Sunday, October 14, 2018

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ ከበረ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ 

አምላክ

“ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ  ከበረ 

እንጅ

ፀረ ተዋሕዶ አይደለም”

ክፍል- አንድ
====================
ይድረስ ለአከማቸዉ ደሴ( በዲማ ስሙ አብርሃም ደሴ )
“ነጭ ዉሸትህን የምንፍቅናህ መደበቂያ አታድረገዉ”›››››››ብለህ ለለጠፍካት የሙት መንፈስ ለሚስተዋልባት የክሕደት ሀሳብ ማክሰሚያ ፡፡
============================
ነገሩ እንዲህ ነዉ ወዳጄ አከማቸዉ ሆይ! ይህ ማኅበራችሁ እናተን ከአጠመቀ በኋላ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር አብራችሁ እንዳትበሉ ፣ በእነሱ ቤተክርስቲያን እንዳስቀድሱ ፣ በእነሱ ካህናት እንዳትሳለሙ ፣ …..ሌላም ሌላም እያለ በልሙጥ ኅሊናችሁ ስለሚሰልባሁ እና ድጋሚ ሲያጠምቋችሁ በ7ቱ ሐብታተ መንፈስ ቅዱስ አንጻር ሰባቱን አጋንንት ስለምትቀበሉ ፤ እዉነትን አትመለከቱም ፡፡ እንበልና ማኅበሩ ሰዉ እየገደለ ቢሆን! አስቡ ቢሆን ነዉ ያልኩት ፤ ለምን ሰዉ ትገድላለህ? ብሎ ማኅበሩን የሚጠይቅ ሰዉ ሁሉ መናፍቅ ወይም ተሐድሶ ነዉ ብላችሁ እንድታምኑ አእምሯችሁ በዚህ ልክ የተቀረጸ ነዉ ፡፡ እኔ የምጠይቀዉ አሳረኛዉ ተሐድሶና መናፍቅ የእናተን የክሕደት ካባ መደበቂያ ሁኖ የሚቀጥል እስከመቼ ይሆን? ፡፡ ሁለተኛ የምትጠመቁ እናንተ ፣ አረማዊ የሚባለዉ ሌላዉ ፤ ሁለተኛ በማጥመቅ ጥምቀትን የምታድሱ እናንተ ተሐድሶ የሚባለዉ ሌላዉ……ብቻ ይህ የእናንተ መደበቂያ እስከመቼ እንዲቀጥል አላዉቅም ፡፡ ትዉልዱም ዓይን እያለዉ የማያይ ፤ ጆሮ እያለዉ የማይሰማ ሆነላችሁ እንደፈለጋችሁ ትጫወቱበታላችሁ ፡፡ ወደጠቀስካቸዉ ሀሳቦችህ እናምራ!!!



ብሂል አንድ
=======================
,“ብርሃኑ የአቡነ ማርቆስ የግብር ልጅና የቅብዓት እምነት አራማጆች ፀረ ተዋህዶ ከሆኑ ጥቂት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነዉ”›››››››››››››››››››››ብለህ ጽፈሃል ፤ “መጠኑ ለረድእ ከመ ሊቁ--የደቀ መዝሩ መጠን እንደመምህሩ ነዉ” እንዳለ ማቴ 10 ቁ 25 ፤ የአቡነ ማርቆስ ልጅ ብሆን በታደልኩ እንጅ ነበር ፡፡ ፤ በሚያዉቀዉም  በማያዉቀዉም ፤ በሚያምነዉም በማያምነዉም በሁሉም አፍ ገብተዉ “የፌስ ቡክ ቀለብ” ሁነዉ ፤ አምላካቸዉ ሰያሚያቸዉ ወልደ እግዚአብሔር ሕያዉ ወልደ ማርያም ሥግዉ በአይሁድ በአረማዉያን የጸራቢዉ ልጅ ፣ አጋንንትን በአጋንንት ስም ያወጣል ሌላም ሌላም እየተባለ እንደተሰደበዉ ፤ እሳቸዉም ብዙ የመንፈሰ ጽርፈት ዉርጅብኞች ሲዘንቡባቸዉ ማየት ምንኛ መታደል ነዉ! አይሆንልኝም እንጅ ክርስትናን ከአዉቀት ጋር ይዘዉ ከሚገኙ ቅዱስ አባት መወለድ ምንኛ መታደል ነበር! ዳሩ ግን እኔ ልጃቸዉ ልሆን ይቅርና ጫፋቸዉን እንኳን ለማየት የማልበቃ ከንቱ ፤ የሃይማኖቴ ጉዳይ ሲነሳ እና ሲሰደብ ስሰማ ግን እሳት የምሆን ነኝና ከእሳቸዉ ልጅነት የለኝም ፤ እንዲኖረኝ ግን እጅጉን አብዝቸ እመኛለሁ ፡፡

