በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!!!!
ሃይማኖት መሢሐዊት‹‹‹‹‹‹‹ ክፍል አንድ›››››››››
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ዉሉደ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዉያን የተሰኛችሁ
ማኅበረ መሢሐውያን እንደምን ሰነበታችሁ እንደምን አላችሁ እንደምንስ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ደረሳችሁ?አሜን እግዚአብሔር ይመሥገን
ብለን ስሙን በኃጢአተኛ አንደበታችን እድንጠራው የወደደና የፈቀደ ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት አንደበት ሁሉ
ስሙ ከአጽናፈ ዓለም እስከ ዓጽናፈ ዓለም ፣ ከአድማስ እስከ አድማስ ፣ ከበርባሮስ እስከ ጽርሐ አርዓያም ድረስ የተመሰገነ ይሁን ፡፡ እሱን ጠርተን እሷን የማንተዋት የንጽኅናችን
መሠረት የጽድቃችን አክሊል ፤ በካሮቹ ዘንድ ያለ ስማችን ስም የተሰጠንባት (ተቀባት ይላሉ እያሉ የሚናሩባት) አምላክን በድንግልና
ጸንሳ በድንግልና የወለደች መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ የሆነች ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሐን ክብርት ድንግል ማርያም አምላክ
በሰጣት ክብር መጠን የተመሠገነች ትሁንልን ፡፡ ጻድቃን ሰማዕታት ፣ ደናግል
መነኮሳት ፣ ነቢያት ሐዋርያት ፣ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔር አምላክ በሰጣቸው ጸጋ መጠን የተመሰገኑ ይሁኑ ፡፡
===============================+===================================
ለዛሬው የማስተላፍላችሁ መልእክት በደቡቧ ኢትዮጵያ ለዘመናዊ (አስኳላ) ትምህርት
ለመማር ወደ አርባ ምንጭ መካነ አእምሮ (ዩኒቨርሲቲ) ሂዳችሁ ሳላችሁ ፤ ልክ እንደ ሠለስቱ ደቂቅ “በግቢ ጉባዔ ፍየሎች” ሃይማኖታችሁን
ቀይሩ ተብላችሁ የምትንገላቱ የምሥራቅ ከዋክብት ተማሪዎች የተነሳባችሁን የጠማሞች ጥያቄ ማስታገሻ ይሆናችሁ ዘንድ ከእናንተው መካከል
አንዲት ድንቅ እህት በቴሌ ግራም የላከችልኝን መልእክት በመመርኮዝ የኦርቶዶክሳዊት የክርስትና ሃይማኖት የነገረ ሥጋዌ አስተምህሮ
ምን እንደሚመስል ከእኔ አንደበት ሳይሆን ደገኞች አባቶቻችን እነ ቅዱስ ቄርሎስ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተናገሩትን ፤ ደጋግ
ሐዋርያት ከመድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበሉትን ፣ በብሉይ ኪዳን ነቢያት ካህናት ይከብሩበት የነበረውን ፣ በሐዲስ ኪዳንም
አማናዊ መሢሕ ኢየሱስ ክርስቶስ መሢሕ በመንፈሰ አቡሁ የተሰኘበትን ምሥጢረ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስን ወደፊት በሰፊው የምንማማር ይሆናል
፡፡ በዛሬው ክፍል ግን በትኩረት የምጽፍላችሁ እህታችን ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ውድ ወንድሞቸና
እህቶቸ እንዴት ሰነበታችሁ ማቴ1:16አንድምታ ትርጒሜ ሲቀባም ሲዋሀድም ከመቅፅበት አይን አንድ ጊዜ ነው የሚለዉን ቃል ትርጉሙን ባጭሩ ብታብራሩልን ምክንያቱም ካሮች በወልድ አብ መፅሀፍ ገፅ
