በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ
ይድረስ ምን
ብለን እንደምናምን
ለማታዉቀን ፤
ዳሩ ግን
ዘወትር እንደምታዉቀን አድርገህ
ለምትበዘብዘን ወንድማችን
=================================================
“
ዘመኑ ዋለልኝ
“
===========
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹
“በህያው ቃል ህልው
ሆኖ የሚኖረው
መንፈስ ቅዱስ የት
ሄደ??? ነው
አብ ወልድና
መንፈስ ቅዱስ በህሎና
ይለያያሉ???”›››››››››››ብለሃል ወንድሜ ዘመኑ እንኳን
ደህና መጣህ
፤ ወልደ እግዚአብሔር
ሕያዉ ወልደ
ማርያም ሥግዉ የባሕርይ
፡ ሕይወቱ
መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ የተባለው
እኮ ሕያው
መንፈስ ቅዱስ የሌለው
ሥጋን ተዋሕዶ
ክብር የሌለው
ስለተባለለት ነው ፡፡
የተቀበለውም የባሕርይ ሕይወቱን
እንጅ ሌላ
አይደለም ፡፡ ጥያቄ
ሞተ ብለህ
ስታምን ወልድ የሞተዉ
ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ
ተለይቶት ነውን? አይደለም
መዋቲ ሥጋን
ተዋሕዷልና መዋቲነትን ገንዘቡ
በማድረጉ ሞተ በሥጋ
ተባለለት እንጅ ሕይወቱ
መንፈስ ቅዱስ ተለይቶትስ
አይደለም ፡፡ ተቀብዐ
መባሉም እንደዚሁ ነዉ
፡፡
አብ ወልድ
መንፈስቅዱስ በአነዋወር(በህልውና)
አንድ ናቸው
እንጅ አይለያዩም
፡፡ ዳሩ
ግን መዋቲ
ሥጋን ተዋሕዷልና
ከአብ ከመንፈስ
ቅዱስ በአነዋወር
ሳይለይ ሞተ በሥጋ
እንደተባለለት ፤
ክብር የሚሻ
ሕይወትነትን ገንዘቡ ያላደረገ
ሥጋን ተዋሕዷልና
ሕይወቱን በሥጋዉ ተቀበለ
ተባለለት ፡፡
2ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹
“ ለስጋ ክብርን
የሰጠው መንፈስ ቅዱስ
ከአብና ከወልድ ይለያልን?
ወልድንስ በስጋና በመለኮት
ብለን መለየት
ወይም መከፋፈል
እንችላለን???›››››››››››››ብለሃል ከላይ በ1ኛ ብሂል እደተገለጸዉ ሁሉ ክብር የሚሻ
ሥጋን በመዋሐዱ
"ተቀብዐ በመንፈስ ከመ
ካህናት ሐዲስ" ተብሎ
ተነገረለት ፡፡ "ለሥጋ
ክብርን የሰጠው" ሳይሆን
"በሥጋው ክብር የሆነው"
ብለህ አስተካክለው
፤ አስተካክለውና
ልጠይቅህ እስኪ አምበሳየ!!!!
መንፈስ ቅዱስ ለአብና
ለወልድ ሕይወታቸው ነው
ሲባል ይለያልን?
:: አቶ ዘመኑ
ስትጠየቅ ብን ብለህ
እንዳትጠፋ እሽ?::::ለመጨረሻዋ
"ወልድን በሥጋና በመለኮት
ብለን መከፋፈል
እንችላለን?? ላልካት ሀሳብህ
ሞተ በሥጋ
ብለህ ስታምን
እየከፋፈልከው ይመሥልሀልን?
3ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “እኔ
እኮ የምትገርሙኝ
ሲጠይቋችሁ መልሱን በመመለስ
ፋንታ ያንኑ
ጥያቄ አዙሮ
ለመመለስና የክህደት መልስ
ለመመለስ ስትረባረቡ ነው!!!”››››››ስድብ ጥላቻን እዚያዉ ከቁም ሳጥንህ ወይም ከሻንጣህ ቆልፍበትና በስነ ስርዓት እንነጋገር ፡፡ እኛ
ስትጠይቀን አዙረን የምንጠይቅህ የጥያቄህ መልስ በጥያቄያችን መልስ ዉስጥ ስላለ እንጅ ለሌላ አይደለም ፡፡
4ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ መጀመሪያ
ህልው ቃል
ከስጋ ጋር
ሲዋሃድ መንፈስ ቅዱስ
ክብር ሆነው
አላችሁ አብና ወልድ
ስልጣን የላቸውም??? በህሎናስ
ተለያይተዋል???”››››››››››ብለሃል ወዳጄ ዘመኑ
አሁንም ቢሆን ጥያቄውን
የምጠይቅህ መልስ ስለሆነ
ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ
ክብር ሆነው
መባሉ የባሕርይ
ሕይወቱ ነውና በሱ
ሕያው ሆኖ
ስለሚኖር በመንፈስ
ቅዱስ ሕያው
ሆነ ይባልለታል(እልመስጦ አግአያ
2:5):: አብና ወልድ
ሥልጣን አላቸው፡፡ በህልውናም( በአነዋወርም) አብ ልባቸዉ ወልድ ቃላቸዉ መንፈስ ቅዱስ ሕይወታቸዉ ሁነዉ ይኖራሉ እንጅ አልተለያዩም
