በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
“ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”==ከፍል ሦስትት
===========================+====================
ይድረት ለ “frehiwot aregie”
“ዛቲመ ትርጓሜሃ ለቅብዓት እስመ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋሁ ለአዳም”==ከፍል ሦስትት
===========================+====================
ይድረት ለ “frehiwot aregie”
========+==========
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹
“3ኛ ንባብ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው ሲተረጉም የመንፈስ ቅዱስ ቅብአት ተብሎ እንጅ ቅብአት ያለው መንፈስ ቅዱስ አይደለም” ›››››››››››››ብለሃል ፤
ወዳጃችን አክሲማሮስ እየነገረን ያለው “ወአንትሙሰ ቅብዓት ብክሙ እምነ መንፈስ ቅዱስ” እንዳለ ፤ ሕዝቡ አሕዛቡ የጸጋ ልጅነት
የተወለድንበት እርሱ መድኅን ክርስቶስ በማኅፀነ እሙ ሰው ስለመሆኑ በሰውነቱ ልደት ባሕርያዊትን ከአብ የተወለደበት ቅብዓቱ
መንፈስ ቅዱስ እደሆነ ነው ፡፡ “ይህ ቅብዓት ምንድን ነው ቢሉ መንፈስ ቅዱስ ነው” ብሎ እየነገረን ሳለ ልቡናን እንደፈርዖን
ማደንደን አይጠቅምህም ፡፡
2ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “4ኛ ለቅዱሳት መጻሕፍት ረቂቁን ነገር ለመንፈስ ቅዱስ መስጠት ልማድ ነው ።ወልህቀ በመንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ አደገ መንመንፈስ ቅዱስ አደረባት እያለ ረቂቁን የመይመረመር ነገር ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ ይሰጣልና ። ስለዚህ ቅብአት ነን ባዮች አስተውሉ”›››››››››››››ብለሃል ወዳጃችን እኛ አንተ ሳትነግረን ቅዱስ መጽሐፍ ረቂቁን ነገር ለመንፈስ ቅዱስ እየሰጠ እንዲናገር በደንብ እናውቀዋለን ፡፡ አስተውል ! መጻሕፍት ረቂቁን ነገር ለመንፈስ ቅዱስ መስጠታቸው እኛ ሰዎች ሥራችንን የምንሰራው በነፍሳችን ሕያዋን ሁነን እንደሆነ ሁሉ ሥላሴም ማንኛውንም ሥራቸውን ሲያከናውኑ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ሁነው ነውና ስለዚህ ነው ፡፡
2ኛ‹‹‹‹‹ “አብ
ቀበኢ ወልድ ተቀባኢ መንፈስ ቅዱስ ቅብእ ብሎ መተርጎም ይገባል?
ወልደ አብ ገጽ 79 አእማደ ምስጢር ገጽ 21”››››››››››››››ሊቃውንት እንደነገሩን አዎ በደንብ ይቻላል ማስረጃውንም ስንደርስበት እንመለከተዋለን ፡፡
ወልደ አብ ገጽ 79 አእማደ ምስጢር ገጽ 21”››››››››››››››ሊቃውንት እንደነገሩን አዎ በደንብ ይቻላል ማስረጃውንም ስንደርስበት እንመለከተዋለን ፡፡
3ኛ‹‹‹‹‹‹
“✅ማሳሰቢያ በተለይ ቅብአት ነን ስለ ቅብአት እናውቃለን የምትሉ ከስሜት እርቃችሁ ከእልከኝነት ወጥታችሁ አንብቡት እንነጋገር እንወያይ”››››››››››››››እኛ ቅቡዓን
ወይም መሢሐውያን ለውይይት መጽሐፍ ይዘን ስንቀርብ እናንተ ፖሊስ
ይዛችሁ እየቀረባችሁ አስቸገራችሁን እንጅ ቅዱስ መጽሐፍ እየተገለጠ እውነት እውነቱን ለመወያየት ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ ነን ፡፡
4ኛ‹‹‹‹‹‹‹በነገረ
ቅብአት በየአረፍተነገሩ የሚነሳ ሥለ ቅብአት አውቃለሁ የሚል ሁሉ የሚጠቅሰው ጥቅስ በቅዱሳት መጻሕፍት የለም”›››››››››››››››››ይህ ውሸት ብቻ ሳይሆን
ዓይንህን በጨው አጥበህ የተናርከው ክሕደትህ ነው ፡፡ አንተና መሰሎችህ አበበን ከበደ እያላችሁ እየተረጎማችሁ ነው እንጅ እኛ
መሢሐውያን መጽሐፍ የማይለውን ሊቃውንት ያላስማሩትን አንናገርም ፤ ነግግሩ እንኳን “የጦጣ ልጅ በዛፍ የካራ ልጅ በአፍ
የቅብዓት ልጅ በመጽሐፍ” አይደል የሚባለው ፡፡ እስኪ ለውይይት እንዲመቸን ይህ በመጽሐፍ የለም ብለህ አንቀጽ ገልጸህ ምሳሌ
ጠቅሰህ ጻፍልንና እንታዘብህ መምሕሩ ፍሬሕይወት! ፡፡
5ኛ‹‹‹‹‹‹‹”ወልደ አብ አለ ለማለት ብዙ ነገሮችን ጠቅሷል ለማስመሰል ነው”›››››››››››ብለሃል ፤ ወዳጃችን ፍሬሕይወት
ወልደ አብ የጠቀሳቸው አናቅጽት በሙሉ ስለ ቅብዓት በደንብ አድርገው የሚናገሩ ናቸው ፡፡ አንተ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ፊት
ሳይሆን በኋላው የቆምክ ዓይነት ስለሆንክ ሙልጭ አድርገህ ክደኸዋል እንጅ ለማስመሰል ሳይሆን ትክክለኛውም በነቢያት የተነገረውን
፣ በመድኅን ክርስቶስ የተገለጠውን ፣ በሐዋርያት ስብከት ለሰብአ ዓለም የደረሰውን ፣ በሊቃውንት ትርጓሜ የጠራውን እውነት ነው
የነገረህ ፡፡ “መሪር ስምዐጽድቅ ለሐሳዊ እስመ ይከስታ ለሐሰቱ” እንዳለ አባ ጊዮርጊስ ሐሰትህና ሐሰተኛነትህን የሚገልጥብህ
በመሆኑ ለማስመሰል ነው ብትል መደበቂያ ያገኘው መስሎህ ነው እንጅ ወልደ አብ ማስመሰል የሚባል ነገር የለበትም ፡፡
6ኛ‹‹‹‹‹‹ “ወልደ
አብ አንዲህ ይላል .. አብ ቀባኢ ማለት ሰጠ ማለት ነው ይልና በሰውነቱ የባሕሪይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን ሊሰጠው ፈቃዱ ሆነ ማለት ነው ይላል።ቀጥሎ እንዲህ ይላል ወልድ ተቀባ ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተቀበለ ማለት ነው ይላል።ቀጥሎም እንዲህ ይላል መንፈስ ቅዱስ ቅብእ ነው ማለት ምስጢሩ ምንድን ነው ቢሉ ተሰጠ ማለት ነው ይላል፡፡….እንዲህ ይልና ዝቅ ብሎ በምስጢረ ቅብአት ነስአ ተወክፈ የባህሪይ ነው ይላል።”›››››››››››››ብለሃል አዎ ወልደ
አብ እንዲህ አንተ እደተናገርከው የተቆራረጠ ባይሆንም ይላል፡፡ ወልደ አብ አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ” ብሎ
ሲናገር እንዲሁ በፈጠራ በልብ ወለድ ሳይሆን “ እምትርጓሜ መልእክት ዘሮሜ ይቤ መተርጉም እስመ ብሂሎቱ በዝየ ጽውዓን በስመ
ክርስቶስ ወለእመ ኮነ ዘክሮቱ እግዚአብሔር እዘዝ ለስሙ አኮኑ ተዓውቀ እምቅድመ ዓለም ፡፡ ወዘክሮተ መንፈስ ቅዱስኒ ተዓውቀ
በነቢያት ፤ ወዘክሮተ ክርስቶስኒ በእንተ ዘመጽአ ለመድኃኒተ ዓለም እስመ ዝክረ ክርስቶስ ይመርኅ ኀበ ሠለስቱ አካል ዝ ውእቱ
አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅብዕ ዘቦቱ ተቀብዓ ሥጋ ወልድ” ብሎ ቅዱስ ቄርሎስ በተረፈ ቄርሎስ የቆሮንቶስን “ጽውዓን አንትሙ
በስሙ ለክርስቶስ” የሚለውን አንቀጽ በተረጎመበት ክፍል ላይ የተናገረውን መሠረት አድርጎ ነው ፡፡ አብ ሰጠ ማለቱም “ወበከመ
ለአብ ቦቱ ሕይወት ኀቤሁ ከማሁ ለወልድኒ ወሀቦ ሕይወተ ከመ ይኩን ሕይወት ኀቤሁ(ለአብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ
ለወልድም ሕይወት ይኖረው ዘንድ ሕይወትን ዘጠው)” ብሎ ወንጌላዊ ዮሐንስ 5 ቁ 25-26 የተናገረውን መሠረት አድርጎ ነው ፡፡
በሌላም አንቀጽ “አብሰ ያፈቅር ወልዶ ወኩሎ ኩነኔሁ አወፈዮ ለወልዱ(አብ ልጁን ይወደዋልና ሁሉን በእጁ ጭብጥ በእግሩ እርግጥ
አድርገ አስገዛለት)” ብሎ ወንጌላዊው ዮሐንስ ምዕ 3 ቁ 35 ላይ የሰበከውን ይዞ ነው ይሰማል መምሕሩ ፍሬ ሕይወት! ፡፡ በዚህ
አብ ሰጠው ሲል የወልድን ተቀባዒነትም አብረን እንመለከተዋለን ፡፡ ሕይወት ብሎ መንፈስ ቅዱስን ያወሳልናልና መንፈስ ቅዱስ
ተሰጠ መባሉን በደንብ ይነግረናል ፡፡ አስተውል መምሕር ፍሬሕይወት! ሕይወትን ብቻም አይደለም ስልጣንንም እንደሰጠው “ወወሀቦ
ሥልጣነ ከመ ይግበር ፍትሐ ወኵነኔ(ይፈርድ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠው) በማለት ምዕ 5 ቁጥር 27 ላይ ሰብኮልናል ፡፡ አሁንም
መምሕሩ ፍሬ ሕይወት ሆይ አስተውል! ሰጠው ተብሎ የተነገረበትን
ምሥጢር ወንጌላዊ ዮሐንስ ምዕ 5 ቁጥር 27 “እስመ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ እጓለ እመሕያው(የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ
ነውና) ፤ ወሀቦ ሕይወተ ቦ ዘይቤላ መጻሕፍት በእንተ ትስብእቱ እንዲል ፡፡ አንድም የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ ነውና)”
በማለት ቁልጭ አድርጎ ነግሮናል ወዳጃችን ፡፡ መቼ ሰጠው ብለህ ትጠይቀኝ እንደሆነ! “ወቀርበ እግዚእ ኢየሱስ ወተናገሮሙ እንዘ
ይብል ተውኅበኒ ሥልጣነ ሰማይ ወምድር(ጌታ ቀርቦ ሰማይን ምድርን የማሳልፍበት ሥልጣን ተሰጠኝ ብሎ ነገራቸው ፡፡ ሐተታ ነፍሱና
ሥጋው ተለያተው ነበርና የነዚያን የኒያን ተዋሕዶ ሲያይተውህበ ሊተ አለ እንጅ የተሰጠው በማኅፀን ሲዋሐድ ነው)” በማለት
ወንጌላዊ ማቴዎስ ምዕ 28 ቁ 18 ላይ እንደሰበከልን በማኅፀነ እሙ ነው ብየ እመልስልሃለሁ ፡፡ ታዲያ ይህ ንሥአትና ተወክፎ
የባሕርይ እንጅ እንደ ምእመናን የጸጋ አይደለምና ወልደ አብም የተናገረው እውነታው ይህ ሁኖ ሳለ አንተ በድፍረትህና በቅሌትህ ‹‹‹‹‹‹“ይህ አነጋገር የክህደት ክህደት ነው። ለምን ካላችሁኝ 1ኛ በሥላሴ ሰጪ ተቀባይና ሥጦታ ካለ መበላለጥ አለ ያሰኛል”›››››››በማለት ትወራጫለህ ፤
ይህንን ጥያቄ ሀሳብህን ከላይ ከዮሐንስ ወንጌል ጋር አዛምደህ ተመልከተው እስኪ ወዳጄ? አንተን በአካል ባላገኝህም በአካል ያገኘኋቸውና
መጽሐፋቸውን ያነበብኩላቸው “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” የሚሉ ሊቃውንት ጥያቄአችሁ እጅጉን ያስቃል ፡፡ ጎበዝ በእናንተ ልክ
እየቀደዳችሁ እየሰፋችሁ ይህ እንዲህ ያመጣል እያላችሁ ባትጠፉ ይሻላችኋል እላለሁ ፡፡ እህ ወንጌሉ አብ ለልጁ ለወልድ ሕይወትን
ሰጠው እያለ እናንተ አልሰጠውም ብላችሁ እንደፈርዖን ለምን ልቡናችሁን ታደነድናላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስን አታምኑምን? እንደ እኔ
ሀሳብ ግን ዝም ብላችሁ መምሕራን የተባላችሁ ሳትሆኑ አትቀሩም ፡፡ እንግዲያ ማን ይሙት አሁን አብ ለልጁ ይፈርድ ዘንድ
ስልጣንን ሰጠው እያለው እነሱ አልሰጠውም ብለው የእውር ክርክር መከራከር ምን ይሉታል ፡፡ መበላለጥ ስላልካት አብ ወላዲ ወልድ
ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ ስትል ይበላለጣሉን? አይበላለጡም ይህም እንደዚያ ያለ ነው ፤ ወሀቢ መለኮት ተወካፊ ትስብእትን
ተዋሕዶ በተዋሕዶ ተወካፊነትን ገንዘቡ ስላደረጋት በሰውነቱ ወሀቦ
ሕይወተ ተብሎ ተነገረለት ይህ ይበልጠዋል ማለት ሳይሆን የተዋሕዶ አገናዛቢነት ያጣውን የግብር ተዋሕዶ መግለጫ ነው ፡፡ ይኸውም
ተወካፊነት የሥጋ ግብር ሲሆን ወሀቢ መለኮት ወሀቢነቱን ሳይለቅ በተዋሕዶ ተወካፊነትን ገንዘቡ በማድረጉ በሰውነቱ ተሰጠው ተብሎ
ተነገረለት ፡፡ “ሰማይንና ምድርን የማሳልፍበት ሥልጣን ተሰጠኝ” ብሎ ራሱ ክርስቶስ የተናገረውን ቸላ ብሎ አልሰጠውም እያሉ
መደናበር ወይም ደግሞ ማበላለጥ ነው እያሉ የክሕደት ጉድጓድን መቆፈር “ከባለቤት ወዲያ መስካሪ ከእግዜር ወዲያ ፈጣሪ” የለምና
ባለቤቱ የተናገረውን የካዳችሁ ከሐድያን ቢያሰኛችሁ እንጅ አማንያን አያሰኛችሁም ፡፡ እህ ተሰጠኝ ብሎ ራሱ ባለቤቱ ሲናገር
የሚበላለጡ ከሆነማ ለምሥጢሩ ከእኔና ከእናንተ ይልቅ ራሱ ባለቤቱ አይቀርብም ነበርን?ከባለቤቱ ቀጥሉ ከባለቤቱ እግር ሥር ቁጭ
ብሎ የተማረው ወንጌላዊ ይህ እናንተ የምትጠይቁት ጥያቄ ሳይገለጥለት ቀርቶ ነውን? ፡፡
7ኛ‹‹‹‹‹‹‹
“2ኛ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነ ያሰኛል ።ለምን ቅብአት የመንፈስ ቅዱስ የተለየ አካሉ ግብር ብሏል።እርሱ ለስጋ ተሰጠ ከተባለ ሰው ሆነ ማለት ነው”›››››››››››ብለሃል ፤ አለማወቅ
ደጉ ብዙ ነገር ያናግርሃል ፡፡ በዚያ በሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ላይ አድሮ “በእንተዝ ሰበከ እንዘ ይብል እስመ መንፈስ ዘዚአየ
