Friday, October 25, 2019

“የተቀብዐ እንግዶች” ክፍል ሦስት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ !!!
“የተቀብዐ እንግዶች” ክፍል ሦስት
==============+==============
“ሰላም ለክሙ ወጸጋ ለእግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ነአኵቶ ለእዚአብሔር አቡሁ ለእዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘልፈ በእንቲአክሙ፤ ወንጼሊ እምአመ ታፈቅርዎሙ ሰማዕነ ሃይማኖተክሙ በኢየሱስ ክርስቶስ ወዘከመ ታፈቅርዎሙ ለኵሎሙ ቅዱሳን ፤ በእንተ ተስፋክሙ ዘሥዩም ለክሙ በሰማያት ዘአቅደምክሙ ሰሚዐ በቃለጽድቅ ትምርተ ወንጌል
ሰላም ለእናንተ ይሁን የአባችን የእግዚአብሔር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይደርባችሁ ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔርን ዘወትር ስለ እናንተ እናመሰግነዋለን ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናችሁንና ቅዱሳንን ሁሉ መውደዳችሁን ከሰማንበት ጀምሮ እንጸልያለን ፡፡ የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል ትምርት አስቀድሞ ስለ ሰማችሁት በሰማያት ስለ ተዘጋጀላችሁ ስለተስፋችሁ” ቆላ ምዕ 1 ቁ 2-5 ፡፡
ወንድም እህቶቼ መሢሐውያን እደምን ሰነበታችሁ?ከመጻሕፍት ዓለም የራቁ  ዘላን የምድረበዳ እንግዶች አማናዊ መሢሕ ኢየሱስ ክርስቶስ መሢሕ ወበኩረ ምእመናን የተሰኘባትን እውነት ሙጥጥ ጭልጥ አድገው ክደው የራሳቸው መካድ ሳያንስ ማንም ሳይነካቸው ማንም ሳያስገድዳቸው ቤታችንን ለነኩን ዉልደ መጥባሕት በሙሉ ኦርቶዶክሳዊ መልሳችንን እንሰጣቸው ዘንድ ተገቢ በመሆኑ በባለፈው ክፍል  ላይ ስሙን የጠቀስኩለት እንግዳችን/ ሁነኛው ተሾመየጻፈውን ጦማረ ክሕደት መሠረት አድርጌ ክፍል ሦስትን እንደሚከተለው ጻፍኩላችሁ
፡፡
1ኛ ‹‹‹”ከአብ በባሕርይ ክብሩ ከብሮ ክርስቶስ የተባለ እሱ ቀዳማዊ ነው ፡፡ ድርሳን ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ 24” ብሏል በጹሁፉ ገጽ 24 ላይ፡፡
አምላክ በቸርነቱ ሲያናግር እንዲህ ነው ፡፡ ከአሁን በፊት በተመለከትነው በክፍል ሁለት መልእክቴ ላይ እንዳየነው እንግዳችን “ዲ/ን ሁነኛው ተሸመ” የሚሉት ሰው “ያለሃሰት በውነት የሚበልጥ ቃል የሚያንሰውን ሥጋ ያከብረዋል” ብሎ አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሽና ትልቅ አድርጎ ከፋፍሉ የልዮንን እና የንስጥሮስን ክሕደት አጉልቶ አመሥጥሮ መናገሩን አይተናል ፡፡ አሁን ደግሞ አዙሮ ከአብ በባሕርይ ክብሩ ከብሮ በማለት የአብን አክባሪነት የአብን ቀባዒነት ሳያውቀውም ቢሆን ተናግሮት እርፍ አለ ፡፡ አምላክ የተመሠገነ ይሁን መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን የሥላሴ ሕይወታቸው ነውና ክብራቸው መንግሥታቸው እያሉ ይገልጹታል ፡፡ ለአብነትም “ወወሀበኒ ብዕሎ ከመ እትመሰል ኪያሁ ዝ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘነሥኦ እምአብ በማኅፀን እንበለ ጊዜ ወሰዓት (እሱን እመስል ዘንድ ክብሩን ሰጠኝ ፤ ይሐውም ጊዜና