Thursday, October 25, 2018

(ብዙዎች ያላወቁት እሱ)

(ብዙዎች ያላወቁት እሱ)
========================
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
==================================
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ዉሉደ እግዚአብሔር በመንፈሥ ቅዱስም መንፈሳዉያን የተሰኛችሁ ኦርቶዶክሳዉያን ሁላችሁ እንደምን አላችሁልን?ሁሉም ነገር ሠላም?መልካም ሁሉን የፈጠረ ልዑል አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና በፈጠረዉ ፍጥረት አንደበት ሁሉ ከአጽናፈ ዓለም እስከ አጽናፈ ዓለም በፈጠረዉ ፍጥረት አንደበት ሁሉ ይመስገን ፡፡ እሱን ጠርተን እሷን የማንተዉ  በአላዋቂዎች ዘንድ ካለ ስማችን ስም የተሰጠንባት(ተቀባት ይላሉ የተባልንባት) በአዋቆዎች ዘንድ የንጽሕናችን መሠረት የድኅነታችን መሰላል ሆና የተነገረች ፤ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አምላክ ባከበራት መጠን የተመሰገነች ትሁን ጻድቃን ሰማዕታት ደናግል መነኮሳት ሐዋርያን ነቢያት ቅዱሳን አበዉ ቅዱሳን መላእክት በተሰጣቸዉ ክብር መጠን የተመሰገኑ ይሁኑ ፡፡
እግዚአብሔር እንደፈቀደልን መጠን ዛሬ የምናየዉ አንድ ምሥጢር ቢኖርእነሱ ያላወቁት እሱበሚል ርእስ የማስታዉሳችሁ ምሥጢር አለ ፡፡ በቤተ ቢለዋ(በተለምዶ ተዋሕዶዎች እያሉ ራሳቸዉን  በሚጠሩ ሰዎች ቤት) “ቅብዐትየተሰኘዉ ቅዱስ ቃል በከፍተኛ አመፅ ይጾማል እንዲያዉም ብዙኃኑ ያከፍሉታል ብንል ማጋነን አይሆንብንም ፡፡ በተለይ ደግሞ ሁለተኛ የተጠመቁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንማ ይህንን ቅዱስ ቃል ለማቃለል ፤ በአጠገባቸዉ ባገኙት ከንቱ ነገር ሁሉ እየመሰሉ ለመሳደብ ሳጥናኤል እንኳን የሚቀድማቸዉ አይደሉም ፡፡ ብዙዎቹ ቅብዐቱን ከማጣት የተነሳ የተራቆቱ ናቸዉና(ወስሕከ ሥጋየ በኃጢአ ቅብዕ እንዳ ክቡር ዳዊት) አመዳም ፊታቸዉን በሚያብሱበት ቆረቆንዳ የሆነ ራሳቸዉን በሚያርሱበት
ጭቅቅት የወረሰዉን እግር እጃቸዉን በሚያለሰልሱበትኮኮሳቸዉ” አንጻር ይመለከቱታል ፡፡ ይህ ደግሞ የእነሱ አቅምም ይሁን የማመን ሁኔታከኮኮስ” ያልዘለለ መሆኑን ያሳያል ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ አንዱቫዝሊንብሎ ሲሳደብ ሰምተዉ አብረዉ ይንጋጉበታል ይወርዱበታልም ሶበ አእመርዎ ለእግዚአ ስብሐት እምኢሰቀልዎ አዉቀዉትስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር እንዳለ ሐዋርያዉ አዉቀዉትስ በሆነ ኖሮ የክብርን አምላክ የሥላሴን ሕይወትቫዝሊንእያሉ ባልሰደቡት እንደ አባታቸዉ እንደ መቅዶንዮስ ባላቃለሉት ነበር ፡፡ ዳሩ ግን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከአዕሩግ እስከ ሕጻን አንዳችም የሚያዉቀዉ ባለመኖሩ የክብር ጌታ ሲሰደብ ሲዋረድ ይገኛል ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ እያዋረዱት ያሉት ደግሞ በመጽሐፍ የተነገረላቸዉ ፤ ፍርድ የሚጠብቃቸዉ ፤ ከእኛዉ ማኅበረ ሰብ የወጡ ፤ ድጋሚ በመጠመቅ ልጅነታቸዉን ያጡ ፤ ከክርስትና ሕግ የወጡ ሰዎች ናቸዉ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላቸዋል ፤ “ወበዝንቱ ፡ አዕመርነ ፡ ከመ ደኃሪት ሰዓት ይእቲ (በዚህም ይህች ሰዓት የኋላ ሰዓት ፡ አንድም የኋለዉ ዘመን ጊዜ ፤ የዛሬ ሰዓት የኋላ ሰዓት ይህች ፤ አንድም የኋላ ሰዓት ይህች ሰዓት እንደሆነች አወቅን) ፤ እስመ እምኔነ ወፅኡ እለ ኢኮኑ ባሕቲቱ እምኔነ(በሃይኖት ከእኛ ጋር አንድ ያልሆኑ ሰዎች በአማርኛ ከእኛ ተለይተዋልና) ፤ ወሶበሰ እምኔነ እሙንቱ እምነበሩ ምስሌነ(በሃይማኖት ከኛ ጋር አንድ ሁነዉ በሆነስ ባማርኛ ከእኛ ጋር አንድ በሆኑ ነበር) ፤ ወባሕቱ ከመ ይትዐወቁ ከመ ኢኮኑ ኩሎሙ እምኔነ(ዳ ግን በሃይማኖት ከእኛ ጋ በሃይማኖት አንድ እንዳልሆኑ ይታወቁ ዘንድ ወጡ፤ አንድም በልጅት በቦታ ከእኛ ተለይተዋልና ወጡ ፤ አንድም በሃይኖት ባማርኛ ከእኛ ጋር አንድ ሆነዉ ቢሆን በሃይማኖት በአማርኛ ከእኛ ጋር አንድ ያልሆኑ እኒህ በልጅነት በቦታ ከእኛ ጋር አንድ እንዳይደሉ ይታወቅ ዘንድ ወጡ”  1ኛ ዮሐ 2፡ ቁጥር 18-19 ፤ ይህንን ስንመለከተዉ ምሥራቃዊት ጎጃም በዘመነ ገላዉዴዎስ በአዘዞ በኩል የመጣዉን ባህለ ምንታዌ ባለመቀበሏና “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” ብላ ባለማመኗ በአለአዋቂዉና በጨዋዉ ነጭ ጣሊያን ሠራሽ ትዉልድ “ቅብዓት ናችሁ” ሲባሉ አእምሯቸዉም ልቡናቸዉም ከእኛ አይደለምና ድጋሚ በመጠመቅ ጥለዉን ይኮበልላሉ ፤ ይህ ኩብለላና ማስኮብለል ደግሞ በምሥራቃዊት ምድር ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎባት ይስተዋላል ፡፡ የሚደንቀዉ ግን በወቅቱ ኢትዮጵያን ወክለዉ ባህለ ምንታዌን በአፍንጫዉ የደፉት ከዋክብተ ጎጃም አባ ዝክረ ማርያምና አባ ጳዉሊ እንደሆኑ የታክ መዛግብት ያስረዳሉ ፡፡ ጣሊያናዊዉ ትዉልድ ግን በጭፍኑ “ቅብዓትን አልፎንሱ አመጣዉ” እያለ ተረት ተረቱን ይቀባጥራል፡፡ እነ አባ ዝክረ ማርያም ከተናገሩትና የካሮቹ ሞረድ ፤ በአስተሳሰባቸዉ ግን አሁን ካሉት ካሮች እጅግ የሚሻሉት “መልአከ ብርሃን” አድማሱ ጀንበሬ መጽሐፈ ዝክሪን ቆርጠዉ ካቀረቡት ኃይለ ቃል ተነስተን ሜንዴዝ ተከለዉ የሚለዉን ተረት ተረት አፈር ድሜ እናስግጠዉማ!!! ተከተሉኝ


“መልአከ ብርሃን” አድማሱ ጀንበሬ ከዝክሪ የወሰዱትን እና ለማስመሰል የጣሩበትን ቃል ተመልከቱልኝ “በንግድ ምክንያት መጥቶ እስክንድርያዊ መስሎ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖር አንድ ሰዉ ተነሥቶ እንዲህ ሲል ተናረ እናንተ ኢትዮጵያዉያን ቃል ሥጋ በለበሰ ጊዜ በማኅፀነ ማርያም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የባሕርይ አምላክ ኾነ ትላላችሁ፤ መንፈስ ቅዱስን ሲቀበል ያየዉ የለም ፡፡ ሮማዉያን ግን እስከ ሠላሳ ዘመን በሰብአዊ ግብር ኖሮ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ ሰዉ ኹሉ እያየዉ በራሱ ላይ በራሱ ላይ ስለተቀመጠበት የፀጋ አምላክ ኾኖ  የአምላክነት ሥራ ሠራ ይላሉና ከእስክንድርያ ሃይማኖት የሮማ ሃይማኖት ትሻላለች አለ” መድሎተ አሚን መቅድም ገጽ 15 ፤ አስተዉል አንባቢ ሆይ የብራናዉ ዝክሪ “አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ትላላችሁ” የሚል ነበር ፤ “መልአከ ብርሃን” አድማሱ ጀንበሬ ግን ቆርጠዉ አስቀርተዉታል ፡፡ ቆርጠዉ ማስቀረታቸዉም ከታች አባ ጳዉሊ የመለሰዉን መልስ ባስቀመጡበት ኃይለቃል ይታወቃል ፡፡ ይሁን እሳቸዉ እንዳሉት ብንሄድም ደስተኛ ነኝ ፡፡ ሰዎቹ(አዳዲስ ተጠማቅያንን ተስፋ የሚያስቆርጡ ዉሉደ ሱስንዮስ) የዋሁን የምሥራቅ ጎጃም ምእመን “አንተ ቅብዓት ነህ” እያሉ ተስፋ የሚያስቆርጡበት ተረት ተረት መነሻዉ ከዚህ ነዉ ፡፡ እሱም “ቅብዐት በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን ከሮም የመጣ ትምህርት ነዉ” በማለት ትዉልዱን እያሸማቀቁ ሳይወድ በግድ ሳያዉቅ በጨለማ ድጋሚ በማጥመቅ ልጅነቱን ያሳጡታል፤ አረሚ እስላም ያደርጉታል ፡፡
ወደ ሀሳቤ ልመለስና ቅብዐት ከሮም የመጣ ነዉ ከተባለ ከሮም የመጣዉ ነጋዴ “እናንተ ኢትዮጵያዉያን” ብሎ የተናገራቸዉ ደብረ ወርቆችን ነዉን?ወይስ ምሥራቅ ጎጃሞችን ነዉን?ወይስ እነማንን ነዉ?መቸም እንግዲህ እናንተ የጻፋችሁት ነዉ እንዳትሉኝ እሽ ካሮቹ!!!! እናተዉ አንቱ እያላችሁ በምታኮባብሯቸዉ “በመልአከ ብርሃን” አድማሱ ጀንበሬ መጽሐፍ ላይ በ1950ዎቹ ተጽፎ የሚገኝ ነዉ ፡፡  እነ አባ ዝክሪ ደግሞ በዘመነ ገላዉዴዎስ ጊዜ ከሮማዉያኑ ጋር ያደረጉት ክርክር ነዉና ኢትዮጵያዉያን ተብለዉ በሮማዊዉ ነጋዴ የተጠሩት እነማን ናቸዉ?መልሱን ከመለሳችሁ በኋላ ፤ “ወልድ በማኅፀነ ማርያም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የባሕርይ አምላክ ሆነ ትላላችሁ” አላቸዉ እንጅ “ወልድ በተዋሕዶ የባሕርይ አምላክ ሆነ” አላቸዉን? ፤ በተለይ በተለይ ሊቀ ሊቃዉንት ስምዐኮነ መልአክ እና ቤተ ዲማዎቹ ሆይ!  እነ አባዝክረ ማርያም “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” ብለዉ የሚያኑ “የተዋሕዶ” ሊቃዉንት ናቸዉ ብላችሁ በስማቸዉ ትነግዳላችሁና  መልሱን እንሻለን ፤እኛ ግን እኒህ እነ አባዝክረ ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ብለዉ የሚያምኑ መሆናቸዉን ከዚህ ከሮማዊዉ ነጋዴ ንግግር እንረዳለን ፡፡ ማለትም እነ አባ ዝክሪ “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” የሚሉ ቢሆኑ ኑሮ ሮማዊዉ ነጋዴ “እናንተ ኢትዮጵያዉያን ወልድ በማኅፀነ ማርያም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የባሕርይ አምላክ ሆነ ትላላችሁ” ሲላቸዉ ፤ አይ እኛ “በተዋሕዶ ከበረ” እንላለን እንጅ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ አንልም” ባሉት ነበር ፤ ዳሩ ግን በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ብለዉ የሚያምኑ በመሆናቸዉ ምንም ሳያመነቱ ሮማዊዉ ነጋዴ ለጠየቀዉ ጥያቄ መልስ ወደመስጠት ገቡ እንጅ አላቅማሙም ነበር ፡፡ እዉነታዉ ይህ ሁኖ ሳለ ብዙዎች አዳዲስ ዳግም ተጠማቅያን በአፈወርቅ ዮሐንስ  አነጋገር አረማዉያን ዘወትር ለማወቅ ሳይሆን ዳግም ለመጠመቅ ይቀናቸዋል ፤ ዳግም ለመጠመቅ የሚያደርጉት ሩጫቸዉን ብንመለከተዉ የሰማይ መላእክት እንኳን የእነሱን ያህል የሚፈጥኑ አይመስሉም ፡፡ እንዲያዉ ተጠማቅያ ሆይ እስኪ ዳግም ለመጠመቅ ከምትፋጠኑ ለማወቅ ጣሩ እስኪ? :: በአማርኛም በሃይማኖትም ከእኛ እንዳልሆኑ ይታወቁ ዘንድ ዳግም በመጠመቅ ከእኛ እየወጡ ያልቃሉ ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስያን የበላይ ጠባቂ እንደመሆኑ መጠን ይህንን የተረት ተረት ሁለተኛ ጥምቀት( እስልምና) ያስቆም ዘንድ ኃላፊነት አለበት ፡፡  ያ ካልሆነ ግን ሲኖዶስነቱ እንኳን አጠራጣሪ ይሆናል ፡፡
ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና ብዙዎቹ ባለማወቃቸዉ ስተዉና አስተዉ የባሕርይ አምላክ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን “ቫዝሊን” እያሉ መሳደባቸዉ ዛሬ ለእነሱ ምንም የሚያመጣባቸዉ መስሎ ቢታያቸዉ ፤ ከፍርድ የሚያድናቸዉ አይደለም ፤ ማቴ 12 ፡ ቁጥር 31 “ወበእንተዝ እብለክሙ ኵሉ ኃጢአት ወጽርፈት ይትኃደግ ለሰብእ(ስለዚህ ሰዉን የሰደበ ሁሉ ኃጢአቱ ይሠረይለታል ብየ እነግራችኋለሁ) ፤ ወዘሰ ጸረፈ ላዕለ መንፈስ ቅዱስ ኢይትኃደግ ሎቱ(መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ማለት ሕፁፅ ያለ ኃጢአቱ አይሠረይለትም”  በማለት ይናገራል ፡፡ እንግዲህ ዓይን ያለዉ ይይ ጆሮም ያለዉ ይስማ!!!! “ነሕነሰ ንነገር ወኢንዘብጥ”  እኛን መናፍቃን ፣ ከሐድያን ፣ አረማዉያን እያላችሁ ብትሳደቡ ኃጢአታችሁ ይሠረይላችሁ ዘንድ አለዉ ፤ እሱን ግን “ቫዝሊን” እያላችሁ የምትሰድቡ ሰዎች እባካችሁ ለአፋችሁ በር አብጁለት ፤ ይህንን የምላችሁ ለእኔ አይደለም ለራሳችሁ እንጅ ፤ ምክንያቱም ሥርየተ ኃጢአት የሌለዉ ጽኑዕ ፍዳን የሚያመጣባችሁ ስለሆነ ፡፡ ባለማወቃችሁ ይህንን ያህል በደል በራሳችሁ ላይ እያከማቻችሁ ነዉ ፡፡


