Thursday, October 18, 2018

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ ከበረ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ አምላክ

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ

 ከበረ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም”

ክፍል- ዐራት
====================
ይድረስ ለአከማቸዉ ደሴ( በዲማ ስሙ አብርሃም ደሴ )
“ነጭ ዉሸትህን የምንፍቅናህ መደበቂያ አታድረገዉ”›››››››ብለህ ለለጠፍካት የሙት መንፈስ ለሚስተዋልባት የክሕደት ሀሳብ ማክሰሚያ ፡፡
ብሂል አንድ
=====================================================
ምስራቅ ጎጃም ውስጥ ከዲማ ውጭ ሌላ ቦታ ሂዳችሁ ተክሊል እንዳትፈፅሙ ያለው እሱ ነዉይህን ካለ ትክክል ነው። ምክንያቱም እውቱን ማሳየት የሃይማኖታችን ግዴታ ነው “›››››››››››ብለሃል ወዳጄ አከማቸዉ ደሴ !!!!!!! መጻሕፍት ፡ በአንደበታቸዉ ፡ የሚሰማቸዉ አጥተዉ ዘወትር የሞጮሁት ጩኸት ቢኖር “ወመኑ ፡ ሐሳዊ ዉእቱ ዘእንበለ ዘይክሕድ ወይብል ከመ ኢየሱስ ኢኮነ መሢሐ( ኢየሱስ መሢሕ አይደለም ብሎ ከሚክድ በስተቀር፤ የሚክድ ነዉ እንጅ ሐሰተኛ ማን አለ?” 1ኛ ፡ ዮሐ 2፡22 ላይ የተጻፈዉና መሢሕ በመንፈሰ አቡሁ ተብሎ የተነገረለት የወልደ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን የተቀብዖ ስም ባለማወቅ እና ምሥጢረ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስን በማጣት የጠወለገ እና ልቡናዉ ሁሉ የሻከረ ትዉልድ በመምጣቱ ነዉ ፡፡ 


በተለይ እንደ አንተ ያሉ “ሁለት ጊዜ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የተተጠመቁ ፤ በዮሐንስ አፈወርቅ አጠራር አባስያን ፤ እስመ ፡ ዘይጠመቅ ዳግመ ዉእቱኬ ዘረሥዐ ሀብተ ጸጋ ዘቀዲሙ(ሁለተኛ እጠመቃለሁ የሚል ሰዉ በመጀመሪያ ጥምቀት ያገኘዉን ጸጋ ክብር የነቀፈ አንድም የዘነጋ ስለሆነ ነዉ ፡፡ ወአበሰ አበሳ ምኑነ (የተናቀ በደል የበደለ ነዉ ፤ አለ ጌታን ሁለተኛ ይሰቀል የሚል ስለሆነ ነዉ “ ብሎ ድርሳ 9 ቁ 213-14 ላይ እንደተናገረዉ አምላክ ወልደ አምላክ ድጋሚ ይሰቀልልን ብላሁ የምታስቡ ክፉ በደልንም የበደላችሁ መሆናችሁን አሥረግጦ ይነግረናል ፡፡ ታዲያ ዲማ ጊዮርጊስ ላይ የሚደረገዉ ይህ ከአይሁድ እንኳን የከፋ እኩይ ተግባር ምኑ እዉነት ነዉ? ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወመኑ ዉእ ሐሳዊ ብሎ የተናገረዉ አንቀተ መሢሕ ከታች ለምትጠቅሰዉ የሥልጣነ ክህነት ጉዳይ ሰፊ ትንታኔና መንደርደሪያ ስለሚሰጥበት ከዚህ ላይ ብዙ  አልልህም ፡፡
አስከትለህም‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “በምስራቅ ጎጀም አብዛኛው ቤተክርስቲያን ግን <<አብ ቀብዐይ ወልድ ተቀብዐይ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ወይም አብ አክባሪ ወልድ ከባሪ መንፈስ ቅዱስ ክብር >>የሚለውን ክህደት የሚከተሉ ናቸው። ስለሆነም እንደ ዳማ በተዋህዶ ከበረ ብለው ከሚያምኑት ቤተክርስቲያን ውጭ ምስጢራትን መፈጸም ምን ዋጋ አለው “›››››››››››››››››››››››››››አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ፡ ቅዱስ ቅብዕ የሚለዉ የተቀብዓ  ምሥጢር ስለከዊነ ትስብእት የተፈጸመ ልክ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ (አብ ልብ ፣ ወልድ ቃል ፣ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ) ማለት