Thursday, June 4, 2020

“ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”==ከፍል ሁለት


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”==ከፍል ሁለት
===========================+====================
ይድረት “frehiwot aregie”
========+==========
1ኛ‹‹‹‹‹‹ “3ተኛ ተዋሐደ ተብሎ ይተረጎማል ።ቅብአቶች ከእኛ የሚለዩበት አንዱ ይህ ነው። የፈለገው ቢሆን ቀብአን ተዋሐደ ብለው አይተረጉሙም ግን መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦አባ ጊወርጊስ በመጽሐፈ አርጋኖን ላይ እንዲህ ይላል ዘተቀባአከ ስጋሃ ለማርያም ይላል ።ይህ ንባብ የሚተረጎመው የማርያምን ስጋ የተዋሐድህ ተብሎ ነው። ከዚህ ውጭ የፈለገው ሊቂ ይምጣ ሊተረጉመው አይችልም”››››››››ብለሃል ፤ ከዚህ በፊት በክፍል አንድ እንደጻፍኩልህ ከቄርሎስና ከአፈወርቅ ትምህርት ጋር የማይገጥም ነውና በምንም ተዓምር ተቀብዐ ተዋሐደ ተብሎ አይተረጎምም ፡፡ የጠቀስካት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የአርጋኖን መልእክት” ዘተቀባዕከ ሥጋሃ ለማርያም” የሚለው ቃል ትርጓሜው ሰም ለበስ ግስ ነውና ሰም ለበስ ትርጓሜ ይተረጎማል ፡፡ ይህም ማለት  አባ ጊዮርጊስ በአንቀጸ ተቀብዓ ተገብቶ ምሥጢር ስቦታልና ዘተቀባዕከ ሥጋሃ አለው ፤ ትርጓሜው ግን እዚያው አርጋኖን ላይ ቁልጭ ብሎ አለ ይህንን ከተናረ በኋላ “እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ በከመ ተርጎመ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት)” በማለት አስቀምጦታል ፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ የተረጎመው ደግሞ “በእንተ ቅብዓት ተሰምየ ክርስቶስ እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ በመንፈስ ቅዱስ ብሂል” ብሎ ነው ፡፡በመሆኑም ይህች ዘተቀባዕከ ሥጋሃ ለማርያም የሚለው ቃል በሥጋ ማርያም የተቀባህ አንተነህ ማለቱ ነው ይህ የወርቅ አነጋገር ነው ፡፡

2ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “በከበረ እንዳይተረጎም የማርያምን ስጋ የተከበርህ አይባልም።በቀብአ እንዳይተረጎም የማርያምን ስጋ የተቀባህ አይባልም ሥጋ ቅብ ይሆናል”››››››በማርያም ሥጋ የከበርክ ማለት እኮ ሥጋ አከበረህ ማለት ሳይሆን ከማርያም በነሣኸውና በተዋሕዶ ገንዘብ ባደረግኸው በሰውነትህ ተቀባህ ከበርክ ማለት ነው መምሕሩ ፍሬ ሕይወት፡፡
3ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “ሥለዚህ የቅብአት ተከታዮች ቀብአን ተዋሐደ ብሎ የተረጎመ አባ ጊወርጊስ ነው።ሥለዚህ የእናንተን እንቀበል ወይስ አባ ጊወርጊስን ? እኛ ከአባ ጊወርጊስ አረዳድ አንወጣም። ›››››አባ ጊዮርጊስ የተናገረውን ነጠላ አንቀጽ ብቻ ይዘህ ከምትሮጥ ከላይም ከታችም ብትመለከተው ይነግርሃልና አስተውለው ወዳጃችን ፡፡
4ኛ‹‹‹‹‹ “አንዳንድ ቦታ ደግሞ አንድ ንባብ ሁለት ትርጓሜ ሁለት አረዳድ ይኖረዋል ።ለምሳሌ ክርስቶስ ማለት በጽርእ ነው ፣መሲህ ማለት በእብራይስጥ ነው፣ቅቡእ በግእዝ ነው ። ቅቡእ ማለት ግን የተዋሐደ የከበረ ተብሎ ይተረጎማል”››››››ቅቡዕ ማለት የተቀባ የከበረ ማለት እንጅ የተዋሐደ የሚል ትርጓሜ የለውም ፤ አለው ካልክ ማስረጃህን ላክልኝ? ሌላው ትክክል ነህ ፡፡
5ኛ‹‹‹‹‹‹ “ሁሉ ግን እንዲህ ይተረጎማል ማለት አይደለም ።ለምሳሌ ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው ይላል ይህ የሚተረጎመው ሲከብር ተብሎ ብቻ ነው ።ሥለዚህ እንደ አመጣጡ ይተረጎማል”››››ይህንንም “ከመረቁ አውጡልኝ ከሥጋው ጾመኛ ነኝ” ዓይነት ሀሳብ ብየዋለሁ ፡፡ ምክንያቱም ሲቀባም ሲዋሐድም ከመ ቅጽበት አንድ ጊዜ ነው መባሉ ቃል ከሥጋ ጋር ሲዋሐድና በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ሲከብር አንድ ጊዜ ነው ለማለት በመሆኑ አንድ ጊዜ ተዋሕዶ አንድ ጊዜ ቅብዓት እያሉ እያለባበጡ መናገር ከንቱነት እንደሆነ ተረዳው ፡፡
6ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “በነገረ ቅብአት መንፈስ ቅዱስን ቅብአት ብሎ መተርጎም የተለመደ ሆኗል ። ለዚህም መነሻቸው እና ምክንያታቸው ገጸ ንባብ ነው። ነገር ግን መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ንባብ ላይ የተመሠረተ አይደለም።እራሱ መጽሐፍ ቅዱስ "ንባብ ይቀትል ወትርጓሜ የሐዩ" ንባብ ይገላል ትርጓሜ ያድናል ይለናል።ቅብአት ነን ባዮችን የገደላቸው ንባብ ነው”›››››››ብለሃል ፤ ቅብዓትን መንፈስ ቅዱስ ብሎ የመተርጎም ምሥጢሩ ሊቃውንት ያመሠጠሩት ፣ መጻሕፍት የመሰከሩት ነባራዊ ሐቅ ነው ፡፡ በክፍል አንድ የተወሰኑትን ጠቅሰናል አሁንም አንተ ራስህ የጠቀስከውን ተቀበለ!!! ቅዱስ ኢጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ዘሠሉስ ምዕ 2 ቁ 18 ላይ “ወእምዝ ተቀብአ ቅብአ ትፍስስሕት ዘክርስቶስ ዘቦቱ ይነስኡ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ ኩሎሙ አህዛብ ይልና እንዲህ ይላል ይህስ ቅብአት ምንድን ነው ቢሉ ቀድሞ ጌታችን ከባህሪይ አባቱ በባህሪይ ልጅነቱ ተወልዶ የባህሪይ ልጅነት ያገኘበት መንፈስ ቅዱስ ነው።ዛሬ ህዝቡ አህዛቡ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነትን የሚወለዱበት ቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ይህ ነው። ይህም ቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ነው”›››ብሏል፡፡ ዘእሁድ ክፍል 4 ቁ 1 ላይም በደንብ ተናግሮታል ፡፡ ይህም ቃል ትክክለኛ ምሥጢራዊ ትርጓሜው እንደሆነ መረዳት ይቻላል ፡፡ ንባቡ ቅብዓት የሚለው ክብር ማለት ሲሆን ፤ ክብር የተባለ ምሥጢሩ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን እወቀው ፡፡
7ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “ቅብአት ነን ባዮቹ ባረዳድ ከእነዚህ የተለዩ አይደሉም። እንዲህ ይላሉ ቅብአት ማለት ምስጢራዊ ትርጉሙ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው ይላሉ (ወልደ አብ ገጽ 181፣አእማደ ምስጢር ገጽ 19) ። ለዚህም መነሻቸው መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘማክሰኞ ነው እንዲህ ይላል ወእምዝ ተቀብአ ቅብአ ትፍስስሕት ዘክርስቶስ ዘቦቱ ይነስኡ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ ኩሎሙ አህዛብ ይልና እንዲህ ይላል ይህስ ቅብአት ምንድን ነው ቢሉ ቀድሞ ጌታችን ከባህሪይ አባቱ በባህሪይ ልጅነቱ ተወልዶ የባህሪይ ልጅነት ያገኘበት መንፈስ ቅዱስ ነው።ዛሬ ህዝቡ አህዛቡ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነትን የሚወለዱበት ቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ይህ ነው። ይህም ቅብአተ መንፈስ ቅዱስ ነው ይላል ።መነሻቸው ይህ ነው መንፈስ ቅዱስን ቅብአት ለማለታቸው። ነገር ግን ስህተቱ ከመጽሐፍ አይደለም ከአረዳዳቸው ነው እንጅ። ከዚህ ላይ ቅብአት ያለው መንፈስ ቅዱስን ሳይሆን ግብረ መንፈስ ቅዱስን ነው”›››››››ሞኝ ትውልድ እንደ አንተ አላየሁም “ይህ ቅብዓት ምንድን ነው ቢሉ መንፈስ ቅዱስ ነው” ይላል እንጅ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ ነው” ይላልን?ወይ ጉድ ጎበዝ የእናንተ የምሥጢር ትርጓሜ እንዲህ ነው!?
8ኛ‹‹‹‹‹‹ “ግብረ መንፈስ ቅዱስ ማለት ደግሞ የማይመረመር አምላካዊ ግብር ነው።እንዴት ካላችሁኝ አብ ወልድን ወለደው ስንል ከማይመረመር አምላካዊ ግብር ነው።ያንን ነው መንፈስ ቅዱስ ያለው።ለመጽሐፍ ግብረ መንፈስ ቅዱስን መንፈስ ቅዱስ ማለት ልማድ ነው እና ።ከውሀና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም እንዲል።አሁን ሰው የሚወለደው ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ሆኖ አይደለም መንፈስ ቅዱስ ያለው ግብረ መንፈስ ቅዱስ ነው እንጅ”›››››››በጣም ጥሩ ብለሃል ቅብዕ መሆን ግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እኛም የምናምነው ነውና ለማያምኑቱ ወገኖችህ ንገርልን ፡፡
9ኛ‹‹‹‹‹ “ሌላም ማቴ (1) እስመ ዘይትወለድ እምኔሃ ወእመንፈስቅዱስ እንዲል የሚወለደው ከእርሷ እና ከመንፈስ ቅዱስ ነው ይላል።አሁን እመቤታችን ከመንፈስ ቅዱስ ወልዳ አይደለም አሁንም መንፈስ ቅዱስ ያለው ግብረ መንፈስ ቅዱስ ( የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው ) አምላካዊ ግብር ነው እንጅ”››››››››የዚህን ትርጓሜ ተቀበለኝ “…እስመ ዘይትወለድ እምኔሃ እመንፈስ ቅዱስ ውእቱ (ከእሱዋ የሚወለደው በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና ማቴዎስ እመንፈስ ቅዱስ ያለውን ፣ሉቃስ መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ያለውን ኢሳይያስ መንፈሰ እግዚአብሔር ዘላዕሌየ ዘበእቲአሁ ቀብዓኒ ያለውን ሊቁ ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም ብሎ ወስዶታል ፡፡ ንጽሕን ክብር የሚል ወዴት አለ ቢሉ ወሠዓርኮ እምጽሑ ይላልማቴ ምዕ 1 20 አንድምታ) ፡፡ አባቶቻችን እንዲህ በማለት ነግረውናል ፡፡ አስተምረውንማል ፡፡
10ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹ “ሥለዚህ ቅብአት ነን ባቹ ሆይ አስተውሉ ይህንን ንባብ መንፈስ ቅዱስ ብላችሁ ከተረጎማችሁት ብዙ ነገር ያፍልሳል።1 ከፍ ብሎ መላዕክትን ሰማያትን ቀባ ይላል ቅብአቱ መንፈስ ቅዱስ ከሆነ መላዕክት ሰማያት የባህሪይ አምላክ ሆኑ ያሰኛል”››››››››››››ብለሃል ፤ በጣም ጥሩ ነው በአክሲማሮስ ዘእሁድ ክፍል ዓራት ላይ መላእክትን የመላእክትን ከተሞች ሰማያትን እንደቀባ ይናገራል ፡፡ ይህን ይዞ መላእክት በመንፈስ ቅዱስ ስለተቀቡ የባሕርይ አምላክ ሆኑ እያሉ መናገር ክሕደት ነው ፡፡ አየህ መምሕሩ ፍሬ ሕይወት! ልዩነታችን እኮ እዚህ ላይ ነው የጸጋ ቅብዓትንና የባሕርይ ቅብዓትን አለመለየታችሁ ነው ይህንን የሚያናግራችሁ ፡፡ ይህንን የአንተን ጥያቄ የሚመልሰው ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ጳውሎስ “አፍቀርከ ጽድቀ ወጸላእከ ዓመጻ በእንተዝ ቀብአከ እግዚአብሔር ቅብዓ ትፍስሕት ዘይኄይስ እምእለ ከማከ(ጽድቅን ወደድቅ አመጻን ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባለንጀሮችህ በሚበልጥ የደስታ ዘይት ቀባህ)” ብሎ በዕብራውያን 1 ቁ 9 ላይ የተናገረውን በድርሳኑ ሲተረጉምልን “ወበእንተሰ መላእክቲሁ ይቤ ዘይሬስዮሙ ለመላእክቲሁ መንፈሰ ወለእለ ይለአክዎ ነደ እሳት ወበእንተ ወልዱሰ ይቤ መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም ወመትልው ዝንቱ (ቀብዓከንም ተናገረ ዝንቱ መንበርከ መትልቅ ቀብዐከ ነው) ብሎ በሚጀምረው ሦስተኛው ድርሳኑ ቁጥር 90-1 ላይ “ናሁ አዖቀ ከመ ልደተ ወከዊነ ተፈጥሮ ኢኮነ አሐደ (ቀዳማዊ ልደቱና የመላእክት ተፈጥሮ አንድ እንዳይደለ አስረዳ) ፡ ሶበሰ አሐዱ እሙንቱ እምኢይቤ በእንተ ወልዱሰ ይቤ መንበርከ ኦ አምላክ ለዓለመ ዓለም (አንድ ሁኖስ ቢሆን ስለወልድ መንበርከ አለ ብሎ ጳውሎስ ባልተናገረም ነበር ፡፡አንድም የጌታ የባሕርይ ልደቱ እኛ በሐዲስ ከምንፈጥረው ተፈጥሮ አንድ እዳይደለ ኢኮኑ ይላል አንድ እንዳይደሉ አስረዳ ፡፡ አንድ ሁኖስ ቢሆን ዘይኄይስ ባላለም ነበር” በማለት የመላእክትን መቀባትን የክርስቶስን መቀባት አንድ አድርገን እንዳጠፋ አስረድቶናል ፡፡

11ኛ‹‹‹‹‹‹‹“2
ምስጢረ ሥላሴን ያፍልሳል ወልድ ከባህሪይ አባቱ ተወልዶ የባህሪይ ልጅነት ያገኘበት መንፈስ ቅዱስ ነው ማለት”››››››› ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወልደ ማርያም ሥግው ስለሰውነቱ ከአባቱ ከአብ የባሕርይ ልጅነት የተወለደበት ቅብዓቱ መንፈስ ቅዱስ ስለመሆኑ ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ ብሏል ““ይጽሕፍ እንዘ ይብል ጳሎስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስሙይ ሐዋርያ ስተ መንገለ እግዚአብሔር ዘአቅደመ ነጊረ በነብያቲሁ ወበመጻሕፍቲሁ ቅዱሳት ፤ በእንተ ወልዱ ዘኮነ እምዘርዐ ዳዊት በሥጋ ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝ እቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ፤ እፎ ንግረኒ አምላክ ውእቱ ፤ ዘእምዘርዐ ዳዊት ተወልደ ወመጽአ ፤ ወሀሎ እምቅድመ ዓለም ወልድ ፤ ዘለዝላፉ ይሄሉ ምስለ እግዚአብሔር አብ፤ በአይ እንከ ፍና ተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝ ውእቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ፤እስመ ይቤ ውእቱ በእንተ ርእሱ እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ፤
እስኪ ንገረኝ አምላክ ሲሆን በእንተ ወልዱ እንደምን አለው?፤ እምዘርዐ ዳዊትስ እንደምን አለው?፤ ቅድመ ዓለም የነበረውን፤ ከአብ ጋር በቅድምና የነበረ እርሱን ፤ ወአርአየ ከመ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ወበመንፈስ ቅዱስ እንደምን አለው፤ በዳዊት አድሮ እሱ ስለራሱ እንዲህ ብሏልና ፤ አንድም እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ አለኝ ብሏልና ተሠርዓ አለው” (በሕትሙ ድርሳን 24 t 1- 3) ብሏል ፡፡ በመሆኑም በሰውነቱ በባሕርይ ሕይወቱ ቅብዓትነት ከአባቱ ልደት ባሕርያዊትን ስለ ሰውነቱ ተወልዷል ፡፡
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ይቀጥላል




No comments:

Post a Comment