በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ !!!
“የተቀብዐ እንግዶች” ክፍል ሁለት
==============+==============
“ሰላም
ለክሙ ወጸጋ ለእግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ነአኵቶ ለእዚአብሔር አቡሁ ለእዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘልፈ በእንቲአክሙ፤
ወንጼሊ እምአመ ታፈቅርዎሙ ሰማዕነ ሃይማኖተክሙ በኢየሱስ ክርስቶስ ወዘከመ ታፈቅርዎሙ ለኵሎሙ ቅዱሳን ፤ በእንተ ተስፋክሙ ዘሥዩም
ለክሙ በሰማያት ዘአቅደምክሙ ሰሚዐ በቃለጽድቅ ትምርተ ወንጌል
ሰላም
ለእናንተ ይሁን የአባችን የእግዚአብሔር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይደርባችሁ ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔርን
ዘወትር ስለ እናንተ እናመሰግነዋለን ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናችሁንና ቅዱሳንን ሁሉ መውደዳችሁን ከሰማንበት ጀምሮ እንጸልያለን
፡፡ የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል ትምርት አስቀድሞ ስለ ሰማችሁት በሰማያት ስለ ተዘጋጀላችሁ ስለተስፋችሁ” ቆላ ምዕ 1 ቁ
2-5 ፡፡
ወንድም
እህቶቼ መሢሐውያን እደምን ሰነበታችሁ?ከመጻሕፍት ዓለም የራቁ
ዘላን የምድረበዳ እንግዶች አማናዊ መሢሕ ኢየሱስ ክርስቶስ መሢሕ ወበኩረ ምእመናን የተሰኘባትን እውነት ሙጥጥ ጭልጥ አድገው ክደው ፤ የራሳቸው መካድ ሳያንስ ማንም ሳይነካቸው ማንም ሳያስገድዳቸው ቤታችንን ለነኩን ዉልደ መጥባሕት በሙሉ ኦርቶዶክሳዊ መልሳችንን እንሰጣቸው ዘንድ ተገቢ በመሆኑ በባለፈው በክፍል አንድ ላይ ስሙን የጠቀስኩለት እንግዳችን “ዲ/ን ሁነኛው ተሾመ” የጻፈውን ጦማረ ክሕደት መሠረት አድርጌ ክፍል
ሁለትን እደሚከተለው ጻፍኩላችሁ፡፡
1ኛ‹‹‹‹‹ “ወእንዘ ኢይትዌሰክ ክብረ እንዘ እግዚአብሔር ውእቱ ነሥአ ሥጋ” ድ/ቄ
ምዕ 26 ዘዮሐንስ ኤጲስ ቆጶሰ ክፍል 7”
በማለት ጠቅሷል
፡፡
ይህንን
ከንቱ ሀሳብ በተዋሕዶ ከበረ ለማለት ያቀረበው ይመስላል ፡፡ ዳሩ ግን ድርሳነ ቄርሎስ ምዕ 26 የብራናውም የሕትሙም እንዲህ የሚል
ቃል የለውም ፡፡ ዘዮሐንስ ተብሎ የተጠቃሰው ኤጲስ ቆጶስም የየት ሀገር ኤጲስ ቆጶስ እንደሆነ በግልጽ አልጠጠቀሰም ፡፡ እርሱ በግልጽ
ባያስቀምጠውም በሃይማኖተ አበው ከተገለጹት ዮሐንስ የሚባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ከጻፏቸው መልእክታት ጋር ሁሎችንም ብንመለከታቸው ከነዚህ
ውስጥ አንዱ የአንጾኪያውና የሩቅ ምሥራቅ ሊቀ ጳጳስ የሚገኝ ሲሆን ያስተማረው ትምህርትም በአንድ ቦታ ማለትም ሃይማኖተ አበው ገጽ 453-468 ላይ ያለው ሁለት ክፍል
እና ሁለት ምዕራፍ (ምዕ 102 እና 103) ብቻ ያሉት ነው እንጅ ክፍል ሰባት የሚባል ክፍል የለውም፤ የጠቀሰው ቃልም ተጽፎ አይገኝም
፡፡ ሌላው በሃይማኖተ አበው ገጽ 534-546 ላይ ያለው መልእክቱ
ሁለት ምዕራፍ(113-114) እና ሦስት ክፍል ሲሆን ከላይ የተቀሰው ቃል ተጽፎ አይገኝም ፡፡ ሌላኛው ዮሐንስ ደግሞ የኢየሩሳሌም
ሊቀ ጳጳስ ነው እሱም በጻፈው መልእቱ በሃይማኖተ አበው ገጽ 167-171 ድረስ ባለው አንድ ምዕራፍ (ምዕ 52) እና አንድ ክፍል
ያለው ሲሆን ልጁ የጻፈው መልእክት የለም ክፍል 7 የሚባል ክፍልም ተጽፎ አይገኝም ፡፡ እናም ከየት ከየት አጠረቃቅሞና ለቃቅሞ
እንደጠቀሰው አሳማኝ ምላሽ ለመስጠት አመች አይደለም ፡፡
ይሁን
እንጅ የጠቀሰው የግእዝ ቃል ወደ አማርኛ ሲመለስ “እግዚአብሔር ነውና ክብርን አይሻም እሱ ሥጋን ገንዘብ አደረገ” የሚል ነው ፡፡
ይህ የተናገረው ቃል ተቆርጦ የተጠቀሰ በመሆኑ ትርጉሙንም ምሥጢሩንም አጥፍቶበታል ፤ ዳሩ ግን አምላክ ወልደ አምላክ መድኅነ ዓለም
ኢየሱስ ቅርስቶስ በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ወይም “ተቀብዐ በመንፈስ ቅዱስ” ተብሎ የተነገረለት በባሕርየ ትስብእቱ ነው እንጅ
በባሕርየ መለኮቱ አይደለምና ተቆርጦ የተጠቀሰው ቃል የሚያሥረዳን ከበረ መባሉ በባሕርየ መለኮቱ እንዳይደለ ነው ፡፡ እሱ ለጠቀሰው
በተዋሕዶ ከበረ ለማለት ማስረጃ አይሆንለትም ፡፡ እንዲያውም እንደሱ ነገር እናጣም ከተባለ “እግዚአብሔር ነውና ክብር አይሻም”
እያለው ሳለ እሱ እና ቤተሰቦቹ “በተዋሕዶ ከበረ” የሚሉት ክብሩ የትሄዶበት ፣ እግዚአብሔርነቱ የትሄዶበት በተዋሕዶ ከበረ? ቢሏቸው
መልስ የላቸውም ፡፡ ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና የተቀብዐ እንግዳው ሁነኛው ተሾመ የጠቀሰው ቃል በጠቀሰው ምዕራፍና ቁጥር አይገኝም
፡፡ ምን አልባት አስተካክሎ የሚጠቅስልን ከሆነ እንደገና እመለስበታለሁ አልያ ደግሞ ምዕራፍ ቁጥር ስቶ ከሆነ የጠቀሰው በመጀመሪያ
አጠቃቀሱን ማስረጃውን ያስተካክልና ወደ መምህርነት ይግባ እላለሁ ፡፡ ሳይማር መምህር መሆን እንዲህ ምዕራፍና ቁጥሩ የማይገናኝ
፤ ሀሳቡንና እምነቱን የማይገልጽ ቃል ሲያስጠቅሰው ይኖራል እንጅ ሌላ አንዳችም አይፈይድለትም ፡፡ የቄርሎስ ነው ብሎ የጠቀሰውን
ቃል በሌላ ምዕራፍና ቁጥር ስለምናገኘው ያኔ ሰፊትንታኔ እሰጥበታለሁ ፡ አሁን ጉዞ ወደ ቀጣዩ ጥያቄ ፡፡ እስዚያው ግን ቅዱስ ቄርሎስ
በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ የሚል ንስጥሮሳዊ ትምህርትን እንዳላስተማረ እናውቅ ዘንድ ይገባናል ፡፡