የሚያጠይቅ የምሥጢረ ክርስቶስ መሠረት እንጅ ክሕደት ፡ አይደለም ፡፡ ለምን ያልን እንደሆነ ፤ “እስመ በፈቃዱ ወበሥምረተ አቡሁ ወበመንፈስ ቅዱስ መጽአ ወአድኃነነ(በእርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ምጥቶ አዳነን” ብሎ ኤፍሬም ሶርያዊ  እንደገለጠዉ በሰዉ ልጅ ድኅነት መሠረት ሲጣል ፈቃደ ሥሉስ ቅዱስ የተፈጸመበት ረቂቅ ምሥጢር ነዉ ፡፡ እሱም አፈወርቅ ዮሐንስ(ወልደ ሴኮንዶ(ሲፋኒዶስ)) ሊቀ ጳጳስ ዘአንጾኪያ  በድርሳኑ ድርሳን 2 ቁ 253-55 ላይ “እስመ በከመ አዕምሮቱ ፡ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐቲ ይእቲ ዘእንበለ ተፈልጦ (ተሰምሮተ አብ ወመንፈስ ቅዱስም ይላል፤ አብ በወላዲነት ፣ ወልድ በተወላዲነት ፣ መንፈስ ቅዱስ በሠራፂነት የሚታወቁበት መታወቅ መለየት የሌለበት አንድ እንደሆነ መጠን) ፤ ከማሁ ዉእቱኒ ነሥአ ፡ አሐደ አካለ (ወልድም በተወላዲነቱ የሚታወቅበት መታወቅ መለየት የሌለበት አንድ ነዉና ሥጋን ተዋሐደ) ፤ ለምን ብለን የምንጠይቅ ሰዎች ብንኖር “ለአጽንዖተ ክልኤሆሙ(አብንና መንፈስ ቅዱስን በጥንተ ስማቸዉ ለማስጠራት ፣ በቀድሞ ግብራቸዉ ለማጽናት) ፤ አንድም ፡ አብን በልብነት መንፈስ ቅዱስን በእስትንፋስነት ገንዘብ ለማድረግ  ሥጋ ቃልን ተዋሐደ” ብሎ ተናሯል እንላለን  ፡፡  

ይህ አፈወርቅ እደተናረዉ አብ ቀባዒ ማለት ቀድሞ ለወልድ አእምሮዉ ልቡናዉ እንደሆነ እንዲሁ በጊዜ ተዋሕዶ ለወልድ በሥጋዉ ልቡና አእምሮ በመሆን ወለደዉ ማለት ሲሆን ፤ ወልድ ተወባዒ ማለት ደግሞ ቀድሞ ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ እንደተወለደ ሁሉ ዛሬም ስለከዊነ ትስብእት በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ተወለደ ማለት ሲሆን ፤   መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ማለት ደግሞ ቅድመ ዓለም ለቃል ሕይወቱ እደሆነ ሁሉ በገዜ ተዋሕዶ ደግሞ ለወልድ ስለከዊነ ትስብእት ሕይወት እስትንፋስ ሆነዉ ማለት ነዉ ፡፡ እንጅ በጠማማ አእምሮ ከላይ ጥሬ ንባብ ይዞ አብ አክባሪ ቃል ከባሪ መንፈስ ቅዱስ ክብር እያላችሁ ብትበሩ ገደል ነዉ የምትገቡ ፡፡ በቤታችሁ ትርጓሜ ያሻዋል እያላችሁ ትናገራላችሁና እስኪ ቅብዓት የሚለዉን ቃል በደረቁ ክብር ብቻ እያላችሁ ከመተጐም ተሻገሩና የቅብዓት ጣዕመ ምሥጢሩ ይግባችሁ ወዳጄ? ፡፡ ሶርያዊ ሊቀ ጳጳስ አባ ኤፍሬም በእሱ በአባቱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መጥቶ አዳነን ያለዉ የፈቃድ ፍጻሜ የወልድ ፈቃድ ሥጋን በመዋሐድ እስከ መሞት ድረስ ባለዉ ጉዞ ሲፈጸም የአብ ፈቃድ ደግሞ ወልድ ለተዋሐደዉ ሥጋ ልቡና አእምሮ በመሆኑ ሁሉን በፈቃዱ እንጅ ተገዶ እንዳያደርግ አስቻለዉ ፤ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት በመሆኑ መዋቲ በስባሽ የነበረ ሥጋ አዳም በስብሶ ሳይቀር ከመለኮት ጋር ተዋሕዶ በጊዜ ተዋሕዶ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏልና ከሙታን መካከል እንዲነሳ አስቻለዉ ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነዉ ስለ ሥጋ ንዴትና እንግድነት እንጅ በባሕርየ መለኮቱ አንዳችም ጉድለት የለበትም ፡፡ እስኪ በእናንተ ቤት “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” እየተባለ ይዘመራልና::

ሀ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹በተዋሕዶ ከበረ የተባለዉ ማን ነዉ?በተዋሕዶ ጊዜ ቃል ከሥጋ ጋር በግብር ፣ በአካል ፣ በባሕርይ ተዋሐዱ እንጅ አንዱ አክባ ሌላዉ ከባሪ የሚል አለ?
