም ትርጉም፣ ያለ ፍችው ፍች ፣ያለ ምስጢሩ ምስጢር ተሰጥቶት እናያለን”››››ብለህ ጽፈሃል ፤ በአምላክ
ቸርነት ልለምንህና የት ላይ ያለ ፍችው ፍች ያለ ምሥጢሩ ምሥጢር እደሰጠነው ልትጽፍልኝ ይቻልህ ይሆን? ይህች በስማ በለው
እየተውተረተረች የምትነገረዋ ከንቱ ለፈፋችሁ ሊያበቃላት ጫፍ ላይ ደርሳለች ፡፡
2ኛ‹‹‹‹‹‹
“በእኛ ቤትም ቀብአ ወይም ቅብአት የሚል ገጸ ንባብ ሲያገኙ ይህ የቅብአቶች ነው እያሉ ያለ መልሱ መልስ የሚሰጡን እንሰማለን”›››››››ይህ ሀሳብ አንተን ጨምሮ ይመለከትሃልና ስሕተት
መሆናችሁን በደንብ መረዳት አለብህ፡፡
3ኛ‹‹‹‹‹‹“ቅብአትን ቅብአት
ነን ባዮች ሲተረጉሙ እንዲህ ይላሉ፦
1ቀብአ ማለት ቀባ ፣ለከከ፣ለቀለቀ፣ማለት ነው ፤ 2 ቀብአ ማለት አከበረ ማለት ነው ይሉና ከዚህ ውጭ ግን ቀብአን ተዋሐደ እያሉ ያለ ቋንቋው ያለ አገባቡ ያለ ስልቱ መተርጎም ስህተት ነው ብለው ተቀብአን ተዋሐደ ብሎ መተርጎም እንደማይገባ ይናገራሉ”››››››››ብለሃል ፤ በነገራችን ላይ ቀብዓን ቀብዓ ለከከ ለቀለከ ብለው የተረጎሙት ኢትዮጵያውያን የልሳነ ግእዝ ሊቃውንት ናቸው እንጅ እኛ የተረጎምነው አይደለንም ፡፡ ለአብነትም የቀለም ቀንድ አለቃ ኪዳነ ወልድ ቅብዓት ማለትን “መቅባት መቀባት አቀባብ ቅብነት ቅባት” ይሉታል ፤ ቀቢዕ የሚለውን ደግሞ መቅባት መቀባት መላከክ መለቅለቅ መሾም ለማክበር ለመፈወስ” ብለው ያብራሩታል (ገጽ 779-80) ፤ ሌላው ሊቅ ደስታ ተክለ ወልድም እንዲሁ “ቀባ(ቀብዐ) ላከከ ለቀለቀ ደለሰ(ቅቤን) ፡፡ የሕጻንን ሕዋሳት ሜሮን አስነካ ፤ በራስ ላይ ዘይት አፈሰሰ ፤ አከበረ ሾመ ሥልጣን ሀብት ሰጠ ችሎት አሳደረ ዐደለ ሰጠ ካህን ነቢይ ንጉሥ አደረገ” ብለው ትርጉመውታል (ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ደስ ተክለወልድ) ፡፡ አስተውል እንግዲህ ይህንን ቀብዓ ወይም አከበረ የሚለው ቃል እንዴት እንደሚተረጎም ከሰዋስው ምሁራን መረጃ ከጠቀስን ቀብዐን ተዋሐደ ብሎ መተርጎም ጽኑዕ ክሕደት መሆኑን አጥብቀን እንናገራለን ፡፡ “ተቀብዓን ተዋሐደ” ብላችሁ ሰሙን ወርቅ አድርጋችሁ ያለ አገባቡ ብትተረጉሙት በክሕደት አረንቋ ውስጥ የሚዘፍቃችሁ ነው የሚሆነው ፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳ 3 ላይ “መለኮቱሰ ኢይትቀባዕ(መለኮቱ ቅብዓትን አይሻም)” ይላልና ቅብዓት የሚለው ተዋሕዶ ተብሎ ተለውጦ ቢተረጎም “መለኮት አልተዋሐደም ተዋሕዶን አይሻም)” የሚል ክሕደትን ያሽክማችኋል ፡፡ ቅዱስ ቄርሎስም ድር 29 ላይ “ኢይጽሕቅ ቅብዓተ በህላዌሁ(በባሕርየ መለኮቱ ቅብዓትን አይሻም)” ብሏልና ቅብዓትን ያለ ምሥጢሩ ለውጦ ተዋሕዶ ቢሉት “በባሕርየ መለኮቱ ተዋሕዶን አይሻም)” ያሰኛልና ጽኑዕ ክሕደትን ያመጣል ፡፡ በመሆኑም ቅብዓት ክብር ተብሎ ሲተረጎም ተዋሕዶ ማለት ደግሞ አንድነት ተብሎ ይተረጎማል እንጅ ገልብጦ ቢተረጉሙት ገልብጦ ነው የሚጥል ፡፡

4ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “3ቅብአት ማለት መንፈስቅዱስ ተብሎ ይተረጎማል ይላሉ”››››››››ብለሃል ፤ አዎ ይህንንም እውነት ነው እንላለን ፤ ይህንንም ስንል እንደ እናንተ በአሉ ይባላል ተረት ተረት ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ነው ፡፡ ተቀበል!!! ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት ምዕ 38 ቊ 9 ላይ “መንፈሰ እዚአብሔር መሰጦ ለፊልጶስ (የእግዚአብሔር ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው) ፡፡ ሐተታ ቅብዓ ትፍስሕ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደለት ለማጠየቅ ነው” ብሏል፡፡አስተውል ቅብዓ ትፍስሕት መንፈስ ቅዱስ የሚለውን ከመዝሙር 44 ቁ 7 ጋር አስማምተህ ተርጉመው ፡፡ ዮሐንስ አፈወርቅም መዝሙር 44 ቁ 7ን ሲተረጉም “እስመ ለእግዚእ ክርስቶስ አኮ በመስፈርት ዘተውህቦ መንፈስ(መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ በልክ በመጠን የተሰጠው አይደለምና ይቤ ቅብዓ ትፍስሕት እእለ ከማከ)” ብሏል ድር 3 ላይ ፡፡ ከዚህም ላይ ቅብዓ ትፍስሕት የተባለ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እወቀው አንተ ሞኝ ፡፡
5ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹ “4ቅብአትን ሕይወት እያለ ሲተረጉም ወልደአብ በሚባል የኑፍቄ መጽሐፍ ይታያል (ወልደ አብ ገጽ 179) አሁንም አእማደ ምሥጢር የሚባል የኑፍቄ መጽሐፍ አለ (ገጽ 22)።”›››››ወልደአብ በዚህ በጠቀስከው ገጽ ላይ “ወአርአየ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ በኃይሉ ወበመንፈሱ ቅዱስ(ኃይሉ ሕይወቱ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አሳየ)” ብሎ ሮሜ 1 ቁ 4ን ጠቅሶ ያብራራል ወልደ አብ ፤ ምክንያም ከላይ እንዳየነው የቅብዓት ጣዕመ ምሥጢሩ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ክብርነት አንድም ሕይወትነት ከአብ በሰውነቱ በማኅጸነ ማርያም መወለዱን ሲነግረን ነው ፡፡ “ተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝ ውእቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ(ኃይሉ ሕይወቱ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ተባለ ይኸውም ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ነው)” እንዳለ ቅዱስ ቄርሎስ ምቅዋም 8 ላይ ፡፡
6ኛ‹‹‹‹‹‹‹
“ቅብዓትን ቅብአትን ቅዱሳት መጽሐፍት ሲተረጉሙት፦በዓለም ላይ ብዙኀኑ መጽሐፍ ቅዱስን ይቀበላል ። ግን በእምነት ይለያያል ብዙኀኑ በአንድ መጽሐፍ ቅዱስ እንመራለን ይላል ግን ይለያያል ። በአንድ በክርስትና ስም እንኳን ከሃምሳ ሺህ በላይ የእምነት ልዩነት አለ ። ለምን ካልከኝ ችግሩ ከንባብ ሳይሆን ከአረዳዱ ከአተረጓጉሙ ነውና ፡፡ ለዚህም ነው የብዙኀኑ ጥያቄው የሚበዛ ከንባቡ ከጥቅሱ ሳይሆን ከአረዳዱ ከአተረጓጉሙ ነው፡፡”›››››ብለሃል መጻሕፍት እና ደጋግ ሊቃውንት እንደ አንድ
ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሁነው የተረጎሙት ትርጓሜ ከላይ እንደገለጽኩልህ ሲሆን ቅብዓትን ለውጦ ተዋሕዶ ብሎ
የመተርጎም ጠማማ አእምሮን የተቀበላችሁ እናንተ ጠፍታችሁ ሌላውን እያጠፋችሁ ነውና ከቻላችሁ ከስህተታችሁ ተመለሱ ካልቻላችሁ ደግሞ
ለእናተ ክሕደት እንዲመቻችሁ መጻሕፍትን እየቆራረጣችሁ እየዘነጣጠላችሁ አታስቀምጧቸው ፡፡ ስለ ቅብዓት ትርጓሜ እነቅዱስ ዮሐንስ
ጥርት አድርገው ሲተረጉሙ ተዋሕዶ ተብሎ ይተረጎማል አላሉንም ፤ እንዲያው እናንተ ከማን ተማራችሁት? የቀናውን አተረጓጎም እነ
አፈወርቅ አብራርተው ተርጉመውልናልና እነሱን እንመስላለን እንጅ እንደ እናንተ እየለወጥን እየገለበጥን ንስጥሮስን አንመስልም
፡፡
7ኛ‹‹‹‹‹ “ለዚህም
ነው የቅብአት እምነት ተከታዮች ብዙዎችን እያወዛገቡ ያሉ በንባብ በጥቅስ ነው”››››› ዓይንና እዝነ ልቡና ካለህ
የቅብዓትን ትርጉም ተመልከተው “…እስመ ዘይትወለድ እምኔሃ እመንፈስ ቅዱስ ውእቱ (ከእሱዋ የሚወለደው በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና ፤ ማቴዎስ
እመንፈስ ቅዱስ ያለውን ፣ሉቃስ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ያለውን ፣ ኢሳይያስ መንፈሰ እግዚአብሔር ዘላዕሌየ ዘበእቲአሁ
ቀብዓኒ ያለውን ሊቁ ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም ብሎ ወስዶታል ፡፡ ንጽሕን ክብር የሚል
ወዴት አለ ቢሉ ወሠዓርኮ እምጽሑ ይላል” ማቴ ምዕ 1 ቁ 20 አንድምታ ትርጓሜ ፡፡ ታዲያ በዚህ ላይ መልስህ ምን እንደሆነ እጠብቃለሁ??ወዳጃችን
ልጅ ለእናቷ ምጥ አታስተምርም ይገባሃል ፡፡ እኛ የምናምነው በትርጓሜ እንጅ በነጠላ ዘር ብቻ አይደለምና ከንቱ ለፈፋህን አትናገር
፡፡
8ኛ‹‹‹‹‹‹ ቅብአትን ቅዱሳት
መጽሐፍት ሲተረጉሙ ፦
1 ቅብአት ማለት በቁሙ ቅብአት ማለት ነው ።ለከከ ፣ለቀለቀ፣ቀባ ፣የሚለውን ትርጉም ያመጣል ።ዩሐ 12:3 "ወማርያምሰ ነስአት እፍረተ ለጥረ ዘናርዱ ጵስጥቂስ" ብሎ ማርያም ጌታን ሽቱን ቀባችው ብሎ እንደተረጎመው ።በዚህ ትርጓሚ እነሱም እኛም እንስማማለን ።
2 ቀብአ -ከበረ ተብሎ ይተረጎማል ማቴ 1 ፦ ትርጓሜው እንዲህ ይላል ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው ይላል ።ሲከብርም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው ሲል ነው።ማለትም ስጋ ከቃል ጋር ሲዋሐድ መጀመሪያ ተዋሕዶ አልከበረም ከብሮም ሳይዋሐድ አልቆየም ሲከብርም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው ሲል ነው ።እስከ አሁን በአለው ትርጓሜ አንለያይም”››››››››ደግ ብለሃል ፡፡

ስብሐት ለሥሉስ ቅዱስ
ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment