Tuesday, November 20, 2018

“እንዘቦ በክሕደት ያወግዙ ካልአ--እነሱ በክሕደት ሳሉ ሌላዉን ያወግዛሉ”



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
እንዘቦ በክሕደት ያወግዙ ካልአ--እነሱ በክሕደት ሳሉ ሌላዉን ያወግዛሉ
=============================================================
የዛሬዋ መልእት የምታተኩረዉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ቅዱስ ሲኖዶስና የዉግዘት ሥርዓቱ  ላይና የሚናገሩትን በማያዉቁ ቤተ አይሁድ ካሮች ላይ ይሆናል ፡፡ በዚህ ላይ አንተ ምን አገባህ ሲኖዶሱን የምትከስ የምትወቅስ ሌላም ሌላም ሀሳቦችን የምታንሸራሽሩ ሰዎች አትታጡም፡፡ ይሁን እንጅ የምንነጋገርበት ጉዳይ የሃይማኖት ልዕልና እንጅ የሲኖዶስ ልዕልና እስካልሆነ ድረስ አስፈላጊዉን ግብዓት የማስቀመጥ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነዉና የበኩሌን እል ዘንድ እሻለሁ ፡፡ የኢትዮጵያችን ሲኖዶሰ ክርስትና ከተወሰኑ አሠርት አመታት ወዲህ ልዕልናዉ አስቸጋሪና አዳጋች ሁኔታ ላይ እየወደቀ መሆኑን እየታዘብነዉ እንጀኛለን ፡፡ 1980ዎቹ መግቢያ ላይ በከባድ መንግስታዊ ፈተና እና ጭቆና ዐራተኛዉን በትረ ያሬክ በግፍ አባረዉበት ራቁቱን የቆየ ከዚያም ነፍሰ ኄር አባ ጳዉሎስ የተረከቡበት ዘመንን አሳልፏል ፡፡ አሁን በሕይወት  ያሉት አባ መርቆርዮስ ሀገራቸዉን ለቀዉ ከወጡ በኋላ ሲኖዶሱ በአንድ የሆነ ማኅበር የሚመራ እስከሚመስል ድረስ ዝብርቅርቁ ወጥቶ እስከ አሁኗ ድረስ የወረደ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ፡፡ ባሳለፍነዉ 2010 ዓ.ም የመጽሐፉን ማንነት እኳን በደንብ አድርጎ ሳያይ በተለይ የሲኖዶሱ
አባላት ስንኳን ምሥጢሩን  የመጽሐፉን ሽፋን እንኳን ያላዩት እነሱ ለመጽሐፉ ዉግዘት ቀዳሚ ተዋናይ የሆኑ እንደነበሩ በጊዜዉ ታዝበናቸዋል ፡፡ ይሁን ይወገዝ እኔ ለምን ተወገዘ አይደለም ጠቤ ፤ ዳሩ ግን የአወጋገዙ ሥርዓት እንዴት ነዉ?እንዲያዉ ሲኖዶሱ ጉባዔ ኒቂያን ፣ ጉባዔ ኤፌሶንን ፣ ጉባዔ ቁስጥንጥንያን በስም ብቻ ነዉ የሚያዉቃቸዉ?