ለ‹‹‹‹‹‹‹‹‹በፈቃድ አንድ የሆኑ ሥሉስ ቅዱስ ወልድ ሥጋ ሲዋሐድ ፤ አብና መንፈስ ቅዱስ በተለየ አካላቸዉ ፣ በተለየ ግብራዉ ፡ ወልድ ለተዋሐደዉ ሥጋ ምን ሥራ ሠሩ?ተብሎ ቢጠየቅ ቤተ ድማኅ መልስ አለዉ?
ለቤተ ዲማ ይልቁንም የሚቀናዉ ሰዎችን እየወረወረ ገደል መጣል አልያም በዱላ መደባደብ እንጅ አንዳችም የሊቃዉንትን የአበዉን መጽሐፍ የሚጠቅስ የለም ፡፡ እዉነቱን ንገረኝ ካልከኝ ዲማ ልትጠመቅ ሂደህ ጥያቄ ካነሳህ በቆመጥ ነዉ እየዠለጡ ያጠድፉሀል እንጅ አንድም መልስ አይሰጡህም ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለትም ከእስላ ከአረሚ ያልተናነሰ ያዉም የሚበልጥ ክሕደት ነዉ የክሕደቱን አራት ፈርጦችም በክፍል አንድ ላይ ስለጻፍኩልህ ከዚህ ላይ አልደግመዉም ፡፡

 ስለዚህ ከዲማ ዉጭ ሌላ ቦታ ክርስትና የለም እያልክ የምትዘፍነዉ ዘፈንህ ዲማ ዉስጥ የጸጎች አስተምህሮ ጥንተ አብሶ በሰፊዉ የሚሰበክና የሚታመንበት ገዳም እንደሆነ መድሎተ አሚን መቅድም ገጽ 16 ላይ ያለዉ የአንጽሐ ብሂል ትንታኔ በግልጽ ያስረዳል ፡፡ በዚያዉም ላይ በ1620ዎቹ በኢትዮጵያ ኦርቶሶክሳዊት ቤተክርስቲያን  ላይ በዓለ ሰንበትን ያሻረ ፣ ጾመ ድኅነትን ያስፈረሰ ርጉም ንጉስ አጼ ሱስንዮስ ያደረገዉን የሁለተኛ ጥምቀት የሚተገብሩ አባቶች ያሉበት ገዳም ስለሆነ በአሁኑ ሰዓት ዲማ ዉስጥ እዉነት አለች ማለት ገነት በርባስ ወይም ገሃነመ እሳት ናት እንደማለት ነዉ ፡፡ እኒህ ክፉ ሰዎች የሚሸዉዱበት አንደኛዉ በዚህ በፍትሐ ነገሥት ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 3 ቁ 24 ላይ  “ወለእመቦ ብእሲ ዘተወክፈ ጥምቀተ እምዓላዉያን ኢኮነ ዉእቱ ምእመነ(ከመናፍቃን ጥምቀትን የተጠመቀ ሰዉ ቢኖር አማኒ አይደለም” `የጠቀሰዉን ቃል ይዘዉ “እናት ቅብዓቶች ሃይማኖት በሌላቸዉ ካህናት ስለተጠመቃችሁ የእነሱ ጥምቀት አይሰራም” እያሉ የጨዋና የአለአዋቂ ንግግርን በመናገር ነዉ ፡፡

ሀ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹በመጀመሪያ ደረጃ የአለአዋቂነታቸዉ ምልክት “እናተ ቅብዓቶች” ብለዉ በመናር ነዉ ፤ ሲጀመር እና ቤተክርስቲያ የምታዉቀዉ ቅብዓት አንድ እሱም በ1ኛ ዮሐ 2፡ 20-26 ላይ በሰፊዉ የተጠቀሰዉ ቅዱስ ቅብዓት በጣዕመ ምሥጢሩ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ፤ በሰዎች ልክ እሱን ቆጥሮ “ቅብዓቶች” ማለት እጅጉን አለአዋቂነት ነዉ ፡፡ ዳሩ ግን እናንተ ቅቡዓን እንባላለን እንጅ ቅብዓቶች አንባል ዘንድ ቋንቋም ፤ አገባብም የለዉም ፡፡
