Saturday, October 27, 2018

መሰረታችን ጽኑ ነው!

እውነትን አንለቅም፤ በክህደት አንጠመድም ብላችሁ አንጀታችሁ እያረረ፤ ዐይናችሁ የእንባ ውሃ እየቋጠረ፣ በምድር ላይ ሀሰት ነግሦ ውሸት ከምድር ልትጠፋ ብትቃረብም መጥፋት ግን ከቶ አትችልምና  እራሳቸውን “ተዋህዶ” ብለው በመለኮታዊ ምስጢር ስያሜ  የሚጠሩ ግብራቸውም:-
¨  ሰውን ማሳደድ አልፎም እስከ ማስገደል፣
¨  ሃይማኖትን በግድ እንዲቀበል ማስገደድ፣
¨  መጽሐፍትን መቆነጻጸል[ቃላትን እየቆረጡ ማውጣትና አጣሞ መተርጎም]፣
¨ለምን” እንዲህ ሆነ ብሎ የሚጠይቀውን ምዕመን መናፍቅ፣ ተሃድሶ በማለት እንዲሸማቀቅ ማድረግ ቤተ ክህነቱንና ቤተ መንግስቱን፤ ፖለቲካዉንና መንፈሳዊ ሕይወቱን መለየት እስኪያቅተን ድረስ ብልሹ አሰራርን በመስራታቸው ተቸግረናል::  

Thursday, October 25, 2018

(ብዙዎች ያላወቁት እሱ)

(ብዙዎች ያላወቁት እሱ)
========================
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
==================================
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ዉሉደ እግዚአብሔር በመንፈሥ ቅዱስም መንፈሳዉያን የተሰኛችሁ ኦርቶዶክሳዉያን ሁላችሁ እንደምን አላችሁልን?ሁሉም ነገር ሠላም?መልካም ሁሉን የፈጠረ ልዑል አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና በፈጠረዉ ፍጥረት አንደበት ሁሉ ከአጽናፈ ዓለም እስከ አጽናፈ ዓለም በፈጠረዉ ፍጥረት አንደበት ሁሉ ይመስገን ፡፡ እሱን ጠርተን እሷን የማንተዉ  በአላዋቂዎች ዘንድ ካለ ስማችን ስም የተሰጠንባት(ተቀባት ይላሉ የተባልንባት) በአዋቆዎች ዘንድ የንጽሕናችን መሠረት የድኅነታችን መሰላል ሆና የተነገረች ፤ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አምላክ ባከበራት መጠን የተመሰገነች ትሁን ጻድቃን ሰማዕታት ደናግል መነኮሳት ሐዋርያን ነቢያት ቅዱሳን አበዉ ቅዱሳን መላእክት በተሰጣቸዉ ክብር መጠን የተመሰገኑ ይሁኑ ፡፡
እግዚአብሔር እንደፈቀደልን መጠን ዛሬ የምናየዉ አንድ ምሥጢር ቢኖርእነሱ ያላወቁት እሱበሚል ርእስ የማስታዉሳችሁ ምሥጢር አለ ፡፡ በቤተ ቢለዋ(በተለምዶ ተዋሕዶዎች እያሉ ራሳቸዉን  በሚጠሩ ሰዎች ቤት) “ቅብዐትየተሰኘዉ ቅዱስ ቃል በከፍተኛ አመፅ ይጾማል እንዲያዉም ብዙኃኑ ያከፍሉታል ብንል ማጋነን አይሆንብንም ፡፡ በተለይ ደግሞ ሁለተኛ የተጠመቁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንማ ይህንን ቅዱስ ቃል ለማቃለል ፤ በአጠገባቸዉ ባገኙት ከንቱ ነገር ሁሉ እየመሰሉ ለመሳደብ ሳጥናኤል እንኳን የሚቀድማቸዉ አይደሉም ፡፡ ብዙዎቹ ቅብዐቱን ከማጣት የተነሳ የተራቆቱ ናቸዉና(ወስሕከ ሥጋየ በኃጢአ ቅብዕ እንዳ ክቡር ዳዊት) አመዳም ፊታቸዉን በሚያብሱበት ቆረቆንዳ የሆነ ራሳቸዉን በሚያርሱበት