=====================================+=================================
2ኛ‹‹‹‹‹‹
“የክርስቶስ ክብር ከራሱ እንጅ ከሌላ የተገኘ አይደለም ፤ በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት ከአብ በተገኘ ባሕርይ ከብሯልና ስለዚህ ክርስቶስ
ተባለ ፤ ክብሩም አካለ ቃል ነው ፤ሥጋን ያልተዋሐደ ዕሩቅ ቃልስ ከሆነ ከበረ መባልን አይሻም በባሕርይ ክብሩም ላይ ክብር አልተጨመረለትም
፤ ያለሃሰት በውነት የሚበልጥ ቃል የሚያንሰውን ሥጋ ያከብረዋል ፡፡ ለሰው ባሕርይ በነፍስ በሥጋ ከበረ መባል ይገባዋልና (ድርሳን
ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕ 29) ብሏል ገጽ 23-24 ባለው የክሕደት ጽሁፉ፡፡
ይህ
የተደናበረ ሰው እየቆረጠ እየቆመጠ ያስቀመጠው ቃል መገኛው አባ እዝራ ሐዲስ ተቀብዐን ግሱን እየቀያየሩ እየቆራረጡ አውጥተው ባሳተሙት
ድርሳን ምዕ 47 ቁጥር 9 ላይ የሚገኝ ቃል እንጅ ድር 29 ላይ አይደለም ፡፡ “፤ሥጋን ያልተዋሐደ ዕሩቅ ቃልስ ከሆነ ከበረ መባልን
አይሻም በባሕርይ ክብሩም ላይ ክብር አልተጨመረለትም ፤ያለሃሰት በውነት የሚበልጥ ቃል የሚያንሰውን ሥጋ ያከብረዋል ፡፡ ለሰው ባሕርይ
በነፍስ በሥጋ ከበረ መባል ይገባዋልና” የሚለው ቃል ከድርሳኑ ፈጽሞ አይገኝም ራሱ ልጁ የጨመረው የክሕደት የእርምና ቃል ነው ፡፡
“የክርስቶስ ክብር ከራሱ እንጅ ከሌላ የተገኘ አይደለም” የሚለውም በመጽሐፉ ተጽፎ የሚገኝ አይደለም ራሱ ሁነኛው የወለደው ትምህርተ
ሳምሳጢ ጳውሎስ ነው ፡፡ “በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት ከአብ በተገኘ ባሕርይ ከብሯልና ስለዚህ ክርስቶስ ተባለ ፤ ክብሩም አካለ
ቃል ነው” የሚለውን ቃል ግን ከእዝራ ሐዲስ የአንድምታ ስርዋጽ ቃል በቃል ገልብጦ የወሰደው ሲሆን ሲገለብጥ እንኳን አስተካክሎ
መገልበጥ የማይችል ከንቱ ነውና ሰውየው “ከአብ በተገኘ ክብር ከብሯልና” ያሉለትን “ከአብ በተገኘ ባሕርይ ከብሯልና” ብሎ ነው
የጻፈው ፡፡ አሁን ማን ይሙት አስተካሎ እንኳን መጻፍ የማይችል ይህ ባዶ የሆነ ሰው አስተምሯችሁ ነው ሁለተኛ ለመጠመቅ የተገደዳችሁ
ወንድሞቼ የዓርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆናችሁ መሢሐዉያን? በእዉነቱ ይህ ሰው ስንኳንስ አስተማሪ ለመሆን ይቅርና ተማሪ ለመሆን
እንኳን ገና አቡጊዳን መቁጠር የሚጠበቅበት ጮርቃ ሰው ነውና ንቁ እባካችሁ ከብቱ ሁላ እየመጣ ሲነዳችሁ አትነዱ በድንግል፡፡ እሱ
የጠቀሰውን ቃል ከብራናው ድርሳነ ቄርሎስ እና የጎንደሩ አባ እዝራ ሐዲስ ቆማምጠው ቆራርጠው ካሳተሙት ድርሳነ ቄርሎስ ጋር እያመሳከርን
ከግእዙ ጀምረን አንድ በአንድ እንመልከተው ፡፡
ግእዙ