ሰዓት ሳይኖረው በማኅፀን ከሥጋ ጋር በተዋሐደ ጊዜ ከአብ የተቀበለው መንፈስ ቅዱስ ነው” ብሏል ቅዱስ ኤፍሬም በድርሳኑ፡፡ ስምዖን ዘአምድም ወዘሰ ኢያጠሪ እምብዕለ ክርስቶስ ዝ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ነዳይ ውእቱ(የክርስቶስን ክብር ይኸውም መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ ያላደረገ ድሃ ነው ፤ አንድም የጸጋ ልጅነት የለውም)” ብሏል፡፡ ጴጥሮስ ዘሰርመምቴም “አክበረነ በክብሩ ወአብዓለነ በብዕሉ ማኅየዊ ( ማኅየዊ በሚሆን ክብሩ አከበረን) ፤ ዝ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘሀሎ ውስቴቱ እምቅድመ ዓለም(ይኸውም በእሱ ዘንድ ከዓለም አስቀድሞ ያለ መንፈስ ቅዱስ ነው” ብሏል ፡፡ እናም ወዳጃችን ሁነኛው ከአብ በባሕርይ ክብሩ ከብሮ ያለው ሀሳቡ ትክክል ነው ፡፡ ያ የባሕርይ ሕይወቱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በጊዜ ተዋሕዶ ስለከዊነ ትስብእት ሕይወቱ ሆኖታል ከብሮበታልና እነሆ ከአብ በባሕርይ ከብሮ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቶ ክርስቶስ የተባለ እሱ ቀዳማዊም ብቻ ሳይሆን ዘለዓለማዊ እንደሆነ እናምናለን እንታመንማለን ፡፡
ነገር ግን እንግዳችን ሁነኛው ድር 24 ብሎ ከጠቀሰው ቁጥር ላይ የተናገረው ቃል ፈጽሞ ተጽፎ አይገኝም ፡፡ የድርሳን 24ን መልእክት ቁልጭ አድርጌ ላስቀምጥላችሁና በዚያውም መዝሙር 2 ቁ 7 ያለውን ዮም ወለድኩከን የተረጎመበትን ፤ እነ “ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ” የካዱት ሐዲስ አምላክ የሚለው ምሥጢር በደንብ የተብራራበትን ክፍል ይዞ የሚገኝ ስለሆነ በደንብ ተከታተሉኝ ፡፡
የድርሳ 24 ሐተታ መጀመሪያው ድርሳን 23 ቁ 11 ላይ ያለው “ወኮነ ሰብአ ሰዊጦ ርእሶ በዘኢኮነ ቀዳሚ(ጥንቱን ገንዘቡ ያይደለ ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ሆኗልና..” የሚል ሀሳብ ያለው የአምላክ ሰው መሆን ምሥጢር ነው ፡፡ ከዚያም ክርስቶስ ከሁለት ባሕርያት አንድ ባሕርይ እንደሆነ እያስረዳ ፣በእኛ ባሕርይ ተገልጦ የባሕርይ አምላክ መሆኑን ለማሳመን እንደሆነ ከገለጠ በኋላ ቁጥር 13 ላይ ሲደርስ “ይጽሕፍ እንዘ ይብል ጳውሎስ ገብሩ ለኢየሱስ (የኢየሱስ አገልጋይ የሆነ ጳውሎስ እንዲህ እያለ ጻፈ) ፤ ዝ ውእቱ መለኮት ወትስብእት (ይኸውም መለኮት ትስብእት ነው አለ) ፡፡ ንባብ “ይጽሕፍ እንዘ ይብል ጳውሎስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስሙይ ሐዋርያ ወወጻሕኩ ውስተ መንገለ እግዚአብሔር ዘአቅደመ ነጊረ በነቢያቲሁ ወበመጻሕፍቲሁ ቅዱሳት በእንተ ወልዱ ዘኮነ እምዘርዐ ዳዊት በሥጋ ፤ ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል” ብሏል …..