Wednesday, March 6, 2019

ውሉደ ይሁዳ (ክፍል ሁለት)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አምላክ አሜን!
==========================================
በባለፈው በክፍል አንድ መልእቴ “ዐራት ዓይናው” አባ “ሰሎሞን ዳዊት” “ቅባትን በእሳት” የምትል የጨዋ ንግግርን በተናሩባት ወቅት እሳትን በእሳት የሚል ሀሳብን ማንሳታቸውንና ዐራት ዓይናው አንድ ዓይና እንኳን የማያስብላቸውን ነገር መናገራቸውንና እንደይሁዳ አምላካቸው መንፈስ ቅዱስን እየሰደቡ በ30 ብር እየቸበቸቡ የሚገኙ መሆናቸውን በሐተታ አንስቼ መዘከሬ ይታወሳል ፡፡ እነሆ በቀጠሮየ መሠረት ዛሬ ደግሞ በመጽሐፏ ውስጥ ብዙውን ስፍራ የያዘው “ተዋሕዶ ሃይማኖታችን” የሚል ቃል አንስቼ እንድንወያይ አምላክ በፈቀደልን መጠን ይህችን ጽሁፍ እንካችሁ ብያለሁ፡፡  
ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ በአምላኩ ተገብቶ “አነ ፈጣሪሆሙ ለእሉ ፍጡራን ፤ አነ ገባሆሙ ለእሉ ግቡራን) ብሎ በመካድ አምላኩን በመገዳደሩ ከክብሩ ተዋርዶ ከመላእክተ ብርሃን ወገን እንደተለየ መጽሐፈ እክሲማሮስ ይናገራል ፡፡ እንደዚህም ሁሉ የዛሬ ዘመን ከንቱ ትውልድ አምላክ ሰው የሆነበትን ፣ ሰውም አምላክ የሆነበትን ምሥጢር ሳይረዳ ሳይመለከት በአምላኩ ተገብቶ “እኔ ተዋሕዶው ፣ እኛ ተዋሕዶዎች ፣ እኛ የተዋሕዶ ልጆች ፣ ዘራፍ የተዋሕዶ ልጆች…..ወ.ዘ.ተ” እያለ ከንቱ ንግግርን ሲናገር መስማት የተለመደ ሆኗል ፡፡
 በተለይ ደግሞ ምሥጢርና ሃይማኖት ያለየውና በማን መጠራት እንዳለበት እንኳን ያላስተዋው መጣት “ዘራፍ የተዋሕዶ ልጅ” እያለ ሲፎክር ይስተዋላል :: ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱሳን ብላ የሰየመቻቸው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ግን አንዳቸውም “እኛ ተዋሕዶዎች ፣ እኛ የተዋሕዶ ልጆች” እያሉ የተናገሩ አይደሉም ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ፤ ከቀሌምንጦስ እስከ ሥርዓተ ጽዮን ብንፈልግ አንዲት ቦታ ላይ እኛ ተዋሕዶዎች ያሉ አባቶች ነቢያት ፣ አባቶች ሐዋርያት ፣ አባቶች ሊቃውንት ፣ አባቶች መነኰሳት የሉም ፡፡ 

እንግዲህ ሳይዘራ የበቀለ ርጉም ትውልድ ይሉሃል እንደዚህ ያለው ነው ፡፡ ከመጽሐፍ አላገኙት ፣ ከአባቶች አልተማሩት ከየት አምጥተው “እኛ ተዋሕዶዎች” እንደሚሉ ጥያቄው ለራሳቸው ይሁንና ፤ ለአሁኑ የውይይታችን አጀንዳ የሚሆነው የ “ሊቀ ሊቃውንት” ሰሎሞን ዳዊት “ተዋሕዶ ሃይማኖታችን” የሚለው ንግግር ይሆናል ፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ተዋሕዶዎች” ተብለው የተጠሩ የሉም ፤ እንደዚሁም ሁሉም ቅዱሳን አባቻችን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስንመለከታቸው “ተዋሕዶ ሃይማኖታችን” ብሎ የተናገረ የለም ፡፡  ለውይይታችን ዓቢይ መነሻ ይሆነን ዘንድ የሰውየውን አንድ ሁለት ሀሳቦችን ጠቀስ አድጌ ለማንሳት እወዳለሁ፡፡  


በዚህ ክፍል በእይታችን መነጽር ውስጥ የምንመለከታው የሊቀ ሊቃውንት ሰሎሞን ዳዊት በፈጠራቸው እንዲህ ይላል ፡-
1ኛ‹‹‹‹‹‹ ““ተዋሕዶ ሃይማኖት ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በልበ ሥላሴ ተመክራ ተዘክራ ተሰፍራ ተቆጥራ ተወስና የኖረች…” ገጽ 1” ለመጀመሪያ ጊዜ  ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ያስተማረ የነገረ ያበሰረ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው” ገጽ 2 ፤ “ተዋሕዶ ሃይማኖት በፍጡር ሳይሆን በፈጣሪ….ለቅድስት ድንግልማርያም የተነገረች በእሷ የተፈጸመች እግዚአብሔራዊት ፣መልአካዊት ፣ ትንቢታዊት ፣ ወንጌላዊት ፣ ማርያማዊት ሃይማኖት መሆንዋን ነው” ገጽ 3 ፤ “ከተዋሕዶ ሃይማኖት መገለጫዎች አንዱ የሆነውን ጾም በገዳመ ቆሮንቶስ በጀመረ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት አብረው ነበሩ ማቴ 4-11”›ገጽ4›››››››ብለው ጽፈዋል፡፡

 እሳቸው እንዲህ ቢቀባጥሩም መጽሐፍ ቅዱስ “ተዋሕዶ ሃይማኖት” የሚል አንድም አንቀጽ የለም ፡፡ ቅዱሳን አበው ከተናገሩት “ተዋሕዶ” የሚባል ሃይማኖትም እደሌላቸውና እነሱም እኛ ተዋሕዶዎች ብለዉ የሚናገሩ እዳይደሉ ለማስቀመጥ እወዳለሁ ፡፡
ሀ‹‹‹‹ እኛ  ኦርቶዶክሳውያን  ግን  እግዚአብሔር  ቃል  ፍጹም  ሥጋን  ነሥቶ  አንድ  አካል ፣ አንድ  ባሕርይ  በመሆኑም ፤ እሱን  ተዋሕዶ  ከእመቤታችን  እንደተወለደ  እናምናለን”  እንዳለ  ቅዱስ  አባ  ሱኑትዩ  (በሃይ.አበው  ምዕ 110  ክ  2  ቁ  36) ፤
ለ. “  ኛ  ኦርቶዶክሳውያን  ግን  ዛሬ  በእውነት  ሰው  የሆነው  አምላክ  በባሕርየ  መለኮት  ከአብ  ጋር  አንድ  ነው ፤ በሥጋ  ባሕርይም  እኛን  ይመስለናል  ብለን  እንናገራለን”  እንዳለ  ቅዱስ  አባ  ሱኑትዩ  (ሃይ.አበው  ምዕ 110  ክ  2  ቁ 46) ፤
ሐ. “ርቶዶክሳውያን  ምዕመናን  በሰዎች  የማይወሰን ፤ አምላክ ፤ በድንግል  ማኅፀን  እንደተወሰነ  እሱ  ክብር  የሌለውን  ሥጋ  በመዋሐዱ ፤ እኛ  እንከብር  ዘንድ  ክብር  ያለው  እሱ ፤ ክብር  የሌለው  ሥጋን  እንደተዋሐደ  እንዲህ  ፈጽመው  አምነው  ይናገሩ  ዘንድ  ይገባል”  እንዳለ  ቅዱስ  አባ  ሱኑትዩ  (ሃይ.አበው  ምዕ 110  ክ  2  ቁ  52) ፤
መ. “ሁንም  የመናፍቃንን  ነገራቸውን  ሁሉ ፤ መለያየታቸውንም  ኦርቶዶክሳዊት  ሃይማኖትን  የካደውን  ሁሉ  ፈጽመን  ከእኛ  እናርቅ”  እንዳለ  ቅዱስ  አባ  ሱኑትዩ  (ሃይ.አበው  ምዕ 110  ክ  2 ቁ 62) ፤
ሠ. “እኛ  ኦርቶዶክሳውያን  ግን  ባሕርይ  አንድ  ሲሆን  በሦስቱም  አካላት ፣ በሦስቱም  ገጻት  በእውነት  እናምናለን”  እንዳለ  ቅዱስ  እክርስቶዶሎስ  (ሃይ.አበው  ምዕ 112  ክ 1  ቁ  6)
ረ. “እኛ  ኦርቶዶክሳውያን  ዐዋቂዎች  ነን  ሲሉ  ልብ ፣ ዕውቀት  የሌላቸው  ሰዎች  እንደተናገሩ  ከተዋሕዶ  በኋላ  ለጌታችን  ለኢየሱስ  ክርስቶስ  ሁለት  ባሕርያት  አሉት  አንልም”  እንዳለ  ቅዱስ  እክርስቶዶሎስ  (ሃይ.አበው  ምዕ 112  ክ  1  ቁ 13)
ሰ. “ዋርያት  በተገኘ  ሹመት  ትምህርትህ  ክቡራን  በሚሆኑ  በሁለቱ  መናብርት  መካከል  ታወቀ  እነዚህም  የከበረች  የጴጥሮስ  መንበርና  (አንጾኪያ) ፤ ኦርቶዶክሳዊት  ሃይማኖታችንን  የሚያስተምር  የማርቆስ  መንበር  (እስክንድርያ)  ናቸው”  እንዳለ  ቅዱስ  እክርስቶዶሎስ  (ሃይ.አበው  ምዕ 112  ክ 1  ቁ  13)
ቀ. “  ኦርቶዶክሳውያን  ግን  ከአባቱ  ጋር  አንድ  የሚሆን  እሱ  ራሱ  የአብ  ቃል ፤ ዘር  ምክንያት  ሳይሆነው  ከእመቤታችን  ከነፍሷ  ነፍስን  ነሥቶ  የባሕርይ  አምላክ  የሆነውን  ሥጋውን  ሊክስበት  ፈጥሮ  ተዋሐደ እንዳለ  ቅዱስ  እክርስቶዶሎስ  (ሃይ.አበው  ምዕ 112  ክ  2 ቁ 20
በ. “ርቶዶክሳውያን  እኛ  ግን ፤ እነዚህን  የረከሱ  እምነቶችን  ከእኛ  እናርቃለን ፤ የማይለይ  የማይከፈል  የማይቀላቀል  ተዋሕዶን  እናምናለን እንዳለ  ቅዱስ  እክርስቶዶሎስ  (ሃይ.አበው  ምዕ  113  ክ 1  ቁ  19)
ተ. “ለእኛ  ለክርስቲያን  ግን  ስለአብ  ስለወልድ  ስለመንፈስ  ቅዱስ  እንደ  ሐዋርያት  ሥርዓት  የምናምነው  ሃይማኖታችን ፤ በእውነት  አንድ  መለኮት ፣ አንድ  ምስጋና ፣ አንድ  ስግደት ፣ አንድ  ክብር ፣ አንዲት  ሥልጣን ፣ አንድ  ጌትነት ፣ አንዲት  መሻት ፣ አንድ  ፈቃድ ፣ የአብ ፣ የወልድ ፣ የመንፈስ  ቅዱስ  ገንዘብ  ነው እንዳለ  ቅዱስ  ዮልዮስ  (ሃይ.አበው  ምዕ 118  ክ  4  ቁ  4
ነ. “ነሰ  መሢሓውያን  ኢንፈልጦ  ለእግዚአብሔር  ቃል  እምትስብእቱ  አላ  ክመ  አሐዱ  ውእቱ (እኛ  መሢሓውያን  ግን  እግዚአብሔር  ቃልን  ከተዋሐደው  ሥጋ  አንለየውም  እርሱ  አንድ  ነው  እንጅ)”  እንዳለ  ቅዱስ  ጎርጎርዮስ  ነባቤ  መለኮት  (ሃይ.አበው  ምዕ 120  ክ  1  ቁ  2)  
ኀ. “  ክርስቶሳውያን  ግን  በተዋሕዶ    የኾነው  አምላክ  በእውነት  በባሕርዩ  አንድ  ነው ፤ አካሉ  አንድ  ነው ፤ ገጹ  አንድ  ነው ፤ ነፍስም  ሥጋም  አለው  ልንል  ይገባናል ፤ ሁለት  ባሕርያት ፣ ሁለት  አካላት ፣ ሁለት  አምላክ ፣ ነፍስና  ሥጋም  ያለው  ስለሆነም  ሁለት  ሰው  አይባልም”  እንዳለ  ቅዱስ  ጎርጎርዮስ  ነባቤ  መለኮት  (ሃይ.አበው  ምዕ  120  ክ  5  ቁ  8)
አ. “ርቶዶክሳዊት  ቤተ  ክርስቲያን  የሚሰዋው  የክርስቶስ  ሥጋው  ምትሐት  ነው  እንጅ  እውነተኛ  ሥጋው  አይደለም  የሚል ፤ በእውነት  የእግዚአብሔር  ሥጋ  ነው ፤ ምትሐትም  አይደለም ፤ እርሱ  በሥጋ  የሚታመም  በመለኮት  ግን  ሕማም  የሌለበት  ቅዱስ  ነው”  እንዳለ  ቅዱስ  ጎርጎርዮስ  ነባቤ  መለኮት  (ሃይ.አበው  ምዕ  120  ክ  12  ቁ  16)
ከ. “  ክርስቲያን  ግን  እንደተረዳነው  ቃል  ሥጋ  ኾኗል”  እንዳለ  ቅዱስ  ቄርሎስ  (ሃይ.አበው  ምዕ  121  ክ  1  ቁ 40
ይህንን ለአብነት አነሳን እንጅ በእጅጉ ብዙ ምሥክሮች አሉ ፤ ታዲያ ሊቁም ደቂቁም ዝም ብሎ የሚዋዥቅበት የምንታዌ ትምህርት መደበቂያ ሲያጣ “እኛ ተዋሕዶዎች” ፤ “ሃይማኖታችን ተዋሕዶ” እያሉ ፈጠራን ቢጽፉ የራሳው ክሕደት እየበዛ ይሄዳል እንጅ እውነትን ከቶ ሊያገኟት የሚጓዙ አይደሉም፡፡

 በየትኘውም ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በምትመራበት ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ “ተዋሕዶ ሃይማኖት” የሚል አንድም የለም ብቻ ምሥጢር እያለ ያስተምረናል እንጅ ፡፡

ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ክብር ለቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ
ክብር ለመስቀለ ክርስቶስ እጸ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ ይቆየን

ይቀጥላል ..........

,

No comments:

Post a Comment