የሚለን “እስመ ሶበ ቃል ሥጋ ኮነ አሜሃ ንብል ተሰምየ ክርስቶስ እስመ እንከ ተቀብዐ ቅብዓ ሐሴት እመንፈስ ቅዱስ በኀበ እግዚአብሔር
አብ ወበእንተዝ ተሰምየ ክርስቶስ” ነው ፡፡ ወደ አማርኛ ስንመልሰውም “ቃል ሥጋ በሆነ ጊዜ ክርስቶስ እንደተባለ እንናገራለን ፤
ከአብ በተገኘ የደስታ ዘይት በመንፈስ ቅዱስ ከብሯልና ክርስቶስ ተባለ” የሚል ነው ፡፡
ከዚህ
ላይ አባ እዝራ ሐዲስ በብራናው “እስከ እንከ ተቀብዐ ቅብዓ ሐሴት” የሚለውን ግስ “እስመ እንከ ከብረ ክብረ ሐሴት” ብለው ዘሩን
ለውጠውታል ፡፡ ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት ሲሉ መጽሐፍ ቅዱስን እያደሱ እውነት ለማስመሰል እንዲህ ሲያደርጉም ይገኛሉ ካሮች ፡፡
ዘሩን ከቀየሩ በኋላ ከላይ በቀጥታ እንደጻፉኩት ሁነኛውም በቀጥታ አባ እዝራ የተናገሩትን ገልብጦ አስቀምጦታል ፡፡ ሃይማኖታቸውም
ትምህርታቸውም ተሐድሶ ምንታዌ ነውና “ተቀብዐ በቅብዓ ሐሴት እመንፈስ ቅዱስ” የሚለውን ለውጠው “በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት” ብለው
ተርጉመውታል ፡፡ ግእዙ ግን ቅብዓት የሚል እንጅ ተዋሕዶ የሚል መልእክት የለውም ፡፡ እነሱ በነሲብ አበበን ከበደ እያሉ ትውልድ
ሲያደናግሩ ይገኛሉና መሢሐውያን ንቁና ክርስትናችሁን ጠብቁ ፡፡ እጅጉን የሚደንቀው ደግሞ “ከአብ የተገኘ ክብርም አካለ ቃል ነው”
ብለው የተናገሩት ፈጠራ ነው ፡፡ እንደነገርኳችሁ ግእዙ ላይ “እመንፈስ ቅዱስ” ይላል እንጅ “እምአካለ ቃል” የሚል የለም ፡፡
እነሱ በሚመቻቸው እየተረጎሙ ወደ ክሕደት ወደ ምንፍቅና እየነጎዱ ይገኛሉ ፡፡ እነሱ እንዳሉት “ከአብ የተገኘው ክብር አካለ ቃል”
ከሆነ የከበረው እና ክርስቶስ የተባለው ማን ነው? እነሱ እንዳሉት እንኳን ቢሆን “ከአብ በተገኘ ክብር ከብሯልና ክርስቶስ ተብሏል”
ብሎ ሲናገር ክርስቶስ የተባለው ሥጋ ብቻ ያሰኝባቸዋል ፡፡ ምክንያቱም እነሱ እንዳሉት ክብር አካለ ቃል ከሆነ! ክርስቶስ የተባለ የከበረው እንጅ ክብር የሆነው
ስላልሆነ ሳይወዱ በግዴታ ክርስቶስ የሚባለው ትስብእት ብቻ ነው ያሰኝባቸዋል ፡፡ በመሆኑም እንግዳችን ሁነኛው የጠቀሰው ቃል ትክክለኛው
ትርጓሜ “በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት” ሳይሆን “ከአብ በተገኘ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዓትነት (ቅብዓ ሐሴት እመንፈስ ቅዱስ/በመንፈስ
ቅዱስ ሕይወትነት) ተቀብቷልና (ከብሯልና) ክርስቶስ ተባለ” የሚል እንደሆነ ልንረዳው ይገባናል ፡፡
አስከትሎም
ይህ እንግዳችን ሁነኛው “ያለሃሰት በውነት የሚበልጥ ቃል የሚያንሰውን
ሥጋ ያከብረዋል” በማለት አንድ ወልድን ትንሽና ትልቅ አድርጎ ሲናገር እንሰማዋለን ፡፡ ተዋሕዶ ማለት ደግሞ “አንድነት” ማለት
