ክፍል [1/2]
የድርጅቱ ስያሜ:- “ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡” ይላል::
ቅዱሳን አበው [ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል መነኮሳትና ሌሎችም የክርስቶስ ቤተሰቦች] የሚከተለውን ሲያደርጉ:-
፩ኛ. ሃይማኖትን ከምንፍቅና፤ ክርስትናን ከእርምና፣ ጽድቅን ከኃጢያት፤ እውነትን ከሀሰት በመለየት ትክክለኛውን መንገድ አሳዩን::
፪ኛ. ፍቅር አንድነትን፣ የዋኃት ትዕግስትን አስተማሩን::
፫ኛ. ስለ ክርስቶስ ሲሉ አንገታቸውን ለስለት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት አሳልፈው ሰጡ:: "ሰማዕታት የዚህን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሡ፤ ደማቸውን ስለ ክርስቶስ ፍቅር አፈሰሱ፡፡" እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም
፬ኛ. “አፌ የሰውን ልጆች ግብር እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ቅዱሳን አበው እኛ ኃጢያተኞች ሆነን ሳለ በሌሎች ሰዎች ላይ እንፈርድ ዘንድ አይገባንም በማለት ያለቅሱ ነበር እንዲያውም ስለኃጢያተኛው ሰው ይጸልዩለትም ነበር::
፭ኛ. አበው የአገልግሎትን ምንነት የሚያውቁት በመማርና በማስተማር ብቻ ሳይሆን በተግባር ነበር:: ለአገልግሎታቸው አንዳችም ነገር ክፍያን አይጠይቁም ነበር እንዲያውም የራሳቸውን ገንዘብና ጉልበት ምጽዋት ያደርጉ ነበር::
ድርጅቱ[የጨዋው ስብስብ = ማኅበረ ሰይጣኑ] ግን
1ኛ. በተቃራኒው ምንፍቅናንና ሃይማኖትን፤ እርምናንና ክርስትናን፤ ኃጢያትንና ጽድቅን፤ ሀሰትንና እውነትን ቀላቅሎ አሳየን::
2ኛ. በእውነተኛ ፍቅር ፋንታ ከንቱ[ሰይጣናዊ፣ ጊዜያዊ፣ የማስመሰል] ፍቅርን ሰበከን:: አበው አንድነትን ሲሰብኩልን ድርጅቱ መለያየትን፣ ዘረኝነትን አስተማረን፤ አበው የዋኅትን፣ ትግስትን ሲያስተምሩን ድርጅቱ ጥላቻን፣ ከንቱ ውዳሴን፣ የማስመሰል ትህትናን[ከዜሮ በታች] ትህትናን አስተማረን::
3ኛ. ስለ ገንዘብ፣ ስለ ዝና፣ ስለ ሥልጣን ሲሉ እራሳቸውን አራቆቱ፣ በሥጋ ከብረው በነፍስ ተሰደዱ:: ለክብራቸው ሲሉ ሰው አሳደዱ፣ ክርስቲያኑን አረመኔ አደረጉ:: “....... ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች. 3፥18-20) እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ የማህበሩ አባላትም ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸውም በነውራቸው ነው፥ አሳባቸውም ምድራዊ ነው::
አብ የተከለኝ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ነኝ ይልና የሰይጣንን ስራ ይሰራል፣
በአካፋ ይወስድና በማንኪያ ይመልሳል፣
ንዑስ አገልጋይ ነኝ ይልና የጀርባ አጥንት ነኝ ይላል፣
መንፈሳዊ ይመስልና ፖለቲካውን ሲያናፍስ ይውላል፣
የቤተ ክርስቲያንን ሙዳዬ ምፅዋት ባዶ ያስደርግና የእሱን ካዘና ይሞላል::
4ኛ. ድርጅቱ ግን በአባቶች ላይ የሚያደርገው ዘማቻ መጀመሪያ የእሱን[የድርጅቱን] ዓላማ ያሳካ ዘንድ በፀባይ፣ በትህትና በለሰለሰ መንፈሳዊነት[በእግር በራሳቸው ገብቶ ለማሳመን ይሞክራል] ይጠይቃል፤ ነገር ግን ቀድመው የድርጅቱን መጥፎነት፣ እኩይ ተግባራት የማያውቁ ከሆነ በቶሎው ይታለሉና ውስጠ ምስጢሩን ሳያውቁ አብረው ይሮጣሉ:: የሚገርመው ነገር ቢኖር “ጉንዳን የክረምት ምግቧን በበጋ እንደምትሰበስብ” ሁሉ ድርጅቱም በተለያየ አጋጣሚ በፀባይ፣ በትህትና ብቻ ካሳመናቸው አባቶች ጋር ቢጣላ የኅሊና እስረኛ አድርጎ ለማስቀመጥ የግል ገመናቸውን ከልጅነታቸው ጀምሮ ይሰበስብና ያስቀምጣል::
ካልሆነም እንደ ዶክመንተሪ ፊልም[የጤና ምርመራ ይደረግልዎት ይልና] ባለቤቱ በማያውቁት[ባለቤቱ በየዋኃነት፣ ድርጅቱ በሰይጣንነት ዓላማ] መልኩ ይዘጋጅና መረጃው በስውር ይቀመጣል:: ከዚያ በኋላ አሁንም በገሀድ እንደምናየው አንድ ጊዜ ለድርጅቱ[ለማቅ] አንድ ጊዜ ደግሞ ለእውነት እየቆሙ በሕይወተ ሥጋ እያሉ የቁም እስረኛ ሆነው የተቀመጡ እጅግ ብዙ አባቶቻችን አሉ::
ሁለተኛው ደረጃ የመያዣ ዘዴ ደግሞ የሚተገበረው ይብዛም ይነስም ጥቅም በሚፈልጉ አባቶች ላይ ነው:: ይህ አይነቱ ዘዴ “እከከኝ ልከክልህ” አይነት ሆኖ ለጋራ ጥቅም አንዱ የአንዱን ችግር ለመሸፈን ደፋ ቀና የሚልበት መንገድ ነው:: ክርስትናው ከተረሳ ውሎ አድሯል ዳሩ ግን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” እንዲሉ መንፈሳዊ ኃላፊነትንም ለገንዘብ ማግኛ የሚጠቀሙበት ጥቂት አይደሉም::
በመሆኑም ይችም ውለታ ናትና በስውር መዝገብ ተይዛ ትቀመጣለች:: ከዚህ በኋላ በልቶ መሸሽ የሚባል ነገር በድርጅቱ ዘንድ አይሰራምና እያንዳንዱ ጳጳስ ይሁን ካህን፣ ዲያቆን ይሁን ጨዋ ምዕመን፣ መንፈሳዊም ሆነ ፖለቲከኛ በድርጅቱ ሳንባ ካልተነፈሰ መከራ ነው:: እያንዳንዷ እንቅስቃሴው ሁሉ በድርጅቱ ፍቃድ ይሆናል ሳይወድ በግድ ለጥቅም ብቻ ብሎ ከርቸሌ ይገባል::

ሦስተኛው[የመጨረሻ እንዳልለው ሌላም ስለሚኖር] ዘዴው ደግሞ አባቶች የድርጅቱን ዓላማ፣ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ፣ አጀማመሩንና አሁን ያለበትን ደረጃ አንድ በአንድ የሚያውቁ ስለሆነ ከዚህ ድርጅት ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መገናኘት ስለማይፈልጉና ክፉ ሥራውን ስለሚያወጡበት፣ እንደ ፈለገውም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስራውን በማን አለብኝነት ይሰራ ዘንድ ስለማይፈቅዱለት ማጥመድ ይጀምራል:: እንዲህ የሚያደርጉ አባቶች “እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር” የሚል አቋም የያዙና ለማን፣ እንዴት፣ የትና መቼ ማገልገል እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለሆኑና የድርጅቱን ስድ አደግነት የሚረዱ በመሆናቸውና “በጎቼን ጠብቁ” ብሎ መድኅን ዓለም ክርስቶስ የሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዘወትር ጠዋት ማታ ደፋ ቀና የሚሉ ናቸው::