እነኛ ጉባዔዎች ሲደረጉ በጉባዔዉ ላይ ትልልቅ አጀንዳ የሆኑት መናፍቃን የተሰኙት ሰዎች በጉባዔ ፊት የእምነት ክሕደት ቃላቸዉን ሰጥተዉ ሲጨርሱ ከመጻሕፍት አንደበት ኃይለ ቃል እየተጠቀሰ ብርቱ ክርክር ከተደረገ በኋላ  አልመለስ ካሉ አዉግዞ የመለየት ሥራ የተሠራባቸዉ ብርቅየ ጉባዔያት ነበሩ ፡፡ ዛሬ ወደቤታችን ስንመጣ ግን መጽሐፉን ያዘጋጀዉ አካል እንዲቀርብ አይፈለግም ፤ ለምን ያልን እንደሆነ ብዙ ክሕደት በካባ ተደብቆ እየተሸሞነሞነ የሚገኝ በመሆኑ ያ ካባ ከተገለጠ ጉድ ስለሚፈላ ቤቱን ዘግቶ አዉግዘናል የሚል ጩኸት በሩቁ ማሰማት ቀዳሚ አጀንዳዉ ሁኖ ዘወትር ይስተዋላል ፡፡ እኔ ደግሞ ይህንን ስመለከት በአንድ በኩል አዝናለሁ በሌላ በኩል ደግሞ እደሰታለሁ የማዝነዉ እናት ቤተክርስቲያን የሲኦል ደጆች እንዳይችሏት ፣ የገሃነም ልጆች እንዳይነግሡባት በደመ ክርስስ በምሥጢረ ኰኵሕ የተመሠረተች መሆኗን ስናዉቅላት ፤ እንዲህ የእቃቃ ጫወታ ተጫዋቾች እየዘፈኑባት ማየት እጅጉን ያበሳጫል ያናድድማል ፤ ዳሩ ግን ቤቱን ማጽዳት የሚቻለዉ አምላክ ቀስ በቀስ እየጠራረገ እንደሚያስወጣቸዉ በማሰብ ያ የሚጠራርግበት ጊዜ መቼ ይሆን?እያልኩ ዘወትር እተክዛለሁ ፡፡ የሚያስደስተኝ ደግሞ እነ ግዘት በጉንጩ በሃይማኖታቸዉም በማንነታቸዉም የማይኮሩ በመሆናቸዉ ወልደ አብን አወገዝን ብለዉ ጮሁ እንጅ አንዳችነንም አልጠሩንም ቤታቸዉን ዘግተዉ አወገዙት እንጅ ፡፤ በዚህም እነሱ የማይማመኑና ሥር የሌላቸዉ መጤዎች መሆናቸዉን እናረጋግጣለን ፤ ሥራ ያላቸዉ ቢሆኑ ኖሮ አዘጋጅና አሳታሚዉን ጠርተዉ እንወያይ ይሉን ነበር ፤ ነገር ግን ሁለመናቸዉ አልቦ ነዉና በሩቁ ብለዉ ጮሁ ፡፡ በዚህም እኔ እጅጉን ደስ አለኝ ፡፡ እነሆም በመጻሕፍት ከተማ ምንታዌን የሚሰብኩ እነሱ የተወገዙ በግዘተ አበዉ ተጠፍረዉ የተያዙ ሲሆኑ ሌላዉን ያወግዙ ዘንድ ይቻላቸዋል? “ወአበዊነሂ ቅዱሳን ኢመሀሩነ ንእመን በክርስቶስ ዋሕድ ከመ ዉእቱ ክልኤቱ ህላዌያት ወባሕቱ ለሊክሙ ትፈልጥዎ እንዘ ትብሉ ከመ እሙንቱ ይቤሉ እስመ ለክርስቶስ ቦቱ ክልኤቱ ህላዌያት እምቅድመ ይተዋሐድ ወእምድኅረ ተዋሕዶ ገብሩ ተዋሕዶተ ወእሙንቱሰ መሀሩ በኵሉ ጊዜ ወአጠየቁ ከመ አሐዱ ህላዌ ዉእቱ--ቅዱሳን አባቶቻችንም አንዱን ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ ፣ ሁለት አካል ብለን እናምን ዘንድ አላስተማሩንም ፤ እነሱ ከተዋሕዶ አስቀድሞ ለክርስቶስ ሁለት ባሕርያት ነበሩት ከተዋሕዶ በኋላ አንድ ሆኑ ብለዋል እያላችሁ እናንተ ትከፋፍሉታላችሁ እንጅ እነርሱ(አባቶቻችን) ክርስቶስ አንድ አካል ፣ አንድ ባሕር እንደሆነ በየጊዜዉ አስረድተዉ አስተምረዋል”.እንዳለ ቅዱስ ቄርሎስ በሃይማኖተ አበዉ ምዕ 75 ቁጥር 15 አበዉ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አንድ ግብር ብለዉ የሰበኩትን ወልድ ዋሕድ ክርስቶስን መንፈቁን አክባሪ መንፈቁን ከባሪ በማድረግ የከፋፈሉ ነዚህ አረማዉያን ራሳቸዉ በክሕደት ያሉ ሲሆኑ ሌላዉን የሚያወግዙ በመሆናቸዉ እጅጉን ያስገርሙናል ፡፡ 



“ዘኢተብህለ እምኀበ መኑሂ እምአበዊነ ቅዱሳን ቅድመ ወኢተእኅዙ ቦቱ ይእዜ ሶበ ፈቀዱ እሙንቱ ይግበሩ   ዓመፃሆሙ ሰበኩ ይትወከፉ ክልኤተ ህላዌያት ከመ ይቅልል ለሰማዕያን ከመ ይትወከፍዎ---ከቅዱሳን አባቶቻችን በማንም ያተነገረዉን ፤ እነሱ ዛሬ ክሕደታቸዉን ያላሙ ዘንድ በወደዱ ጊዜ ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል ብለዉ እንዲያምኑ አስተማሩ እንዲቀበሉት ለሚሰሙ ሰዎች ይቀል ዘንድ” ቄርሎስ ሃይ.አበዉ ምዕ 75 ቁ 16 ፡፡ ይህ አነጋር ደግሞ የሲኖዶሱንም ይሁን የሊቃዉንት ጉባዔ የሚባለዉን በደንብ አድርጎ ይገልጠዋል ፡፡ እሱም እነሱ የሚሰማዉን ሰዉ ጆሮ ለማግኘት ሲሉ “ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ብላ ታስተምራለች” እያሉ መርዛቸዉን ይተፋሉ ፤ በዚህ መርዛቸዉም ብዙ ምእመናንን እያስካዱ ይገኛሉ ፡፡ ይህንንም መርዝ አባቻችን አስተማሩት እያሉ ያታልሉበታል ፡፡ ለሰሚዉ ቀለል እንዲልላቸዉ ተዋሕዶን ይጠራሉ በተዋሕዶ ከበረ በማለት አንድነትን ያጠፋሉ ምታዌን ያሰለጥናሉ ፡፤ ዳሩ ግን የጥፋት ሰዎች ናቸዉና ሲያጠፉ ሲጠፉ ይራሉ እንጅ እዉነት በቤታቸዉ አትገኝም ፡፡ “የመናፍቃን ደቀ መዛሙርት ስለሆኑ ነገር በልባቸዉ ስላ ነዉ እንጅ ስለ ቅዱሳ አባቶቻችን እነሱ ይህንን እንዳልተናገሩ ከተናገሩ በነዚያ በመናፍቃን ትምህርት ምክንያት ሁለት ባሕርያት የማለት ክሕደትን ሊያስፋፉ ይወዳሉ ፡፡ እንዲሁ ደግሞ እነርሱ ይዘባበቱባቸዋልና በክሕደት ሳሉ ሌላዉን ሊያወግዙ ይሻሉ” ሃይ.አበዉ ዘቄርሎስ ምዕ 75 ቁጥር 17
ስለዚህ እኒህ ዉጉዛን አወገዝን እያሉ ቢዝቱ በመጀመሪያ ራሳቸዉ የተወገዙ መሆናቸዉን እንረዳለን ፡፤ ስለዚህም እነዚህ ከንቱ የሆኑ ሰዎች እነሱ እያወገዙ ከእነሱ ጋር ሕብረት ሊኖረን አይችልምና ጎጃም ጥያቄህን አጠናክረህ ቀጥል እስከ አሁን ድረስ ባለኝ የእንቅስቃሴ መረጃ ይበል የሚያሰኝ ነዉ ግፉበት ይህ ወፈ ገዝት የሆነ ትዉልድ አወገዝኩ እንዲህ አደረግሁ ቢላችሁ አትስሙት