ለ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ሲቀጥል ደግሞ ዓላዉያን የተባሉ እነማን ናቸዉ?የወልደ እግዚአብሔርን ሰዉ መሆን ከማመን የወጡ ፤ ከላይ እንደተገለጠዉ መሢሕነቱን የካዱ እነሱ እንደሆኑ ይነግረና ፡፡ ጥቀትማ እኮ ፕሮቴስታቱም ፣ ካቶሊኩም ፣ ጆቫዉም ያጠምቃል ፤ ካቶሊካዉያን አንድ ወልድ በአንድ አካል ሁለት ባሕርያት አሉት ብለዉ ያምናሉ ፤ በተዋሕዶ ከበረ ማለትም አንዱን ወልድን ቃን አክባሪ ሥጋን ደግሞ በቃል ከባሪ አድርጐ ማመን በመሆኑ ከካቶሊክ ምንታዌ የተወሰደ መሆኑን ፡ ልብ እንላለን ፡፡ ፕሮቴስታንቱ ወልደ እግዚአብሔር ሕያዉ ወልደ ማርያም ሥግዉ አማላጅ ነዉ ብለዉ ያምናሉ ፤ ጆቫዎች ደግሞ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ አልቦ ትንሣኤ ምዉታን የሚሉ ናቸዉ ፡፡ እነዚህ ሦስቱም ከኦርቶዶክስ የተለዩ ናቸዉ ፡፡ 

ታዲያ ከእነዚህ ዓላዉያን የተጠመቀ ሰዉ ዳግመኛ ሊጠመቅ ይገባዋል ተባለለት ፡፡ አንባቢ አስተዉል ይህ ዳም የተባለዉ አንዲት ጥምቀት የምትጠመቀዉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ ብሎ አምኖ የተጠመቋት ጥምቀት የማትደገም የማትከለስ ናት ፡፡ እኒህ የዘረዘርናቸዉ ሦስቱ (ወልድ ቅብዕና ካቶሊክ ፣ ፕሮቴስታንት ፣ ጆቫ) አንዱን ወልድን ሁለት ያደረጉና የካዱ በመሆናቸዉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ያልተጠመቁ በመሆናቸዉ ይጠመቁ ዘንድ የፍትሕ መንፈሳዊ ትእዛዝ ይመለከታቸዋል ፡፡ ይህንን ሳያዉቁና ሳይረዱ በስማ በለዉ በጅምላ “እናንተ ቅብዐቶች መናፍቃን” ናችሁ እያሉ ብዙዉን ትዉልድ ማሳት አባትን ሳያዉቁ አያትን መናፈቅ ነዉ ያሰኝባቸዋል ፡፡
ሳጠቃልለዉ ማኅበረ ዲማ በራሱ  የእነጨት ምንቸት ሲሆን ሌሎችን ሊያድናቸዉ ሕይወት ሊያሰጣቸዉ የሚችል አይደለምና የሚመርጡት ሳይሆን ሊርቁት የሚገባ ቦታ ነዉ ፡፡
ብሂል ሁለት
================================================
“በምስራቅ ጎጃም ውስጥ ዲማን ውጭ አይልም ሌላም ቤተከርስቲያናት ተዋህዶን ስለሚያሙኑ”›››››››››››ይህ ሀሳህ ደግሞ የአንተን የአለአዋቂነት ልክ የሚያሳይ ነዉ ፡፡ ምክንያቱም በተለምዶ በእናንተ “ቅብዓቶች”  እየተባልን የምጠራ ኦርቶዶክሳዉያን ፣ ክርስቶሳዉያን ፣ ቅቡዓን እየተባልን የምንጠራ ሰዎች ተዋሕዶን የማናምን ከሆነ ፤ እናንተ ከ አራት አመት አንድ ጊዜ በ28 በዓለ ልደትን በምታከብሩበት ወቅት መከበር ያለበት ዘወትር በየ ዓመቱ ታኅሣሥ 29 ብቻ ነዉ እያልን ለምን እንጨቃጨቃለን?