108 ከመቅፅበት አምላክነቱን አጣ እንደገና ደግሞ የባህርይ አምላክ ሆነ የሚል ቃል አለ እያሉ እያስተማሩ ስለሆነ”›››››››› ብላ በላከችልን መሠረት
እያንዳንዱን በማብራራት መልስ መስጠት ላይ እናተኩራለን ፡፡ የምሥጢር ባለቤት ምሥጢሩን አምልቶ አስፍቶ ይግለጥልን፡፡
እህታችን
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹ ““ማቴ1:16አንድምታ
ትርጒሜ ሲቀባም ሲዋሀድም ከመቅፅበት አይን አንድ ጊዜ ነው የሚለዉን ቃል ትርጉሙን ባጭሩ ብታብራሩልን”›››››››› ብላ ጠይቃለች ፡፡
================================+===================================
ይህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ቁጥር አሥራ ስድስት ላይ የተጠቀሰው ሲቀባም
ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው የሚለው የአንድምታ መልእክት መነሻው ምዕራፍ አንድ ቁጥር አንድ ነው ፡፡ ይኸውም “መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ (የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
የልደቱ ነገር አንድም ቁጥር እንዲህ ነው አንድም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ ወግ ታሪክ እንዲህ ነው) ፤ አብርሃም ወለዶ
ለይስሐቅ (አብርሃም ይስሐቅን ወለደው) ፣ ወይስሐቅኒ ወለዶ ለያዕቆብ(ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ) ፣ወያዕቆብኒ ወለዶ ለይሁዳ ወአኃዊሁ(ያዕቆብም
ይሁዳን ወንድሞቹን ወለደ) ፣ ወይሁዳኒ ወለደ ፋሬስሃ ወዛምራሃ እምትዕማር(ይሁዳም ፋሬስን ዛራን ከትዕማር ወለደ) ፣ወፋሬስኒ ወለደ
ኤስሮምሃ(ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ) ፣ ወኤስሮምኒ ወለደ አራምሃ(ኤስሮምም አራምን ወለደ) ፣ ወአራምኒ ወለደ አሚናዳብሃ(አራምም
አሚናዳብን ወለደ) ፣ ወአሚናዳብኒ ወለደ ነዓሶንሃ (አሚናዳብም ነዓሶንን ወለደ) ፣ ወነዓሶንኒ ወለደ ሰልሞንሃ(ነዓሶንም ሰልሞንን
ወለደ) ፣ ወሰልሞንኒ ወለደ ቦኤዝሃ እምራኬብ( ሰልሞንም ቦዔዝን ከራኬብ ወለደ) ፣ ወቦዔዝኒ ወለደ ኢዮቤድሃ እምነ ሩት(ቦዔዝም
ኢዮቤድን ከሩት ወለደ) ፣ወኢዮቤድኒ ወለደ ዕሤይሃ (ኢዮቤድም ዕሤይን ወለደ) ፣ ወዕሤይኒ ወለደ ዳዊትሃ ንጉሠ (ዕሤይም ንጉሥ
ዳዊትን ወለደ) ፣ ወዳዊትኒ ንጉሥ ወለደ ሰሎሞንሃ እምነ ብእሲተ ኦርዮ(ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ከቤርሳቤህ ሰሎሞንን ወለደ)
፣ ወሰሎሞንኒ ወለደ ርብዓምሃ (ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ) ፣ ወሮብዓምኒ ወለደ አብያሃ (ሮብዓምም አብያን ወለደ) ፣ ወአብያኒ
ወለደ አሳፍሃ(አብያም አሳፍን ወለደ) ፣ ወአሳፍኒ ወለደ ኢዮሳጥሃ (አሳፍም ኢዮሳፍጥን ወለደ) ፤ ወኢዮሳፍጥኒ ወለደ ኢዮራምሃ
(ኢዮሳፍጥም ኢዮራምን ወለደ) ፣ ወኢዮራምኒ ወለደ አካዝያስሃ (ኢዮራምም አካዝያስን ወለደ) ፣ ወአካዝያስኒ ወለደ አሜስያስሃ
(አካዝያስም ኢዮአስን ወለደ) ፣ ወኢዮአስኒ ወለደ አሜስያስሃ (ኢዮአስም አሜስያስን ወለደ) ፣ ወአሜስያስኒ ወለደ ዖዝያንሃ ዘተሰምየ
አዛርያስ (አሜስያስም አዛርያስ የተባለ ዖዝያንን ወለደ ) ፣ ወዖዝያንኒ ወለደ ኢዮአታምሃ (ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ) ፣ ወኢዮአታምኒ
ወለደ አካዝሃ( ኢዮአታምም አካዝን ወለደ) ፣ ወአካዝኒ ወለደ ሕዝቅያስሃ (አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ) ፣ ወሕዝቅያስኒ ወለደ ምናሴሃ
(ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ) ፣ ወምናሴኒ ወለደ አሞፅሃ(ምናሴም አሞፅን ወለደ) ፣ ወአሞፅኒ ወለደ ኢዮስያስሃ (አሞፅም ኢዮስያስን
ወለደ) ፣ ወኢዮስያስኒ ወለደ ኢኮንያንሃ ወአኃዊሁ አመ ፍልሰተ ባቢሎን(ኢዮስያስም ኢኮንያንን ወንድሞቹን የባቢሎን ሰዎች ወደ ኢየሰሩሳሌም
በዘመቱ ጊዜ አንድም የኢየሩሳሌም ሰዎች ተማርከው ወደባቢሎን በወረዱ ጊዜ ወለደ) ፣ ወእምድኅረ ፍልሰተ ባቢሎን ኢኮንያንኒ ወለደ
ሰላትያልሃ (ኢኮንያንም ሰላትያልን የኢየሩሳሌም ሰዎች ተማርከው ወደ ኢየሩሳሌም ከወረዱ በኋላ ወለደ)፣ ወሰላትያልኒ ወለደ ዘሩባቤልሃ(ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ) ፣ ወዘሩባልኒ
ወለደ አብድዩሃ(ዘሩባቤል አብድዩን ወለደ) ፣ ወአብድዩኒ ወለደ ኤልያቄምሃ (አብድዩም ኤልያቄምን ወለደ)፣ ወኤልያቄምኒ ወለደ አዛርሃ(ኤልያቄምም
አዛርን ወለደ) ፣ ወአዛርኒ ወለደ ሳዶቅሃ(አዛርም ሳዶቅን ወለደ) ፣ ወሳዶቅኒ ወለዶ አኪንሃ (ሳዶቅም አኪንን ወለደ) ፣ ወአኪንኒ
ወለደ ኤልዩድሃ (አኪንም ኤልዩድን ወለደ) ፣ ወኤልዩድኒ ወለደ አልዓዛርሃ (ኤለዩድም አልዓዛርን ወለደ)፣ ወአልዓዛርኒ ወለደ ማትያንሃ(አልዓዛርም ማትያንን ወለደ) ፣ ወማትያንኒ ወለደ
ያዕቆብሃ (ማትያምን ያዕቆብን ወለደ) ፣ ወያዕቆብኒ ወለደ ዮሴፍሃ ፈኃሪሃ ለማርያም እንተ እምኔሃ ተወልደ እምኔሃ ተወልደ ኢየሱስ
ዘተብህለ ክርስቶስ (ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስ ከእሷ የተወለደ የማርያም (የእመቤታችን) እጮኛ፣ አገልጋይዋ ፣ ጠባቂዋ
/ዓቃቢሃ ተለአኪሃ የሚሆን ዮሴፍን ወለደ መገናኛው ጉንዱ አልዓዛር ነው” ማቴ ምዕራፍ አንድ ቁጥር 1-16 የሚል ነው፡፡
==============================+=====================================
አሁን ከዚህ ከቁጥር 16 ላይ እስከምንደርስ ድረስ እከሌ እከሌን ወለደ እያልን የጠቀስነው
ቃል በሰፊው ማብራሪያና አንድምታ ያለው መሆኑን መዘንጋት የለብንም ፡፡ በመሆኑም እስከ ያዕቆብ ድረስ የጠቀስኩት ጥሬ ዘሩን ብቻ
እንጅ አንድምታውን እንዳልሆነ ልብ በሉልኝ ፡፡ ሙሉ አንድምታውን ያልጠቀስኩበት ምክንያት የውይይታችን ዓቢይ ማረፊያ “ዘተብህለ
ክርስቶስ” ከሚለው ላይ በመሆኑ ነው ፡፡ በመሆኑም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ እንዲህ ከተነገረ
በኋላ ከዚህ ከቁጥር አሥራ ስድስት ላይ “ዘተብህለ ክርስቶስ(ክርስቶስ የተባለ)” የሚለውን ስም ሲተረጉም ነው “ሲቀባም ሲዋሐድም
አንድ ጊዜ ነው” የሚለው ምሥጢረ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስን ግልጥ ቁልጭ
አድርጎ የሚነግረን ፡፡ ማለትም -“…ዘተብህለ ክርስቶስ
(ይህም ስም ብቻ የትስብእት ብቻ ማለት አይደለም ከሁለት አካል አንድ
አካል ፤ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢሆን የወጣለት ስም ነው እንጅ) ወእነግር አነሂ ከመ
ኢመፍትው ዝ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእንበለ ትስብእት ወኢለትስብእት ዘእንበለ መለኮት ክርስቶስሃ ይሰመይ ወእምቅድመ
ትስጉት አልቦ ዘይሰምዮ በዝንቱ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ እንዲል ፡፡ በዝንቱ ስም ተሰምዩ ነቢያት ቅቡዓነ ፡፡ እስመ ስመ ክርስቶስ ይትበሃል ላዕለ ብዙኅ ጾታ ከመ ነገሥተ እስራኤል ወካህናቲሆሙ ከመ
አሮን ወዳዊት ወዘኃረዮሂ ከመ ሥርዓተ ቂሮስ ውእቱ ይላልሳ ቢሉ ፤ ይህንን እንጅ ወተቀብዖሰ በመንፈስ ከመ ካህናተ ሐዲስ ውእቱ ወላእለ ዘተወልደ እምእግዝእትነ ማርያም ይትበሃል እንበይነ
ተዋሕዶ ዘኮነ ለመለኮት በእንተ ተሠገወ እምድንግል ህየንተ ቅብዓተ ቅብዕ ባለው አፍርሶታል ፤ እንዲህ ከሆነ ማንን ሲያይ ተናግሮታል ቢሉ ፤
አንዱን ሲያይ ገብርኤል ስሙ ዘአምኃ ለማርያም ዘበትርጓሜሁ አምላክ ውእቱ እንዲል ፡፡ ኤልንም
ሲያይ ይህም አምላክ ሰው ቢሆን የወጣለት ስም ነው ፡፡ ወዝ ስም ዘውእቱ ክርስቶስ ወፍካሬሁ ቅብዓት ምስለ አምጣነ ትስብእቱ ረከቦ ለዋሕድ እንዳለ
፤ ከበረ መባሉም በሥጋ ነው ፡፡ ወቅብዓቱሰ ዘተወክፋ በትስብእቱ ይእቲ ወኢኮነ ቅብዓቱ አምሳለ ቅቡዓን
እስመ እለ ይትቀብዑ ይፈቅዱ ቀሪበ ኀቤሁ ለከዊነ ወልድና ውእቱሰ አምላክ በጠባዒሁ ዘእንበለ ፈቂድ እንዳለ ፡፡ አንድም ቦ እለ ይቤሉ እምቅድመ ተዋሕዶ ወቦ እለ ይቤሉ እምድኅረ ተዋሕዶ
እንዳለ ወገባሪሁሰ ለውእቱ ሥጋ መንፈስ ቅዱስ እስመ ውእቱ ቀብዖ ወተዋሕደ ቦቱ አምላክ ቃል ያለውን ይዘው ተቀብቶ ተዋሐደ የሚሉ አሉ
፤ ተሠጊዎ ነሥአ ቅብዓተ በዘተሰብአ ተቀብዐ
ያለውን ይዘው ሰው ሆኖ ከዚያ በኋላ ተቀባ የሚሉ አሉ ነገር ግን እንደዚህ አይደለም ፡፡ ሲዋሐድም ሲቀባም
አንድ ጊዜ ነው ከመ ቅጽበተ ዓይን እለሰ የአምኑ ርቱዓ ይሜህሩ ከመ ተቀብዓ ቃል
በሥጋሁ ወእምአመ ኮነ ቃል ሥጋ አሜሃ አስተርአየ በመንፈስ ቅዱስ” በማለት አብራርቶ ነግሮናል ፡፡ አሁን ከዚህ ጊዜ “ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ
ጊዜ ነው” ማለቱ አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ስለመሆኑ ክብር(ቅብዓዓት) የሚፈልግ ሥጋን ተዋሕዶ የሥጋን ገንዘብ
(መቀባትን መክበርን) በተዋሕዶ ገንዘቡ አድርጎታልና ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ ክብር ስለሚሻ ስለሥጋው በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ሲከብር
ጊዜው አንድ ነው ፡፡ መናቃን እንደሚሉት ቅድመ ተዋሕዶ ተቀባ ድኅረ ተዋሕዶ ተቀባ አይባልም ፤ ቃል ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ በማኅፀነ
ማርያም በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ሲከብር ምንም መቀዳደም መከታተል የለበትም አንድ ጊዜ ነው ሲለን ነው ፡፡
============================+======================================
ይህንን አንድ ጊዜ የተከወነ