፡፡ ስዚህ ሕያዉ የሚሆኑት በመንፈስ ቅዱስ ነዉና ሕያዉ ባልነበረ በሥጋዉ በመንፈስ
ቅዱስ ከበረ ሕያዉ ሆነ ተባለለት ፡፡ .ይኸውም
መዋቲ ሥጋን
ተዋሕዷልና ከአብ ከመንፈስ
ቅዱስ ሳይለይ
ሞተ ተባለት፡፡
መቀባቱም ቅብዓት የሚሻ
ሥጋን ተዋሕዷልና
ከአብ ከመንፈስ
ቅዱስ ጋር
ክቡር ሲሆን
በሥጋው ተቀባ ይባልለታል ፡፡
5ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹
“ቃል ከስጋ
ጋር ስዋሀድ
ወይም ራሱን
ዝቅ አድርጎ
ስጋን ለብሶ
ፍፁም ሰው
ፍፁም አምላክ
ሲሆን በአብ
ፈቃድ በራሱ/በወልድ ፈቃድ
:በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ
አይደለምን??? ሳትቀላምዱና ሳትዘላብዱ
ይሄን በትክክል
ከመለሳችሁልኝ ነገ በጧት
ወደ እናንተ
እቀላቀላለሁ አለዚያ ግን
"BLOCK"”››››››››››ብለሃል ወዳጄ ዘመኑ የምን
መቀላመድ አመጣህ?ምን አልባት ያለበት ተክላላበት እንዳይሆንብህ እሰጋለሁ ፡፡ እመብርሃንን እኔ በመልካ የተዋሕዶ ምሥጢር የምንነጋገር
ከሆነና ነጠላ ተዋሕዶን ትተተህ ጽንዓ ተዋሕዶን የምታነጋግረኝ ከሆነ መቀላመድ የሚባል አባቶቼም አላስተማሩኝም ፤ እኔም አላዉቅም
፡፡ ወደ ጥያቄህ ሳመራ ?????“እስመ በፈቃዱ ወበሥምረተ አቡሁ ወበመንፈስ ቅዱስ መጽአ ወአድኀነነ” እንዳለ ኤፍሬም ሶርያዊ ወልድ ሰው የሆነው
በእሱ በአባቱና
በሕይወቱ ፈቃድ ነው እንጅ ብቻ በእሱ ፈቃድ አይደለም ፡፡
ግን እስኪ
ልጠይቅህ ፍጹም ሰው
ሆነ ማለት
ምን ማለት
ነው? ወልድ
በእሱ በአባቱና በሕይወቱ ፈቃ ሰዉ ሲሆን የእሱ ፈቃድ በተለየ አካሉ ፣ በተለየ ግብሩ ሥጋን በመዋሐድ ሲገለጥ ፤ የአብና የመንፈስ
ቅዱስ ፈቃድ እንዴት ተገለጠ?በራሱ ፈቃ ብቻ ሰዉ የሆነ አይደለምና አብ በተለየ አካሉ ፣ በተለየ ግብሩ ምን አደረገ?መንፈስ ቅዱስም
እንዲሁ በተለየ አካሉ በተለየ ግብሩ ምን አደረገ? ምንም ካረደጉ ፈቃዳቸዉ የተፈጸመዉ እንዴት ነዉ?
6ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “ወልድ
በስልጣን ያንሳል?ወይስ
ክብርን ይሻል???”››››››››››ብለሃል
ወዳጄ ወልድ
በሥልጣን አያንስም ፤
ዳሩ ግን
ሕያው ሲሆን
መዋቲ ሥጋን
በመዋሐዱ ከአብ ከመንፈስ
ቅዱስ ሳይለይ
በሥጋው ሞተ እንደተባለለት
ሁሉ ፤
ሥልጣን የሌለውን ሥጋ
ተዋሕዷልና ሥልጣንን ከአብ
ተቀበለ(ዮሐ 5:26-27) :: በባሕርየ
መለኮቱ እንደ አብ
እንደመንፈስ ቅዱስ ክቡር
ሲሆን ፤
ክብር የሚሻ
ሥጋን ተዋሕዷልና
ከአብ ክብርን
ገንዘብ አደረገ(ሃይ
.አበው ዘቄር
79 ፤ 74:75)
7ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹ በመጨረሻም
"BLOCK” ብሎክ ላልካት ሀሳብህ የቀድሞ አባቶችህ እነ ዮሐንስ ዐራተኛ
እና እነ ዳግማይ ግራኝ ብሎም ሌሎቹ ካሮች ፤ ኃይለ ቃል ጠቅሰዉ መጽሐፍ
አገላብጠዉ ለሚጠየቁት ጥያቄ መልስ መመለስ
ሲያቅታቸው ፤ በሰይፍ
እየቆራረጡ ነበር
አበውን የሚገድሏቸው ፡፡ አንተም የእነሱ
ልጅ ነህና
ብሎክ ብታደርገኝ
አይደንቀንም ፡፡ ምክንያቱም እኛን
ብታደርገን ፈጣሪን ማድረግ
አትችልምና ፡፡ እኔን ብሎክ ከምታደርገኝ ሃይማኖትህን ብታስረዳኝ አይሻልህምን? ሐዋርያዉ
ቅዱስ ጴጥሮስ “ወድልዋኒክሙ ሀልው ከመ ታውሥእዎሙ ቃለ ለእለ ይሴአሉክሙ በእንተ ዛቲ ተስፋክሙ--ስለ ሃይማኖታሁ ለሚጠይቋችሁ ሰዎች መልስ ለመስጠት
ትችሉ ዘንድ አንቀጽ አውጥታችሁ ፣ እልባት አልባችሁ፣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ” ብሎ በ1ኛ ጴጥ ምዕ 3 ቁ 15 አለ እንጅ
ብሎክ አድርጉ ብሎ አላዘዘንምና
ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ
No comments:
Post a Comment