Thursday, December 6, 2018

ወልድ በሥጋው ሞተ እንደተባለ በሥጋው ፍጡር እንደሚባል የአበው ምስክር




፩ኛ............  “ወንነጽር  ለለ፩ዱ ቃል እምቃላት ወኃይለ ዘውስቴቶሙ ወንትናገር ዳግመ ምክንያተ ነገር ዘይቤልዎ ዘከመ ትስብእቱ ናሁ ------ ከመጽሐፍት ቃላት እያንዳንዱን ቃላት በውስጣቸውም ያለውን ምስጢር እናስተውል፤ ሰው እንደመሆኑ የተነገሩለትን፤ የነገሩንም ምክንያት ዳግመኛ እንናገር::  ዮሐ 5፥39 ፤
 ናሁ አቅደምነ ወተናገርነ ባህሎ  ዘይቤ አምላኪየ ዘውእቱ አምላክክሙ ብዙኃ ጊዜያተ ከመ ይለቡ ዘአልቦቱ አእምሮ ፍናወ ፩ዱ ቃል ወዘተብህለ ከመ ውእቱ ሰብእ ወአልቦ ዘየአምሮ----  ይኸውም ፈጣሪያችሁ ነው፤ እነሆ አምላኪየ ያለበትን ነገር አስቀድመን መላልሰን ተናግረናልና፤ ሰው  እንደሆነ የሚያውቀውም እንደሌለ የተናገረለትን እያንዳንዱን ቃል መንገድ (ምስጢር) ዕውቀት የሌለው ሰው ያውቅ ዘንድ ፤
  ወበዝንቱ ቃለ መጽሐፍ ቅዱስ ይትዐወቅ ከመ ውእቱ እም፪ቱ ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ ፩ዱ ሕላዌ በእንተሰ ዘያስተርኢ ይቤ አምላኬየ ወበእንተ ዘያስተርኢ ይቤ አቡየ ---- በዚህም በቅዱሳት መጽሐፍት ቃል እርሱ ከሚታየውና ከማይታየው ከሁለቱ አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ ይታወቃል፤ ስለ ክበበ ትስብእት አምላኪየ አለ ስለ መለኮት አባቴ አለ::
ወአልቦ ዘይክል መኑሂ ያውሥእ ቃለ በእንተ እሉ ፪ቱ ሥርዓታት እፎኑ ውእቱ ሰብእ ዘኢኮነ ፍጡረ  ወለእመ ኢኮነ ሰብአ እፎመ ተሰምየ ሰብአ ---- አባቴ አምላኪየ ስለ አላቸው ስለ እነዚህ ምስጢራት መልስ ሊሰጥ የሚችል የለም፤ ፍጡር ያይደለ ሰው እንደምን ያለ ነው? ሰውስ ካልሆነ እንዴት ሰው ይባላል? ” ሃይ/አበው  ዘኤጲፋንዮስ ምዕ 54፥16 – 19 ይላል::
፪ኛ........... “ወዘሰ ንቤ ፍጡር ውእቱ በእንተ ዘተሣተፈ ሥጋ ድካምነ በሥርዓት ዘገብሮ በእንቲአነ-- ፍጡር[ሰው] ነው ያልነውም ስለ እኛ ባደረገው ተዋሕዶ ደካማ ባሕርያችንን ስለተዋሐደ ነው” ሃይ/ አበው ዘጎርጎርዮስ 35፥3


፫ኛ........ “ወዓዲመ ይትበሀል ፍጡረ በእንተ ዘኮነ ሥጋ ወኀደረ ላዕሌነ ዝንቱ ሶበ ኮነ ሥጋ ከሠተ ስብሐቲሁ በምግባር ከመ እግዚአብሔር አስተርአየ በሥጋ ወውእቱ አምላክ ወልድ ዋሕድ ዘሀሎ ውስተ ሕፅነ አቡሁ -- ዳግመኛም ባሕርያችንን ተዋሕዶ ሰው ስለሆነ ፍጡር/ሰው ይባላል እርሱ ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር  በሥጋ እንደ ታየ በሥራው ጌትነቱን ገለጠ እርሱ አምላክ ወልድ በአባቱ ዕሪና ያለ ነው:: ”  ሃይ/ አበው ዘጎርጎርዮስ 35፥6
፬ኛ ........ “.........ወዓዲ ይቤ በእንተ ተሠግዎቱ ለመድኅን ከመ ፍጡር ውእቱ -- ዳግመኛም መድኅን ሰው ስለ መሆኑ ሲናገር ፍጡር [ሰው] እንደ ኾነ ተናገረ” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥17
፭ኛ.......... “.......... ንሕነሰ ንረክቦ ለዝንቱ ወልድ ዋሕድ አምላክ ወውእቱ ሰብእ ለሊሁ እግዚእ ወለሊሁ ገብር፤ ለሊሁ በግዕ ወለሊሁ ሊቀ ካህናት፤ ወውእቱ ፍጡር ወፈጣሪ -- እኛስ ይህን አንድ ወልድን አምላክ ሰው፤ ገዥ ተገዥ፤ ሠዋዒ ተሠዋዒ፤ ፍጡር ፈጣሪ ሆኖ እናገኘዋለን” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥18
፮ኛ ........... “.........ለሊሁ ፍጡር ወለሊሁ ፈጣሪ ንብሎ  ፈጣሪ በእንተ ከመ ውእቱ አምላክ ወእግዚአብሔር ውእቱ ወዓዲመ ንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲት -- እሱ ፍጡር [ሰው] ነው እሱ አምላክ ነው፤ አምላክ እግዚአብሔር ስለሆነ ፈጣሪ እንለዋለን ወዲህም ከድንግል በሥጋ ስለተወለደ ፍጡር[ሰው] እንለዋለን” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥19
፯ኛ .......... “........ በደኃሪ መዋዕል ወከመዝ ተሰይመ ፍጡረ፤ በዝንቱ አርአያ በከዊኖቱ ሰብአ ፍጹመ -- በኋላ ዘመን በሥጋ ባሕርዩ ኾነ፤ ፍጹም ሰው በመሆኑም በዚህ መልክ ፍጡር ተባለ ” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥24
፰ኛ........... “.......ወከመዝ ዓዲ አመ ለብሰ አርአያ ሰብእ በእንተ መድኃኒተ ኩልነ ይብል እሙነ ከመ ሰብእ እስመ እግዚአብሔር ፈጠረኒ -- እንዲሁ ደግሞ እኛን ሁላችንን ለማዳን የሰውን ባሕርይ በተዋሐደ ጊዜ በእውነት ሰው እንደመሆኑ እግዚአብሔር ፈጠረኝ ይላል” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥25
፱ኛ ......... “....... እስመ ሰብእሰ ፍጡር ውእቱ  ወእንበይነ ዝንቱ ይብል እግዚአብሔር ፈጠረኒ -- ሰው ፍጡር ነውና ስለዚህም እሱ ሰው ስለሆነ እግዚአብሔር ፈጠረኝ ይላል” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥26
፲ኛ ....... “ወዓዲ ይቤ እስመ እግዚአብሔር ኮነ ሰብአ ከመ ይፈጽም ምግባራተ ወይኩን ቅድመ በውስተ ፍናዋት ወከመዝ ዓዲ ንሕነኒ ንብል በእንቲአሁ ባሕቲቱ እስመ እግዚአብሔር ፈጠረኒ -- ዳግመኛ የሰውነትን ሥራ ይሰራ ዘንድ ለትሩፋትም መምህር ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሰው ሆነ አለ፤ እንዲሁ ደግሞ እኛም እግዚአብሔር ሰው አድርጎ ፈጠረኝ ማለትን ሰው ስለሆነው ስለ እርሱ ብቻ እንናገራለን” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥27
፲፩ኛ.......... “....... ወከመዝ እንከ ሶበ ፈጠረ ሥጋሁ በእንቲአሁ ውእቱ ከመ ፍጡር እስመ ሥጋ ዘተፈጥረ ረሰየ ሎቱ ወህላዌ መለኮቱሰ ኢፍጡር ውእቱ -- እንዲህ ሥጋን ፈጥሮ ስለተዋሐደም እሱ ፍጡር ኾነ ይባላል የተፈጠረ ሥጋን ለእርሱ ገንዘብ አድርጓልና ባሕርየ መለኮቱ ግን ፍጡር አይደለም” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥28
፲፪ኛ......... “....... ከመ ለሊሁ ፍጡር ወመዋቲ በሥጋ ኢፍጡር ወኢመዋቲ በመለኮት --  እሱ በሥጋ ፍጡር መዋቲ ነው፤ በመለኮቱ ግን ፍጡር መዋቲ አይደለም፤ ...... ዘተዋሐደ ምስለ ሥጋ ንብል በእንቲአሁ ፍጡር ውእቱ ወመዋቲ ኢፍጡር እንከ ወኢመዋቲ በህላዌ መለኮት -- ሥጋን ስለተዋሐደ ፍጡር መዋቲ ነው እንላለን በባሕርየ መለኮት ግን ያልተፈጠረ የማይሞት ነው ብለን እንናገራለን”ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥29
፲፫ኛ ....... “......ወዓዲ ይቤ በዝንቱ ቃል ዘተብህለ አንሰ ተፈጠርኩ ኢያጤይቅ በእንተ ባሕርየ ቃል አላ ዳእሙ ያሌቡ ፈድፋደ እንበይነ ምጽአቱ ኀቤነ ወለቢሶቱ ሥጋ ፍጡረ ከማነ በዝንቱ ዘተብህለ በእንቲአሁ ተፈጥረ ውእቱ ወካዕበ ይቤ በእንተ ዘኮነ ሰብአ ደለዎ እሙነ ይበል እስመ እግዚአብሔር ፈጠረኒ ቅድመ ለፍኖተ ተግባሩ -- ዳግመኛ እኔ ተፈጠርኩ የተባለው ቃል[ኃይለ ቃል] ስለ ቃል ባሕርይ አያመለክትም እንደ እኛ ያለ ፍጡር ሥጋን ስለተዋሐደ ሰው መሆኑን ያስረዳል እንጅ ተፈጠረ ተብሎ ስለእርሱ የተነገረለት ይህ ነው አለ ዳግመኛ ሰው ስለሆነ ፍጥረቶቹ ሊድኑበት እግዚአብሔር ፈጠረኝ ይል ዘንድ ተገባው” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥30
፲፬ኛ....... “....... ወበእንተ ዝንቱ ተብህለ በእንቲአሁ ከመ ውእቱ ተፈጥረ አው ተገብረ -- ስለዚህ ሥጋ ስለሆነ ስለእርሱ ተፈጠረ ተብሎ ተነገረ”ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥33
፲፭ኛ ...... “...... ወከመዝ እሙነ ንብል በእንቲአሁ ባሕቲቱ ይቤ ከመ እግዚአብሔር ፈጠረኒ ቀዳሚ ለፍኖተ ሠናይቱ ውእቱሰ ቀዳማዊ በኩሉ ጊዜ በህልው ዘልፈ ፈጠረ ሥጋሁ በእንተ ምክንያት ዘተነግረ -- ለቸርነቱ ሥራ ጀማሪ አድርጎ እግዚአብሔር ፈጠረኝ አለ ብለን እንዲህ ስለ እርሱ ብቻ በእውነት እንናገራለን፤ እሱስ ሊያድርበት አልፈጠረውምና በጊዜው ሁሉ በቅድምና የነበረ ለዘላለም የሚኖር ነውና ስለ ተነገረው ምክንያት ሥጋን  ፈጠረ እንጅ” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥35
፲፮ኛ...... “....... ሰብእሰ ፍጡር ውእቱ ወበእንተ ዝንቱ ይብል እስመ እግዚአብሔር ፈጠረኒ በእንተ ዘኮነ ሰብአ -- ሰው ፍጡር ነውና ስለዚህ ሰው  ስለሆነ እግዚአብሔር ፈጠረኝ ይላል አለ” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥36
፲፯ኛ....... “........ ወይደሉ በእንቲአሁ ልደት ወተፈጥሮ ወቦቱ መንፈስ ቅዱስ ወካዕበ ይቤ ወእመኒ አኮ አሐደ እምነ ፍጡራን ወውእቱሰ ይትሌዐል እምኩሉ ፍጥረት -- ተወለደ ተፈጠረ መባል ይገባዋል መንፈስ ቅዱስም ገንዘቡ ነው ዳግመኛም እንዲህ አለ ምንም ከፍጡራን እንደ አንዱ ቢሆን እሱስ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ነው ” ሃይ/አበው ቃለ ስምዓት 124፥39
/ይችን ኃይለ ቃል ሊቀ ሊቃውንት ሥምዓኮነ በቃለ ጽድቁ መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰዋታል ዳሩ ግን ካሮች በሥጋው ፍጡር አይባልም ይላሉ/
፲፰ኛ ........ “ወሶበ ትሰምዕ ከመ ውእቱ ፍጡር ኢተሐሲ ግሙራ ከመ ዝንቱ ይትበሀል በእንተ ቃል ከመ እግዚአብሔር ፈጠሮ በከመ ይቤ አርዮስ ርጉም አላ ይትበሀል በእንተ ሥጋ ከመ ውእቱ ፍጡር -- እርሱ ፍጡር እንደተባለ ብትሰማ ርጉም አርዮስ ፍጡር ነው ብሎ እንደተናገረው ይህ አነጋገር እግዚአብሔር ቃልን እንደፈጠረው የተነገረ ነው ብለህ አታስብ ሥጋን ስለተዋሐደ ፍጡር[ሰው ሆነ] ነው ተብሎ ይነገራል እንጅ” ሃይ/አበው ዘቴዎዶስዮስ ምዕ 83፥14
፲፱ኛ......... “እግዚአብሔር አብ ውእቱ አቡሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በህላዌ መለኮቱእግዚአብሔር አብ አምላኩ ለወልድ ውእቱ በእንተ ትስብእቱ  -- እግዚአብሔር አብ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርየ መለኮቱ አባቱ ነው ሰው ስለሆነ ወልድ እግዚአብሔር አብ አምላኩ ነው” ሃይ/ አበው ዘኤጲፋንዮስ ምዕ 549
፳ኛ ........ “......... አዐርግ ኀበ አቡየ ወአቡክሙ ኀበ አምላክየ ወእምላክክሙ -- ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም ዐርጋለሁዮሐንስ 20÷17 አንድምታ ...... አቡየ ብሎ የእሱን ልደት ተናገረ አቡየ ያለው የእርሱ የባሕርይ ነው አቡክሙ ያለው የእኛ የጸጋ ነው አምላኪየ አለ በሥጋ ይፈጥረዋል፤ አምላክክሙ አለ በጥንተ ተፈጥሮ በሐዲስ ተፈጥሮ ይፈጥረናልና::
በማለት ቅዱሳን አበው ወልድ  በሥጋው  ተወለደ አደገ፤ በላ ጠጣ፤ ታመመ ደከመ፤ ጾመ ሰገደ፤ ተራበ ተጠማ፤ ሞተ ተነሳ፤ ዐረገ  ብለው እንደተናገሩት ሁሉ ፍጡር መዋቲ አዳማዊ ሥጋን ስለተዋሐደ በሥጋው ፍጡር እንደሚባልለት በመጽሐፋቸው ጽፈው ደጉሰው ምስክር ይሆን ዘንድ ስላስቀመጡት ወልደ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ባዮች ደግሞ በሥጋው ፈጣሪ እንጅ ፍጡር ይባል ዘንድ አይገባም ብለው ሲከራከሩ ስለነበር ከዚያ ላይ ጥቂት ማስረጃዎችን እነሆ  ብያለሁ::
 እናንተም[በተዋሕዶ ከበረ ባዮች በሙሉ] እኒህን ጥያቄዎች ትመልሱልኝ ዘንድ እማጸናችኋለሁ:-
ሀ/  አካላዊ ቃል በባሕርይ አንድነቱ በተለየ አካሉ በተወላዲነት ግብሩ በባሕርዩ ፍጡር መዋቲ ከሆነ ሥጋ አዳም ጋር ተዋሕዶ ሥጋ በቃል ርስት አምላክ፣ ፈጣሪ፣ ወሀቢ ሲሆን ቃል በሥጋ ርስት ምን ሆነ ትላላችሁ? [መልስ ከምስክር ጋር]
ለ/ ከሁለቱ ብሂሎች የትኛውን ነው የምትቀበሉት ? ለምን? [መልስ ከምስክር ጋር]
  1ኛ ........ለሊሁ ቀባዒ ወለሊሁ ተቀባዒ ወለሊሁ ቅብዕ - እራሱ አክባሪ  እራሱ  ከባሪ እራሱ ክብር ይላሉ፤
2ኛ ..... .. ለሊሁ ቀባዒ ወቅብዕ -- እራሱ[አካለ ቃል አክባሪም ክብርም ነው] ወአካለ ቃል አክበሮ ለሥጋሁ [አካለ ሥጋ በቃል ከባሪ] ትላላችሁና እስኪ የሁለቱንም ብሂላችሁ ሰፋ ባለ ማብራሪያና ምስክር ጋር ቢሆን ይመረጣል::
 ሐ/ ወልድ ቅብዕ፤ በተዋሕዶ ከበረ[ቃል ሥጋን አከበረው፤ ሥጋ በቃል ከበረ] የሚለውን  “ክርስቶስ በሥጋ ሞተ” ከሚለው ጋር እስኪ አስማሙት ቃል ሥጋውን ገደለው ትሉት ይሆን? ቃል ሥጋን አከበረው የሚል መጽሐፋዊ ምስክር አላችሁን?
መ/ ወልድ ዋሕድ ክርስቶስን  አምላክወሰብእ  ብላችሁ ስታምኑ ፍጡር ያልሆነ ሰው እንደምን ያለ ነው? ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችስ ትቀበሏቸው ይሆን?
ሠ/ በተዋሕዶ ከበረ [ቃል ሥጋን አከበረው] ብላችሁ  ወልድ ዋሕድ [አንድ ልጅ] ማለት እንዴት ይገኛል? እንዲህስ ትሉ ዘንድ ምንታዌን ከተዋሕዶ ጋር እንዴት ልታስታርቁት ትችላላችሁ?
ረ/ ስላሴ አካላዊያን ናቸው:: ስለዚህ የአብ ልብነት የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ያልነበሩት ሥጋ ከቃል ጋር ሲዋሐድ የአብን ልብነት የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስነት እንዴት ተቀበለ?
ለጊዜው እነዚህን ጥያቄዎች ከነ ሙሉ ማስረጃቸው መልሱና እንነጋገራለን!

================================//=========================//==============================
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

1 comment:

  1. እና ፍጡር እንበል ወይስ ፈጣሪ

    ReplyDelete