ሲሆን ቃል ከሥጋ ጋር በአካል በባሕርይና በክብር አንድ መሆኑን የሚናገር ምሥጢር ነው ፡፡ ተዋሕዶ አንድነት ማት ሲሆን እሱም ቃልና
ሥጋ አንድ የሆኑበትን ነገር የሚያሥረዳን ረቂቅ ምሥጢር ነው ፡፡ ጮርቃው መናፍቅ “ዲ/ን ሁነኛው ተሾመ” ግን ለስሙ የተዋሕዶ አማኝ
ነኝ እያለ አንድ ወልድ መንፈቁን ትልቅ መንፈቁን ትንሽ እያደረገ እዲህ እየከፋፈለ ምንታዌን(ሁለትነትን ሲሰብክ ይገኛል ፡፡ ይህ
ሁለትነት ደግሞ ነንስጥሮስና የነ ልዮን ትምህርት ነው ፡፡
“ወእሉ
ኩሎሙ መናፍቃን መደልዋን ይትዌከፉ ስሕተቶ ለልዮን መስተቃርን ወሰመይዋ ሃይማኖተ ርትዕተ ዝኩ ዘረሰዮ ለክርስቶስ ክልዔቱ ህላዌያተ
ወከፈሎ ለዘኢይትከፈል ኀበ ክልዔቱ ክፍል ፤እነዚህ ሁሉ መናፍቃን ግብዞች ናቸው የተቃዋሚውን የልዮንን ክሕደትም ተቀብለው የቀናች
ሃይማኖት አሏት ፤ ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ ያደረገው የማይከፈለውን ወደ ሁለት የከፈለው ያ ልዮን ነው) ፤ ንሕነሰ ንትአመን ወንብል
በእንተ ትሥጉተ እግዚአብሔር ቃል አሐዱ ህላዌ ወአሐዱ አካል እንበለ ዉላጤ ወኢተፈልጦ ወኢሚጠት (እኛስ /እኛ ግን እግዚአብሔር
ቃል ሰው ስለመሆኑ ያለመለወጥ ያለመናወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው ብለን እናምናለን)ሃየ.አበው ዘዮሐንስ ምዕ
103 ቊ 10 እንዳለ ፤ አንድ ክርስቶስን መንፈቁን አክባሪ(አካለ ቃልን) መንፈቁን ከባሪ(አካለ ሥጋ በአካለ ቃል) አድርጎ ነጣጥሎ
ለያይቶ ሁለት አድጎ ሲናገር እንሰማዋለን ፤ አንዱን አካል ትልቅ (አካለ ቃልን) አንዱን አካል ትንሽ (አካለ ሥጋን) አድርጎ ነጣጥሎ
ለያይቶ የተዋሕዶ አማኝ ነኝ ብሎ ዓይኑን በጨው ታጥቦ መጣ ፡፡ የርጉም ልዮንን የሁለትነት ትምህርት የርትዕት ሃይማኖት ትምህርት
ነው ብሎ መጣ ፡፡ እኛ ግን ቃል ከሥጋ ጋር በማይረመር ተዋሕዶ በአካል በባሕርይ በግብር አንድ ሆኗልና ከበረ ስንልም ሆነ ታመመ
ስንል አምላክ በሰውነቱ ብለን እንናገራለን እንጅ ፤ ቃል ሥጋን አከበረ ብለን የምንነጣጥለው የምንከፋፍለው አይደለንም ፡፡ ከበረ
የተባለም በቃል ሳይን በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ከላይ ቅዱስ ቄርሎስ የተናገረው ቃል አሳማኝ መልእክት ነው ፡፡ ይኸውም “እንከ
ተቀብዐ ቅብዓ ሐሴት እመንፈስ ቅዱስ በኀበ እግዚአብሔር” ሲለን ከበረ ለመባሉ መደቡ አስረጅ ምስክሩ “ተቀብዐ ቅብዓ ሐሴት” የሚለው
ነው ፡፡ የአማርኛ ትርጉሙ የደስታ ዘይት ተቀብቷልና የሚል ነው ፤ ይህ የደስታ ዘይት የተባለ ማን ነው ያልን እንደሆነ ደግሞ መንፈስ
ቅዱስ ነውና “እመንፈስ ቅዱስ” ብሎ ገልጦ ነግሮናል ፡፡ እኒህ ጥቃቅን ንዑሳን ቀበሮ ካሮች ግን አካለ ቃል ነው ተቀባዒው አካለ