ዘህላዌየ ለሊሁ ኀደረ ላዕሌየ(ስለዚህ በባሕሪዬ ገንዘቤ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ በእኔ ላይ አደረ” ብሎ ነገረን ሳዊሮስ 87 ቁ
17 ላይ ፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ “በእኔ ላይ አደረ” አለ እንጅ “እኔን ተዋሐደኝ” ብሏልን?አላለንም ፡፡ አንችው ታመጭው
አንችው ታሮጭው እንዲሉ እናንተው እየቆፋፈራችሁ እየጫጫራችሁ የክሕደት መዓት ትወልዳችሁ እንጅ ወልደ አብ “መንፈስ ቅዱስ በእኔ
ላይ አደረ ብሏል ሳዊሮስ” ብሎ ይገልጠዋል እንጅ በራሱ ፈጥሮ የተናገረው አይደለም ፡፡ ለማስመሰልም ያስቀመጠው አይደለም ፡፡
ከላይ ሕይወትን ሰጠው መባሉ በሰውነቱ መሆኑን እንደተመለከትን ሁሉ “በእኔ ላይ አደረ” ያለውም በሰውነቱ መሆኑን ሳዊሮስ
“ወለምንትኑ ተሰመይኩ መሢሐ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ኮንኩ ሰብአ (ሰው ብሆን ነው እንጅ ያለዚያ ለምን ክርስቶስን ተባልኩ?)”
በማለት አብራርቶ ይግረናል ፡፡ አክሎም “ወዘሰ ኀደረ ላዕሌሁ መንፈስ ቅዱስ በእንተ ሥርዓተ ትስብእት ውእቱ(መንፈስ ቅዱስ
በእሱ ላይ ኀደረ(ገንዘቡ ሆነ) መባሉ ቃል ሰው ስለሆነ ነው)” በማለት ቁልጭ አድርጎ ይነግረናል ቁጥር 18 ላይ ፡፡ ክርስቶስ
መባሉ በሰውነቱ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱ በኅድረተ መንፈስ ቅዱስ በመክበሩ ነውና ሰው ብሆን ነው እንጅ ለምን ክርስቶስን ተባልኩ
ብሎ አብራርቶ ይነግረናል እንጅ መንፈስ ቅዱስ ተዋሐደኝ የሚል ርጉም ትምህርት የለበትም ወልደ አብ ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ መክበሩ ከፍጡራን እንደ አንዱ ነው ብለን እንዳንክድ “ወበዝ ግብር ኢኮነ ክፉለ ዘከመ አሐዱ እምነቢያት
ወኢበእተዝ ኀደረ ላዕሌሁ መንፈሰ እግዚአብሔር(በዚህም ግብር እንደነቢያት በተከፍሎ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት አይደለም)” ብሎ
ይነግረናል ቁጥር 19 ላይ ፡፡
8ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹“3ኛ ሦስትነትን ያፍልሳል ለምን በምስጢረ ሥላሴ ሥላሴ በግብር ሦስት ናቸው። እርሱም ወላዲነት አስራጺነት ተወላዲነት ሰራጺነት ብቻ ነው። ሥለዚህ የመንፈስ ቅዱስ የተለየ ግብሩ ሰራጺነት ብቻ ነው ።ወልደ አብ ቅብአት የመንፈስ ቅዱስ የተለየ ግብሩ ነው ካለ ሥላሴ በግብር ሦስት ናቸው ማለት አይደለም።