Monday, November 5, 2018

“ሃይማኖት መሢሐዊት” ክፍል ሁለት


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!!!
ይድረስ ምኑንም ሳትረዳዉ ከአባ ስምዓኮነ እና ከዓባይነህ ካሴ ገልብጠህ ለጠየቅኸኝ “Habtamu St” ለሚሉህ ግለሰብ
በአስተያየት መልክ ለሰጠኸኝ ጥያቄ መልስ
ሃይማኖት መሢሐዊትክፍል ሁለት

======================
ሌላ ዝርዝር ሐተታ ሳልገባ በቀጥታ ወደ ጥያቄዎችህ መልስ አመራለሁ ፡፡
1‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “እንደው ሲጀመር ታድሶ፣ፔጤ(ቅባት)ቻሱን ሰጠን ልንከራከር አንችልም።ምክነያቱም ሌሎች ከተዋህደ ውጭ ክርስተያን አይባሉም”›››››››››››››››› ብለሃል ይህ የድኩማን ሀሳብ ነዉ ፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያን የተሰኘነዉ በክርስቶስ ተቀብዖ ስለመሆኑ መጽሐፈ ምሥጢር እንዲህ ይለናልእኛ ግን ከእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አፀድ የሚያወጡንን መምህራን አንሻም በስማቸዉ ልንጠራ አንፈቅድም መምህራችን ክርስቶስ መምህራችሁ አንድ ክርስቶስ ነዉና ለራሳችሁ መምህራንን አትሰይሙ ብሎናልና።ስለዚህም እኛ ክርስቶስ እንደተባለ ክርስቲያን መሲሕ እንደተባለ መሲሐውያን ናዝራዊ እንደተባለ ናዝራውያን እንባላለን።የእኒህ የሦስቱ አጠራር ትርጓሜአቸዉ በአንድነት የተቀባ የተቀቡ ተብሎ ይተረጎማልናመጽሐፈ ምሥጢር 2049 ፡፡ ስለዚህ ቅቡዓን እኛ ክርስቶሳዉያን እንደምንባል መጽሐፍ ቅዱስ ይገርልናል ፡፡ እስኪ አንተ ንገረንተዋሕዶዎችብሎ ክርስቲያኖች የሚል ምን ማስረጃ ???????
2‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “መተቸት ትችላለህ እንጂ መቼም አንድ አይደለንም ። እንደማንገናኝም ይሄው እየቃዠህ ነው”›››››››ብለሃል ወዳጄ ትችት ብቻ ሳይሆን ቃለ ግዘት ሁሉ እነግርሃለሁወመኑ ሐሳዊ ዘእንበለ ዘይክሕድ ወይብል ከመ ኢየሱስ ኢኮነ መሢሐ--ኢየሱስ መሢሕ አይደለም ብሎ ከሚክድ በቀር ሀሰተኛ ማን አለ” 1 ዮሐ 222
3‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “የሚስጥረ ስላሴን ይንድብናል የህልውና መገናዘብን ያፍልስብናል።”››››››››››››ብለሃል በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ምሥጢረ ሥላሴን ያጸናል እንጅ አይንድም ስላሴ በአብ ልብነት ያስባሉ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያዋን ሁነው ይኖራሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ሆነ ማለት ነው:: ዮሐ :፳፮-፳፯:: በህልውናም አብ ልብ ወልድ ቃል መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ናቸው፡፡በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ማለትም በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያው ሆነ ማለት ስለሆነ ህልውና አይፈርስም ይፀናል እንጅ፡፡

4‹‹‹‹‹‹‹‹ “እየሱስን ከፍጡር እንዳንዱ ያደርግብናል”››››››››ብለሃል ኢየሱስን ከፍጡራን እንደ አንዱ ያደርገዋል ላልከው አፈወርቅ ዮሐንስ ዳዊት የተናገረውን ሲተረጉም "ወለጳውሎስ ሳምሳጢ ይትዋስኦሙ በእንተ ሀልዎተ ወልድቀዳማዊ--እለ ሳምሳጢ ጳውሎስንም ቅድመ ዓለም እንደነበረ ተናግሮ አስረዳ በብሂሎቱ መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም ወክመ ባሕርዩ ኢኮነ ፍጡረ" በማለት ድር 3 78 ላይ ተርጉሞታል ፡፡ ሳዊሮስም በሃይማኖተ አበው 87 17-19 ባለው ሐተታው " ወዝ ግብር ኢኮነ ክፉለ ከመ አሐዱ እም ነቢያት" ብሎ ከፍጡራን የተለየ የባሕርይ እንደሆነ አትቷል፡፡አንብብ፡፡ ክብር የማይሻ አምላክ መሆኑን ካመንክ "ተዋሕዶ የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርይ ክብሩ ከብሮ ተወለደ ነው" ስትል ምን ጎድሎበት በባሕርይ ክብሩ ከበረ? በባሕርይ ክብሩ ከበረ የሚል የት ይገኛል? የባሕርይ ክብሩስ ምንድን ነው?በባሕርይ ክብሩ ከበረ ስትሉ የባሕርይ ክብሩን አጥቶ ነበርን?



6‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “አባቶቻችን በትምርታቸው አውግዘውታል”›››››››ብለሃል ይህም የነ ስምዐ ኮነ ተረት ተረት ነዉ የትኛዉም ቦታ ላይ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለዉን ያወገዘ የለም እንዲያዉምዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ ቅዱስ ወረሰዮ ቅዱሰ ወማኅየዌ--የአዳምን ባሕርይ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ያከበረዉ የባሕይ አምላክ ያደረገዉ እሱ ነዉብለዉ እልመስጦአግአያ 25 ላይ ገልጸዋል እንጅ ሲያወግዙት አልተመለከትንም ፡፡ ነቢዩ ክቡር ዳዊት ቀብዓከ እግዚአብሔር አምላክከ ቅብዓ ትፍሥሕት እምእለ ከማከ(እግዚአብሔር አምላክህ ከባለንጀሮችህ ይልቅ የደሥታ ዘይትን ቀባህ)” ብሎ  የተናገረውን ረቂቅ ትንቢታዊ ምሥጢር ሐዋርያው ጳዉሎስ ዘይኄይስ እምእሊአሆሙ(ዕብ 1 9) ሲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እስመ ለእግዚእ ክርስቶስ አኮ በመሥፈርት ዘተውህቦ መንፈስ(መንፈስ ቅዱስ ለክርስቶስ በልክ በመጠን የተሰጠው  አይደለም)” (ድር 3 87) ሲል ቅዱስ ቄርሎስ ደግሞ በቅብዓት ነከራ እምእለ ተሳተፎሙ ዘውእቶሙ ንሕነ(እኛ ካገኘነው በሚበልጥ ክብር ከበረ እንዳለው እወቅ) እምእለ ተሳተፎሙ የተባልን እኛ ነን (ጰላድ 155 8 - 9) ብለዋል ፡፡
7‹‹‹‹‹‹ “ስላሴን ድነውበት አድነውበት ይኖራሉ ማለት”››››››››ብለሃል ይህም መባሉ የሥላሴ የባሕርይ ሕይወታቸዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉና ሕያዋን ይሆኑበታልና  ድነዉበት አለ በእሱ ደግሞ እኛን ሕያዉ በጸጋ ያደርጉናልና ማኅየዊ በመንፈስ ቅዱስ ቢባሉ የሥላሴን ከዊን ማስረዳት ነዉ እንጅ ስህተት አይደለም ፡፡ ጥያቄ ሥላሴ በአብ ልብነት ያስባሉ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያዉ ሁነዉ ይኖራሉ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልታብራራልኝ ይቻልሀል?
8‹‹‹‹‹‹‹‹‹ከመለኮት የተወለደውን መለኮት ከመለኮት የሰረፀውን መለኮት ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሕያው ሆነ ማለት ነው።ብለሃል፦”›››››››ወዳጄ ይህንን አላልኩም ብየ ከሆነ ብታሳየኝ ፡፡ ነገር ግን ከመለኮት አብ የተወለደዉን ወልድን መለኮት ከመለኮት አብ የሠረፀዉን መንፈስ ቅዱስን መለኮት ብየ ብናገር ምንድር ነዉ ስህተቱ?ከአብ የተወለደዉ መለኮት እንጅ ምን ይባላል??????
9‹‹‹‹‹‹ “ምን ለማለት ፈልገህ ነው? / ይቅር ይበልህ አብ፣ወልድ በመንፈስ ህያው የሚሆኑት? ወይስ ማነው? መንፈስ የምትለው ማንን ነው? አብና ወልድ የራሳቸው የሆነ መንፈስ ቅዱስ አላቸው የላቸውም? ”››››››››››››ብለሃልወዳጄ አንተ የሥላሴን ከዊን የተረዳህ አይመስለኝም ፡፡ አዎ ሥላሴ ሕያዉ ሁነዉ የሚኖሩበት የባሕርይ ሕይታቸዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ ፡፡ ይህ መንፈስ የተባለም መንፈስ ቅዱስ ነዉ ፡፡ ለአብና ለወልድ መንፈሳቸዉ አንድ መንፈስ ቅዱስ እንጅ የተለያየ አይደለም ፡፡ ለዚህም ሠለስቱ ምዕት  “አብ  ብርሃን  ወውእቱ ለሊሁ ወብርሃን ለወልድ ወብርሃን ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ ብርሃን(አብ ራሱ ብርሃን ነው ለወልድም ብርሃን ነው ለመንፈስ ቅዱስም ብርሃን ነው አንድ ብርሃን ነው) ወልድ ቃል ውእቱ ለሊሁ ወቃል ለአብ ወቃል ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ ቃል(ወልድ ራሱ ቃል ነው ለአብም ቃል ነው ለመንፈስ ቅዱስም ቃል ነው አንድ ቃል ነው) ወመንፈስ ቅዱስ ለሊሁ ውእቱ መንፈስ ወመንፈስ ለአብ ወመንፈስ   ለወልድ አሐዱ ውእቱ መንፈስ(መንፈስ ቅዱስ ራሱ እስትንፋስ ነው ለአብም እስትንፋስ ነው ለወልድም እስትንፋስ ነው አንድ መንፈስ ነው ብለዋል (መዝ. ሃይማኖት 1 3) ፡፡
10‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹“በስልጣን በአምላክነት አንድ ናቸው ካል በመንፈስ ይበላለጣሉ ማለት ነው?”››››››››ብለሃል ወንድሜ አብ አባት ወልድ ልጅ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ስንላቸዉ ይበላለጣሉን?ስለመበላለጥ ምን ትቀባጥራለህ፡፡ አምላክ ወልደ አምላክ በባሕርየ መለኮቱ ሕያዉ ወማኅየዊ ሲሆን ሞተ በሥጋ የተባለለት ለምን ይመስልሀል?መዋቲ ሥጋን ተዋሕዶ መዋቲነትን ገንዘብ በማድረጉ አይደለምን?፡፡ ታዲያ ሞተ በሥጋ ሲባልለት በሥልጣን ይበላለጣሉ ማለት ነዉን? አይደለም ስለሥጋ እንግድነት ተነገረ እንጅ ፡፡ ተቀብዐ መባሉም ሕያዉ ሲሆን ሞተ እንዳለዉ ያለ ነዉ ፡፡
 11‹‹‹‹‹‹‹‹አብንና ወልድን ምን እያልክ እንደሆን ገብቶሀል? ህይዋን ያደረገው የማንኛው መንፈስ ነው?”›››››››› አብንና ወልድን  አባትና ልጅ የሆኑ አንድ አምላክ እላቸዋለሁ ሕያዉ ያደረገዉ የባሕርይ ሕይወታቸዉ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነዉ፡፡ አንብብ መጻሕፍትን
12‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቆይ እንጂ ከሆነ የመንፈስ ቅዱስ ህይወትነት በአብ ሰጭነት ከተቀበለ የአብን ልብነት ምን ጊዜ ገንዘብ አድርጎ ነው?”›››››› ብለሃል ይህንን ዮሐንስ 5 ቁጥር  26 ተመልከትና ድርሳነ አፈወርቅ ድርሳ 2 አብረህ አስተባብረህ ተመልከተዉ ያን ጊዜ ቃል ከሥጋ ጋር በአካል በባሕርይ በግብር ሲወለድ ሥላሴ በባሕርይ ሥራ አይለያዩምና ቃል በተለየ አካሉ ሥጋን ሲዋሐድ አብም በተለየ አካሉ በተለየ ግብሩ ልቡና አእምሮ በመሆን ወለደዉ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት እስንፋስ ሆነዉ ፡፡
13‹‹‹‹‹‹‹‹ “በምንስ ቅጵበት ደቂቃና ሰዓት ነው አምላክ የሆነው?”››››››››ይህንን መልስ በጥያቄ በምን ቅጽበት አምላክ ሰዉ ሆነ?በምን ቅጽበት ሰዉ አምላክ ሆነ???
14‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቃል ከባህሪ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ምን ጊዜ ተለይቶ ነው አብ የሚሰጠው?”›››››ወዳጄ ቃል ከባሕርይ ሕይወቱ ተለይቶ ሳይሆን የባሕርይ ሕይወትን ገንዘቡ ያላደረገ ሥጋን ተዋሕዶ የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ በማድረጉ ሰጠዉአብሰ ያፈቅር ወልዶ ወኩሎ ኩነኔሁ አወፈዮ ለወልዱ--አብ ልጁን ይወደዋልና ሁሉን በእጁ ጭብጥ በእግሩ እርግጥ አድርጎ አስገዛለትዮሐ 334 ወበከመ ለአብ ቦቱ ሕይወት ኀቤሁ ከማሁ ለወልድኒ መሀቦ ሕይወተ ከመ ይኩን ሕይወት  ኀቤሁ እስመ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ እጓለ እመሕያዉ ዉእቱ--ለአብ በራሱ ሕይወት እንዳዉ እንዲሁ ለወልድም ሕይወት ይኖረዉ ዘንድ ሕይወትን ሰጠዉ የእግዚአብሔር ልጅ የሰዉ ልጅ ነዉናዮሐ 5 26  ተመልከት ፡፡ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ መባሉ ገንዘቡ ባላደረገ በሥጋዉ ነዉ ፡፡ወዘሂ : ተብህለ : ከመ : ውእቱ : ተሰብሐ : እምአብ : በዐይ : አምሳል : ተሰብሐ : እምአብ : እንዘ : ውእቱ : እግዚአ ስብሐት (ከአብ በክብር እንደተገለጠ የተነገረውም የክብር ባለቤት ሲሆን በምን ነገር ከአብ ተገለጠ ይባላል) ወግብሩሂ : ጥዩቅ : ከመ : ዝንቱ : ነገር : ይመስል : ከመ : ዘይብል : ፍጡር : ውእቱ(ይህ ነገር ፍጡር የሚል እንደሚመስል ነገሩ ግልጥ ነው) ወኢተብህለ ዝንቱ ዘእንበለ ዳእሙ በእንተ ሥርዓተ ትስብእት(ሰው ስለመሆኑ እንጅ ለሌላ አልተነገረም) ለሊሁ ይነሥእ ስብሐተ እምአብ በትስብእቱ እንዘ ለሊሁ ስቡሕ በመለኮቱ(እሱ የባሕርይ አምላክ ሲሆን ሰዉ በመሆኑ ከአብ ክብርን ገንዘብ ያደርጋል)” ብሎ በሃ.አበው( 79 74:) ብሏል ፡፡ ስለዚህ ተቀበለ የምንለዉ በሰዉነቱ ሞተ እንዳልነዉ ሁሉ በሰዉነቱ ተቀበለ ፡፡
15‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “.በቅባት ከብሮ የባህሪ አምላክ መሆን ይቻላልን?መጵሃፍ ቅዱስን አለቦተው ጠቅሶና መንፈስ ቅዱስ አለቦተው መጥራት ለምን አስፈለገ?”›››››››››››ይህም የዓባይነህ ካሴ ተረት ተረት ነዉ ፡፡  መዝ 447 አንብብና ተናረዳዉ በቅብዓት ከብሮ አምላክ ወልደ አምላክ የባሕርይ ልጅ የባሕርይ አምላክ ሆኗል ፡፡ አለታዉና አለ ጊዜዉ ሳይሆን በጊዜዉ በቦታዉ እንደምሥጢሩ አገባብ ተጠቅሶልሃል ፡፡
16‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቅባት ክርስቶስ ከተወለደ በፊትም ነበያቶች ከልደቱም በኃላ እስካሁን በቅባት ያልከበረ የለም ከዲያ የጸጋን ልጅነት እንጂ የባህሪ አምላክነት ያገኘ ማን አለ?”›››››››››››ወዳጄ እነሱ ቢቀቡ የጸጋ ልጅነትን አገኙ ክርስቶስ የተቀባዉ ቅብዓት ደግሞዘይኄይስ እምእሊአሆሙተብሎ በዕብራዉያን 19 ላይ የተነገረለት ነዉና ምእና በፀጋ ሲከብሩ እሱ የባሕርይ ክብር ከብሮ ክርስስ ተባለ እኛ ምእመናን የጸጋ ክብር ከብረን ክርስቶሳዉያን ተባልን ፡፡
16‹‹‹‹‹‹‹.”የመንፈስ ቅዱስን ያለንን እምነት ለመሸርሸር ይሆን?መንፈስ ቅዱስን የሰደበ አጽያቱ አይሰረይለትም”››››››አዎ ወዳጄ ሳታዉቀዉ ቫዝሊን ኮኮስ ሌላም ሌላ እያልክ የምትሰድበዉ አምላክ ፍርድን ያስረክብህ ዘንድ አለዉና ተጠንቅቀህ እመን ማቴ 1232
17‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹”.ቅባት እንደ ሲጀመር ከእየሱስ ልደት(ተዋህዶ ወይም ሚስጥረ ስጋዊ(ስላሴ))የሚያገናኛቸው ነገር አለ?”›››››››አዎ አለዉ ወዳጄመንክረ ገብረ ወልደ እግዚአብሔር ዉስተ ከርሠ እሙ ሶበ ፈጸመ ሥርዓተ ተዋሕዶ ወቅብዓት ምዕረ ከመ ቅጽበተ ዓይንእንዳለ አአዉሳብዮስ የእግዚአብሔር ልጅ ሰዉ ሲሆን በእናቱ ማኅፀን የፈጸማቸዉ የማይነጣጠሉ ሁለት ዓበይት ምሥጢራት ናቸዉና ይገናኛሉ ፡፡
18›››››››››.”በኅቱም ድንግልና እንዲወለድ ማድረግ የመንፈስ ቅዱስ ግብር ብቻ ነው?የአብና የወልድ ሊሆን አይችልም?”››››››ወዳጄ እኛ የመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነዉ መች ወጣን ይህንን ከንቱ ሀሳብ ገልብጠህ ያመጣህላቸዉ እነ ስምዓኮነለሊሁእያሉ ለአንድ ለወልድ ብቻ ያከናንቡታል እንጅ ፡፡
19›››››››››› “መንፈስ ቅዱስ የተለየ መንግስት አው?”›››››››››መንግሥተ ሥላሴ አንድ እንጅ የተለያየች አይደለችም ፡፡
20‹‹‹‹‹‹‹‹ “.መንፈስ ቅዱስ አከበረው ስትል በአካል ነው በጸጋ?”›››››››››››ሲጀመር እንዲህ ተደርጎ አይጠየቅም ፡፡ ምክንያቱም ሥላሴ እኛን በፀጋቸዉ ሲያከብሩን ክብራቸዉ ከአካላቸዉ አይለይምና ፡፡ ስዚህበባሕርይ ነዉ በጸጋብለህ ጠይቅ ፡፡ ዝም ብለህ ሊቅ ናቸዉ የሚባሉ በስምና በካባ የተሸፈኑ ወሽመጣም ከሐዲዎች የጻፉትን ገልብጠህ ሳታላምጥ አትዋጠዉ ፡፡ ስለዚህ ያከበረዉ በባህርያዊት ኅድረት ነዉ ፡፡
21››››››››› “ቅባት ምን ማለት ነው?”›››››››ቅብዓት ማለት ጥሬ ትርጉሙ ክብር ማለት ነዉ፡፡ ጣዕመ ምሥጢሩ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነዉ ፡፡ አክሲማሮስ የብራና ሐዊ የብራና አዕማደ ምሥጢር የብራ አክሲማሮስ ዘእሁድ 41 እና ዘሠሉስ 218 አንብብ ፡፡
22‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “አብም፣ወልድም፣መንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፤ፍጹም ገጵ፤ፍጹም መልክ አላቸው አይደል።ወልድን ሲያከብረው ተደምሮት ነው እንዴት ይመስልሃል?”››››››››››››በአካል በባሕርይ በግብር የተዋሐዱት ቃልና ሥጋ ሲሆኑ ተከፍሎተ አካል ሳይኖር ከአብ ስለከዊነ ትስብእት ተወለደ ተደምሮተ አካል ሳይኖር በመንፈስ ቅዱስ ሕያዉ ሆነ ፡፡ መዝ 27 ኢሳይያስ 111 ኢሳይያስ 611 ሳዊሮስ ሃይ.አበዉ 87 17-19 አንብብ ፡፡
23‹‹‹‹‹‹‹‹‹.“የአብም፤የወልድም፤የመንፈስ ቅዱስም የራሳቸው የሆነ መንፈሰ ቅዱስ አላቸው የላቸውም?ነበያቶች፤ሐዋርያቶችን...የጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያገኙ የአብ ነው፤የወልድነው የመንፈስ ቅዱስ ነው?”››››››የላቸዉም መንፈስ ቅዱስ አንድ ነዉ ፡፡ ለነቢያትም ለሐዋርያትም ጸጋ የተቀበሉበት መንፈስ ቅዱስ የአብ የወልድ የባሕርይ ሕይወታቸዉ እሱ ነዉ፡፡አብ ብርሃን ወውእቱ ለሊሁ ወብርሃን ለወልድ ወብርሃን ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ ብርሃን(አብ ራሱ ብርሃን ነው ለወልድም ብርሃን ነው ለመንፈስ ቅዱስም ብርሃን ነው አንድ ብርሃን ነው) ወልድ ቃል ውእቱ ለሊሁ ወቃል ለአብ ወቃል ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ ቃል(ወልድ ራሱ ቃል ነው ለአብም ቃል ነው ለመንፈስ ቅዱስም ቃል ነው አንድ ቃል ነው) ወመንፈስ ቅዱስ ለሊሁ ውእቱ መንፈስ ወመንፈስ ለአብ ወመንፈስ   ለወልድ አሐዱ ውእቱ መንፈስ(መንፈስ ቅዱስ ራሱ እስትንፋስ ነው ለአብም እስትንፋስ ነው ለወልድም እስትንፋስ ነው አንድ መንፈስ ነው ብለዋል (መዝ. ሃይማኖት 1 3) እንዳሉ ሠለስቱ ምዕት ፡፡
24‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቅባት ትርጉሙ መንፈሰ ቅዱስ ማለት ነው?አይደለም” ›››››አንተ አይደለም ብትል መጻሕፍት ጆሮ ግንድህን እያጣፈሩ ያናግሩሃል ፡፡ አንብብ ዕብራዉያን 19 ላይ የተጠቀሰዉ ቅብዓት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ 1 ዮሐ 2 20-26 ያለዉን አስተባብረህ ተመልከተዉና ከላይ በአክሲማሮስ ከነገርኩህ ጋር አስማማ ፡፡
25‹‹‹‹‹‹‹‹ “ቅባት ማለት አክባሪና ተከባሪ ማለት ነው”››››››የት አገኘኸዉ?መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አስቀምጥና እንነጋገርበታለን ፡፡
26‹‹‹‹‹‹‹ “መንፈስ ቁዱስ ሲጨመር ደግሞ ወልድ በቅባተ መንፈስ ቅዱስ ተቀብለ ዐዋቂ አድስ አምላክ ሆነ ማለት ነው። "እኛ ተዋሕዶች ቃል ያለ መለወጥ ሰው እንደሆነ እንጂ በሰው እንዳደረ አናምንም”››››››››› እናንተ ካሮች አትመኑ እንጅ ኦርቶዶክሳዉያን መጻሕፍት ግን በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ብለዉ ያምናሉ ፡፡ ዳሩ ግን ቃል ሥጋን አከበረ ስለምትሉ ቃል በሰዉ ላይ አደረ የሚል ሰይጣናዊ እምነት አላችሁ ፡፡ አንተ ዝም ብለህ እነ ስምዓኮነ ሲጨንቃቸዉ የጮሁትን ይዘህ ጩህ ፡፡
27‹‹‹‹‹‹‹‹ “ስሕተቱ ቅባዓ መንፈስ ቁዱስ ቢቀበል ከአብ ተወለደ መባሉ ነዉ”››››››››ይህም እንጅ ወልድ ስለ ከዊነ ትስብእት ከአብ አልተወለደም በቃል ልጅነት ልጅ ሆነ እያላችሁ የጸጋ ልጅ አድርጋችሁ ስምታኑት እንጅ እሱስ ልጅነት ስለሌለዉ ስለ ባዕድ ሥጋ ከአብ ተወልዷል መዝ 27 አንብበህ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳ 2 አንብበዉ ፡፡
28‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “ስህተቱ አዲስ አምላክ የሚለው ነው አዲስ ሰው እንጂ አድስ አምላክ የሚል የትም የለም”›››››››አባ ስምዓኮነ መልአክ ላይ የሰፈረዉ ቀንዳሙ ሰይጣን ወደ ገልባጮኡቹ ተሸጋግሯል ፡፡ አባ ስምዓ ኮነ እሳቸዉ ስለታወሩ ሌላዉንም ያሳዉሩታል ፡፡ወሐደሰት በላዕሌሁ ልደቱ እንተ በሥጋ አጽንዐት ሎቱ (በመለኮት በተወለደው ልደት ላይ በሥጋ የተወለዳት ልደት ቃልን ዮም ወለድኩከ አሰኘችው በሥጋ የተወለዳት ልደት ደግሞ ቃልን ሐዲስ አምላክ አሰኘችው ፡፡ አንድም ቃል በሥጋ የተወለዳት ልደት ደኃራዊ ሥጋን ቀዳማዊ አሰኘችዉ (ድርሳን 24 8) ፡፡ዘበእንቲአነ አትሐተ ርእሶ--ስለእኛ ራሱን ትሑት አድርጎ ሰው የሆነ አምላክ እንደሆነ ይታመን ዘንድ ከመ  ተውህቦ ስም ዘመልዕልተ ስም እምአብ--ከስም ሁሉ በላይ ስም ከአብ ተሰጠው ፡፡ ከመ ይትአመን ሐዲስ አምላክ ደኃራዊ--ሐዲስ አምላክ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ ጰላድዮስ $ 7 ብሏል ፡፡ ታዲያ ይህ መጽሐፍ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አይደለምን?ስለ እዉነት እንነጋገር ከተባለ የሌለ ቃሉ ሳይሆን እናንተ ናችሁ ፡፡ አንብቦ ሳታነቡ የለም አትበሉ መንጋ ከብት ዝም ብለህ አትነዳ ፡፡ አባ ስምዓኮነ እንደሆኑ አንድ ጊዜ ስለካዱ ላይመለሱ ጉዞ ወደካቶሊክ ብለዉ ተያይዘዉታል ፡፡
29‹‹‹‹‹‹‹‹‹ “የሚባለው የሚገባህ ከሆነ አብ በልብነቱ ከዊን ልብነትን የራሱ ገንዘብ አድርጎ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በልብነት ህልው ነው”››››››››እንዲህ ከሆነ ወልድ ለተዋሐደዉ ሥጋ ልብ የሆነዉ ማን ነዉ?እንዴት?ምን ጊዜ?
30‹‹‹‹‹‹‹‹፤ወልድም በቃልነቱ ከዊን ለራሱ ቃልነትን ገንዘብ አድርጎ በአብ በመንፈስ ቅድስ በቃልነት ህልው ነው፤መንፈስ ቅዱስም ለራሱ ህይወት ነው ሆኖ በአብ በወልድ በህይወትነት(እስትንፍስነት)ሕልው ነው የሚባለው”››››››ህልዉ መሆኑን የሚክድ የለም ነገር ግን እነዚህን ሕይወትነትንና ልብነትን ገንዘቡ ያላደረገ ሥጋን ተዋሕዶ ሲገለጥ የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ በማድረጉ ተቀበለ ተባለለት ፡፡ ለወልድ በትስብእቱ ሕይወት የሆነዉ ማን ነዉ??
31‹‹‹‹‹‹‹‹ “መንፈስ ቅዱስ ለአብም ለወልድም የባህሪ ህይወትነት ገንዘባቸው ነው ስንል በልህውናቸው የጸና ነው ማለታችን ነው ወልድ መንፈስ ቅዱስም የባህሪ ገንዘቡ ነው።(ሃይ.አበ. 12439)መንፈስ ቅዱስ በህልውና የማይለየው ገንዘቡ ነው።እንዲውም (አይ.አበ..12338)ስጋስ ነባቢት ለባዊነት ነፍስፍ ያላቸው ፍጡር ነው ያልተፈጠረ ቃል ከእርሱ ጋር አንድ አካል አንድ ገጵ አንድ ባህሪ በመሆን ከእርሱ ጋር አንድ አደረገው እንጂ በማለት የስጋ ፍጡርነት ሳይጠፍ ቃልን በማዋህዱ የአብን ልብነት የመንፈስ ቅዱስ እስትፉስነት በህልውና ገንዘቡ አድርጎ የባህሪ አምላክ ሆነ፤ከባህሪ ክብሩ ሳይለወጥ ከሰመያት ወርዶ በማጸነ ድንግል ተወሰነ ብላ ተዋህዶ ሃይማኖት ታስተምረናለች”››››››››››በተናገርከዉ ሀሳብህ ተቃዉሞ የለኝም ፡፡ `ተዋህዶ ሃይማኖት” ላልካት ሀሳብህ ግን ተዋሕዶ የሚባል ሃይማኖት የለም ምሥጢር እንጅ ፡፡ አለ ብለህ ካሰብክ  መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አቅርብ ፡፡ ሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ እንጅ ተዋሕዶ አይደለም ፡፡እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን እግዚአብሔር ቃል ፍጹም ሥጋን ነሥቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆኑም እሱን ተዋሕዶ ከእመቤታችን እንደተወለደ እናምናለን  ብሏል ቅዱስ አባ ሱኑትዩ በሃይ.አበው(ምዕ 110 36)
       እናንተ ቅቡዓን የሃይማታችሁ ጥርየት ምንኛ መንፈስን ያድሳል!ኦርቶዶክሳዉያን እኛ ግን እነዚህን የረከሱ እምነቶችን ከእኛ እናርቃለን የማይለይ የማይከፈል የማይቀላቀል ተዋሕዶን እናምናለን ብሏል በሃ.አበው(ምዕ 113 1 19) ፤ የእነዚህን አበዉ ሃይማኖት ኦርቶዶክስን ከሚያድሱ ካሮች ራሳችሁን ጠብቁ
ዛቲ ሃይማኖት መሢሐዊት ዘትትአመን ባቲ ቤተክርስቲያን ቅድስት

ምስጋና ለሥሉስ ቅዱስ
ወለ ቅድስት ድንግል
ምስለ ክቡር መስቀል


2 comments:

  1. አንድ ጥያቄ ነበረኝ ድንግል ማርያም
    ሀ ፡ መለኮትን ወለደች
    ለ፡ እግዚአብሔርን ወለደች
    ሐ፡ ወልድን
    መ፡ ቃልን
    የትኛው ነው ትክክል የቱ ነው ስህተት ? አመሰግናለው

    ReplyDelete
  2. The Ethiopian orthodox church is the most corrupt, genocidal and unchristian in the world. Hundreds of thousands have died in the past 4 to 5 hundred years due to controversies created among the Tewahdos of Shewa and Kibeat of Gojam/Tigray. The controversies are created to achieve contemporary hegemony for the sake of being favoured by the government. This is even happening today. The church cares less if the people whom it says represent are killed, raped or burned alive, it supports always those in power. The most useless church that will die soon in favour of other religions from abroad, goodbye, goodbye Coptic and Orthodox church in Ethiopia

    ReplyDelete