ተዋሕዶን የማናምን ከሆነማ ዘወትር በቤተክርስቲያናችን የሚፈተተዉ ሥጋወ ደሙ ከየት መጣ ወዳጄ? በዚህ ጽሁፍ ክፍል አንድ ላይ እንደነገርኩህ እኛ የማናምነዉ የተዋሕዶን ካባ ለብሶ የመጣዉን የሮማዊት ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ባህለ ትምህርት የሆነዉን ምንታዌን(ሁለትነትን) እቀፍ ድግፍ አድርጎ የያዘዉን ፤ ከብሉይ እስከ ሐዲስ ፣ ከሊቃዉንት እስከ መነኰሳት በዐራቱ ጉባዔ መጻሕፍት ያልተነገረዉን ፤ በኢትዮጵያ ላይ ደግሞ በዘመነ ገላዉዴዎስ በግፍ ወደ ኢትዮጵያ የገባዉንና በሣልሳይ ሰላማ ዘመነ ጵጵስና በነ አጼ ቴዎድሮስ ሰይፍ የተተከለዉን ፤ በኋላም በነአጼ ዮሐንስ አራተኛ የሰዉ ራስ ምላት እየተቆረጠ የተበላበትን ፤ ምሥጢሩን ለተረዳዉ ግርማዉ ከአይሁድ ክሕደት በላይ የከፋዉን ፤ የዘመኑ ነጭ ትዉልድ ግን ያልተረዳዉን “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” የሚለዉን በተዋሕዶ ስም የተጠጋ የፈጠራ ብሂልን እንጅ ነዉ ፡፡
================================================
ብሂል ሦስት
================================================


በተዋህዶ ሳያምኑ የሚያመጡት ክነት አማናዊ አይደለም ምክንያቱም ያለ እምነት ምንም አይነት የፀጋ ስጦታ የለም”›››››››››››››››ብለሀል በተዋሕዶ እንዴት እንደምናምን ጥሩ አድርጌ ከአሁን በፊት በክፍል አንድ ስለገለጽኩት ከዚህ ላይ መድገሙ አስፈላጊ ሆኖ አልታየኝም ፡፡ ስለ ነገረ ክህነቱ ግን ቀዳሜ በትረ ያሬክ ቅዱስ ጴጥሮስን ልጠራዉ ወድጃለሁና በደንብ አድርገህ ስማዉ ፡፡ ያች የታደለች የፊሊጶስ መንደር ቂሳርያ ያስተጋባችዉንና የሰማችዉን ምሥጢር እንዲህ ሲል ጽፎታል ሐዋርያዉ ማቴዎስ በምዕ 16 ፡ ቁ 13-19 “ወበጺሖ እግዚእ ኢየሱስ ብሔረ ቂሳርያ ዘፊልጶስ(ጌታ የፊልጶስ ግዛት ፡ ከምትሆን ከቂሳርያ አዉራጃ በደረሰ ጊዜ) ፤ ተስእሎሙ ለአርዳኢሁ እንዘ ይብል ሰብእ ለወልደ ዕጓለ እመሕያዉ(ሰዉ እኔን ማን ይለኛል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸዉ) ፤ ወይቤሉ ቦ እለ ይብሉከ ዮሐንስሃ መጥምቀ(ዮሐንስ መጥምቅ  እንደሆንህ የሚናገሩልህ አሉ (ንጽሕናዉን አይተዉ)) ፤ ወካልአን ፡ ይብሉከ ኤልያስሃ (ኤልያስ የሚሉህ አሉ ፣ ኤልያስ እንደሆንክ የሚናገሩልህ አሉ( ድንግልናዉን አይተዉ)) ፤ ወመንፈቆሙ ፡ ይብሉከ ኤርምያስ(ኤርምያስ ነህ የሚሉህ አሉ ፤ ኤርምያስ እንደሆንክ የሚናገሩ አሉ ፡ (ቅድስናዉን አይተዉ)) ፤ ወእመ አኮ አሐዱ እምነቢያት ቀደምት (ይህም ባይሆን ከቀደሙ ነቢያት ማለት ሙሴን ኢያሱን የሚሉህ አሉ ፡ (ተአምራቱን አይተዉ)) አሉት ፡፡ ወይቤሎሙ አንትሙኬ መነ ትብሉኒ(እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ፤ ከዊነ ይላል አብነት በምን ሀለዎት አለ ትሉኛላችሁ አላቸዉ) ፤ ወአዉሥአ ስምዖን ጴጥሮስ ወይቤ አንተ ዉእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያዉ(አንተ የሕያዉ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ፤ አንድም እስከ ክርስቶስ ተብሎ በኢሳይያስ የተነገረልህ የሕያዉ እግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ መለሰ) ፤ ወአዉሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤ ብፁዕ አንተ ስምዖን ወልደ ዮና(ጌታም መለሰ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ አንተ ንዑድ ክቡር ነህ አለ) ፤ እስመ ኢከሠተ ለከ ዘሥጋ ወደም(ይህንንስ ሥጋና ደም አልገለጸልህም ፤ አንድም የእኔን አምላክነት የእኔን ክርስቶስነት ሥጋዊ ደማዊ አእምሮ አልገለጸልህም) ፤ አላ አቡየ ዘበሰማያት (ሰማያዊ አባቴ ገለጸልህ እንጅ ፤ አንድም ሥጋዊ ደማዊ መምህር አላስተማረህም ሰማያዊ አባቴ አስተምሮሃል እንጅ) ፤ ወአነኒ እብለከ ከመ አንተ ኰኵሕ(እኔ መሠረት ነህ ብየ መሠረት እደሆንክ እናርልሀለሁ(በጥንተ ስብከቱ አንተኬ ትሰመይ ኬፋ ብሎት ነበርና)) ያ እንደተፈጸመለት ሲያጠይቅ መሠረትነቱ የሃይማኖት ፣ የሹመት ነዉ ፤ ወዲበ ዛቲ ኰኵሕ አሐንፃ ለቤተክርስቲያንየ(በአንተ አለትነት መሠረትነት ቤተክርስቲያኔን አንፃታለሁ አጸናታለሁ) ፤ ወአናቅጸ ሲዖልኒ ኢይሄይልዋ(አጋንንት አያናዉጧትም ፡ ማለት ድል አይነሷትም) (ግብረ ሐተታ) አናቅጽ ሲዖል አላቸዉ በበር ይወጡበታል ይገቡበታል ፡ በበር እንዲገቡበት ጻድቃን ድል ነሥተዉ ይገቡባቸዋልና ፣ ኃጥአን ደግሞ ድል ተነሥተዉ ይወጡባቸዋልና ፤ ወእሁበከ መራኁተ ዘመንግሥተ ሰማያት(የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ ማለት ከመንግሥተ ሰማያት የምታወጣበት ወደመንግሥተ ሰማያት የምታስገባበት ሥልጣን እሰጥሀለሁ) ፤ ዘአሠርከ በምድር ይኩን እሡረ በሰማያት (በምድር ያሠርከዉ በሰማይ የታሠረ ይሁን) ፤ ወዘፈታሕከ በምድር ይኩን ፍቱሐ በሰማያት(በምድር የፈታኸዉ በሰማይ የተፈታ ይሁን”
ይህንን ጥያቄና መልስ ቅዱስ ሉቃስ በምዕ 9፡ ቁ 20 ላይ ቁልጭ አድርጐ ጽፎልናል ሰብኮልንማል ፡፡ እንግዲህ ግዑዛን ድንጋዮች ካልሆኑ በቀር የዚህ የቅዱስ ማቴዎስ እና የቅዱስ ሉቃስ ስብከት ለማንኛዉም ሰዉ ግልጽ ነዉ ፡፡ ማቴዎስ አንተ ዉእቱ “ክርስቶስ” ያለዉን ቅዱስ ሉቃስ “መሢሑ” ብሎ ወስዶታል ፡፡ እነኝህ ሁለቱ ቃላት ከምድር እስከ ሰማይ ከበርባሮስ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስ ቢወጡ ቢወርዱ የማይዘለቅ የማይጠለቅ የምሥጢር ማኅተም የታተመባቸዉ ስሞች ናቸዉ ፡፡ እነዚህም ስሞች  የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ቅዱስ እንድርያስ ከተናገራት ምሥጢር ተመርኩዞ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ ትርጕሟቸዋል “ዮሐንስ ነዋ በግዑ ሲል ሰምቶ ጌታን ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እድርያስ ነዉ ፡፡ ወለሊሁ አቅደመ ረኪበ እኅዋሁ ስምዖንሃ (እርሱ አስቀድሞ ወንድሙን ስምዖንን አገኘ) ፤ ወይቤሎ ረከብናሁ  መሢሕ ዘይብልዎ ክርስቶስ( ክርስስ የተባለ መሢሕን አገኘነዉ )፤ ማስያስ በዕራይስጥ ፣ ክርስቶስ በጽርዕ ፣ መሢሕ በዓረብ ፣ ቅቡዕ በግዕዝ) ብሏል ሉቃ 1፡ 41-42 ፡፡
 የከላላዉ(ደቡብ ወሎ ዉስጥ ያለ ወረዳ) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ደግሞ  “ዘፍካሬ ስሙ መሢሕ ዘበትርጓሜሁ ቅቡዕ ዘዉእቱ ናዝራዊ  ፤ ብለ ክርስቶስ ወመሢሕ ወናዝራዊ ወክርስቶስ አሐደ ይተረጐም ለብሂለ ቅቡዕ(የስሙ ትርጓሜ ክርስቶስ የሆነ ለእግዚአብሔር የተለየ የተቀባ የሆነ ፤ ክርስቶስም መሢሕም ናዝራዊም ማለት በአንድነት የተቀባ ተብሎ ይተረጐማል” መ.ምሥጢር 20 ቁ 40 ላይ ተርጕመዋቸዋል ፡፡ በእነዚህ ቅዱሳን ስሞች እኛ ምእመናንም ክርስቲያን ተብለንበታል(ሮሜን ተመልከት) ፡፡
ወደ ጭብጡ ስመጣ ቀዳሜ በትረ ያሬክ ቅዱስ አባ ጴጥሮስ የማሠር የመፍታት ሥልጣነ ክህነት የተቀበለበት ረቂቁ ምሥጢር “እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ቃል ተቀብዐ በሥጋሁ” የሚለዉ እንደሆነ ማወቅ አዳጋ አይደለም ፡፡ ማንም ያልተናገራትን ሰማያዊት ምሥጢር በመናገሩ አለት የተሰኘዉ አባ ጴጥሮስ ለክህነት የበቃበት ምሥጢር በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በማመኑ እንጅ በተዋሕዶ ከበረ በማለቱ አይደለም ፡፡ አንተ ዉእቱ መሢሑ ለእግዚአብሔር(አንተ ከእግዚአብሔር የተቀባህ የእግዚአብሔር መሢሕ ነህ ብሎ በመመስከሩ የማሠር የመፍታት ሥልጣነ ክህነትን ተቀበለ ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ የሚሉ ሰዎች ዛሬ ክህነት የእኛ ነዉ ፣ ቤተክርስቲያን የእኛ ነዉ ፣ ሁሉም እኛ ነን ፣ ንብረታችን ፣ የእኛችን ፣ ተዋሕዷችን ፣ ሌላችን …አንዲሀችን እያላችሁ ብትቀላዉጡ እናት ቤተክርስቲያንን የማታዉቁ ፤ ነቢያት ከተነበዩት ፣ ሐዋርያት ከሰበኩት ፡ ሊቃዉንት ከተረጎሙት ሃይማኖት የወጣችሁ ዘላን ባዳ ፣ ከቤተክርስቲያን የሌላችሁ የምድረ በዳ እንግዳ እንደሆናችሁ እወቁት ፡፡ እናንተ በቅሌትና በድፍረት ቅብዓት ምንፍስና ነዉ እያላችሁ ብትሰድቡት ፣ ብሎም ብትክዱት ፤ እሱስ ሥላሴ በባሕርይ ሕያዉ ሁነዉ የሚኖሩበት ፤ እኛ ምእመናን በጸጋ ከሥላሴ ልጅነት ተወልደን መንፈሳዉያን የምንሰኝበት ፤ እናት ቤተክርስቲያን ስትታነጽ እና ለአገልግሎት ዝግጁ ስትሆን የምትባረክበት ፤ በዉስጧ ያሉ ቅዱሳት ንዋያት የሚከብሩበት ፤ እንዲሁም ምእመናን ለክህነት ሥልጣን (ከዲቁና እስከ ጵጵስና) የምንሾምበት አማናዊ ቅዱስ ቅብዓት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ዘወትር እንነግራኋለን ፡፡ለምን ያልን እንደሆነ “እንዘ  ታጸንዑ ሕሊናተ በርእስክሙ (ሕሊናችሁን በዕዉቀት አጽንታሁ) ፤ ተጋደሉ ፍቁራንየ በእንተ ጽድቅ(ወንድሞቼ ስለሃይማኖት ስለመንግሥተ ሰማያት መከራ ተቀበሉ) እዲል ተረፈ ቄርሎስ ምዕ 10 ቁ 22 ለመንግሥተ ሰማያት ለሃይማኖት እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ ተዋግተን ክብርን እንወርስ ዘንድ ሕሊናችንን በዕዉቀት መሙላት ስላለብን ለሰሚ ጆሮና ለአስተዋይ ዕዝነ ልቡና እንናራለን እንጮህማለን ፡፡ ይህንን አልሰማ ላለ  ሰዉ ደግሞ “ዘቦ ዕዝን ሰሚዓ ለይስማዕ” ብለን እንናራለን ፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያዉ ካህን አባ ጴጥሮስ ስልጣን ሊቀበልበትና ቤተክርስቲያን ልትታነፅበት የቻለዉ ምሥጢር ተቀብዐ እንጅ “በተዋሕዶ ከበረ” ማለት ስለሆነ ፤ በተለምዶ “ቅብዐቶች” የምንባል ካህናት ክህነታን ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ፤ የሐሰዊ ያልሆነ የአማናዊ  ክህነት መሆኑን ልታዉቅ ይገባሀል ፡፡
================================================
ብሂል ዐራት
================================================

“አንድ ሰው ወልድ በተዋህዶ ከበረ ብሎ ካመነና ወልድ በተዋህዶ ከበረ ብሎ በሚያምን ካህን ወይም ጳጳስ ተቀብቶ ዲያቆን ቢሆን ዲቁናው አማናዊ ነው፣ ካህን ቢሆን ክህነቱ አማናዊ ነው ቢጠመቅ ጥምወቱ አማናዊ ነው ቢቆርብ ቁርባኑ አማናዊ ነው ተክሊል ቢፈፀም ተክሊሉ አማናዊ ነው። ይህ ሳይሟላ የሚገኝ ክህነትም ሆነ የሚፈፀሙ ምስጢራት ከንቱ ናቸው።”››››››››››››››››››››››››››ብለሃልና ይህ የተናገርከዉ ከንቱ ነገር ሁሉ በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ በምትሉ በእናንተ ዘንድ የሚፈጸም ከሆነ አልቦ መሆኑን ከላይ ብሂል ሦስት ያስረግጥልናል ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ከተባለ ምንታዌ ነዉና ሁሉም ነገር ከምንታዌ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ለዚያ ነዉ ሁለተኛ ጥቀት ፣ ሁለተኛ  ምንኩስና ፣ ሁለተኛ ጋብቻ እና የመሳሰሉትን የምትደጋግሙት ምንታዌ በቤታሁ ከጣራ እስከ ግድግዳ ከመሰረቱ እስከ ባጡ ድረስ ስለወረራችሁ ነዉ፡፡
ዛቲ ሃይማኖት መሢሐዊት ዘትትአመን ባቲ ቤተክርስቲያን ቅዱስት
ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ




No comments:

Post a Comment