Thursday, October 18, 2018

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ ከበረ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ አምላክ

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ

 ከበረ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም”

ክፍል- ዐራት
====================
ይድረስ ለአከማቸዉ ደሴ( በዲማ ስሙ አብርሃም ደሴ )
“ነጭ ዉሸትህን የምንፍቅናህ መደበቂያ አታድረገዉ”›››››››ብለህ ለለጠፍካት የሙት መንፈስ ለሚስተዋልባት የክሕደት ሀሳብ ማክሰሚያ ፡፡
ብሂል አንድ
=====================================================
ምስራቅ ጎጃም ውስጥ ከዲማ ውጭ ሌላ ቦታ ሂዳችሁ ተክሊል እንዳትፈፅሙ ያለው እሱ ነዉይህን ካለ ትክክል ነው። ምክንያቱም እውቱን ማሳየት የሃይማኖታችን ግዴታ ነው “›››››››››››ብለሃል ወዳጄ አከማቸዉ ደሴ !!!!!!! መጻሕፍት ፡ በአንደበታቸዉ ፡ የሚሰማቸዉ አጥተዉ ዘወትር የሞጮሁት ጩኸት ቢኖር “ወመኑ ፡ ሐሳዊ ዉእቱ ዘእንበለ ዘይክሕድ ወይብል ከመ ኢየሱስ ኢኮነ መሢሐ( ኢየሱስ መሢሕ አይደለም ብሎ ከሚክድ በስተቀር፤ የሚክድ ነዉ እንጅ ሐሰተኛ ማን አለ?” 1ኛ ፡ ዮሐ 2፡22 ላይ የተጻፈዉና መሢሕ በመንፈሰ አቡሁ ተብሎ የተነገረለት የወልደ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን የተቀብዖ ስም ባለማወቅ እና ምሥጢረ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስን በማጣት የጠወለገ እና ልቡናዉ ሁሉ የሻከረ ትዉልድ በመምጣቱ ነዉ ፡፡ 


Monday, October 15, 2018

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ ከበረ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ 

አምላክ

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ 

ከበረ 

እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም


ክፍል- ሦስት
====================
ይድረስ ለአከማቸዉ ደሴ( በዲማ ስሙ አብርሃም ደሴ )
“ነጭ ዉሸትህን የምንፍቅናህ መደበቂያ አታድረገዉ”›››››››ብለህ ለለጠፍካት የሙት መንፈስ ለሚስተዋልባት የክሕደት ሀሳብ ማክሰሚያ ፡፡
============================

1ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “እገሌ ጳጳስ የእኛ  ፣ እገሌ የተባለው አባት የእኛ   እገሌ ተሐድሶ   እገሌ ጳጳስ መናፍቅ እገሌ ካህን መናፍቅ ....ምናምን ምና ምን እያለ በባዶው አዕምሯችን እንድንስል ያደረገን እሱ ነው >>ይህ አነጋገሩ ከዛሬ ከሰምንት አመት በፊት የሚነገር የተሐድሶዎች ጩኸት ነበር ማህበረ ቅዱሳን በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሐድሶ የሚል ቡድን አለ ብሎ ሲናገር የወጣለት ክስ ነው ማህበረ ቅዱሳን የእኔ የሚለው ጳጳስ ፣አባት የለም “›››››››››››››››››››››አሁን እየተናገርኩት ሳለ ፈቀቅ ሳትል ደገምከዉ ፡፡ አቡነ ፡ ማርቆስና አቡነ ቶማስ እኛል አይወክሉንም ፤ የእኛ አባቶች አይደሉም  እያላችሁ የምትጮሁት የእኛ የምትሉት ጳጳስ ስሌላችሁ ሆን ይሆን?የደብረ ማርቆስ ሀገረ ስከት ሠራተኞች እኛን አይወክሉም እያላችሁ ዋሻ ዉስጥ (ዋሻዉ ሚካኤል ) ተደብቃችሁ እገሌ የተባለዉን ካህን እንዲህ እንዳርገዉ ፤ እከሌ ዘማዊ ነዉ ፣ እከሌ ደግሞ ህንን ያህል ብር ዘርፏል እኛን አይወክልም እያላችሁ የምታሴሩት ሴራ የመለያየት ሴራ አይደለምን?.....አረ የእናንተ ክህደት የቱ ተነግሮ የቱ ይቀራል ወዳጄ? ካህንን ከካህን ፣ ጳጳሳትን ከጳጳሳት ፣ ምእመናንን ከምእመናን እያጫችሁ ሳላችሁ ተዉ ብሎ የሚገስፃችሁ ሁሉ ተሐድሶ ነዉን?

ካላወቃችሁ አትበዝብዙን



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

ይድረስ ምን ብለን እንደምናምን ለማታዉቀን ዳሩ ግን ዘወትር እንደምታዉቀን አድርገህ ለምትበዘብዘን ወንድማችን
=================================================
ዘመኑ ዋለልኝ
===========
1‹‹‹‹‹‹‹‹ “በህያው ቃል ህልው ሆኖ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ የት ሄደ??? ነው አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በህሎና ይለያያሉ???”›››››››››››ብለሃል  ወንድሜ  ዘመኑ እንኳን ደህና መጣህ ወልደ  እግዚአብሔር ሕያዉ ወልደ ማርያም ሥግዉ የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን  ተቀበለ የተባለው እኮ ሕያው መንፈስ ቅዱስ የሌለው ሥጋን ተዋሕዶ ክብር የሌለው ስለተባለለት ነው ፡፡ የተቀበለውም የባሕርይ ሕይወቱን እንጅ ሌላ አይደለም ፡፡ ጥያቄ ሞተ ብለህ ስታምን ወልድ የሞተዉ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ተለይቶት ነውን? አይደለም መዋቲ ሥጋን ተዋሕዷልና መዋቲነትን ገንዘቡ በማድረጉ ሞተ በሥጋ ተባለለት እንጅ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ተለይቶትስ አይደለም ፡፡ ተቀብዐ መባሉም እንደዚሁ ነዉ ፡፡  አብ ወልድ መንፈስቅዱስ በአነዋወር(በህልውና) አንድ ናቸው እንጅ አይለያዩም ፡፡ ዳሩ ግን መዋቲ ሥጋን ተዋሕዷልና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ በአነዋወር ሳይለይ ሞተ በሥጋ እንደተባለለት ክብር የሚሻ ሕይወትነትን ገንዘቡ ያላደረገ ሥጋን ተዋሕዷልና ሕይወቱን በሥጋዉ ተቀበለ ተባለለት ፡፡
2‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ ለስጋ ክብርን የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ይለያልን? ወልድንስ በስጋና በመለኮት ብለን መለየት ወይም መከፋፈል እንችላለን???›››››››››››››ብለሃል ከላይ በ1ኛ ብሂል እደተገለጸዉ ሁሉ ክብር የሚሻ ሥጋን በመዋሐዱ "ተቀብዐ በመንፈስ ከመ ካህናት ሐዲስ" ተብሎ ተነገረለት ፡፡ "ለሥጋ ክብርን የሰጠው" ሳይሆን "በሥጋው ክብር የሆነው" ብለህ አስተካክለው አስተካክለውና ልጠይቅህ እስኪ አምበሳየ!!!! መንፈስ ቅዱስ ለአብና ለወልድ ሕይወታቸው ነው ሲባል ይለያልን? :: አቶ ዘመኑ ስትጠየቅ ብን ብለህ እንዳትጠፋ እሽ?::::ለመጨረሻዋ "ወልድን በሥጋና በመለኮት ብለን መከፋፈል እንችላለን?? ላልካት ሀሳብህ ሞተ በሥጋ ብለህ ስታምን እየከፋፈልከው ይመሥልሀልን?