ወደ ላይኛዉ ሀሳቤ ልመልሳችሁና ከእኛ ጋር አንድ እንዳልሆኑ ይታወቁ ዘንድ የወጡ ወዳጆቻችን አምላክን በመሳደባቸዉ ፍርድን ይቀበላሉ ይህ እኔ ያልኩት ሳይሆን ወንጌል ያስቀመጠዉ ቃል ነዉ ፡፡ ያ ወጡ ብሎ ያወጀዉ ሐዋርያ ያስከትልና “ወአንትሙሰ ቅብዐት ብክሙ እምነ መንፈስ ቅዱስ(እናንተ ግን አንድም ለእናንተስ ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበላችሁት ዕዉቀት ፣ ልጅነት ፣ ክብር አላችሁና ፤ አንድም አላችሁ)  ፤ ወተአምሩ ኵሎ( ሁሉን ታዉቃላችሁ፡ አንድም ዕዉቀትን ፣ ልጅነትን ፣ ክብርን ከመንፈስ ቅዱስ ገንዘብ አድርጋችሁ ሁሉን ታዉቃላችሁ ፤ አንድም አድርጋችኋልና ሁሉን ታዉቃላችሁ)” 1ኛ ዮሐ 2፡ 20 (የአማርኛዉ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ እናንተስ ከቅዱስ ቅብዓት ተቀብታችኋልና ሁሉን ታዉቃላችሁ” በማለት ቁልጭ አድርጎ ያስረዳናል ፡፡ ታዲያ ርጉማኑ ወዳጆቻችን “ቫዝሊን” እያሉ ቢሰድቡት ትግላቸዉ ከእኛ ጋር ሳይሆን ከ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነዉ ፤ ተቃዉሟቸዉ እኛን ሳይሆን ሐዋርያዉን ነዉ ፡፡ ስለዚህ እነዚህ አመጸኞች በቅዱሱ ቅብዐት ላይ ቢያምጹ የመቅዶንዮስ ፍርድ የሚጠብቃቸዉ ናቸዉ እንጅ ሌላ አይደለም ፡፡ ምክንያቱም “ቅዱስ ቅብዓት” አለዉ እንጅ ፤ “ኮኮስ ፣ ቫዝሊን” ሌላም ሌላም ልቅምቃሚ ነገር አልተናገረምና ፡
 ሳጠቃልለዉ ወንድም እህቶቼ መሢሐዉያን ኦርቶዶክሳዉያን በአንድም በሌላም ሊያስቷችሁ ቢሞክሩ እዉነትን አትልቀቁ በስድብ ሊያሸማቅቋችሁ ቢፋትሩ ወገንተኝነታቸዉ ከዲያብሎስ እንደሆነ ተረዱ ፡፡
ወንድም እህቶቼ ለስድብ እንጅ ለስነ ምግባር ያልታላችሁ ፤ በአሉ ይባላል ተረት ተረት ያደጋችሁ ፤ በአምላክ ላይ የስድብ አፋችሁን የከፈታችሁ “አነ ዉእቱ ፈጣሆሙ ለእሉ ፍጡራን” እንዳለ እንደዲያብሎስ አምላክ ወልደ አምላ ከሥጋ ጋር በአካል በባሕርይ በግብር አንድ በሆነበት ምሥጢር ገብታሁ “እኛ ተዋሕዶዎች” በማለት “እኛ ክርስቶሶች” እያላችሁ መሆኑን ለማታዉቁ ምላሳችሁ ለረዘመ  ፤ አስተሳሰባችሁና እዉቀታችሁ ላጠረ ለሁላችሁም እግዚአብሔር አምላክ አስተዋይ እዝነ ልቡናን ያድልልኝ ፤ ከእናንተ የሥድብና የርግማን  መንፈስ ይጠብቀን ፡፡


ምስጋና ለአንድ አምላክ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ለቅድስት ድንግል ፤ ምስለ ቅዱስ መስቀል
ይቀጥላል



No comments:

Post a Comment