Monday, September 30, 2019

“የተቀብዐ እንግዶች” ክፍል አንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ !!!
==============+==============
“ሰላም ለክሙ ወጸጋ ለእግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ነአኵቶ ለእዚአብሔር አቡሁ ለእዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘልፈ በእንቲአክሙ፤ ወንጼሊ እምአመ ታፈቅርዎሙ ሰማዕነ ሃይማኖተክሙ በኢየሱስ ክርስቶስ ወዘከመ ታፈቅርዎሙ ለኵሎሙ ቅዱሳን ፤ በእንተ ተስፋክሙ ዘሥዩም ለክሙ በሰማያት ዘአቅደምክሙ ሰሚዐ በቃለጽድቅ ትምርተ ወንጌል
ሰላም ለእናንተ ይሁን የአባችን የእግዚአብሔር የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይደርባችሁ ፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባቱ እግዚአብሔርን ዘወትር ስለ እናንተ እናመሰግነዋለን ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናችሁንና ቅዱሳንን ሁሉ መውደዳችሁን ከሰማንበት ጀምሮ እንጸልያለን ፡፡ የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል ትምርት አስቀድሞ ስለ ሰማችሁት በሰማያት ስለ ተዘጋጀላችሁ ስለተስፋችሁ” ቆላ ምዕ 1 ቁ 2-5 ፡፡

Monday, September 23, 2019

ክፍል 3

ቀመር
ቀመር ማለት ማስላት ፣ መቁጠር ማውጣት ማለት ነው ፡፡ ቀመርም ጥንታትን መሠረት ያደረገ ነው ፡፡ ጥንት ማለትም ለዘመን መቆጠር መሠረት የሆነ ማለት ነው ወይም መነሻ መጀመሪያ ማለት ነው ፡፡ እነዚህም ሦስት ናቸው ፡፡ ምን ምን ቢሉ ፤ አንድ ዓለም የተፈጠረችበትን ቀን ዕለት እሑድ ሲሆን ፤ ይኸውም ጥንተ ዕለት ይባላል ፡፡ አንድም አትክልት ዕፅዋት ተፈጥረው ዕድሜ የተቆጠረላቸውን ቀን ዕለት ሠሉስ ሲሆን ፤ ይኸውም ጥንተ ቀመር ይባላል ፡፡ አንድም ፀሐይ ፣ ጨረቃ ከዋክብት የተፈጠሩበት ዕድሜም መቆጠር የተጀመረባቸውን ቀን ዕለት ረቡዕ ሲሆን ፤ ይኸውም ጥንት ዖን ይባላል ፡፡ ዖን ማለት ብርሃን ማለት ነው ፡፡ በዚህ መሠረት መታሰቢያ ቀመርን ለመስፈረያ ወይም ለመቁጠሪያ የሚያገለግሉት ሰባት(፯) ናቸው ፡፡ ከምን አገኘነው ቢሉ ፤ አቡሻሕር “ወሤሞ በመካነ ቀዳማይ ዕለታት ዓመት ወርኃዊት ፤ ወበመካነ ዕለተ ኍልቊ ኬክሮስ ፤ ወበመካነ ኬክሮስ ኍልቊ ካልዒት ፤ ወበመካነ ካልዒት ኍልቊ ሣልሲት ፤ ወበመካነ ሣልሲት ኍልቊ ራብዒት ፤ ወበመካነ ራብዒት ኍልቊ ኃምሲት ፤ ወበመካነ ኃምሲት ኍልቊ ሳድሲት ብሎዋልና ፤ ይኸን መሠረት አድርገን ቀመርን የምንሰፍርባቸው 7 ናቸው ፡፡ 

ክፍል 1

ክፍል 1
ባሕረ ሐሳብ
ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው ፡፡ እንዴት ቢሉ ፤ ባሕር ዘመን ፣ የተቆጠረ ተብሎ ይተረጎማልና ፤ ይህስ ከምን እናገኘዋለን ቢሉ ፤ ዕዝራ ሱቱኤል ተናግሮታል ፡፡ ይኸውም “ይህ ዓለም በሚዛን ተመዝኗልና ፤ ባሕሩንም በመስፈሪያ ሰፍሮታልና ፤ የተሰጠውንም መስፈርት እስኪፈፀም ድረስ ዝም ይላል ፤ አይነቃምም (ምዕ 2 ቊ "7)” በማለት ባሕር የተቆጠረ ፤ ዓለምም የተመዘነች ፤ የተለካች መሆንዋን እግዚአብሔር በነቢያት አድሮ ገልፆልናል ፡፡
ባሕርን በመስፈሪያ ቆጥሮታል ካልን መስፈሪያውንስ ለማን ገለጸው ቢሉ ፤ መቁጠሪያ ዘመንንስ በሱባኤ ፣ በኢዮቤልዩ እንዲቆጥር ለአዳም (ሱባኤ አዳም) ፤ መስፈሪያንም ለሄኖክ ሰጥቶታል ፡፡ ሐሳብስ ማን ቁጥር አለው ቢሉ ፤ ቅዱስ ዳዊት ነው ፡፡ ምን አለው ቢሉ ፤ “ብፁዓን እለ ተኀድገ ሎሙ ኃጢአቶሙ ፤ ወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኵሎ ጌጋዮሙ ፤ ብፁዕ ብእሲ ዘኢኈለቈ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጥአቱ (ኀጥአታቸው ይቅር የተባለላቸው ብፁዓን ናቸው ፤ በደላቸውንም ኹሉ ያልቆጠረባቸው ፤ እግዚአብሔርም ኃጢአቱን ያልቆጠረበት ሰው ብፁዕ ነው” እንዳለ (መዝ " ቊ -2) ፡፡ ስለዚህም ባሕር ሐሳብ ማለት ቀድሞ የነበረ ፣ አሁንም ያለ ፣ ለወደፊትም የሚኖር ዘለዓለማዊ እግዚአብሔር በዚች ባለንባት ዓለም ሌሊቱንና ቀኑን እያፈራረቀ የሚመግብ እግዚአብሔር መሆኑን በቁጥር ፣ በስፍር መዝኖ የሚያስረዳ ማለት ነው ፡፡
ባሕር ሐሳብ በስንት መንገድ እናየዋለን እንተ