እነዚህን እንቁ አባቶች ደግሞ በእያንዳንዷ እንቅስቃሴያቸው ላይ አሁንም መረጃ ይሰበስብና ድርጅቱ በሚፈልገው መልኩ እንዲዘጋጅ ይደረጋል:: መቁረጥ መቀጠል ሥራቸው ነውና ከስብከት ላይና ከመዝሙር ላይ “እንዲህ አሉ፣ እንዲህ ብለው ተናገሩ” በማለት ከፊትና ከኋላ ያለውን ኃይለ ቃል ያስቀሩና እነሱ የፈለጓትን ብቻ ለይተው በማውጣት ለየዋኃን ምዕመናን ይናገሩና ምዕመኑ ጥርጣሬ እንዲያድርበት፣ ከቤተ ክርስቲያን እንዲርቅ፣ ስለ ሃይማኖቱ እንዳይማር፣ ቅዳሴ እንዳያስቀድስ፣ ኪዳን እንዳያደርስ ጠባሳ ያሳድሩበታል::

በዚህ ምክንያት በእውነት ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ የሆኑ ምዕመናን “ለምን ሃይማኖታችን ተነካ” ይሉና የውስጡን ስውር አጀንዳ ሳይረዱ እንደ በግ የሚነዱ እጅግ ብዙ ናቸው:: እውነታው ግን እንደዚያ ያደረጓቸው አባት ስህተት ሰርተው ሳይሆን ከድርጅቱ ጋር ስላልተስማሙ ነው ዓላማው ያልገባው ምስኪኑ ምዕመን ግን በከንቱ ይደክማል::
በዚህ ምክንያት ያለ አንዳች ምክንያት ከሃገራቸው የተሰደዱ፣ ከየደብሩ የተባረሩ፣ መናፍቅ፣ ተሃድሶ የተባሉ በጣም ብዙ ናቸው::
ስለዚህ ይህ ድርጅት “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው ወይንስ “ማኅበረ ሰይጣን”?
በዚህ ምክንያት ያለ አንዳች ምክንያት ከሃገራቸው የተሰደዱ፣ ከየደብሩ የተባረሩ፣ መናፍቅ፣ ተሃድሶ የተባሉ በጣም ብዙ ናቸው::
ስለዚህ ይህ ድርጅት “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው ወይንስ “ማኅበረ ሰይጣን”?
5ኛ. ይህ ድርጅት ግን ዓላማው ሌላ ስለሆነ አገልግሎትን በተግባር ከቶ አያውቀውም:: ስለ ሃይማኖት ምንነት ሳያውቁና ሳይገነዘቡ ጠዋት ጠዋት ብቻ ለኪዳን የሚሄዱ ከሆነ እንደ ታላቅ ሰው በማየት የማይገባውን ክብር ይሰጥና[ከዜሮ በታች ትህትና]፣ የክፍላት ሰብሳቢ፣ የግቢ ጉባኤ ኃላፊ ማድረግ ሥርዓት እንዲጣስ፣ ሃይማኖት እንዲጣረስ በር ከፋች ማድረግ:: የድርጅቱ አባላት በተለይ ደግሞ ግቢ ጉባኤ ላይ “እዩኝ እዩኝ ” ባይ ስለሆኑ ሳይማሩ ለማስተማር መሞከር፣ ምንም ሳያውቁ እራሳቸውን እንደአዋቂ መቁጠር፣ በማያገባቸው መግባት፣ እኔ ካልሰራሁት እኔ ካላየሁት ማለት፣ ከንቱ ውዳሴ መስጠት/ መቀበል ኧረ ስንቱ ጉድ ተዘርዝሮ ያልቃል:: ቤተ ክርስቲያን ስለተመላለሰ ብቻ የቤተሰብ እናት አባት፣ ልጅ በማድረግ ይመድብና እናትና አባት ስልክ በመቀያየር ሌላ አጀንዳ ይዘረጋሉ፤ ልጆችም ይበተናሉ:: በዚያው እንደጠፉ የቀሩም አሉ:: ሰው መጀመሪያ ስለ ክርስትናው ሳያውቅ ስለ ማህበሩ[ድርጅቱ] እንዲያውቅ ማድረግ እና ሁሌም የድርጅቱ ጠበቃ እንዲሆን መጎትጎትና ሌሎችም አንድ መንፈሳዊ ነኝ ከሚል ማኅበር የማይጠበቁ መጥፎ ተግባራት ናቸው:: ይህ ሁሉ ችግር የተፈጠረውም የአገልግሎትን ምንነት ካለማወቅ የመጣ መዘዝ ነው:: ደግሞ የሚገርመው ከሰራተኛው ላይ የሚወስደው ገንዘብ ሳያንስ ከተማሪው ላይ የሚዘርፈው ገንዘብ ነው:: “በልጅ አመኻኝቶ ይበላል አንጉቶ ” እንደሚባለው እስኪሰበሰብ ድረስ ስሙ በቤተ ክርስቲያን ነው ከተሰበሰበ በኋላ ደግሞ የድርጅቱ ነው:: ከዚህ በላይ ዓለም ላይስ ምን ይሰራል?
የገንዘብ ምንጭ ከተማሪዎች:-
ሀ/ ከእለት ጉርሳቸው በመቀነስ ለቤተ ክርስቲያን [ለነፍሳቸው] ሰጠን እያሉ ድርጅቱ ለእራሱ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ያውለዋል:: [ደብረ ማርቆስ ግቢ ጉባኤን መመልከት በቂ ነው የቀለበት መግዣ ሲያደርጉትና 95 ሺህ ብር እንደመለሰ ይታወሳል]::
ለ/ “ወርሐዊ መዋጮ” በማለት “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” የሚለውን ቅዱስ ቃል ለእሱ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሲጠቀምበት ይስተዋላል:: የቤተ ክርስቲያን አስራት በኩራት ይሰብሰብ አይሰብሰብ ለእሱ ምኑም አይደለም:: ዕጣኑ፣ ዘቢቡ፣ ሻማው፣ ጧፉ ..... ይለቅ አይለቅ አይመለከተውም ወርኃዊ ክፍያው ካልተከፈለች ግን መጨረሻ ላይ ቢሆን አይለቅህም:: ሞኞችን የሚያታልልበትና ገንዘብ የሚሰበስብበት “የመመረቂያ መጽሔት” ስላለች ምስኪን ምዕመናንን በዚያ በማጥመድ ያስከፍላቸዋል:: ለመሆኑ መቅደም ያለበት ሰውየው ነው ወይንስ ገንዘቡ?
ሐ/ ሌላው ሳይቀር እንደ ምቀኛ ጎረቤት የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በሙሉ ወደ እሱ ለማድረግ የሚጥር .... የተማሪዎችን ጀሪካን ሳይቀር ከእነሱው ሰብስቦ[ሰኔ ላይ] ለእነሱው ይሸጣል [መስከረም ላይ]::
መ/ የኮርስ ወረቀት ኮፒ፣ አርብን በአንድ ብር፣ የመጽሔት ዕጣ ..... በማለት ለእሱ ገንዘብ ለመሰብሰብ የማይወርደው ቁልቁለት የማይወጣው ዳገት የለም:: ይህ ሁሉ ገንዘብ በራሷው ቅጽር ግቢ ውስጥ ሲሰበሰብ ግን ቤተክርስቲያኗ “የበይ ተመልካች” ነች::
ለዚህ ነው የገንዘብ ጥማት ያለበት፣ ስግብግብ የሆነ ድርጅት ስለሆነ ቅዱሳንን በስም እንጅ በግብር ስለማይመስላቸው ማህበረ እኩያን፣ የጨዋ ስብስብ የምንለው:: ቅዱሳን አበው ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን ለቤተ ክርስቲያን ሲያውሉ ድርጅቱ ደግሞ ለራሱ ያውላል:: ስለዚህ የዚህ መርዘኛ ድርጅትና የአበው ቅዱሳን ልዩነቱ እንደ ሰማይና መሬት እጅግ ሰፊ ነው::

የድርጅቱ ራዕይ:- “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ አገልግሎትና ኢኮኖሚያዊ አቅም ተጠናክሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ ወንጌል በመላው ዓለም ተስፋፍቶ በሃይማኖት ጽኑዓን የሆኑ ምእመናን በመላው ዓለም በዝተው ማየት፡፡” ይላል::
አሁን አሁን ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና መዳፈር ሲጀምር እኔ ለቤተ ክርስቲያን "የጀርባ አጥንት" ነኝ ማለት ጀምሯል:: ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ያህል ዘመን የተሻገረችው ድርጅቱ ስላለ ነውን ወይንስ የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጠበቃት ነው?
"እንዘ ቦ በክህደት ያወግዙ ካልአ" እንዲሉ አበው ድርጅቱ የሚያምነውንም በደንብ ሳያውቅ ሰው ላሳምን ብሎ ይንተፋተፋል:: ምዕመናንን ያስክዳል፣ በማያገባው ይገባና አንዲትን ጥምቀት ሁለት ሦስት ጊዜ ያስደግማል፣ ባለ ልጅ ሆነውም ዲቁና መስጠት ለእሱ አዲሱ አይደለም፣ አንድ ጊዜ በተክሊል ካገባ በኋላም በእነሱ ቤት ለመድገም ችግር የለባቸውም:: በአጠቃላይ የማይደገሙትን ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን[ምስጢረ ጥምቀትን፣ ምስጢረ ተክሊልን] እንዲደገሙ በማድረግ መነኮሳትንም ዳግመኛ እንዲመነኩሱ ማድረጉ የማይካድ ሀቅ ነው:: ድርጅቱ አልተረዳውም እንጅ የቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት ሳይሆን የጀርባ ቅንቀን ነው የሆነው::
ጭራሽ ዘመን ተሻጋሪ የሆነችዋን ቤተ ክርስቲያን "ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር" ይቺ ቤተ ክርስቲያን ምን ትሆን ነበር ባማስባል ቤተ ክርስቲያን ምንም ተስፋ እንደለላት አድርጎ የሚያስወራ ከንቱ ማህበረ ደናቁርት ነው:: የጨዋ ስብስብ ሆኖ እንጅ ቤተ ክርስቲያንስ በእነ ዲዮቅልጢያኖስ፣ በእነ ግራኝ፣ በእኔ ዮዲት ጉዲት የነበረው መከራ አልፋ ዛሬ ላለችበት ዘመን የደረሰችው በዚህ ክፉ መዘዘኛ ማኅበር[ድርጅት] እርዳታ ሳይሆን “የገሃነም ደጆች አይችሏትም” ተብሎ የተነገረላት ስንዱ እመቤት በመሆኗ አይደለምን? ወዳጄ ዝም ብለን በአንድ አቅጣጫ ብቻ እያየን የምንጓዝ ሰነፍ አይደለንምና የሚያመዛዝን፣ እውነቱን ከሀሰት፣ ጽድቁንም ከኃጢያት የምንለይበት አዕምሮ እግዚአብሔር አምላክ ስለቸረን ልንጠቀምበት ግድ ይለናልና ነው::
የምዕመናን ብዛትም እንኳንስ ሊጨምር ይቅርና በከፍተኛ ፍጥነት እያሽቆለቆለ ሄዷል:: ስለዚህ ድርጅቱ ከዓላማው ውጭ እየሄደ እንደሆነ እራሱ ምስክር ይሆናል ማለት ነው:: ስንቶችን ተሃድሶ፣ መናፍቅ እያለ ከቤቱ በማሳደድ ተስፋ ቢስ አድርጓቸዋል:: ችግር ቢኖርስ ክርስቶስ ያስተማረን ማስተማርን ነው ወይንስ መሳደብን፣ ትህትናን ነው ወይንስ ዘለፋን፣ መባረርን[መሰደድን] ነው ወይንስ ማባረርን[ማሳደድን]፣ መሞትን ነው ወይንስ መግደልን፣ አንድነትን ነው ወይንስ ዘረኝነትን፣ ፍርቅን ነው ወይንስ ጥላቻን? እናም ወገኔ ይህ መርዘኛ ድርጅት እንኳንስ ለቤተ ክርስቲያን ለመንግስትም ስጋት እንደሆነ ልታውቅ ይገባሃል::
ክፍል 2 ይቀጥላል .......
No comments:
Post a Comment