Saturday, January 12, 2019

ሲያምኑ ፡ ግማሽ ፡ ሲተረጉሙ ፡ ዳሽ


በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አሐዱ ፡ አምላክ ሲያምኑ ፡ ግማሽ ፡ ሲተረጉሙ ፡ ዳሽ ፡ ይህች ፡ ብሂል ፡ “የነሲብ ፡ ትርጓሜ” ፡ ብለን ፡ እንመለከታለን ፡፡

===============================================
በኢትዮጵያ ፡ ኦርዶክሳዊት ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ውስጥ ፡ የሚገኙ ፡ “በተዋሕዶ ፡ ከበረ ፡ ወልድ ፡ ቅብዕ” ፡ ብለው ፡ የሚያምኑ ፡ ልዮናውያን ፤ የወልደ ፡ እግዚአብሔርን ፡ አምላክነት ፡ እናምናለን ፤ ተዋሕዶንም ፡ እንከተላን ፣ ይባስ ፡ ብሎም ፡ ስማችን ፡ ተዋሕዶ ፡ ነው ፡ ሲሉ ፡ ይደመጣሉ ፡፡ እነኝህ ፡ ሰዎች ፡ ተዋሕዶን ፡ እናምናለን ፡ እያሉ ፡ በተዋሕዶ ፡ ከበረ ፡ ወልድ ፡ ቅብዕ ፡ ማለትን ፡ ዘንቀው ፡ ቀላቅለው ፡ ያስተምራሉ ፡ ይደናበራሉም፡፡ ያም ፡ ሆነ ፡ ይህ ፡ ተዋሕዶና ፡ በተዋሕዶ ፡ ከበረ ፡ በመጻሕት ፡ ምሥጢርም ፡ ይሁን ፡ በቋንቋ ፡ ሕግ ፡ አንድ ፡ አይደሉም ፡ ልዩነታቸውም ፡ የሰማይና ፡ የምድር ፡ ያህል ፡ ነው፡፡ 
እነዚህ ፡ ሰዎች ፡ ተዋሕዶን ፡ እናምናለን ፤ “እንቲአሁ ፡ ለቃል ፡ ኮነ ፡ ለሥጋ ፤ ወእንቲአሁ ፡ ለሥጋ ፡ ኮነ ፡ ለቃል” ፡ እናምናለን ፡ ይላሉ፡፡ ነገር ፡ ግን ፡ እስከ ፡ አሁን ፡ እንደምንመለከታቸው ፡ እንቲአሁ ፡ ለቃል ፡ ኮነ ፡ ለሥጋን ፡ ብቻ ፡ የሚያምኑ ፡ ናቸው ፤ እንቲአሁ ፡ ለሥጋ ፡ ኮነ ፡ ለቃል ፡ ማለትን ፡ አያምኑም ፡፡ በዚህም ፡ “ሲያምኑ ፡ ግማሽ” ፡ ብያቸዋለሁ፡፡ እሆም ፡ በዚህ ፡ አንጻር(በእንቲአሁ) ፡ የተነገረውን ፡ “ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ--አንተ ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ዛሬ ፡ ወለድኩህ” ፡ ብሎ ፡ ክቡር ፡ ዳዊት ፡ በመዝ 2 ፡ ቁ ፡ 7 ፤ የሚለውን ፡ ኃይለ ፡ ቃል ፤ “ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ--እኔ ፡ ዛሬ ፡ ወለድኩህ” ፡ የሚለውን ፡ ሲተረጉሙ ፤ አልወለደውም ፤ በቃል ፡ ልጅነት ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ አለው ፡ እንጅ ፡ እያሉ ፡ ይተረጉማሉ ፡፡ በዚህም ፡ “ሲተረጉሙ ፡ ዳሽ” ፡ ብያቸዋለሁ፡፡ የዚህ ፡ መዝሙርም ፡ ትክክለኛ ፡ ትርጓሜ ፤ ቃል ፡ ልጅነት ፡ ያለው ፡ ሲሆን ፡ ሥጋ ፡ ልጅነት ፡ የለውም ፡ ነበር ፤ እነሆም ፡ ሁለቱ ፡ ሲዋሐዱ ፡ “እንቲአሁ ፡ ለቃል ፡ ኮነ ፡ ለሥጋ --የሥጋ ፡ ገንዘብ ፡ ለቃል ፡ ሆነ” ፡ በሚለው ፡ ሚዛን ፡ “ወልድየ ፡ አንተ--አንተ ፡ ልጄ ፡ ነህ” ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ያስረዳል ፡ ይህም ፡ ቅድመ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቃል ፡ ልጅ ፡ ነበርና ፡ በቃል ፡ ገንዘብ ፡ ሥግው ፡ ቃልን ፡ አንተ ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ አለው ፡፡ እሆም ፡ “እንቲአሁ ፡ ለሥጋ ፡ ኮነ ፡ ለቃል--የሥጋ ፡ ገንዘብ ፡ ለቃል ፡ ሆነ” ፡ ባለው ፡ “ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ--እኔ ፡ ዛሬ ፡ ወለድኩህ” ፡ በማለት ፡ ሥጋ ፡ ልጅነት ፡ የለውም ፡ ነበርና ፡ በሥጋ ፡ ርስት ፡ “እኔ ፡ ዛሬ ፡ ወለድኩህ” ፡ ብሎ ፡ ለሥግው ፡ ቃል ፡ ቁልጭ ፡ አድርጎ ፡ ተናገራት ፡፡ ልዮናውያን ፡ ግን ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ የተባለ ፡ ለቃል ፣ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ የተባለ ፡ ለሥጋ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እያሉ ፡ አንድ ፡ ወልድን ፡ ለሁለት ፡ ይከፋፍላሉ ፡ ይዘነጣጥላሉ፡፡ ወደዱም ፡ ጠሉም ፡ እንደ ፡ ፈሪሳውያን ፡ አይሁድ ፡ የክሕደት ፡ ማዕበል ፡ ጠራርጎ ፡ እከሚወስዳቸው ፡ ድረስ ፡ እውነትን ፡ እንነግራዋለን ፡፡ ጆሮ ፡ ካላቸው ፡ ይሰማሉ ፡ ጆሮ ፡ ከሌላቸው ፡ ደግሞ ፡ እንደ ፡ ፈሪሳውያን ፡ አንሰማም ፡ ብለው ፡ መንኮታኮት ፡ መብታቸው ፡ ነው ፡፡ “ንሕነሰ ፡ ንነግር ፡ ወኢንዘብጥ--እኛስ ፡ እንናገራለን ፡ እንጅ ፡ አንማታም” ፡ እንዳሉ ፡ አበው ፡ መናገራችን ፡ እስከ ፡ ሕይወታችን ፡ ሕቅታ ፡ ድረስ ፡ ይቀጥላል፡፡ 

እናንት ፡ በልዮን ፡ ስብከት ፡ አምናችሁ ፡ ድጋሚ ፡ የምትጠመቁ ፡ ሰዎች ፤ ዛሬ ፡ በተረት ፡ ተረትና ፡ በነሲብ ፡ ትርጓሜ ፡ ከካዳችሁ ፤ ነገ ፡ ጊዜ ፡ የሚሰጠው ፡ ሐሳዊ ፡ መሢሕ ፡ ፀሐይን ፡ በአንድ ፡ እጁ ፤ ጨረቃን ፡ በአንድ ፡ እጁ ፡ ይዞ ፡ ሲመጣ ፡ ደግሞ ፡ መጥባሕትን ፡ ትታችሁ ፡ ያንን ፡ የምትከተሉ ፡ ሳትሆኑ ፡ አትቀሩም፡፡ ድጋሚ ፡ ለመጠመቅ ፡ እንደምትሯሯጡት ፤ እስኪ ፡ ሱባዔ ፡ ለመግባት ፣ ምሥጢረ ፡ መጻሕፍትን ፡ ለመረዳት ፣ ማነታሁንና ፡ ምንነታሁን ፡ ለማወቅ ፡ ሩጡ ፣ ምግባር ፡ ትሩፋት ፡ ለመሥራት ፡ ተፋጠኑ! ፤ እስኪ ፡ ስለማንነታሁ ፡ ለመረዳት ፡ በመጀመሪያ ፡ የክርስትናውን ፡ ሕግ ፡ አጥኑ! ፤ 
ውድ ፡ አንባብያን ፡ ኦርቶዶክሳውያን ፡ ሁላችሁም ፡ እንደምን ፡ ሠነበታችሁ ፤ ይህች ፡ የዛሬዋ ፡ መልዕክቴ ፡ የምታተኩረው ፤ መልካሙ ፡ በየነ ፡ የሚሉት ፡ ግለሰብ ፤ “፫.፪.፩. የጌታ ልደታት” ፡ በሚል ፡ ርእስ ፡ በጻፋት ፡ የነሲብ ፡ ትርጓሜ ፡ ላይ ፡ ነው ፡፡ ነሲብ ፡ ያልኳት ፡ ሰውየው ፡ በራሱ ፡ ፈቃድ ፡ መጻሕፍትን ፡ እየገለበጠ ፡ በሚመለከትበት ፡ ዓይኑ ፡ ያስቀመጣቸውን ፡ ፈጠራዎች ፡ የምጠራበት ፡ ሌላ ፡ ቋንቋ ፡ ስላላገኘሁለት ፡ ነው፡፡ የእሱን ፡ ሀሳብ ፡ በብሂል ፡ ካስቀመጥኩ ፡ በኋላ ፡ በእያንዳንዱ ፡ ብሂል ፡ ስር ፡ መልሱን ፡ አስቀምጨዋለሁ ፡፡ ሠላማችሁ ፡ ይብዛ፡፡
===============================================
1ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹<<<< “መጽሐፍ እንደሚነግረን ሊቃውንት መምህራንም እንደተረጐሙልን እንዳስተማሩን የጌታ ልደታት ኹለት ናቸው። እነዚህ ልደታትም ቀዳማዊ ልደት ከአብ በመለኮት ደኃራዊ ልደት ከድንግል ማርያም በሥጋ የተወለዳቸው ናቸው። ቀዳማዊ ልደቱ በምስጢረ ሥላሴ መነገር የሚገባው ቢኾንም በጎላ በተረዳ ነገር የታወቀው በደኃራዊ ልደቱ ነውና አይነጣጠሉም ቀዳማዊ ልደቱ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቈጠር ቀመር ሳይቀመር ወልድ ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልዶ ከአባቱ ሳይከተል አባቱን መስሎ አባቱን አህሎ አባቱን ተካክሎ የተገኘበት ረቂቅ ጥበብ ነው። ይህንንም ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ፡-«ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ - ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ» መዝ 109 ፡ ቁ 3 ሲል ይገልጠዋል። ይህ ልደት ከፍጥረታት መፈጠር አስቀድሞ የነበረ እንደኾነ በዚህ መረዳት ይቻላል። በርግጥ እንደ ሊቃውንቱ አነጋገር ይህ ጥቅስ ለቀዳማዊ ልደቱ ብቻ አይጠቀስም። ድንግል ማርያም ጌታን የወለደችው በእኩለ ሌሊት በዶሮ ጩኸት ነው። የአጥቢያ ኮከብ የሚወጣው ደግሞ ሊነጋ ሲል ነው። ይህም ማለት ድንግል ማርያም ጌታን የወለደችው የአጥቢያ ኮከብ ከመውጣቱ በፊት ነው ማለት ነው። ስለዚህ ነው ለደኃራዊ ልደቱም የሚቀጸለው።”›››››››››››››››››››››››››››››› ብለሀል ፡ አዎ ፡ መድኅን ፡ ክርስቶስ ፡ ሁለት ፡ ልደታት ፡ እንዳለው ፡ እኛም ፡ እናምናለን ፡ እንታመንማለን፡፡

2ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “«ወለድሁህ» ማለቱ ግን አብ ኹለተኛ በሥጋ የሚወልደው ኾኖ አይደለም። የቃል ገንዘብ ኹሉ ለሥጋ ገንዘቡ ነውና በሥጋው «ወልደ አብ» ተባለ፤ አብም ልጁ ወልድ የተዋሐደውን ሥጋ «ልጄ» አለው ማለት ነው እንጂ”››››››››››››››››››››››››ብለህ ፡ ጽፈሃል፡ እኔም ፡ “የነሲብ ፡ ትርጓሜ” ፡ ያልኳት ፡ ይህችን ፡ ሀሳብህንና ፡ የፈጠራ ፡ ብሂልህን ፡ ነው ፡ ወዳጄ ፡ መልካሙ ፡ በየነ ፡፡ ነሲብነቱም ፡ ወለድኩከ ፡ ብሎ ፡ አብ ፡ የተናገረውን ፡ አልወለደውም ፡ ብሎ ፡ መተርጎሙ ፡ ላይ ፡ ነው ፡፡ የሥጋ ፡ ገንዘብ ፡ ሁሉ ፡ ለቃል ፡ በመሆኑ ፤ “ወልድየ ፡ አንተ” ፡ ያለው ፡ የዳዊት ፡ የምሥጢር ፡ ሁለተኛ ፡ ዋዌ ፡ የምሥጢር ፡ አስረጅ ፡ ነው ፤ እነሆም ፡ ተዋሕዶ ፡ አገናዛቢ ፡ በመሆኑ ፡ የቃልን ፡ ለሥጋ ፡ ብቻ ፡ ሰጥቶ ፡ የሚያቆም ፡ አይደለምና ፤ እንቲአሁ ፡ ለሥጋ ፡ ኮነ ፡ ለቃል ፡ ባለው ፡ አንጻር “ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ አለው ፡ እንጅ ፡ ሳይወልደው ፡ ወለድኩህ ፡ ያለው ፡ አይደለም፡፡ ሲቀጥል ፡ “አብ ፡ኹለተኛ ፡ በሥጋ ፡ የሚወልደው ፡ ሁኖ ፡ አይደለም” ፡ ያልከው ፡ ሀሳብህ ፡ ሁለተኛ ፡ ብለህ ፡ ለመቁጠር ፡ በመጀመሪያ ፡ ሥጋ ፡ ከአብ ፡ የተወለደ ፡ በሆነ ፡ ነበር ፤ ዳሩ ፡ ግን ፡የአብ ፡ ልጅ ፡ ወልደ ፡ አብ ፡ ቃለ ፡ አብ ፡ ቃለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በመለኮት ፡ ርስት ፡ እምቅድመ ፡ ዓለም ፡ ከአብ ፡ የተወለደ ፡ ነውና ፡ “ወልድየ ፡ አንተ” ፡ ብሎ ፡ ተናገረ ፤ እነሆም ፡ ከአብ ፡ ያልተወለደን ፡ ሥጋ ፡ በመዋሐዱና ፡ የሥጋን ፡ ገንዘብ(ከአብ ፡ መወለድን) ፡ ገንዘቡ ፡ በማድረጉ ፡ “ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ ተብሎ ፡ ተነገረለት ፡፡ በዚህ ፡ ጊዜ ፡ ሁለት ፡ ጊዜ ፡ ወለደው ፡ ማለት ፡ አይደለም፡፡ 
ይህም ፡ ልክ ፡ እደንሞቱ ፡ ያለ ፡ ነው፡፡ ማለትም ፡ ሕያው ፡ አምላክ ፡ ሞተ ፤ በሥጋ ፡ ሲባል ፡ የሚሞትና ፡ የማይሞት ፡ ተብሎ ፡ ሁለት ፡ ወልድ ፡ እንዳይባል ፡ ሁሉ ፡ እምቅድመ ፡ ዓለም ፡ በመለኮቱ ፡ ድኅረ ፡ ዓለም ፡ በትስብእቱ ፡ ከአብ ፡ የተወለደው ፡ ልደት ፡ አንድ ፡ እንጅ ፡ ሁለት ፡ አይባልም፡፡ ከዚህም ፡ ጋር ፡ ተያይዞ ፡ “አብ ፡ ኹለተኛ ፡ በሥጋ ፡ የሚወልደው ፡ ኾኖ ፡ አይደለም” ፡ ላልካት ፡ ሀሳብህ ፡ አፈወርቅ ፡ ዮሐንስ ፡ እንዲህ ፡ ይልብሃል ፡ “ወልድየ ፡ አንተ ፡ ያለውን ፡ ስለባሕርይ ፡ ልጅነቱ ፡ ይነገራልን ፡ የሚል ፡ ቢኖር ፤ አዎን ፡ ስለባሕርይ ፡ ልጅነቱ ፡ ይነገራል ፡ ብለን ፡ እንመልስለታለን ፡፡ አንድም ፡ ወአነ ፡ ዮምን ፡ ይሻዋል ፡ የባሕርይ ፡ ልጁን እንደገና ፡ በሥጋ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ አድርጎታልና” ፡ ድር 8፡ቁ 74 ፡ በማለት ፡ የባሕርይ ፡ ልጁን ፡ በሥጋው ፡ እደወለደው ፡ አብራቶ ፡ ተናገረ ፡ እንጅ ፡ አልወለደውም ፡ አላለንም፡፡ 

3ኛ‹‹‹‹‹‹‹ “ዳዊት ከዚህ በተጨማሪም ቀዳማዊ ልደቱን ከደኃራዊ ልደቱ ጋር እንዲህ ይገልጠዋል፡- «እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ - እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኹህ» መዝ 2፡ ቁ 7እዚህ ላይ «እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ» ብሎ ቀዳማዊ ልደቱን ይናገራል። ይህ ቀዳማዊ ልደት ከፍጥረት አእምሮ በላይ ነው። «እኔ ዛሬ ወለድኹህ» ብሎ ደግሞ ደኃራዊ ልደቱን ይናገራል። እዚህ ላይ አብ ወልድን በድጋሜ የሚወልደው ኾኖ አይደለም ቀድሞ ሥጋን ሳትዋሐድ ልጄ እልህ እንደነበረ ዛሬም ሥጋ ብትዋሐድ ልጄ እልሃለሁ ማለቱ ነው። ይኸውም ለሥጋ እንግድነት የተነገረ ነው”›››››››››››››››››››››››ብለሃል ፡ ከዚህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ የነሲብና ፡ የምንታዌ ፡ ትርጓሜ ፡ አስቀምጠሃል ፡፡ 
እሱም ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ ተብሎ ፡ የተነገረው ፡ ብቻ ፡ ለቃል ፡ የተነገረ ፡ አስመስለህ ፡ የተናገርከው ፡ ቃልህ ፡ ነው፡፡ በእናንተ ፡ ቤት ፡ ቀዳማዊና ፡ ደኃራዊ ፡ እየተባለ ፡ የሚቆጠረው ፡ “ወልድየ ፡ አንተ” ፡ የሚለውና ፡ “ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ የሚለው ፡ ከሆነ ፤ ከእመብርሃን ፡ የተወለደውን ፡ ከየትኛው ፡ ልደት ፡ ልትመድቡት ፡ ይሆን? ፡፡ ያም ፡ ሆነ ፡ ይህ ፡ “ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ የሚለው ፡ ልደት ፡ አንድ ፡ ልደት ፡ እንጅ ፡ ቀዳማዊ ፡ ደኃራዊ ፡ ተብሎ ፡ ለሁለት ፡ የሚከፈል ፡ አይደለም ፡፡ ምንም ፡ እንኳን ፡ ጊዜው ፡ ራቀ ፡ ብላችሁ ፡ ብትከፍሉት ፡ ቅሉ ፤ ወላዲውም ፡ አንድ ፤ ተወላዲዉም ፡ አንድ ፡ ነውና ፡ አንድ ፡ ልደት ፡ እንጅ ፡ ሁለት ፡ አይደለም ፡፡ ስለ ፡ ሥጋ ፡ እንግድነት ፡ ብለህ ፡ ያስቀመጥካትን ፡ ሀሳብ ፡ ብትመረምራት ፡ ምሥጢረ ፡ ወልደ ፡ አብን ፡ በደንብ ፡ ታጠግብሃለች ፡ ወዳጄ ፡፡ እሷም ፡ በባሕርዩ ፡ ከአብ ፡ አካል፡ ዘእም ፡ አካል ፡ ባሕርይ ፡ ዘእምባሕርይ ፡ የተወለደ ፡ ቃል ፡ ልጅነት ፡ የሌለውን ፡ ባዕድ ፡ ሥጋን ፡ ተዋሕዶ ፤ የባዕዱን(የእንግዳውን) ሥጋ ፡ ገንዘብ ፡ ገንዘቡ ፡ በማድረጉ ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ ተብሎ ፡ ተነገረለት ፡፡ የሥጋ ፡ እንግድነት ፡ ይሉሃል ፡ ይህ ፡ ነው ፡፡ ሌላም ፡ እንግድነት ፡ በአንቀጸ ፡ ተቀብዐ ፡ የሚነገር ፡ አለው ፡ እሱን ፡ በቦታው ፡ እንነጋገራለን ፡፡ 

4ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ በድርሳኑ ድርሳን 2÷298 ላይ ምንም በማያሻማ ቃል እንዲህ ይተረጒምልናል፡-«ወብሂሎቱሰ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ ዝኒ በእንተ ልደቱ እምቅድመ ዓለም እምኔሁ - አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኹህ ያለው ቅድመ ዓለም ከአብ ስለተወለደው ልደት ነው» ይላል። ድርሳን 2÷303 ላይ ሊቁ ይህንኑ ቃል ሲተረጒም ደግሞ፡- «ነገር ግን መለኮት በሰውነቱ ወአነ ዮም ወለድኩከ መባልን ገንዘብ እንዳደረገ መጠን ወልድየ አንተ መባልን ገንዘብ ስላደረገ። ስለ ሥጋ ተናገረ» ይላል”››››››››››››››››ብለህ ፡ ያነሳሃቸው ፡ መልእክታትም ፡ ውብ ፡ ናቸው ፡፡ ነገር ፡ ግን ፡ ያልተብራራውን ፡ ጥሬ ፡ ዘር ፡ ብቻ ፡ ይዘህ ፡ ተናግረሃልና ፡ ሀሳህን ፡ ውዱቅ ፡ ያርግብሃል ፡፡ ምክንያቱም ፡ በቁጥር ፡ 298 ፡ ላይ ፡ በድፍኑ ፡ የተናገረውን ፡ ቃል ፡ በብልት ፡ በብልቱ ፡ ሲተረጉመው ፡ ቁጥር ፡ 301 ፡ ላይ ፡ “ወብሂሎቱሰ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ ዝኒ ፡ ካዕበ ፡ በእንተ ፡ ትስብእቱ ---ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ ያለው ፡ ስለ ፡ ሰውነቱ ፡ ነው” ፡ ብሎ ፡ ተርጉሞታል ፡ እንጅ ፡ ሁለቱንም ፡ “ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ ማለቱ ፡ ለቅድመ ፡ ዓለም ፡ ልደቱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያለበት ፡ የሚል ፡ አይደለም ፡፡ በሚገባ ፡ በሚገባ ፡ የተረጎመበትን ፡ ክፍል ፡ በደንብ ፡ ማጤን ፡ ያሻሃል ፡፡ ቁጥር ፡ 203 ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ ደግሞ ፡ እነሆ ፡ በጽንዓ ፡ ተዋሕዶ ፡ ሲመዘን ፤ መለኮቱ ፡ የሥጋን ፡ ገንዘብ ፡ ገንዘቡ ፡ ስላደረገ ፡ በሰውነቱ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ መለድኩከ ፡ ሲባልለት ፤ እሆም ፡ ሥጋ ፡ የመለኮትን ፡ ገንዘብ ፡ ገንዘቡ ፡ ስረደገ ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ መባልን ፡ ገንዘቡ ፡ አድርጓል ፡ የሚለውን ፡ የሚያሳየን ፡ ነው ፡፡
5ኛ‹‹‹‹‹‹‹ ጠቢቡ ሰሎሞንም የጌታን ቀዳማዊ ልደት አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡-«ቀላያትን ሳይፈጥር የውኃ ምንጮችም ሳይፈልቁ ተራሮች ሳይመሠረቱ ከኮረብቶች በፊት እኔን ወለደኝ» ይላል ምሳ 8÷24-25።የጌታ ቀዳማዊ ልደት ከፍጥረታት መፈጠር አስቀድሞ ነው የምንለውም ለዚኹ ነው። ”›››››››››››››››በዚህ ፡ ሀሳብህ ፡ ላይ ፡ ተቃውሞ ፡ የለንም ፡፡

6ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ደኃራዊ ልደት ስንል እግዚአብሔር ለአዳም የሰጠው ተስፋ ሲፈጸም ከቀኑ ቀንን ከዕለቱ ዕለትን ከሰዓቱ ሰዓትን ከደቂቃው ደቂቃን ከሰከንዱ ሰከንድን ሳያፋልስ ያለ ወንድ ዘርዕ በግብረ መንፈስ ቅዱስ (በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጥበብ) ሥጋ ማርያምን ተዋሕዶ የተወለደው መወለድ ነው። ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ፡-«ነገር ግን ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ የኦሪትንም ሕግ ፈጸመ» ገላ 4÷4።የሚል ሲኾን ቀደም ብሎ በተተረጐመው መጽሐፍ ቅዱስ ግን፡- «ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ» በማለት ይናገራል። ወልድ እንደ እግዚአብሔርነቱ ዕለቱን ተዋሕጀ ዕለቱን ተወልጄ ዕለቱን ልደግ ሳይል 9ወር ከ9 ቀን በማኅፀነ ማርያም ቆይቶ ሕፃናት በሚወለዱበት ሕግና ሥርዓት ተወልዶ አልቅሶ ጡት ጠብቶ ቀስ በቀስ አድጎ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ ተነሥቶ ዓለምን አድኗልና «ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ» አለ”›››››››››››››››››››በዚህም ፡ ሀሳብ ፡ ምንም ፡ ተቃውሞ ፡ አይኖረንም፡፡ 

7ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹ “ላከ መባሉም ላኪ ኖሮበት አይደለም በእግዚአብሔርነቱ ፈቃድ መጥቶ በማኅፀነ ማርያም አደረ የማይወሰነው መለኮት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወሰነ ሲል እንጂ።”›››››››››››››››››ላከ ፡ የሚለው ፡ ሀሳብ ፡ ግን ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ የሚወሰን ፡ አይደለም ፤ ተፈናዊነት ፡ ርስቱ ፡ የሆነ ፡ ሥጋን ፡ ተዋሕዶ ፡ የሥጋን ፡ ገንዘብ ፡ ገንዘቡ ፡ አድጓልና ፤ አቡየ ፡ ፈነወኒ ፡ እያለ ፡ እንዲናገር ፡ የሚያጠይቅም ፡ ጭምር ፡ እንደሆነ ፡ ሰፋ ፡ አድርገህ ፡ አስብ ፡፡

8ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “የጌታ ኹለቱ ልደታት በሊቃውንት መጻሕፍት በብዛት ተጽፈው እናገኛለን። ኾኖም ግን «በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ተወለደ» ለሚለው የቅብዐቶች ሦስተኛ ልደት አንድ ስንኳ ምስክር አይገኝበትም”››››››››››››››››››››መቼም ፡ ላለማመን ፡ የተፈጠርክ ፡ ነህና ፡ አንዱን ፡ ልደት ፡ ሁለት ፡ ብለህ ፡ እየቆጠርክ ፡ ስታባዛው ፡ ስታራባው ፡ ትገኛለህ ፡፡ ቅቡዓን ፡ እኛ ፡ መድኅን ፡ ክርስቶስ ፡ ሁለት ፡ የባሕርይ ፡ ልደታት ፡ ያሉት ፡ እንደሆነ ፡ እናምናለን ፡ እንጅ ፤ ሦስት ፡ ልደት ፡ ብለን ፡ አናምንም፡፡ ዮም ፡ ወለድኩከን ፡ ከወልድየ ፡ አንተ ፡ ነጣጥላችሁ ፡ የምታምኑ ፡ እናንተ ፡ ሦስት ፡ እያላችሁ ፡ ታነባላችሁ ፡ ትጽፋላችሁ ፡ እንጅ ፡ እኛ ፡ እንደ ፡ እናንተ ፡ አነጋገር ፡ “ሦስት ፡ ልደት” ፡ ብለን ፡ ጸያፍ ፡ ነገርን ፡ አንናገርም ፡ አናምንምም ፡፡ 
ስለዚህ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹“በእርግጥ ይህንን በእኛ ዘንድ ተቀባይነት የሌለውን ሦስተኛውን ልደት ይደግፋሉ ብለው መጻሕፍትን ይጠቃቅሳሉ።”›››››››››››››››››ብለህ ፡ የጻፍከው ፡ ሰይጣናዊ ፡ ፈጠራህ ፤ ያልተጻፈ ፡ የምታነብ ፤ ያልተተረጎመ ፡ ጠማማ ፡ ትርጓሜ ፡ የምትተረጉም ፡ መሆንህን ፡ ያሳያል፡፡ 

9ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ከእነዚህም መካከል፡-«እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ - እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኹህ» መዝ 2÷7ያለውን ኃይለ ቃል ይጠቅሳሉ። የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት የተረጐሙት መጽሐፍ ግን «ዛሬ ወለድኹህ» የሚለውን ሲተረጒሙ በቃል ርስት ብለው የቃል ገንዘብ የኾነው ወልደ አብነት ለሥጋም ገንዘቡ መኾኑን ተናግረዋል እንጂ አብ ዳግመኛ በሥጋ ከድንግል ማርያም ወለደው አላሉንም”›››››››››››››››››ብለሃል ፤ ይህች ፡ ከንቱ ፡ ፈጠራህ ፡ ወደማትወጣባት ፡ አዘቅት ፡ እየከተተችህ ፡ እንደሆነ ፡ አላስተዋክም ፡፡ የቤተክርስቲያን ፡ ሊቃውንት ፡ የምትላቸው ፡ እነሱ ፤ በቃል ፡ ርስት ፡ ብለዉ ፡ የሚተረጉሙት ፤ ለቃል ፡ ዮም ፡ ብሎ ፡ የሚቀጽልለት ፡ ማን ፡ ነው?እኒህ ፡ በነሲብ ፡ የሚተረጉሙ ፡ ሰዎች ፡ መጽሐፉ ፡ እኔ ፡ዛሬ ፡ ወለድኩህ ፡ ያለውን ፤ እነሱ ፡ አልወለደውም ፡ ብለው ፡ ቢተረጉሙት ፡ ዘላን ፡ ባዳ ፡ ቢያሰኛቸው ፡ እንጅ ፡ ሊቃውንት ፡ እንኳን ፡ ይቅርና ፡ ክርስቲያን ፡ አያሰኛቸውም ፡፡ ሌላው ፡ ድሞ ፡ “አብ ዳግመኛ በሥጋ ከድንግል ማርያም ወለደው አላሉንም” ፡ ያልከውን ፡ አረማዊ ፡ ንግግር ፡ አስተካክለው ፤ ምክንያቱም ፡ ወልድ ፡ የተወለደው ፡ ያለዘርዐ ፡ ብእሲ ፡ ነዉና ፡ ሲጀመርም ፡ አብ ፡ ከድንግል ፡ ወለደው ፡ ተብሎ ፡ አይነገርም ፡፡

10ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ይህ ከኾነማ ለምድራዊ ልደቱ አባት አትሹለት የሚለው ቃለ ንባብ ታበለ ማለት ነዋ። በቅብዐት አማኞች ዘንድ የሚነሡ መሠረታዊ ኃይለ ቃሎችን ወደፊት ሳንጨምር ሳንቀንስ ከትርጓሜ መጻሕፍት እንመለከታለን”››››››››››››››››› ይህንንም ፡ ያልተከካ ፡ እንደማቡካት ፡ ያለ ፡ ሀሳብህ ፡ ነው፡፡ ለምድራዊ ፡ ልደቱ ፡ አባት ፡ አትሹለት ፡ መባሉ ፤ ርጉማን ፡ አይሁድ ፡ “የጠራቢው ፡ ዮሴፍ ፡ ልጅ ፡ ነው” ፡ ብለው ፡ ይሰድቡት ፡ ነበርና ፤ ለምድራዊ ፡ ልደቱ ፡ አባት ፡ አትሹለት ፡ አለ ፤ በሌላ ፡ በኩልም ፡ አምላክ ፡ ወልደ ፡ አምላክ ፡ ከድንግል ፡ ማርያም ፡ ከሥጋዋ ፡ ሥጋን ፡ ከነፍሷ ፡ ነፍሥን ፡ ነሥቶ ፡ ሲወለድ ፡ በዘር ፡ በሩካቤ ፡ ሳይሆን ፤ በግብረ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንበለ ፡ ዘርዕ ፡ ወሩካቤ ፡ ነውና ፡ ለምድራዊ ፡ ልደቱ ፡ አባት ፡ አትሹለት ፡ ተባለ ፡፡

11ኛ‹‹‹‹‹‹ “ሌላው በቅብዐቶች ዘንድ ሦስተኛ ልደት ያሉትን ይደግፋል ብለው የሚጠቅሱት ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምስጢር 3÷46 ላይ የተናገረውን ነው። ይኸውም፡- «ነገርነኬ በእንተ ህላዌ መለኮቱ ወትስብእቱ እምድኅረ ሥጋዌሁ ኢንቤሎ ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወወልደ እጓለእመሕያው በትስብእቱ። ድንግልኒ ወለደት ዘኢዚአሃ መለኮተ በዘዚአሃ ሥጋ ምስለ ዘዚአሃ ሥጋዌ። አብኒ ወለደ ዘኢዚአሁ ሥጋ በዘዚአሁ መለኮት። ምስለ ዘዚአሁ ኃይል ዘህሉና አምላክ - ስለመለኮቱ እና ስለ ትስብእት ህልውና እነሆ ተናገርን። ሰው ከመኾኑ በኋላ በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱም የሰው ልጅ አንለውም። ድንግልም ለእርሷ በተገባ ሥጋዌ የእርሷ በኾነ ሥጋ የእርሷ ያልኾነውን መለኮት ወለደችው። አብም የባሕርይው ያልኾነውን ሥጋ የባሕርዩ ከኾነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በኾነ መለኮት ወለደ» የሚል ነው`>>>>>>>›››››››››>ከዚህም ፡ ላይ ፡ ሦስተኛ ፡ ልደት ፡ ብለህ ፡ የማንለውን ፡ ከማለትህ ፡ ውጭ ፤ ወልድ ፡ በሰውነቱ ፡ ከአብ ፡ ልደት ፡ ባሕርያዊትን ፡ ገንዘቡ ፡ ማድረጉን ፡ የሚያስረዳውን ፡ የአባ ፡ ጊዮርጊስን ፡ ምሥክርነት ፡ እናምናለን ፡፡ 

12ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹ ከዚህ ትምህርት መካከል ቅብዐቶች አብ በማኅፀነ ማርያም ወልዶታል ለሚለው ክሕደታቸው ቆርጠው የወሰዱት «አብም የባሕርይው ያልኾነውን ሥጋ የባሕርዩ ከኾነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በኾነ መለኮት ወለደ» የሚለውን ነው። መለኮታዊ አካል ሥጋዊ አካልን፤ ሥጋዊ አካልም መለኮታዊ አካልን፤ መለኮታዊ ባሕርይ ሥጋዊ ባሕርይን፤ ሥጋዊ ባሕርይም መለኮታዊ ባሕርይን በባሕርዩ ሊወልድ ይችላልን? ብዬ ብጠይቃችሁ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? በማለት መልሳችሁ እንደምትጠይቁኝ አልጠራጠርም። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ምንም ነገር እንደሌለ እኔም አስረግጨ እመልስላችኋለሁ”››››››››››››››››››ወዳጄ ፡ መልካሙ ፡ በየነ ፡ እመ ፡ ብርሃን ፡ ጸጋውን ፡ ታብዛልህ ፡ ወዳጄ! ፤ አንተም ፡ ቆርጠው ፡ ወሰዱ ፡ ለማለት ፡ በቃህ? መሠንበት ፡ ደጉ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ ያሳየኛል ፡ ያሰማኛልም ፡፡ እኛ ፡ መሢሐውያን(ቅቡዓን) ፤ በተለምደዎው ፡ አጠራራችሁ ፡ “ቅብዓቶች” ፡ የምትሉን ፡ ኩሩ ፡ ኦርቶዶክሳውያን ፤ መቁረጥ ፣ መቁመጥ ፣ እየነቀሉ ፡ ማውጣት ፣ እየጎማመዱ ፡ ማተምም ፡ ሆነ ፡ መጥቀስ ፡ በዘራችንም ፡ የለምንም ፡፡ አሉ ፡ እንጅ ፡ እነ ፡ አባ ፡ ቢለዋ ፡ እየከረካከሙ ፡ የሚያስቀምጡ፡፡ ያም ፡ ሆነ ፡ ይህ ፡ ለጠየቅኸን ፡ ጥያቄ ፡ አብ ፡ የባሕርዩ ፡ ያልሆነውን ፡ ማለትም ፡ በባሕርዩ ፡ ረቂቅ ፡ መለኮትን ፡ አካል ፡ ዘእም ፡ አካል ፡ ባሕርይ ፡ ዘእም ፡ ባሕርይ ፡ መዉለድ ፡ ነበረ ፡ ልማዱ ፤ እነሆ ፡ ስለሥጋ ፡ እንግድነት ፡ ግን ፡ የራሱ ፡ ያልሆነ ፡ ሥጋን ፡ የባሕርዩ ፡ በሆነ ፡ የህልዉና ፡ አምላክ ፡ ኃይል ፡ ጋር ፡ ወለደው፡፡ እነሆ ፡ በአዋለዱም ፡ የአካል ፡ ተከፍሎ ፡ የባሕርይ ፡ ተፋልሶ ፡ የለበትምና ፤ ረቂቁ ፡ አብ ፡ የረቂቅ ፡ ግዙፍ ፡ የሆነ ፡ ወልድን ፡ ወለደው ፡፡ ይህንን ፡ የማያምኑ ፡ አማሌቃውያን ፡ ናቸው ፡፡

13ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ ይህን በተመለከተ «የክርስቶስ ሥጋ እንደ እኛ ያለ ደካማ ሥጋ አይደለም» ያለ አውጣኪን በገሰጸበት በሌላኛው ተግሳጹ መጽሐፈ ምስጢር 14÷7ላይ የተናገረውን መግለጥ እሻለሁ።«እመሰ በአካለ መለኮት ተሠገወ እምኢበቊዖ ርኅበ ዓለም ወድንግልኒ እምኢደለወቶ ለከዊነ እም። ወኮነቶ እም ኀበ ሀለወት እንዘ ኢትትመየጥ እምህላዌሃ። ውእቱኒ ኮና ወልደ ተሠጊዎ በሥጋዌሃ እንዘ ኢያሌዕላ ውስተ ኑኃ አርያም ወእንዘ ኢትመልዕ ይእቲኒ አጽናፈ አጽናፋት - በመለኮት አካል መጠን ሰው ኾኖ ቢኾን የዓለም ስፋት ባልበቃው ድንግልም እናት ለመኾን ባልተገባችው ነበር። ከባሕርይዋ ሳትለወጥ ባለችበት ኹናቴ እናት ኾነችው። እርሱም ወደ አርያም ከፍታ ሳያወጣት እርሷም የዳርቻዎችን ዳርቻ ሳትመላ ከሥጋዋ ሥጋን ተዋሕዶ ልጇ ኾናት» ይላል”›››››››››››››››››ይህ ፡ ኃይለ ፡ ቃል ፡ ከላይ ፡ የጠቀስከውን ፡ የሚያብራራ ፡ ሳይሆን ፡ የመለኮትን ፡ ረቂቅነት ፡ እና ፡ የሥጋን ፡ ዉሱንነት ፡ በጽንዓ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቀምሞ ፡ የሚያስረዳ ፡ ቃል ፡ ነውና ፤ አብ ፡ ስለከዊነ ፡ ትስብእት ፡ አልወለደውም ፡ የሚል ፡ መግቢያ ፡ እንኳን ፡ የለውም፡፡

14ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “አብ በሥጋ ዳግመኛ ወለደው ብሎ መናገር ሥጋን የዓለም ስፋት አልበቃውም ብሎ ውስንነቱን መጠራጠር፤ ድንግልንም ኃይል አርያማዊት ናት ብሎ መካድ ነው። ስለዚህ የመጻሕፍትን ቃለ ንባብ ለመረዳት በእርጋታ በመንፈስ ኾኖ መመልከት ይገባል እንጂ እንደ መሰለን መተርጐም ከልማቱ ይልቅ ጥፋቱ የጎላ ይኾናል”›››››››››››››››››››››ይህም ፡ ላም ፡ ባልዋለበት ፡ ኩበት ፡ ለቀማ ፡ ነው ፡፡ ምክንያቱም ፡ አባ ፡ ጊዮርጊስ ፡ የጠቀሱት ፡ ቃል ፡ የሚለን ፡ አብ ፡ ወለደው ፡ ሲሆን ፤ የአንተ ፡ ማብራሪያ ፡ ደግሞ ፡ “ወለደው ፡ ማለት ፡ ሥጋ ፡ ስፍሐተ ፡ ዓለም ፡ ጠበበው ፡ እንደማለት ፡ ነው” ፡ እያልክ ፡ በነሲብ ፡ ትርጓሜ ፡ አባ ፡ ጊዮርጊስን ፡ ስትቃወም ፡ ትስተዋላለህ፡፡እኛም ፡ ይህ ፡ ሀሳብህ ፡ ለአንተ ፡ የሚሰጥ ፡ ሀሳብ ፡ እንጅ ፡ ለእኛ ፡ የሚሰጥ ፡ ሀሳብ ፡ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ፡ በሥጋ ፡ ወለደው ፡ ማለት ፡ ሥጋ ፡ ስፍሐተ ፡ ዓለም ፡ አልበቃውም ፡ ማለት ፡ ሳይሆን ፤ ልጅነት ፡ ያልነበረው ፡ ሥጋ ፡ ወልደ ፡ አብ ፡ ሆነ ፡ ማለት ፡ ነው ፡፡ ስለዚህ ፡ በእርጋታ ፡ መንፈስ ፡ ሁነህ ፡ የመጻሕፍትን ፡ ቃለ፡ ንባብ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ቃለ ፡ ትርጓሜውንም ፡ ትመለከት ፡ ዘንድ ፤ በተለይም ፡ የነሲብ ፡ ትርጓሜህ ፡ ከልማቱ ፡ ጥፋቱ ፡ ስለሚብስብህ ፡ አቅምህን ፡ ዕወቅ ፡ እልሀለሁ፡፡

15ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ሊቁ ይህን የተናገረው በእውነት እነርሱ እንደሚሉት ነውን? አይደለም። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የእውቀት ጽዋእን የጠጣ አባቶች ያላስተማሩትን እንግዳ ትምህርት ለመናገር ነውን? አይደለም። ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ፷÷፳ ላይ፡-«ዛሬ ግን ከድንግል ብቻ ተወለደ ድንግልናዋንም ባለመለወጥ አጸና ድንቅ የሚኾን መፅነስዋ የታመነ ይኾን ዘንድ ቅድመዓለም ከአብ እንደተወለደም ለማመን መሪ ይኾን ዘንድ» የሚለውን ትምህርተ ሊቃውንት ዘንግቶት ይኾን ለምድራዊ ልደቱ አባት የሻለት? አይደለም”››››››››››››››››ይህም ፡ ሀሳብህ ፡ ከንቱ ፡ እንደሆነ ፡ አልተረዳኸውም ፡፡አንተ ፡ ሞኝ ፡ ሁነህ ፡ እንጅ ፡ ለምድራዊ ፡ ልደቱ ፡ አባት ፡ የሻለት ፡ አይደለም ፤ ያች ፡ ሰማያዊት ፡ ልደት ፡ በተዋሕዶ ፡ ተገናዝባ ፤ “ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ አስባለችዉ ፡ እንጅ ፡፡ እሷም ፤ እንቲአሁ ፡ ለቃል ፡ ኮነ ፡ ለሥጋ ፤ ወእንቲአሁ ፡ ለሥጋ ፡ ኮነ ፡ ለቃል ፡ በሚለው ፡ የቄርሎስ ፡ ድጅኖ ፡ የታረቀ ፡ ቀጥ ፡ ያለ ፡ እውነታ ፡ ነው ፡፡ ታዲያ ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ አንድ ፡ እንጅ ፡ ሁለት ፡ አይደለም፡፡ ነገር ፡ ግን ፡ በቤተ ፡ ምንታዌ ፡ ወልድየ ፡ አንተ ፡ ከወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ ተለያይቶ ፡ የሚነገር ፡ በመሆኑ ፡ አንዱን ፡ ልደት ፡ ሁለት ፡ እያላችሁ ፡ በመቁጠር ፡ በራሳችሁ ፡ ጊዜ ፡ ሦስት ፡ ልደት ፡ የሚል ፡ ፍልስፍናን ፡ እየተፈላሰፋችሁ ፡ ገደል ፡ ስትገቡ ፡ ትገኛላችሁ፡፡ተዋሕዶን ፡ የሚያምን ፡ ሰው ፡ የሥጋ ፡ ከአብ ፡ መወለድ ፡ የሚሰወርበት ፡ አይደለም ፡፡ ነገር ፡ ግን ፤ ተዋሕዶን ፡ የሚጾም ፡ ሰው ፡ ወልድ ፡ በትስብእቱ ፡ ከአብ ፡ ተወለደ ፡ ማለት ፡ ሦስት ፡ መስሎ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ዐራትም ፡ እያለ ፡ መቁጠሩ ፡ አይቀሬ ፡ ነው፡፡ አባ ፡ ጎርጎርዮስ ፡ የተናገረውም ፡ ሀሳብ ፡ ድኅረ ፡ ዓለም ፡ ያለ ፡ ዘርዐ ፡ ብእሲ ፡ በግብረ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተወለደ ፡ በመሆኑ ፤ ከድንግል ፡ ብቻ ፡ ተወለደ ፡ አለ ፡ እንጅ ፤ አብ ፡ አልወለደውም ፡ አላለንም፡፡ 

12ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ሊቁስ ወደ ምስጢር ሄዶ «አብም የባሕርይው ያልኾነውን ሥጋ የባሕርዩ ከኾነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በኾነ መለኮት ወለደ» ብሎ ተናገረ።ከተዋሕዶ በኋላ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብም ለቃል ገንዘቡ እንደኾነ እናምናለን። ቃል ከሥጋ ጋራ በተዋሐደ ጊዜ ሥጋ «ወልደ አብ፣ ቃለ አብ» መባልን ገንዘቡ አደረገ። ስለዚህም ሥጋ ቀዳማዊ አምላክ ኾነ ቀዳማዊ አምላክ በመኾኑም ወልደ አብ ተባለ። ለቃል አባቱ የኾነ አብ ለክርስቶስም (ለሥግው ቃል) አባቱ ተባለ ማለት ነው። ስለዚህ ሥጋ ወልደ አብነትን (የአብ ልጅ መባልን) ገንዘቡ አደረገ አለ ሊቁ። ይህን ምስጢር አርቅቆ የተናገረበት ግሩም ትምህርት እንደኾነ በዚህ እንረዳለን”›››››››››››››››››አይ ፡ ወዳጄ ፡ ቢጨንቅህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡፡ አባ ፡ ጊዮርጊስ ፡ የሄዱበት ፡ ምሥጢር ፡ የባሕርዩ ፡ ያልሆነ ፡ ሥጋን ፡ ወለደው ፡ ብለው ፡ ቁልጭ ፡ አድርገዉ ፡ ተናገሩለት ፡ እንጅ ፡ አልወለደውም ፡ አላሉም ፡ እኮ ፡፡ከተዋሕዶ ፡ በኋላ ፡ የቃል ፡ ገንዘብ ፡ ለሥጋ ፡ እንዲሆን ፡ ስታምን ፤ የሥጋ ፡ ገንዘብስ ፡ ለቃል ፡ መሆኑን ፡ አታውቅምን?፡፡ አየህ ፡ መልካሙ ፡ ከተዋሕዶ ፡ በፊት ፡ ቃል ፡ የአብ ፡ ልጅ ፡ ነበር ፤ ሥጋ ፡ ደግሞ ፡ የባሕርይ ፡ ይቅርና ፡ የጸጋ ፡ እንኳን ፡ ልጅነት ፡ የሌለው ፡ ነበር ፡፡ እኒህ ፡ ሁለቱ ፡ ሲዋሐዱ ፡ ልጅነት ፡ የሌለው ፡ ሥጋ ልጅነት ፡ ካለው ፡ ቃል ፡ ጋር ፡ ተዋሕዶ ፡ የቃልን ፡ ገንዘብ ፡ ገንዘቡ ፡ አድርጓልና ፡ “ወልድየ ፡ አንተ” ፡ ተባለለት ፤ እነሆም ፡ ልጅነት ፡ ያለው ፡ ቃል ፡ ልጅነት ፡ የሌለውን ፡ ሥጋ ፡ ተዋሕዶ ፤ የሥጋን ፡ ገንዘብ (ልጅነት ፡ የሌለው ፡ መባልን ፣ ልጅነትን ፡ መሻትን) ፡ ገንዘቡ ፡ አድርጓልና ፡ “ወአነ ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ” ፡ አለው፡፡ ይህንንም ፡ አፈወርቅ ፡ ድር ፡ 2እና 8 ፤ ቄርሎስ ድር 24 ፡ ላይ ፡ ቁልጭ ፡ አድርገው ፡ ተርጉመውታል ፡፡የቃልን ፡ ገንዘብ ፡ ገንዘቡ አድርጎ ፤ ሥጋ ፡ ቀዳማዊ ፡ አምላክ ፡ ሲባል ፤ ቃልም ፡ ዮም ፡ ወለድኩከ ፡ በመባሉ ፡ ደኃራዊ ፡ አምላክ ፡ ሐዲስ ፡ አምላክ ፡ መባሉን ፡ መዘንጋት ፡ የለብህም ፡፡

13ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “አብ በማኅፀነ ማርያም ወልድን ዳግም ወልዶት ቢኾን ኖሮ በግልጽ በጎላ በተረዳ ነገር በተናገረልን ነበር። ነገር ግን ሊቁ ይህንን አልተናገረውም”››››››››››››››››››››››አይ ፡ መልካሙ ፡ በየነ ፡ “ዓይን ፡ ቦሙ ፡ ኢይሬእዩ----ዓይን ፡ ሳላቸው ፡ አያዩም” ፡ እንደተባለላቸው ፡ እንደ ፡ አዛጦን ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ ዳጎንና ፡ አጵሎን ፡ ልቡናችሁ ፡ አያይም ፡ አይሰማም ፡ ብሎም ፡ አያስተውልም ፡ እንጅ ፤ “የእርሱ ፡ ያልሆነ ፡ ሥጋን ፡ የእርሱ ፡ በሆነ ፡ የህሉና ፡ አምላክ ፡ ኃይል ፡ ጋር ፡ ወለደው” ፡ ብለው ፡ አባ ፡ ጊዮርጊስ ፡ በጎላ ፡ በተረዳ ፡ ነገር ፡ ተናግረው ፡ ነበር ፡፡ አንተ ፡ ግን ፡ እስከ ፡ አሁንም ፡ ድረስ ፡ ከቅዱስ ፡ ቃሉ ፡ ጋር ፡ ራስህን ፡ ስታጋጭ ፡ ትገኛለህ፡፡ ዳግም ፡ ወለደው ፡ እያልክ ፡ ያልተጻፈም ፡ ታነባለህ፡፡ በእርግጥ ፡ ጽንዓ ፡ ተዋሕዶዉን ፡ ሳይሆን ፡ ነጠላ ፡ ተዋሕዶን ፡ የምታምን ፡ በመሆንህ ፡ ይህንን ፡ ባትል ፡ ነበር ፡ የሚገርመን፡፡
14ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “መጻሕፍት ከተዋሕዶ በኋላ የሥጋን ገንዘብ ለመለኮት የመለኮትን ገንዘብም ለሥጋ አድርገው መናገር ልማዳቸው ነው። ለዚህም ወንጌላዊው ዮሐንስ የጻፈውን አንድ ነገር እንመልከት፡-«ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው» ይላል ዮሐ 3÷13 ላይ። የመለኮትን ገንዘብ ለሥጋ ሰጥቶ ነው የተናገረው። መለኮት ዘመን የማይቈጠርለት በመኾኑ በመለኮት ገንዘብ ሥጋንም እንዲሁ ተናገረለት። «የሰው ልጅ ከሰማይ ወረደ» የሚለውን ይዘን ሥጋን ከሰማይ ይዞት መጣ በማለት እንደ ሰነፎች በጥርጥር ውስጥ አንወድቅም። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተናገረው ከዚህ የወንጌል ቃል የተለየ አይደለም። የመለኮትን ገንዘብ ለሥጋ ገንዘቡ አድርጐ የተናገረበት ድንቅ ምስጢር ያለው ንግግር ነው”›››››››››››››››››ይህም ፡ ጽንዓ ፡ ተዋሕዶን ፡ የሚያጠይቅ ፡ እንጅ ፡ አብ ፡ አልወለደውም ፡ ለማለት ፡ የሚጠቀስ ፡ ጥቅስ ፡ አይደለም፡፡ 

15ኛ‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “የአባ ጊዮርጊስን ቃል ይዘው አብ ዳግም በማኅፀነ ማርያም በሥጋ ወልዶታል የሚሉ ከኾነ የዚህን የአቡቀለምሲስን ወንጌል ምን ብለው ይተረጒሙታል? ሥጋን ከሰማይ ይዞ ወረደ ይሉን እንደኾነ እስኪ በትሕትና እንጠይቃቸው”›››››››››››››››››››››ወዳጃችን ፡ መልካሙ ፡ በየነ ፡ እኛ ፡ ሥጋን ፡ ከሰማይ ፡ ይዞ ፡ መጣ ፡ የምንል ፡ ክፉ ፡ ጥፉዎች ፡ አይደለንም ፡፡ ይልቁንም ፡ እነሆ ፡ ከሰማይ ፡ ከወረደው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ በቀር ፡ ወደሰማይ ፡ የወጣ ፡ የለም ፡ የሚለውን ፡ ቃለ ፡ ወንጌል ፡ እነሆ ፡ ወንጌል ፡ መጻፉ ፡ ክርስቶስ ፡ ሥጋ ፡ ከለበሰ ፡ በኋላ ፡ ነውና ፡ ወንጌላዊው ፡ ሲጽፍ ፡ በአየበት ፡ ሰውነቱ ፡ ነውና ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ብሎ ፡ ተናገረ ፤ አንድም ፡ እነሆ ፡ ተዋሕዶ ፡ ያለፈውንም ፡ የሚመጣውንም ፡ አገናዛቢ ፡ በመሆኑ ፡ ከሰማይ ፡ ከወረደው ፡ በቀር ፡ ማለቱ ፡ የሥጋዌው ፡ ምሥጢር ፡ አናግሮት ፡ ነው ፡ እንላለን ፡ እንጅ ፡ ሥጋ ፡ ከሰማይ ፡ መጣ ፡ አንልም፡፡ በሥጋዉ ፡ ተወለደ ፡ ማለታችንም ፡ እኮ ፡ እነሆ ፡ ልጅነት ፡ የሚሻ ፡ ምድራዊ ፡ ሥጋን ፡ ተዋሕዶ ፡ የሥጋን ፡ ገንዘብ(ከአብ ፡ መወለድን) ፡ ገንዘቡ ፡ በማድረጉ ፡ ነው ፡፡

16ኛ ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “አባ ጊዮርጊስ ይህን የወንጌል ቃል ሲተረጒም እንዲህ ይለናል፡-«ዳግመኛ እኔ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ ነኝ አለ። በሥጋው ካልኾነ በውኑ መለኮት እንጀራ ተብሎ ይጠራልን? ሥጋዬ እውነተኛ የጽድቅ መብል ነው ብሏልና። መለኮቱ ነው እንጂ ሥጋው በውኑ ከሰማይ ወርዷልን? ከሰማይ ከወረደ ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ብሏልና። የሰው ልጅ ከሰማይ እንደማይወርድ እናውቃለን። ነገር ግን መለኮትን ከሥጋ ሥጋንም ከመለኮት የተለየ እንዳናደርግ የመለኮትን መውረድ ለትስብእት ቈጠረው። እነሆ በዚህም የትስብእት ከመለኮት ጋራ መተካከል ተገለጠ» መጽሐፈ ምስጢር 2÷15)”››››››››››››››››››››ይህም ፡ ጽንዓ ፡ ተዋሕዶን ፡ የሚያስረዳ ፡ በመሆኑ ፡ እኛም ፡ እናምንበታለን

ዛቲ ፡ ሃይማኖት ፡ መሢሐዊት ፡ ዘትትአመን ፡ ባቲ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ቅድስት
ስብሐት ፡ ለአብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ 
ክብር ፡ ለድንግል ፡ ማርያም ፡ ወላዲተ ፡ አምላክ
ክብር ፡ ለመስቀለ ፡ ክርስቶስ ፡ እጸ ፡ መድኃኒት ፡ ኃይልነ ፡ ወጸወንነ፡፡
ይቆየን

1 comment: