Monday, September 30, 2019

“የተቀብዐ እንግዶች” ክፍል አንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ !!!
==============+==============
“ሰላም ለክሙ ወጸጋ ለእግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ነአኵቶ ለእዚአብሔር አቡሁ ለእዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘልፈ በእንቲአክሙ፤ ወንጼሊ እምአመ ታፈቅርዎሙ ሰማዕነ ሃይማኖተክሙ በኢየሱስ ክርስቶስ ወዘከመ ታፈቅርዎሙ ለኵሎሙ ቅዱሳን ፤ በእንተ ተስፋክሙ ዘሥዩም ለክሙ በሰማያት ዘአቅደምክሙ ሰሚዐ በቃለጽድቅ ትምርተ ወንጌል
ሰላም ለእናንተ ይሁን የአባችን የእግዚአብሔር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይደርባችሁ ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔርን ዘወትር ስለ እናንተ እናመሰግነዋለን ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናችሁንና ቅዱሳንን ሁሉ መውደዳችሁን ከሰማንበት ጀምሮ እንጸልያለን ፡፡ የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል ትምርት አስቀድሞ ስለ ሰማችሁት በሰማያት ስለ ተዘጋጀላችሁ ስለተስፋችሁ” ቆላ ምዕ 1 ቁ 2-5 ፡፡

ክቡራን ወንድሞቼና እህቶቼ መሢሐውያን ኦርዶክሳውያን እንደምን አላችሁ?እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አደረሳችሁ ፡፡ በቸርነቱ ዓመታትን የሚያቀዳጅ አምላክ እድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍስሐ ያድለን ፡፡
እግዚአብሔር እደ ወደደ ዛሬ የምጽፍላችሁ መልእክቴ በባለፈው እደገለጽኩት “ዲ/ን ሁነኛው ተሾመ” የሚሉት አሁን አዋሳ አካባቢ የሚገኝ ግለሰብ በወርኃ ሰኔ 2011 ዓ.ም ለአር ምንጭ ዩኒቨርሲቲ “የማቅ ግቢ ጉባዔ ተማሪዎች” መማሪያ ብሎ “ትምርተ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ” በሚል ርዕስ በጻፋት ልዮናዊት ጦማሩ ኦርዶክሳዊ አስመስሎ ያስተማራትን ካሊካዊት ትምርት አንድ በአንድ እያነሳሁ መልሴን ማስቀመጥን ነው ፡፡ ሀንድአውቷ በአጠቃላይ 38 ገጽ ያላት ናት ፡፡ እናም የእ መልእክትና ምላሽ የሚያተኩረው ከገጽ 23 ላይ “ከብረ በተዋሕዶ” ከሚለው አርእስት ላይ ይሆናል ፡፡ እስከ ገጽ 21 ድረስ ባለው የምንለያይ ስላይደለ ፤ ከገጽ 21 እስከ 23 ድረስ ደግሞ “አባ እዝራ ሐዲስ” ቆማምጠው ቆራርጠው ከተረጎሙት ከድርሳነ ቄርሎስ የጠቀሰው ስነሆነ ለሰፊ ውይይት ይመቸን ዘንድ ከብረ በተዋሕዶ ካው ርዕስ ላይ እጀምራለሁ ፡፡
1ኛ‹‹‹‹‹‹ ወዳጄ ሁነኛው በተዋሕዶ ከበረ ለማለት የጠቀሰው ቃል “ወከመዝ ነአምሮ ከመ ለሊሁ ተቀብዓ ከመ ሥርዓተ ትስብዕት ወዳዕሙ ውእቱ ዘይቀብዕ ርዕሶ በመንፈሱ ባሕቲቱ ፤ ትርጉም፡- ሰው በመሆኑ በተዋሕዶ እንደከበረ እናውቀዋለን ግን በገዛ ሥልጣኑ ራሱን የሚያከብር እሱ ነው ፡፡ ስምዓት ክፍል 2 ቁ 14” የሚለውን ቃል ጠቅሶ ነው ፡፡
ከዚህ ከጹሁፉ ላይ እንደምንመለከተው በልሳነ ግዕዙ ላይ ወከመዝ ነአምሮ ከመ ለሊሁ ተቀብዓ ከመ ሥርዓተ ትስብእት” የሚል ሀሳብ ነው ፡፡ ይህንም በአትኩሮት ስናየው ተዋሕዶ የሚባል ስኳንስ ምሥጢር ሊኖረው ጥሬ ቃል እኳን የለበትም ፡፡ እነሱ ግን “ሰው እንደመኾኑ በተዋሕዶ እንደከበረ እናውቀዋለን ብለው ለእነሱ በሚመቻቸው መልኩ አዙረው አጣመው ተርጉመውታል ፡፡ እንዲህ እንደነሱ አድርጎ መተርጎም በነቢያት ፣ በሐዋርያትና በሊቃውንት ትምህርት ሳያድጉ በዘላልነት ያደጉ መናፍቃን የሚተረጉሙበት የክሕደት ካባ ውጤት መሆኑን ያሳየናል ፡፡ እንዴት ቢሉ ወከመዝ ከማለቱ በፊት “ እልእክተ ቅዱስ ቄርሎስ ኀበ ነገሥት ኀበ ነገሥት እስመ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ ወአኮ ብእሲ ዕሩቅ በባሕቲቱ ይቤ በእንቲአሁ ረድኡ በጥበብ ወበለብዎ ልብ (ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ በብቻው ያለ ዕቅ ብእሲ እንዳይደለ ሲያስረዳ ቅዱስ ቄርሎስ ወደ ነገሥት ከላከው መልእክት ደቀ መዝሙሩ በሃይማኖት በማስተዋል ተናገረ) እስመ ክርስቶስሰ ሐመ በሥጋ በፈቃዱ ወኢሐመ በህላዌ መለኮቱ ወለሊሁ ርሑቅ እምኩሉ ሕማም ወነኪር እኔሁ ሕማም (ክርስቶስ በፈቃዱ በሥጋ እንደታመመ ስለ እሱ ተናገረ ፤ እሱ ከሕማም ሁሉ የራቀ ነው ፤ ሕማምም ከእሱ የራቀ ነው ) ፤ ወባሕቱ ሐመ ይእዜ በሥጋሁ ባሕቲቱ ከመ ተብሕለ በእንቲአሁ ሐመ በሥጋ ከመ ሰብእ ፤ ወውእቱ ኢሐማሚ በህላዌሁ ከመ አምላክ ውእቱ (ዛሬ ግን በሥጋ ብቻ ታመመ ሰው እደመኾኑ በሥጋ ታመመ ፤ አምላክ እደመሆኑ በባሕ ሕማም የሌለበት ነው)” የሚል ሀሳብ አለ ፡፡  አሁን እንደምንመለከተው አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርየ መለኮቱ ሕማም የሌለበት ሲሆን በመጽሐፍ ሐመ በሥጋ ተብሎ እንደተጻፈለት በሥጋ ታመመ በመለኮት ግን አልታመመም የሚል ነው ፡፡ ከዚህ ይቀጥልና “ወከመዝ ነአምሮ ከመ ለሊሁ ተቀብዓ ከመ ሥርዓተ ትስብዕት ወዳዕሙ ውእቱ ዘይቀብዕ ርዕሶ በመንፈሱ ባሕቲቱ” የሚል በግዕዝ የተጻፈ ቃል አለ ፡፡ እኒህ ወሮ በላ መናፍቃን ግዕዝ የሚማር ትውልድ ሲጠፋላቸው ማንም ትርጓሜውን የሚያውቀው ስለሌለላቸው እንደፈለጉ ይፈነጩበታል ፡፡ እመብርሃንን ይህ እየገለበጡ መተርጎም በእኛ ቤት ቢሆን ኖሮ በቁማችን ይሰቅሉን ነበር ፡፡ ወደ ሀሳቤ ልመለስና “ወከመዝ” የሚለው ልሳነ ግእዝ ወደ አማርኛ ሲመለስ “እንደዚህም ሁሉ” የሚል ትርጉም አለው ፡፡ አስተውሉ እንደዚህም ሁሉ የተባለው ከላይ ያነሳነው ሀሳብ እሱም በባሕርየ መለኮቱ ሕማም የሌለበት እሱ ሕማም ገንዘቡ የሆነ ሥጋን ተዋሕዶ ገንዘቡ አድርጓልና ዛሬ ግን ሰው በመሆኑ “ሐመ በሥጋ ባሕቲቱ” እንደተባለለት ሁሉ  ሰው በመሆኑ እንደተቀባ እንደከበረ እናውቀዋለን ሲል ነው ፡፡ ካሮች ግን እንደተናገርኩት ግዕዝን የሚማረውና የሚያውቀው ምእመን ጥቂት በመሆኑ “ተቀብዐ” የሚለውን “በተዋሕዶ ከበረ” ብለው ለውጠው አለ አገባቡ አለ ምሥጢሩ ሲተረጉሙት ይስተዋላሉ ፡፡ ዳሩ ግን ተቀብዐ ማለት ከበረ ማለት እንጅ ተዋሐደ ማለት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባላን ፡፡ “ሰው እንደመሆኑ በሥጋ ታመመ ፣ ሞተመባሉ ሕማምና ሞት ለሰው ልጅ ገንዘቦቹ ናቸውና እርሱም በእውነት ያለሐሰት ሰው ሆኗልና ሕማሙ ፣ ሞቱ ከሰው ልጅ ሕማም ሞት አንድነት ስላለው ከሰው ጋር በንጽጽር ቀረበልን ፡፡ ሰው እንደመኾኑ በተዋሕዶ እንደከበረ እናውቀዋለን የሚለው የፈጠራ ሥራ ግን ትርጓሜ አልባ ሆኖ እናገኘዋን ፡፡ ለምን ቢሉ ፤ ሰው የሆነ ሁሉ በተዋሕዶ የከበረ የለም ይልቁንም በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ እንጅ ፡፡ ስለሆነም ወከመዝ ነአምሮ ከመ ለሊሁ ተቀብዓ ከመ ሥርዓተ ትስብእት (ሰው በመሆኑ እርሱ እንደከበረ እናውቀዋልን ተብሎ ይተረጐማል እንጂ አለአገባቡ አለመንገዱ ይፈቱት ዘንድ አይገባም ፡፡ እነዚህ ምሥጢር የሚያጠፉ ከሐዲዎች በክሕደታቸው ቀጥለው ወለሊሁ ውእቱ ዘይቀብእ ርእሶ በመንፈሱ ባሕቲቱየሚለውንግን በገዛ ሥልጣኑ ራሱን የሚያከብር እሱ ነው ብለው አበላሽተው ተርጉመውታል ፡፡ ይሁን እንጅ በዚህ ጠማማ ትርጉማቸው ዓረፍተ ነገር ውሰጥ “በገዛ ሥልጣኑ” ሲባል ይህ የገዛ ሥልጣኑከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን የተለየ ነውን? ወይስ እንዴት ነው? ፡፡ ሥላሴ በሥልጣን አንድ ናቸውና ይህ ሥልጣንስ አካላዊ ነው ወይስ ዝርው ነው? ብለን ብንጠይቃቸው አስተካክለው አይነግሩንም ፡፡  እነሱ በገዛ ሥልጣኑ ብለው የተረጎሙት በመንፈሱ የሚለውን ቃል ነው ፡፡ መንፈስ ብሎ ሥልጣን የሚል የሰዋስው መደብም አስረጅ ምስክርም የለም ፡፡ ነገር ግንበመንፈሱየሚለው ቃል የአብንና የወልድን ሕይወታቸውን መንፈስ ቅዱስን ይወክላል እንጂ ለወልድ ብቻ በገዛ ሥልጣኑተብሎ የተለየ ሥልጣን እንዳለው መናገርና ማስተማር እንደ አርጌንስ ወልድ ከአብ ያንሳል እንደ መቅዶሰንዮስ መንፈስ ቅዱስ ከወልድ ያንሳልብሎ መካድ ነው ፡፡ ስለሆነም ሰው በመሆኑ እርሱ እንደከበረ እናውቀዋልን ፤ ነገር ግን ሕይወቱ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ራሱን የሚያከብር እሱ ነው ተብሎ መተርጎም የሚገባ ነው እንላለን ፡፡ ለምን ቢሉ ፤ እንደሰውነቱ ይከብራልና እንደአምላክነቱ ከአባቱና ከሕይወቱ ጋር ባንድነት ራሱን ያከብራልና እንዲህ እንመን እንዲህም እንታመን ፡፡ በዚህም በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ብለን እናምናለን እጅ “በተዋሕዶ ከበረ” ብለን ንሥጥሮሳዊ ሃይማኖትን አንሰብክም ብላችሁ ንገሩት ለዚያ ለዘላኑ “ዲያቆን ሁነኛው” ፡፡
ምስጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ክብር ለቅድስት ድንግል
ክብር ለክቡር መስቀል
ይቆየን
በጥቂት በጥቂቱ ይቀጥላል ፡፡

No comments:

Post a Comment