ምሥጢር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንዲህ ሲል ገልጦታል “ወእመ አኮ ቀዲሙ ዘወረደ ወእምዝ ተሠይመ (ቀድሞ ሰው እንዳልሆነ ኋላ እንዳልተሾመ መጠን አንድ ጊዜ ሰው ለመሆን እንደመጣ አስረዳ
፡፡ አንድም ቀድሞ ሰው እንዳልሆነ ኋላ እንዳልተሾመ አስረዳ ፡፡ ሰው
ሁኖ ኑሮ ኑሮ ተቀባ የሚሉ አሉና እንዲህ አለ ፡፡ አንድም በተዋሕደ ጊዜ ተቀባ
አለ)” (ድርሳን 15 ቊ 105)፡፡ አስተውሉ “ተቀብዐ፣
ተቀባ ወይም ከበረ” ሲባል እኒያ ልቡናቸው የጠመመ ክፉ ጥፉ ሰዎች እንደሚሉት እመቤታችንን ተቀባት ማለት ሳይሆን ቀዳማዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሲሆን ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ
የተዋሐደው ሥጋ “መቀባት(መክበር)” የሚሻ በመሆኑና በጊዜ ተዋሕዶ ቃል የሥጋን ገንዘብ(ተቀባዒነትን) ገንዘቡ በማድረጉ ፤ ገንዘቡ
ባደረገው በሥጋው በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ (በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት) ከበረ ማለት ነው ፡፡ “ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ
ቅዱስ ወረሰዮ ቅዱሰ ወማሕየዊ(የአዳምን ባሕርይ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ያከበረው ፣ የባሕርይ አምላክም ያደረገው እርሱ ነው”
እንዳሉ አበው በእልመስጦአግአያ ምዕ 2 ቁ 5፡፡
====================================================================
ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ! ይህ ምሥጢር እኒያ ጨዋ ፍየሎች እንደሚናገሩት በቀላሉ የሚረዳ አይደለም እጅግ በጣም
ረቂቅ ምሥጢር ነው ፡፡ እንደ አባቶች በበርሃ በፍርኩታ ወድቆ ከጣዕመ ዓለም ርቆ እንጅ እደፈለገ እየተናሩ ፣ ጮማ እየጨለጡ ጠጅ
እየጨለጡ ፣ በዓለማዊት ፍርኩታ እያውደለደሉ ልረዳህ ቢሉት ከቶ ከባድ ነው ፡፡ “ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው” የሚለውን ቃል
ያመጣልን ከላይ እንዳየነው “ዘተብህለ ክርስቶስ/ክርስቶስ የተባለ” የሚለው ቃል ነው ፡፡ ከዚህ ላይ በደንብ ተከታተሉኝ ፤ “ኢየሱስ”
የሚለው ስሙ ትርጉሙ መድኃኒት ወይም አዳኝ ማለት ነው ፤ አማኑኤል የሚለው ስሙ ትርጉም ደግሞ “እግዚአብሔር ምስሌነ(እዚአብሔር
ከእኛ ጋር ሆነ)” ማለት ነው ፡፡ እነሆም ክርስቶስ የሚለውን ስም መተርጎም ፈልጓልና ዮሴፍን ወለደ ለማለት “ክርስቶስ የተባለ
ኢየሱስ ከእሷ ለተወለደ ለማርያም ጠባቂዋን ወለደ” ብሎ አስፍቶ ነገረን ፡፡ እናም ዘተብህለ ክርስቶስ ካለ በኋላ ይህ ክርስቶስ
የሚለው ስም ለመለኮት ለብቻው ወይም ለሥጋ ለብቻው የሚሰጥ አይደለም ብሎ መናገሩ ፤ መናፍቃን አካለ ቃልን አክባሪ አካለ ሥጋን
በአካለ ቃል ከባሪ አድርገው ለሁለት ስሚከፍሉትና ከበረ መባልን ለሥጋ ብቻ ነጥለው ስለሚሰጡት ፣ ክርስቶስ ማለት ደግሞ የከበረ
ወይም የተቀባ ማለት በመሆኑ ፣ የተቀባ መባልን ለአንዱ ብቻ ነጥለን መስጠት እደሌለብን ሲያስረዳ ነው ፡፡ ይህ ክርስቶስ የሚለው ስም የክርስቶስ
የተቀብዖ(በመቀባቱ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ በመክበሩ የወጣለት) አምላካዊ ስሙ ነው ፡፡ “እስመ እንከ ተቀብዐ ቅብዐ ሐሴትእመንፈስ
ቅዱስ በኀበ እግዚአብሔር አብ (በእግዚአብሔር አብ የደስታ ዘይትን ተቀብቷልና) ፤ ወበእንተዝ ተሰምየ ክርስቶስ (በተዋሐደው አካል (በትስብእቱ) ከብሯልና ክርስቶስ ተባለ) ፤ ወእለሰ
ርቱዐ የአምኑ (አንድ አካል አንድ ባሕርይ ብለው የሚያምኑ ሰዎች) ፤ ወይሜህሩ ከመ በሥጋሁ ተቀብዓ (በሰውነቱ ተቀባ ከበረ ብለው ያስተምራሉ (ያስተምሩ))” ድርሳነ ቄርሎስ (ብራና 11 ቊ 15-16 ፤ ሕትም 47 ቊ 8-9 ብሏል ፡፡፡ እናም ክርስቶስ ማለት ማለት የሹመት ስም ፣ የተቀባ ፣ ቅቡዕ
እንደ አሮንና እንደዳዊት ተመርጦ የተሾመና የተቀባ ማለት ሲሆን ፤ መቀባቱም ለሦስት ሹመት ነው ፡፡
እነርሱም ለክህነት ፣ ለንግሥና ለነቢይነት ፡፡ እነኝህን ሦስቱን የሚሾም ሰው በመጀመሪያ ደረጃ ከሕዝብ ይመረጣል
፤ ከዚያ
ቀጥሎ ከካህን ወይም ከነቢይ በተቀደሰ
ዘይት ይቀባል ፤ በተቀባ ጊዜም የሹመትን ሥራ የሚያስፈጽም ሀብት ፣ ሥልጣንና ችሎት ያድርበታል(ዘጸ 29 7 ፤ ዘሌ 4 l 3 ፤ 1ኛ ነገ 16 ቊ 11-13 ፤ 3ኛ ነገ ቁ 39) ፡፡ ይህ ኹሉ ለሰው ልጅ አምላክ ዘበጸጋ
የሚያሰኘው ሲሆን ፤ ለጌታችን
ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ
ክርስቶስ ለሥግው
ቃል (ከሥጋ
ጋር ተዋሕዶ አንድ ለሆነ) ግን
ፈጣሪ በመሆኑ ቀቢውና ሚው
ፈጣሪ እንጅ ፍጡር ስላልሆነ ግዙፍ ቅብዓት የለውምና በዘይቱ ፋንታ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ይባልለታል (ሐዋ ምዕ 10 ቊ
38 ፤ አክሲማሮስ
ዘሠሉስ ክ 2 ቊ 18) ፡፡ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌሉ
ምዕ አንድ ቁ 42 ላይ “ወይቤሎ ረከብናሁ ለመሢሕ ዘይልዎ ክርስቶስ (ክርስቶስ የተባለ መሢሕን አገኘነው) ፣ ማስያስ በእብራይስጥ
፡ ክርስቶስ በጽርዕ ፤ መሢሕ በዓረብ ፣ ቅቡዕ በግዕዝ” ብሏል ፡፡
ከዚህ ላይ መሢሕ ማለት
መሥሐ ቀባ ከሚል የግዕዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ፤ በዐረብ ቋንቋ
መሢሕ (መሺሕ) ፤ በዕብራውያን ደግሞ መሽያሕ(ማስያስ) ፤ በሱርስት ምሽሓ ፤ በግዕዝ ቅቡዕ ፤ በአማርኛ የከበረ የተቀባ ንጉሥ
ማለት ሲሆን ፤ በቁሙ
ምሡሕ የተቀባ ቅቡዕ ማለት ነው
፡፡ እናም የእህታችን ጥያቄ ሲጠቃለል ሲቀባም ሲዋሐድም አንድ ጊዜ ነው ማለት ቃል ከሥጋ ጋር በአካል
በባሕርይ በግብር ሲዋሐድና ክብር ወይም ቅብዐት የሚሻ ሥጋን በመዋሐዱ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከብሮ ክርስቶስ ሲባል አንድ ጊዜ ነው መለያየት
መቀዳደም የለበትም ሲለን ነው ፡፡
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
ስብሐት ለቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እግዝእትነ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ እጸ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ፡፡
ይቆየን
ክፍል ሁለት ወልደ አብ ገጽ 108 ብላ ስላነሳችው ጥያቄ ሰፊ መብራሪያ
ይዤ እመጣለሁ እስከዚያው አምላከ ምሕረት በተቀደሰች ክርስትናችን ያጽናን፡፡
No comments:
Post a Comment