ይህንን ንባብ ከሚለው ጀምሮ ያለውን ሀሳብ አባ እዝራ ሐዲስ ወደ አማርኛ አልተረጎሙትም ንባብ ብለው ነው ያስቀመጡት ፡፡ በተጨማሪም “ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል” ያለው የቅዱስ ጳውሎስ ሳይሆን የቅዱስ ቄርሎስ ነው ፡፡ እሳቸውም “ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል” ብቻ ብለው ነው ያቆሙት ፤ የብራናው ድርሳነ ቄርሎስ ግን “ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝ ውእቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ” የሚል ነው ፡፡ እኒህ አደገኛ የተሐድሶ ለመጽሐፍ ቅዱስ አራማጅ “አባ እዝራ ሐዲስ” ቅብዓትን እንደጦር ስለሚፈሩት እየቆረጡ እየቆመጡ አስቀርተውታል ፡፡ ጆሮ ያለህ መስማትን ስማ ፡፡ ለሌላው “መናፍቅ ምናምን” እያሉ ታርጋ እየለጠፉ እነሱ ለራሳቸው በሚመቻቸው መልኩ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲህ እየቆነጻጸሉ ክሕደቱን እውነት ለማስመሰል እስከዚህ ደርሰዋል ፡፡ አንተ የተኛህ ንቃ እነሱ እንደፈለጉ ማመን ይችላሉ ፡፡ ሲፈልጉ አለማመንም ይችላሉ ማንም አይከለክላቸውም ፡፡ እኛ የምናምናትን ከሐዋርያት የተቀበልናትን እውነታ እያጨለሙ ሲያስክዱን ግን ለምን ብለን ለእውነታችንና ለክርስትናችን ልንቆም ይገባናል ፡፡ እነሱ የሚይዙት የሚጨብጡት ስላጡ መጽሐፉን እየገለበጡ መተርጎምን ፣ ስለ ቅብዓት የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲመቻቸው ቆርጠው ማስቀረት ፤ አልመቻቸው ሲል ደግሞ ግእዙ ላይ ቅብዓት እያለ አማርኛውን ሲተረጉሙ ተዋሕዶ እያደረጉ እየለወጡት ስለሆነ ልብ ያለህ ልብ በል ፡፡ ዝም ብለህ እንደጋማ ከብት ሁሉም ሲጎትትህ አትጎተትለት ፡፡ የራሱ መንገዱ ጠፍቶበት እየተደናበረ ያለ ሁላ ሊያደናብርህ አይገባም ፡፡
ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና  ያን በንባብ መልክ ያስቀመጡትን የጳውሎስንና የቄርሎስን መልእክት ትርጉም ስንመለከተው ““ይጽሕፍ እንዘ ይብል ጳውሎስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስሙይ ሐዋርያ ወወጻሕኩ ውስተ መንገለ እግዚአብሔር ዘአቅደመ ነጊረ በነቢያቲሁ ወበመጻሕፍቲሁ ቅዱሳት በእንተ ወልዱ ዘኮነ እምዘርዐ ዳዊት በሥጋ ፤ ዘተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝ ውእቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ (የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ የሚሆን ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ወጣሁ አለ፤ አስቀድሞ በነቢያትና በቅዱሳት መጻሕፍት ከዘርአ ዳዊት በሥጋ ስለተወለደ ስለልጁ እንደተናገረ ፤ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ተባለ ይኸውም ቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ነው)” የሚል ነው ፡፡ የዚህን ዝርዝር ትርጓሜ ከምዕራፍ 24 ቁ 1 ጀምረን እንደሚከተለው እናገኘዋለን “ እፎ ንግረኒ አምላክ ውእቱ(እስኪ ንገረኝ አምላክ ሲሆን በእንተ ወልዱ እንደምን አለው? ፤ ዘእምዘርአ ዳዊት ተወልደ ወመጽአ (ከዘርዐ ዳዊት ተወለደ መጣ ፤ እምዘርአ ዳዊት እንደንም አለው?)፤ ወሀሎ እምቅድመ ዓለም ወልድ(እምቅድመ ዓለም የነበረውን ወልድ)፤ ዘለዝላፉ ይሄሉ ምስለ እግዚአብሔር አብ (ከአብ ጋር በቅድምና የነበረውን) ፤ በአይ እንከ ፍና ተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝውእቱ ቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ( ኃይሉ ሕይወቱ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ቅብዓት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ወአርአየ እንደምን አለው?) ፤ እስመ ይቤ ውእቱ በእንተ ርእሱ እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ (በዳዊት አድሮ እሱ ራሱ እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ ብሏልና ፤ ወልድየ አንተ ያለውንና ዘተወልደ ያለውን ፣ ወአነ ዮም ወለድኩከ ያለውንና ወመጽአ እምዘርአ ዳዊት ያለውን አስማማ ፤፡፡ ወዮም ብሂል አኮ መዋዕለ ዘኃለፈ ዘይነግር (ዮም ያለው ያለፈውን ዘመን የሚያስረዳ አይደለም)፤ አላ ዘሃሎ (የሚመጣውን ዘመን ነው እንጅ (አንድም እምቅድመ ዓለም የነበረውን ዘመን የሚያስረዳ አይደለም ድኅረ ዓለም ያለውን ዘመን ነው እንጅ ፤ አንድም ቀዳማዊ ልደቱን የሚያስረዳ አይደለም ደኃራዊ ልደቱን ነው እንጅ ፡፡ ሶበሰ ይትበሀል ዕሙቀ ምሥጢረ (ወልድየ አንተ ያለው ዮም ወለድኩከ ተብሎ ረቂቅ ምስጢር ሆኖ ቢነገር) አላ ባሕቱ ለእለ ይፈልጡ (መለኮቱን ከትስብእቱ ትስብእቱን ከመለኮቱ ለሚለዩ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ለሚሉ )፤ ዕፁብ አእምሮቱ( ይህንን ማወቅ ጭንቅ ነው እንጅ)፤ ወለግሙራ ዘኢይትከሀሎሙ (እነዚህ ይህንን ማወቅ አይቻላቸውም እንጅ)፤ ወእለሰ ይጸንዑ በትድምርቱ ለአማኑኤል ( አንድ አካል አንድ ባሕርይ ለሚሉስ ይህንን ማወቅ ሩቅ ያይደለ ቅርብ ነው)፡፡ ወድልው አእምሮታ ለቅድስት ንጽሕት ወእንተ አልባቲ ጥልቀት ሃይማኖት(ክብርት የምትሆን ሐሰት የሌለባት ይህችን ሃይማኖት ማወቅ ሰንከልካላ ያይደለ ምቹ ነው፡፡ ጉጻ ጉጽ ያይደለ የቀና ነው)፡፡በማለት እስከ ቁጥር 7 ድረስ ቁልጭ አድርጎ ያብራራልናል ፡፡ ቁጥር 8 ላይ ሲደርስ “ ወሐደሰት በላዕሌሁ ልደቱ እንተ በሥጋ አጽንዐት ሎቱ( በሥጋ የተወለዳት ልደቱ ቀዳማዊ ልደቱን አስረዳችለት…አንድም በመለኮት በተወለደው ልደት ላይ በሥጋ የተወለዳት ልደቱ ቃልን ዮም ወለድኩከ አሰኘችው ፡፡ አንድም በሥጋ የተወለዳት ልደቱ ሐዲስ አምላክ አሰኘችው” በማለት ሐዲስ አምላክ የሚል የለም እያሉ የሚናገሩትን የካሮቹን አባት አባ ስምዐኮነን ወገብ ዛላቸውን ሲላቸው እናስተውላለን፡፡ በመሆኑም ድርሳን 24 የያዘው ይህንን መልእክት እንጅ እንግዳችን ሁነኛው የጻፈውን ጽሁፍ አይደለም፡፡
በቀጣዩ ክፍል ቤተ አይሁድ ካሮች ስለ መሢሐውያን ስለ እኛ የተረቷቸውን ተረት ተረቶች በገለጸበት መልኩ ይዤ እመለሳለሁ እስከዚያው አምላክ ሠላሙን ያብዛልን ፣ ሳይማሩ መምሕር ሆነው ድጋሚ ተጠምቀው አረሚ ሆነው ሌላውን አረሚ የሚያደርጉ ከሐድያንን ልቡና ይስጥልን ፡፡
ዛቲ ሃይማኖት መሢሐዊት ዘትትአመን ባቲ ቤተክርስያን ቅድስት
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ስብሐት እዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ እጸ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ
ይቆየን
ይቀጥላል







No comments:

Post a Comment