ሥጋ ነው እያሉ አንዱን ወልድ ግማሹን አክባሪ ግማሹን ከባሪ አድርገው ለሁለት ሲከፋፍሉት ይገኛሉ ፡፡ ቀባዒው አብ እንደሆነ ደግሞ
“በኀበ እግዚአብሔር አብ” ብሎ ነግሮናል ፤ የአማናዊው ቅብዓት እዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መገኛው አብ መሆኑን ሲያጠይቅ “ከአብ
በተገኘ የደስታ ዘይት(መንፈስ ቅዱስ) ተቀብቷልና ከብሯልና ክርስቶስ ተባለ” ብሎ ቁልጭ አድጎ ነግሮናል ፡፡ ካሮቹ ግን ከሊቅ እስከ
ደቂቅ ዓይናችንን ግንባር ያርገው ብለው ሲደናበሩ ይገኛሉ ፡፡ በሌላም አንቀጽ “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ
በኋይልም ቀባው” ብለዋል ቅዱሳን ሐዋርያት በሐዋ ምዕ 10 ቁ 38 ፡፡ ይህንንም እየለወጡ እያደሱት ይገኛሉ ፡፡ እና ወገኖቼ ምኑ
አጓጉቷችሁ ነው ሁለተኛ ለመጠመቅ የወሰናችሁ? ከልዮን የበለጠ ክሕደትን ታቅፎ ሲግታችሁ እንደምን ማመዛዘን ተሳናችሁ? እናንት የተማራችሁ
ተብላችሁ የምትቆጠሩ የመካነ አእምሮ ምሁራን ሆይ እዴት ማመዛዘንና ማሰላሰል አልችል አላችሁ? አንዱን ወልድ ሁለት አድርጎ እንደ
ልዮን የምንታዌን ትምህርት ሲሰብክላችሁ ልቡናችሁ እንዴት ተቀበለችው? እኔ እንጃ ግዑዛን ፍጥረታት እንኳን የነ ሁነኛው ንስጥሮሳዊ
ትምህርት የሚሰወራቸው አይመስለኝም ፡፡ ያም ሆነ ይህ እሱ “ተዋሕዶ ሃይማኖቴ” እያለ የሚናገረው በተዋሕዶ ከበረ በሚል ንስጥሮሳዊ
ትምህርት የተከበበው ርጉም ትምህርት ነውና ንቁ ፤ ከዚህ ላይ እንደ ማሳሰቢያ እነሁነኛው ስንኳን በምንታዌ ማን ይቅርና ራሹን ሃይማኖት
አልባ መሆን ፈጽሞም አለማመንም መብታው ነው ነገር ግን የራሳውን ክሕደት እደፈለጉ ማድረግ ሲገባቸው እኛ ቤት ገብተው የእኛን ማንነት
የሚንድ ነገር ሲናገሩ ሰምተን ስለምናምነው ነገር መልስ መስጠት ስለሚጠበቅብኝ ሰጠሁ እንጅ ስለ ካሮችና ስለ ሃይማኖታቸው ምንም
መናገር ፈልጌ እዳሆነ ልናውቀው ይገባል ፡፡ በቀጣዩ ክፍል ቤተ አይሁድ ካሮች ስለ መሢሐውያን ስለ እኛ የተረቷቸውን ተረት ተረቶች
በገለጸበት መልኩ ይዤ እመለሳለሁ እስከዚያው አምላክ ሠላሙን ያብዛልን ፣ ሳይማሩ መምሕር ሆነው ድጋሚ ተጠምቀው አረሚ ሆነው ሌላውን
አረሚ የሚያደርጉ ከሐድያንን ልቡና ይስጥልን ፡፡
ዛቲ
ሃይማኖት መሢሐዊት ዘትትአመን ባቲ ቤተክርስያን ቅድስት
ስብሐት
ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ስብሐት
እዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
ስብሐት
ለመስቀለ ክርስቶስ እጸ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ
ይቆየን
ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment