በስመ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ
“ሲያምኑ ግማሽ
ሲተረጉሙ ዳሽ” ክፍል
ሦስት
ይድረስ “Habtamu St”››››››ለሚሉህ
ግለሰብ በአስተያየት መስጫ
ሳጥን ላይ
ለጻፍክልኝ ጥያቄ መልስ
======================================
1ኛ‹‹‹‹‹‹ፊቴ እንዲያበራ እናቴ የቀባችኝ ቅባት፣
ካደረገኝ አምላክ ዘበምድር ወዘበሰማያት፣
የቅቤ መገኛ ላማችን እርሷም ድንቅ አምላክ ናት”›››››››››
ብለህ ለተናርካት ንግግርህ መልሴን በስንኝ ቋጠሮ
አስልተው ካልሰጡት ማረሚያና አራሚ
ንፍጥ ይለቀልቃል አላዋቂ ሳሚ፡፡
እንዳሉን አባቶች በሥነ ቃላቸው፤
ሰምተኸው ለማታውቅ ለአንተ ለእንግዳው፡
ጣዕመ ምሥጢሩ የቅብዓት ምሳሌው
መስሎ ይታይሃል ቅቤ ምናምኑ የላም የፍየሉ የግመል የአህያው፡፡
ዳሩ ግን ወዲህ ነው ድንቅ ንግግሩ፡
የተቀብዐ ዳገት ናሙና ምሥጢሩ፡፡
የሥላሴ ሕይወት መንፈሰ ቅግዚአብሔር፡
በላሞቹ ዉጤት በቅቤ በከንቱው ፡
የሚለካ አይደለም አምላክ ዘለዓለም ነው፡፡
በትምርት ታጥቦ ዓይንን ካልገለጡ፤
ወደ መምህርነት ምንም ቢያንጋጥጡ ፡
የተቀብዐ ዳገት የተሰብአ መውጫ፤
ከቶ አይገኝም በትዕቢት በአፍ ብልጫ፡፡
ብየሀለሁ፡፡