ምክንያቱም አባቱን ሳያዉቅ አያቱን የሚናፍቅ ብቻ ነዉና ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ አይሁድ ካሮች አምላክ ሰዉ ሆነ ሰዉ አምላክ ሆነ ብለን እናምናለን ይላሉ፡፡ ይህንን ይበሉ እንጅ የሚያምኑት ተዋሕዶ የአምላክነቱን ነገር የሚናገር እጅን የሰዉነቱን ነገር አብሮ የሚያወሳ አይደለም ፡፡ ለዚህም እንደ አብነት ብናነሳ ሞተ በሥጋ ብለዉ ይናገራሉ እናምናለንም ይላሉ ፤ በዚሁ አንጻር ተቀብዐ በሥጋሁ(በሥጋዉ ከበረ) ሲባሉ እንግዳ ፣ ዘላን ባዳ ፣ ምድረ በዳ ይሆናሉ ፡፡ በዚህም አያቆሙም ሞተ በሥጋ ብለዉ ያመኑትን አምላክ ፍጡር በሥጋ ተብሎ ሲነገራቸዉ እምቧ ከረዩ ይላሉ ፡፡ አያታቸዉ ንስጥሮስ “የእግዚአብሔር ልጅ(ቃል) በማያም ልጅ(በሥጋ) ቢያርበት ከበረ” ብሎ አስተማረ ፤ የልጅልጆቹ ቤተ አይሁድ ካች ደግሞ ቅርጹን ቀየር አድርገዉ “ቃ አክበሮ ለሥጋሁ ኮኖ ቅብዓት ለሥጋሁ” በማለት የአያታቸዉን አስተምህሮ በተዋሕዶ ስም ለጥፈዉ ይደናራሉ ፡፡ መጻሕፍት በዉስጣቸዉ ሲመረመሩ ደግሞ እነሆ በተዋሕዶ ቃል የሥጋን ሥጋም የቃልን ገንዘብ ገንዘብ በመደራረጋቸዉ አምላክ ወሰብእ ፣ እግዚእ ወገብር ፣ ፍጡር ወፈጣሪ ፣ ካህን ሊቀ ካህን ሲባል የሚኖር ነዉ ፡፡ ፍጡር ነዉ መባሉ ፍጡር የሆነ ሥጋ ተዋሕዶ ካመለወጥ የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ በማረጉ እንጅ ተለዉጦ ፍጡር ሆነ ፣ አምላክነቱን ለቀቀ ማለት አይደለም፡፡ እሱም ከእመቤታን ስለነሣዉ 3 ክንድ ከስንዝር ስለሆነዉ የሥጋ ባሕርይ እንጅ ስለ መለኮት የተነገረ አይደለም ፡፡ እያንዳንድህ አስተዉል ሞተ ብለህ የተናገርክለትና ያመንከዉ መዋ ሥጋን ተዋሕዶ መዋቲነትን ገንዘቡ በማደድረጉ ነዉ ፤ እነሆም ፍጡር በትስብእቱ ብለን መናገራችን ፍጡር ሥጋን ተዋሕዶ ፍጡርነትን በተዋሕዶ ገንዘቡ በማረጉ እንጅ ነዉ ፡፡ “ሞተ ክርስቶስ በእንቲአነ ከመ ይቤዝወነ--ክርስቶስ ያድነን ዘንድ ስለእኛ ሞተ ፤  ወሶበ ሞተ ወልድ ይትበሀል በእቲአሁ ዉእሰ ተወክፈ ዘንተ--ወልድ በሞተ ጊዜ ሞትን ገንዘብ አደረገ ተብሎ ስለእሱ ይነገራል ፤ ወዉእቱሰ ኢይመዉት በህላዌ መለኮቱ--እሱ ግን በባሕርየ መለኮቱ አይሞትም ፤ ወከመ ዝ እንከ ሶበ ፈጠረ ሥጋሁ በእንቲዘሁ ዉእቱ ከመ ፍጡር እስመ ሥጋ ዘተፈጥረ ረሰየ ሎቱ ወህላዌ መለኮቱሰ ኢፍጡር ዉእቱ--እደዚህም ሁሉ ሥጋን ፈጥሮ ስለተዋሐደ ፍጡር ይባላል የተፈጠረ ሥጋን ለእሱ ገንዘብ አድርጓልና ባሕርየ መለኮቱ ግን ፍጡር አይደለም”››››ቃለ ስምዓት 124 ቁ 28 እንዳለ ቅዱስ ቄርሎስ ፡፡  አስከትሎም “ወካዕበ ይቤ ንብል በእንተ ዝንቱ ዋሕድ ቃል አሐዱ ኅቡረ -- ዳግመኛም ስለዚህ ተቀዳሚ ተከታይ ስለሌለዉ በተዋሕዶ አንድ ስለሆነ ቃል ፤ ከመ ለሊሁ ፍጡር ወመዋቲ በሥጋ-- እሱ በሥጋ ፍጡር መዋቲ ነዉ ፤ ኢፍጡር ወኢመዋቲ በመለኮት--በመለኮት ግን ፍጡር መዋቲ አይደለም እንላለን ፤ መባሕቱ እስመ ሞትሰ ወተፈጥሮ ለሥጋ ዉእቱ--መፈጠርና ሞት ለሥጋ ነዉ ፤ ወህላዌ መለኮትሰ ነኪር ዉእቱ እም እሉ-- መለኮት ግን ከመፈጠርና ከሞት የራቀ ነዉ ፤ ወባሕቱ በእንተ ዘተዋሐደ ምስለ ሥጋ ንብል በእንቲአሁ ፍጡር ዉእቱ ወመዋቲ--ነገር ግን ሥጋን ስለተዋሐደ ፍጡር መዋቲ እንላለን ፤ ኢፍጡር እንከ ወኢመዋቲ በህላዌ መለኮት--በባሕርየ መለኮት ግን ያልተፈጠረ የማይሞት ነዉ ብለን እንናገራለን ፤ ወካዕበ ይቤ እመሰ ተወልደ ወተፈጥረ ንሬሲ እሎንተ ክልኤተ  ለዘይደሉ ቦሙ--ከተወለደ ከተፈጠረ እነዚህን ሁለቱን ለሚገባቸዉ እናደርጋለን” ቃለ ስምዓት 124 ቁ 29 በማለት መናፍቃንን ሲያሸማቅቃቸዉ እናስተዉላለን ፡፡ ቤተ አይሁድ ካሮች ሆይ የአምላክን ሰዉ መሆን የምታምኑ ከሆነ በሰዉነቱ የሚነገሩለትን መፈጠር ፣ መቀበል ፣ መክበር ፣ መታመም ፣ መሞት ፣ መራብ ፣ መጠማት …የመሳሰሉትን ነገሮች በአንድ እይታ መመልከት እንደምን ተሳናችሁ?ይህንን ቃ የተናገረዉ የመናፍቃን መዶሻ ቅዱስ ቄርሎስ ነዉ ታዲያ ቅዱስ ቄርሎስን የምታዉቁት ከሆነ በእምነት መምሰላችሁ የት አለ?የተፈጠረ ሥጋን ተዋሕዷልና ፍጡር በትስብእቱ  እንለዋን ብሎ ሲናገር እናተ ቄርሎስን ከአርዮስ ጋር ለመደባለቅ የምትፋትሩት የሐሰት ካባ እስከመቼ ድረስ ያዛልቃችሁ ይሆን?ብቻ ግን ሊቃዉንትንና መጻሕፍትን ያስቀረልን የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ፡፡ እንዲያዉ ታኩንም ዋሽታችሁ ፣ ገንዘቡንም ዋሽታችሁ ፣ ምሥጢሩንም ዋሽታችሁ ያዛልቃችኋል?አምላከ ቅዱሳን የሜቴክን ቀን ይስጣችሁ እንጅ ሌላስ አልልም ፡፡
እናንተ ቅቡዓን ወንድም እህቶቼ እኒህ ቤተ አይሁድ ካሮች እንደ አበደ ዉሻ ያንንም ያንንም መልከፍ ስለጀመሩ በጥንቃቄ ሁናችሁ ራሳችሁን ጠብቁ ፡፡ በሃይማኖታሁ አንዳም ጥርጣሬ አይግባችሁ ፡፡
ዛቲ ሃይማኖት መሢሐዊት ዘትትአመን ባቲ ቤተክርስያን ቅድስት
ምሥጋና ለሥላሴ ይሁን



No comments:

Post a Comment