፩. "ከማኀፀን ጀምሮ በአንተ ተጣልሁ። ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ
አምላኬ ነህ።" መዝሙር 22÷10 ብሎ በዳዊት አፍ እንደተናገረ፣
፪. አብ ለኢየሱስ ክርስቶስ በድንግል ማርያም ማህጸን እስከተጸነሰባት ስዓት ድረስ አባቱ ብቻ ነበር። በድንግል ማርያም ማሕጸን ሰው ከሆነባት ቀን አንስቶ እስካሁን እና ወደፊትም አባቱ ብቻም ሳይሆን አምላኩም ነው።
፫. "ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፤ የተወለደ እንጅ ያልተፈጠረ"
★ ማሳሰቢያ፦ "የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ " የሚለው ኃይለ ቃል ብዙዎች የሚምታቱበት ስለሆነ እዚህ ላይ ቆም ብለን ልናብራራው ግድ ይላል።ሁላችሁም እንደምታውቁት ጌታ ኢየሱስ ሁለት ልደቶች አሉት ቅድመ ዓለም( ዓለም ሳይፈጠር) ከአብ ያለ እናት ተወልዷል።አብ አባት በመባሉ በዘመን አይቀድመውም፣ ወልድም ልጅ በመባሉ ከአብ አያንስም። ስለሆነም አብ ወልድን ወለደው እንጂ ፈጠረው አንልም።
፬. ሁለተኛው ልደቱ ከድንግል ማርያም ሰው ሁኖ የተወለደበቱ ነው።በመሆኑም አብ፣ወልድና፣መንፈስ ቅዱስ የፈጠሩትን ሥጋ በመዋሐዱ ( ሰው መበሆኑ) "የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ "እንዲሉ አባቶች። ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ ብቻም ሳይሆን ፍፁምም ሰው ስለሆነ በሥጋው ፍጡር ነው። ይህ ትክክለኛው ምሥጢረ ሥጋዌ ነው። ሰውና አምላክ ስንል ፈጣሪና ፍጡር ማለታችን ነው። ልብ በሉ አሁንም እንዲህ ሲባል እንደ አሪዮስ ፍጡር አለው የሚሉ አሉ። አሪዮስን አባቶች ያወገዙት ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ስላለ እንጂ በሰውነቱ ፍጡር ስላለ አልነበረም።
"በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል።" ልብ በሉ ወገኖቼ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር የሚተካከለው( እኩል) የሚባለው በመለኮቱ እንጂ በሰውነቱ አይደለም።
፠ በሥጋውማ መላእክትን እንዳይሞቱ አድርጎ የፈጠረ ጌታ የሞትን ጽዋ በመቅመሱ እንኳን ከአብ ከመላእክትም አነሰ ተብሎለታል።
፠ "ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አሳነስኸው፤… ነገር ግን በእግዚአብሔር ፀጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፣ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።" ዕብራውያን 2÷7_9
፠ "ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም ዐርጋለሁ " ዮሐንስ 20÷17
፠ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" ኤፌሶን 1÷3
፠ " በአምላኬ መቅደስ… የአምላኬንም ስምና የአምላኬንም ከተማ ስም፣ ማለትም ከሰማይ ከአምላኬ " ራእይ 3÷12 እና ሌሎችም የኢየሱስ አምላክ የሚሉት ጥቅሶች የሚያስረግጡልን እውነት አንድ ነው እርሱም ኢየሱስ በሥጋው ፍጡር መሆኑን ( በመለኮቱ አላልኩም ደግማችሁ ልብ በሉ።)
፠ " እግዚአብሔር አብ ውእቱ አቡሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በህላዌ መለኮቱ … እግዚአብሔር አብ አምላኩ ለወልድ ውእቱ በእንተ ትስብእቱ።"
፠ ትርጓሜ ፦ "እግዚአብሔር አብ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርየ መለኮቱ አባቱ ነው። … ሰው ስለሆነ ወልድ እግዚአብሔር አብ አምላኩ ነው።ኤጲፋንዮስ ( ሃይማኖተ አበው ምእራፍ 54 ክፍል 1 ቁጥር 9)

No comments:
Post a Comment