ሥለዚህ ምስጢረ ሥላሴን በግብር አፈረሰ ማለት ነው”››››››››››››››ብለሃል ፤ ይህ ንግግርህም ከመጽሐፍ ቅዱስ በስተኋላ የቆምክ እንደሆንክ ይነግረናል ፡፡ ስላሴ ሲኖሩ አንዱ አካል ልብ ፣አንዱ አካል ቃል ፣ አንዱ አካል እስትንፋስ ነው ፡፡ ይህ ቀባዒ ተቀባዒ ቅብዕ የሚለው ምሥጢርም ሊቃውንቱ እነ ቅዱስ ቄርሎስ በተገለጠላቸው መጠን በገባቸው አገላለጥ ስለ ሥጋ እንግድነት የተናገሩት ምሥጢር ሲሆን ተጨማሪ ግብር አድርጋችሁ የምትቆጥሩት ብዙ ናችሁ ፡፡ የሚገርመው እኮ እናተው ራሳችሁ “ለሊሁ ቀባዒ ወተቀባዒ ወለሊሁ ቅብዕ” ብላችሁ ትናራላችሁ ፡፡ ወዳጃችን እስኪ ልጠይቅህ አንተ ወልድን ለይተህ “ራሱ ቀባዒ ራሱ ተቀባዒ ራሱ ቅብዕ” ብለህ ከተናገርክ ምሥጢረ ሥላሴን አያፈርስብህምን? ሌላም ልጨምርልህ እስኪ ሥላሴ በባሕርያቸው ሕያዋን ሲሆኑ አንዱ አካል አብ ወላዲ አሥራጺ ሲሆን አንዱ አካል ወልድ ተወላዲ አንዱ አካል መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሠራፂ ናቸው ፡፡ ታዲያ ይህ በእንዲህ እንደ አለ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በሥጋው ሙቷል ፡፡ መሞት ደግሞ ግብር ነው ፤ በዚህ ጊዜ ምሥጢረ ሥላሴን በግብር አፈረስነው ማለት ነውን? የወልድ ግብሩ መወለድ እንጅ መሞት አልነበረም ዳሩ ግን ሞተ በሥጋ ተብሎ መዋቲነት ለወልድ ሲነገርለት ግብር አይፈርስምን? ይህንን ከመለስከው የቅብዓትና የተዋሕዶ ምሥጢር ይገለጥልሃል ይቀናልህማል ፡፡
9ኛ‹‹‹‹‹‹‹
“4ኛ በወልደ አብ በቅብአት የቅብአት ትርጉም ስንት ትርጉም ? ሥለዚህ ቅብአት ነን ባዮቹ አስተውሉ ።አብ ቀባኢ ወልድ ተቀባኢ መንፈስ ቅዱስ ቅብእ እያላችሁ በክህደት ላይ ክህደት አትጨምሩ ። "በሃይማኖት ድርድር የለም" ሊቁ የኔታ ዘሜካኤል ይሁኔ”››››››››››››ብለሃል ፤ መምሕሩ
ፍሬ ሕይወት ሆይ!! አብ ቀባዒ ወልድ
ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ የሚለውን ቃል እኛ የጨመርነው ሳይሆን ከላይ እንደነገርኩህና እንደጻፍኩልህ ቅዱስ ቄርሎስ ቃል
በቃል የተናገረው ነው ፡፡ ነቢዩ ዳዊትም በመዝሙር 44 ቁ 7 ላይ “ጽድቅን ወደድክ አመጻን ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር
አምላክህ እንደ አንተ ያሉ ካህናት ነቢያት ከተቀቡት ይልቅ የደስታ ዘይት ቀባህ” ብሎ ከተናገረው ላይ ቀባህ የሚለው ተቀባዒ
ወልድን ሲያመለክተን የደስታ ዘይት የተባለው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን 3 ላይ ተርጉሞልናል ፤
ቀባዒው ደግሞ አብ ነውና እግዚአብሔር ብሎ ጠርቶልናል ፡፡ ከዚህ በበለጠ የሚያጎላልን በሐዋርያት ሥራ ቅዱስ ሉቃስ ምዕ 10 ቁ
38 ላይ “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው” ብሎ ነግሮናል ፤ ይህም ተቀባዒ የናዝሬቱ ኢየሱስ
ቅብዕ ኃይል መንፈስ ቅዱስ ቀባዒ ደግሞ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው አብ እንደሆነ እንረዳለን ፡፡ እውነታው ይህ ነው አላንም
እምቢኝ አሻፈረኝ ማለት ትችላለህ ፤ ዳሩ ግን የማታውቀውን ገብተህ ማቡካት አይገባህም ፡፡
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment