Friday, December 14, 2018

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሁለት

ወልደ ፡ አብ ፡ በወልደ ፡ አብ : ክፍል ፡ ሁለት
==================================
የጌታችን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ እና


የቤተ ፡ አይሁድ ፡ ካሮች ፡ ውድቀት
======================================
በገዛ ፡ ሥልጣኔ ፡ ተነሣሁ ፡ ሲል ፡ ለወልድ ፡ ከአብ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተለየ ፡ ሥልጣን ፡ አለውና ፡ በተለየ ፡ ሥልጣኔ ፡ ተነሣሁ ፡ ሲል ፡ ነውን? ፡ ቢሉ ፤ ከአብ ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጋር ፡ በሥልጣን ፡ ዕሪናውን ፡ ሲያጠይቅ ፡ እጅ ፡ የተነሣስ ፡ በ3ቱም ፡ ሥልጣን ፡ ነው ፡፡ “አማን ፡ በአማን ፡ ተንሥአ ፡ እሙታን ፡ በኃይለ ፡ አቡሁ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በሥልጣኑ ፡ ፈቲሆ ፡ ማዕሠሮ ፡ ለሞት()” ፡ እንዳለ ፡ ድርሳነ ፡ ማኅየዊ() ፡፡ በ3ቱም ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ሊቃውንቱ ፡ በዝርዝር ፡ ተናረዋል ፡፡
በአብ ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ቅዱስ ፡ ጳውሎስ ፡ “አብ ፡ አንሥኦ ፡ ለወልዱ ፡ እሙታን” ፡ ብሏል ፡፡ በገዛ ፡ ሥልጣኑ ፡ እንደተነሣ ፡ ቅዱስ ፡ ቄርሎስ ፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ” ፡ ብሏል ፡፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሥልጣን ፡ እንደተነሣ ፡ ባስልዮስ ፡ ዘቂሣርያ ፡ “ወተንሥአ ፡ በኃይለ ፡ መለኮቱ”  ፡ ብሏል(ሃይ.አበው ፡ ምዕ ፡ 34 ፡ ክ ፡ 5 t18) ፡፡ ኃይል ፡ የተባለ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንደሆነ ፡ ለማጠየቅ ፡ ወንጌለ ፡ ሉቃስ(ምዕ ፡ 24t49) ፡ “ወናሁ ፡ እፌኑ ፡ ተስፋሁ ፡ ለአቡየ(እኔም ፡ ተስፋ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ እልክላችኋለሁ) ፡ ወአንትሙሰ ፡ ንበሩ ፡ ሀገረ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ እስከ ፡ ትለብሱ(እናንተ ፡ ግን ፡ ከሰማይ ፡ ሀይልን ፡ ማለት ፡ ሰማያዊ ፡ ሀብትን ፡ እስክትለብሱ ፡ በኢየሩሳሌም ፡ ኑሩ)” ፡ ብሏል ፡፡ይህስ ፡ ይሁን ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ ፡ ማለቱ ፡ በብቻየ ፡ ሲል ፡ አይደለምን? ፡ ቢሉ ፤ ይህስ ፡ ትንሣውን ፡ ሲያይ ፡ የተናረው ፡ ነው ፡፡ ማለትም ፡ አብና ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እንደሱ ፡ ሰው ፡ አልሆኑም ፤ እሱ ፡ ግን ፡ ሰው ፡ የሆንኩ ፣ ከሙታን ፡ የተነሣሁ ፡ በተለየ ፡ አካሌ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ነኝ ፡ ሲል ፡ “ወተንሣእኩ ፡ በሥልጣነ ፡ ባሕቲትየ” ፡ አለ ፡ እንጅ ፡ ከአብና ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የተለየ ፡ ሥልጣን ፡ አለኝ ፡ ሲል ፡ አይደለም ፡፡
ዳግመኛም ፡  የጸጋ ፡ ልጅ ፡ የግድ ፡ ይታመማል ፣ የግድ ፡ ይሞታል ፡ እንጅ ፡ በፈቃዱ ፡ አይታመምም ፣ በፈቃዱ ፡ አይሞትም ፤ እርሱ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ነውና ፡ በፈቃዱ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፤ “ሞተ ፡ በፈቃዱ ፡ ወተቀብረ ፡ በሥምረቱ” ፡ እንዳለ ፡ ዮሐንስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት ፡፡ ዳግመኛም ፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ የራሱን ፡ ይታመማል ፡ ይመሞታል ፤ “እመሰ ፡ ኀደረ ፡ ቃል ፡ ላዕሌሁ ፡ ከመ ፡ ኵሎሙ ፡ ነቢያት ፡ ለምንትኑ ፡ ኢተብህለ ፡ በእንተ ፡ ግብሮሙ ፡ እምልደቶሙ ፡ እስከ ፡ ዕለተ ፡ ሞቶሙ ፡ ኮነ ፡ በእንቲአነ ፡ አላ ፡ በእንተ ፡ ርእሶሙ ፡ ባሕቲቶሙ(በነቢያት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያድር ፤ ቃል ፡ ከአደረበት ፡ ከተወለዱ ፡ ጀምሮ ፡ እስከ ፡ ሞታቸው ፡ ድረስ ፡ የሠሩት ፡ ሥራ ፡ እኛን ፡ ለማዳን ፡ ተደረገ ፡ ለምን ፡ አልተባለም? ፡ ራሳቸውን ፡ ብቻ ፡ ለማዳን ፡ እንደሆነ ፡ ተነገረ ፡ እንጅ ፡፡  
እመሰ ፡ ኀደረ ፡ ላዕሌሁ ፡ ቃል ፡ ከመ ፡ ኩሎሙ ፡ ነቢያት(በነቢያት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያድር ፡ ቃል ፡ ከአደረበት) ፤ ለምንትኑ ፡ ተብህለ ፡ በእንተ ፡ ዝንቱ ፡ ባሕቲቱ ፡ ዘተወልደ ፡ እምእግዝእትነ ፡ ቅድስት ፡ ድንግል ፡ ማርያም ፡ ምዕረ ፡ ቦአ ፡ ውስተ ፡ ዓለም ፡ በደኃሪ ፡ መዋዕል(ከእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ስተወለደ ፡ ስለእርሱ ፡ ብቻ ፡ 5500 ፡ ዘመን ፡ ሲፈጸም ፡ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ሰው ፡ ሁኖ ፡ ተወለደ ፡ ተብሎ ፡ ለምን ፡ ተነገረ)” ፡ እንዳለ ፡ አትናቴዎስ(ሃይ.አበው ፡ ምዕ ፡ 31t31-32) ፡፡ ጌታ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡ ነውና ፡ ለሰው ፡ ብሎ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፤ “ሞተ ፡ ከመ ፡ ያሕይዎሙ ፡ ለምውታን” ፡ እንዳለ ፡ ዮሐንስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት ፡፡
ምነዋ ፡ የጸጋ ፡ ልጆች ፡ ጻድቃን ፣ ሰማዕታት ፡ መታመማቸው ፣ መሞታቸው ፡ በፈቃዳቸው ፡ አይደለምን?፡ እንደምን ፡ የግድ ፡ ይሆናል? ፡ ቢሉ ፡ ጌታ ፡ ሲአስተምር ፡ በወንጌለ ፡ ማቴዎስ(ምዕ ፡ 1t36) ፡ ላይ ፡ “ዘኢሐደገ ፡ አባሁ ፡ ወእሞ ፣ ቤቶ ፡ ወዉሉዶ ፡ ወዘኢፆረ ፡ መስቀለ ፡ ሞትየ ፡ ኢይክል ፡ ይፀመደኒ” ፡ ብሎ ፡ እንደገለጸው ፤ እናት ፡ አባቱን ፣ ቤት ፡ ንብረቱን ፡ ትቶ ፡ እኔን ፡ ያልተከተለ ፡ ከእኔ ፡ አንድነት ፡ የለውም ፡ መንግሥተ ፡ ሰማያትን ፡ እንኳንስ ፡ ሊገባባት ፡ አያያትም ፡ ብሎ ፡ አዋጅ ፡ ተናግሯል ፡፡ ጻድቃን ‹ ሰማዕታትም ፡ ይህ ፡ አዋጅ ፡ ግድ ፡ ብሏቸው ፡ ይታመማሉ ፡ ይሞታሉ ፡ እንጅ ፡ በፈቃዳቸው ፡ አይታመሙም ፡ አይሞቱም ፤ እሱ ፡ ግን ፡ ይጸድቅበታል ፡ እንዳይባል ፡ በባሕርዩ ፡ ጻድቅ ፤ ይብርበታል ፡ እንዳይባል ፡ የባሕርይ ፡ ክቡር ፡ ነውና ፡ ለሰው ፡ ሲል ፡ በፈቃዱ ፡ ታመመ ፡ ሞተ ፡:



ዳግመኛም ፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ አይሰገድለትም ፡ “ዘሰገደ ፡ ለፍጡር ፡ ርጉም ፡ ውእቱ” እንዲል ፤ እሱ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ነውና ፡ ይሰገድለታል ፡፡ “እመቦ ፡ ዘኢይሰግድ ፡ ለዘተሰቅለ ፡ ውጉዘ ፡ ለይኩን (ለተሰቀለው ፡ የማይሰግድ ፡ ቢኖር ፡ የተወገዘ ፡ ይሁን) ፤ ወይትኈለt ፡ ምስለ ፡ ቀታልያነ ፡ እግዚእ (ጌታችንን ፡ ከሰቀሉት ፡ ከአይሁድ ፡ ጋር ፡ ይቈጠር)” እንዳለ ፡ ጐርጐርዮስ ፡ ነባቤ ፡ መለኮት(ሃይ.አበው ፡ ምዕ ፡ 61 ፡ ክ ፡ 4t26) ፡፡
መናፍቃን ፡ የጸጋ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ካሉት ፡ “ዘኢሰገደ ፡ ለዘተሰቅለ ፡ ውጉዘ ፡ ለይኩን” ፡ ያለውን ፡ ምን ፡ ብለው ፡ ይተረጕሙታል? ፡ ቢሉ ፤ በሰውነቱ ፡ ለሞተው ፡ በአምላክነቱ ፡ ያላመነበት ፣ በሰውነቱ ፡ ለተሰቀለው ፡ በአምላክነቱ ፡ ያልሰገደለት ፡ ርጉም ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ይተረጕሙታል ፡፡  እኒህ ፡ በምን ፡ ይረታሉ? ፡ ቢሉ ፤ ወልድን ፡ በሰውነቱ ፡ የጸጋ ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ ካላችሁ ፡ አይሁድ ፡ ሰቀሉት ፡ ትላላችሁ? ፡ ወይስ ፡ አትሉም? ፡ ብሎ ፡ ይጠይቋል ፡፡ እነሱም ፡ ሰቀሉት ፡ ብለው ፡ ይመልሳሉ ፡፡ ሰቀሉት ፡ ካላችሁ ፡ “ዚሰገደ ፡ ለዘተሰቅለ ፡ ውጉዝ ፡ ውእቱ ፡ ወይትኈለቈ ፡ ምስለ ፡ ቀታልያነ ፡ እግዚእ(በተሰቀቀለው ፡ ያላመነበት ፡ አምላክን ፡ ከሰቀሉት ፡ ከአይሁድ ፡ ጋር ፡ ይቈጠራል) ፤ ይህን ፡ ጊዜ ፡ አምላክነት ፡ የሌለው ፡ የጸጋ ፡ ልጅማ ፡ ቢሆን ፡ ኖሮ ፡ “ወይትኈለቈ ፡ ምስለ ፡ ቀታልያነ ፡ ሰብእ” ፡ ባለ ፡ ነበር ፡ እንጅ ፤ “ምስለ ፡ ቀታልያነ ፡ እግዚእ” ፡ ባለ ፡ ነበርን? ፡ ሲሏቸው ፡ በዚህ ፡ ይረታሉ ፡፡
አስተውሉ ፡ ወንድሞችና ፡ እህቶች ፡ የካሮቹ ፡ መውደቅ ፡ ከዚህ ፡ ይጀምራል ፤፡ እስከ ፡ አሁን ፡ ድረስ ፡ ያለውን ፡ ባለማየታቸው ፡ ከማይወጡበት ፡ ገደል ፡ ተንኮታኩተው ፡ ወድቀዋል ፡፡
ካሮቹ ፡ እንደ ፡ ቅድመ ፡ አያታቸው ፡ ልዮን ፡ ላይመለሱ ፡ የሞቱበት ፡ ቃል ፡ ወልደ ፡ አብ ፡ ላይ ፡ እንደተጻፈው ፡ “ምነው ፡ መሰገዱ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነቱን ፡ ያጠይቃል ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ነው ፤ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ለመስቀል ፡ ይሰገድላቸው ፡ የለምን ፤ ክብራቸውስ ፡ የጸጋ ፡ አይደለምን ፡ ቢሉ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡፡ እንዴት ፡ ቢሉ ፡ የጻድቃን ፡ እናቶች ፡ ይሰገድላቸዋልን ፤ ስንኳንስ ፡ ለናቶቻቸው ፡ ለርሳቸው ፡ አይሰገድላቸውም ፤ እርሷ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የሆነውን ፡ ብትወልድ ፡ እሰግድ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ንጽሕተ ፡ ሥጋ ፡ ወነፍስ ፡ ተብሎ ፡ ይሰገድላታል ፡ ሰጊድ ፡ ወክብር ፡ ይደልዋ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ወለደ ፡ ማቴዎስ ፡ ፍሥሓ ፡ እንዳለ ፡ ጊጋር ፡ በነገረ ፡ ማርያም ፤ ለመስቀል ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ እንዴት ፡ ቢሉ ፤ እንግዲያው ፡ የቅዱስ ፡ ጴጥሮስ ፡ የቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ መስቀል ፡ ይሰገድለታልን ፤ ስንኳንስ ፡ ለመስቀሉ ፡ ለርሳቸው ፡ አይሰገድላቸውም ፤መስቀል ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የሆነው ፡ ሥጋው ፡ ቢፈስበት ፤ ደሙ ፡ ቢፈስበት ፡ “እሰግድ ፡ ለመስቀለ ፡ እግዚእነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርሰቶስ ፡ ዘተቀደሰ ፡ በደሙ ፡ ክቡር” ፡ ብለን ፡ እንሰግድለታለን”›››››››ወልደ ፡ አብ ፡ ገፅ ፡ 251 ›››››››የሚል ፡ ሀሳብ ፡ አለ ፡ እኒህ ፡ ዓይን ፡ እያላቸው ፡ የማያዩ ፤ ጆሮ ፡ እያላቸው ፡ የማይሰሙ ፤ ልቡና ፡ እያላቸው ፡ የማያስተውሉ ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፤ ይህችን ፡ ያስቀመጥኳትን ፡ ሀሳብ ፡ ብቻ ፡ ቁርጥ ፡ ቁምጥ ፡ አድርገው ፡ እየተመለከቱ ፡ ወደቅ ፤ መውደቅ ፡ ብቻም ፡ አይደል ፡ ብዙ ፡ ኦርቶዶክሳውያንን ፡ ይዘዋቸው ፡ ወደቁ ፡፡ አምላከ ፡ ቅዱሳን ፡ ልቡና ፡ ይስጣቸው ፡፡ ከላይ ፡ በባለፈው ፡ በክፍል ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ የጻፍኩትን ፤ እሆም ፡ ከአሁን ፡ ከዚህ ፡ በታች ፡ የምጽፈውን ፡ ሳይመለከቱ ፡ ከመሐል ፡ ላይ ፡ ቁርጥ ፡ አድርገው ፡ ወስደው ፤ ስግደት ፡ አይባም ፡ አላችሁ ፡ እያሉ ፡ የሞኝ ፡ የጨዋ ፡ ንግግር ፡ ሲናገሩ ፡ መስማት ፤ በእነሱ ፡ ድንቁርና ፡ ምን ፡ ያህል ፡ ሰው ፡ ወደ ፡ ሲዖል ፡ እየተጓዘ ፡ እንደሆነ ፡ ማስታወስ ፡ ይቻላል ፡፡ እኒያ ፡ “ካራ” ፡ ወይም ፡ “መጥባሕት” ፡ ብለው ፡ ስም ፡ ያወጡላቸው ፡ ሰው ፡  ምንኛ ፡ የአዕምሮ ፡ ምጥቀት ፡ አላቸው ፤ እኒህ ፡ ቆራጮች ፡ እየቆማመጡ ፡ ያወጡታል ፡፡ ከላይ ፡ በገጽ 251 ፡ ያለውን ፡ ቃል ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፤ የሚጠቅሱት ፤ “ስንኳንስ ፡ ለናቶቻቸው ፡ ለርሳቸው ፡ አይሰገድላቸውም” ፡ የምትለዋን ፡ ብቻ ፡ ቆርጠው ፡ ይጠቅሱታል ፤ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ ያለውን ፡ “እርሷ ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የሆነውን ፡ ብትወልድ ፡ እሰግድ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ንጽሕተ ፡ ሥጋ ፡ ወነፍስ ፡ ተብሎ ፡ ይሰገድላታል ፡ ሰጊድ ፡ ወክብር ፡ ይደልዋ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ወለደ ፡ ማቴዎስ ፡ ፍሥሓ ፡ እንዳለ ፡ ጊጋር ፡ በነገረ ፡ ማርያም” ፡ የሚለውን ፡ ቃል ፡ ቢጠቅሱት ፡ ኖሮ ፤ አብዝው ፡ ባልካዱ ፡ ለጻድቃን ፡ አይሰገድላቸውም ፡ የተባለው፡ የትኛዉ ፡ ስግደት ፡ እንደሆነ ፡ ይገባቸው ፡ ነበር ፡፡ ነገር ፡ ግን ፤ እኒህ ፡ ቤተ ፡ አይሁድ ፡ የራሳቸው ፡ ምንፍቅና ፡ ናላቸውን ፡ ያዞራቸው ፡ ስለሆኑ ፤ እነሱ ፡ እየቆራረጡ ፡ እየቆማመጡ ፡ ሲጠቅሱ ፡ በእነሱ ፡ ቤት ፡ ጽድቅ ፡ ነው ፤ ፕሮቴስታንቱ ፡ እየቆማመጠ ፡ እየቆራረጠ ፡ ሲጠቅስ ፡ ግን ፡ ጽድቅ ፡ ነው ፡፡ ለማንኛውም ፡ ካሮችም ፡ ይሁኑ ፡ ፕሮቴስንቶቹ ፡ ቆርጦ ፡ ቆምጦ ፡ በመጥቀስ ፤ አንድ ፡ ዓይነት ፡ ናቸው ፡፡ መልዕክቴ ፡ እንዳይበዛ ፤ ወደ ፡ ሀሳቤ ፡ ልመለስ ፤
እኒህ ፡ ልሙጥ ፡ ሰዎች ፡ የቆረጡት ፡ ቃል ፡ ከነ ፡ ሙሉ ፡ ማብራያው ፡ ሲቀርብ ፡ እንደሚከተለው ፡ ነው ፡፡ በወልደ ፡ አቡ ፡ ላይ ፡ የተጠቀሰው ፡ ሀሳብ ፡ በሰፊው ፡ ሲብራራና ፡ ሲዘረዘር ፤ ለእሱ ፡ መሰገዱ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነቱን ፡ ያጠይቃል ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ነው? ፤ ስግደትማ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፣ ለመስቀል ፡ ይሰገድላቸው ፡ የለምን? ፡ ክብራቸውስ ፡ የጸጋ ፡ አይደለምን? ፡ እንደምን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነቱን ፡ ያጠይቃል ፡ ተባለለት? ፡ የሚል ፡ ሰው ፡ ቢኖር ፤ ማንኛውም ፡ ክርስቲያን ፡ በማንኛውም ፡ ወደ ፡ ቅድስት ፡ ቤተ-ክርስቲያን ፡ ሲገባ ፤ 5 ት ፡ ስግደት ፡ ይሰግዳል ፤ 3ት ፡ ለሥላሴ ፤ 2 ፡ ለመስቀልና ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም  ፡ ስለዚህም ፤ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ እና ፡ ለመስቀል ፡ የጸጋ ፡ ስግደትን ፡ እንሰግድላቸዋለን ፤ ለእነሱ ፡ የጸጋ ፡ ስግደትን ፡ መስገዳችን ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፣ የባሕርይ ፡ አምላክነት ፡ ያጠይቃል ፡፡ እንደምን ፡ ያጠይቃል? ፡ ብንል ፡ የባሕርይ ፡ የሆነውን ፡ አምላክ ፡ ወልደ ፡ አምላክ ፡ ብትወልድ ፡ “እሰግድ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ድንግል ፡ ወላዲተ ፡ አምላክ ፡ ንጽሕተ ፡ ሥጋ ፡ ወነፍስ” ፡ ብለን ፡ እንሰግድለታለን ፡፡ “ሰጊድ ፡ ወክብር ፡ ይደልዋ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ወለደ ፡ ማቴዎስ ፡ ፍሥሐ” ፡ እንዳለ ፡ ጊጋር ፡ በነገረ ፡ ማርያም ፡፡ ለመስቀልም ፡ መሰገዱ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡ የሆነ ፡ ወልደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሕያው ፡ ወልደ ፡ ማርያም ፡ ሥግው ፡ መድኅነ ፡ ዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሥጋው ፡ ቢቈረስበት ፡ ደሙ ፡ ቢፈስበት ፡ “እሰግድ ፡ ለመስቀለ ፡ እግዚእነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርሰቶስ ፡ ዘተቀደሰ ፡ በደሙ ፡ ክቡር” ፡ ብለን ፡ እንሰግድለታለን ፡፡ ለመስቀል ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነቱን ፡ ያጠይቃል ፡ ማለት ፡ ስለዚህ ፤ ነው ፡፡ 
ምነዋ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ መሰገዱ ፡ የእሱን ፡ የባሕርይ ፡ ልጅነት ፡ ያጠይቃል ፡ ማለት ፡ እንዴት ፡ ነው? ፡ የጻድቃን ፡ እናቶችስ ፡ ይሰገድላቸው ፡ የለምን? የእግዝእትነ ፡ ማርያምስ ፡ ከእነሱ ፡ በምን ፡ ይለያል? ፡ የሚል ፡ ቢኖር ፤ ለጻድቃንስ ፡ እንኳንስ ፡ ለእናቻቸው ፡ ይቅርና ፡ ለእነሱም ፡ ቢሆን ፡ ለእመቤታችን ፡ የምንሰግደውን ፡ ስግደት ፡ አንሰግድላቸውም ፡፡ ይህ ፡ ሲባል ፡ ግን ፡ ከላይ ፡ የያዝነው ፡ ምሥጢር ፡ የባሕርይና ፡ የጸጋ ፡ መሆኑን ፡ ለመለየት ፡ እንጅ ፤ ለጻድቃን ፡ ለቅዱሳን ፡ ስግደት ፡ አይገባም ፡ ማለት ፡ አይደለም ፡፡ ማለትም ፡ ለጻድቃን ፡ ስግደት ፡ ስንሰደግድላቸው ፡ ወላድያነ ፡ አምላክ ፡ ብለን ፡ አይደለምና ፡ አይሰገድላቸውም ፡ መባሉ ፡ “ወላድያነ ፡ አምላክ” ፡ ተብሎ ፡ የሚሰገድላቸው ፡ አለመሆኑን ፡ ለማጠየቅ ፡ ሲሆን ፤ እግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ግን ፡ የባሕርይ ፡ አምላክ ፡ የባሕርይ ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ መድኃኔ ፡ ዓለምን ፡ በድንግና ፡ ፀንሳ ፡ በድንግልና ፡ የወለደች ፡ በመሆኗ ፡ “እሰግድ ፡ ለእግዝእትነ ፡ ማርያም ፡ ድንግል ፡ ወላዲተ ፡ አምላክ ፡ ንጽሕተ ፡ ሥጋ ፡ ወነፍስ” ፡ ብለን ፡ እንሰግድላታለን ፤ ለጻድቃን ፡ እናቶችም ፡ ይሁን ፡ ለእሳቸው ፡ ንጽሐ ፡ ሥጋ ፡ ቢኖራቸው ፡ እንጅ ፡ በሁለት ፡ ወገን ፡ ደናግላን ፡ ብሎም ፤ እንደ ፡ እመቤታችን ፡ አምላንክ ፡ የወለዱ ፡ አይደሉምና ፡ ለእመቤታችን ፡ የሰገድነውን(ንሰግድ ፡ ለእግዝእነ ፡ ማርያም ፡ ድንግል ፡ ወላዲተ ፡ አምላክ ፡ ብለን ፡ እንደምንሰግደው ፤ ሁሉ) ፡ ለእነሱም ፡ “ወላድያነ ፡ አምላክ” ፡ ብለን ፡ አንሰግድም ፡ ማለት ፡ እንጅ ፡ ስግደት ፡ አያስፈልጋቸውም ፡ ለማለት ፡ አይደለም ፡፡
ምስጋና ፡ ለአንዱ ፡ አምላክ ፡ ለቅድስት ፡ ሥላሴ
ክብር ፡ ለወላዲተ ፡ አምላክ ፡ ለድንግል ፡ ማርያም
ክብር ፡ ለመስቀለ ፡ ክርስቶስ ፡ እጸ ፡ መድኃኒት ፡ ኃይልነ ፡ ወጸወንነ
ስለመስቀል ፡ ይቀጥላል ፡፡

በካሮቹ ፡ እብደትና ፡ ውድቀት ፡ እኔ ፡ ከሚገባኝ ፡ በላይ ፡ እየተናገርኩ ፡ ውስጤ ፡ አላርፍ ፡ ስላለኝ ፤ ከእኔ ፡ የበረታችሁ ፡ ሁላችሁም ፡ በጸሎታችሁ ፡ አስቡኝ ፡፡ እኒህ ፡ የአይሁድ ፡ ትርፎች ፡ ራሳቸው ፡ ቤት ፡ ያለው ፡ የካራ ፡ ዓይነት ፡ ወደ ፡ 5 ፡ የተጠጋ ፡ ሲሆን ፤ ራሳቸው ፡ አንድ ፡ ሳይሆኑ ፡ ኦርቶዶክሳዊት ፡ ቅድስት ፡ ቤተ-ክርስቲያንንና ፡ ኦርቶዶክሳውያን ፡ ሊቃውንትን ፡ እያሳደዱ ፡ ይገኛሉ ፤ ስለዚህ ፡ ምዕመናን ፡ በተዋሕዶ ፡ ስም ፡ ተደብቀው ፡ የሚዘሩት ፡ እርምና ፡ በዚያ ፡ በጉባዔ ፡ ኬልቄዶን ፡ የተደነገገውን ፡ ባህለ ፡ ምንታዌ ፡ እያሽሞነሞኑ ፡ ይዘውት ፡ እንደሚገኙ ፡ አውቀን ፤ ከሱስንዮሳውያን ፡ ዳግም ፡ ጥምቀት (እርምና) ፡ ራሳችነን ፡ ነጻ ፡ እናወጣ ፡ ዘንድ ፡ ጥሪዬን ፡ አስተላፋለሁ፡፡

1 comment:

  1. የሰላም አምላክ ክርስቶስ እውነትን ይግለጽ።

    ReplyDelete