ሲቀጥል “ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ተዋህዶ ነዉ” መባሉ ትክክል አይደለም ፡፡ ምክንያቱም “ተቀብዐ” የሚለዉ ምሥጢር መነሻዉና መሠረታዊ ሀሳቡ “ተሰብአ” ነዉና ፡፡ “ተሰብአ” ከሌለ እኮ ከበረ ማለት የለም ፡ ለምን ያልን እንደሆነ “ተቀብዐ” ስንል ማን ተቀባ?የሚል ጥያቄ ይነሳል ፤ መልሱም አምላክ ተቀባ ይሆናል ፤ ይህም  እንዴ አምላክ ምን ጎድሎበት ከበረ ይባላላ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል ፤ መልሱም አዎ አምላክስ ክቡር ነዉና ከበረ አይባልም ዳሩ ግን “ክብር የሚሻ ሥጋን ተዋሕዶ ክብር መሻትን ገንዘቡ ስላደረገ በሥጋዉ በቅብዓት ከበረ ተቀባ” የሚል ይሆናል በቅብዓት ከበረ ማለት ምን ማለትስ ነው? ቢሉ ፤ ቃል ከሥጋ ሥጋ ከቃል ጋር በተዋሐደ ጊዜ ቃል በሥጋ ርስት የባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ ፣ በንሥአተ መንፈስ ቅዱስ ፣ በኅድረተ መንፈስ ቅዱስ ፣ ከበረ ማለት ነው ፡፡ “ወቅብዓቱሰ ዘተወክፋ በትስብእቱ ይእቲ” እንዲል ትርጓሜ ወንጌል ፤ “ወዘሰ ኃደረ ላዕሌሁ መንፈስ ቅዱስ በእንተ ሥርዓተ ትስብእት ውእቱ ወእመ አኮሰ እፎ ይትበሀል ከመዝ እስመ መንፈስ ቅዱስ ዘዚአሁ ውእቱ በህላዌ መለኮት ዘከመ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር--መንፈስ ቅዱስ ተሰጠው (ገንዘቡ ሆነ ፣ በእሱ ላይ አደረ) መባሉ ቃል ሰው ስለሆነ ነው ፤ በሰውነቱ ባይሆን ኖሮ(ሰውማ ባይሆን ኖሮ) እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ህልው ነውና መንፈስ ቅዱስ በባሕርየ መለኮቱ ገንዘቡ ሲሆን እንደምን ተሰጠው ይባላል?” እንዳለ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ በሃይ.አበው ምዕ 87 ክ 9 t  18 ቄርሎስም “ወበአምጣነ ንዴተ ትስብእት ዘነሥአ ይትበሀል ከመ ውእቱ ተሰብሐ እምአብ--የተዋሐደው ሥጋ ክብር የሚሻ እንደመሆኑ መጠን ከአብ ክብርን ገንዘብ አደረገ ይባላል” ብሏል በሃይ.አበው ምዕ  79 ክ 50 t 75 ፤ አክሎም “ነሥአ ስብሐተ ወመንግሥተ ወሥልጣነ ላዕለ ኩሉ ነሢእሰ ይትበሃል በእንተ ዓቅመ ትስብእት--ይህም ጌትነትን ፣ መንግሥትን ፣ በሁሉ ላይ ሥልጣንን እንዳደረገ ተነገረ ፤ ክብርን ገንዘብ አደረገ መባሉ ሰው በመሆኑ ነው” ብሏል ፡፡ ስለዚህ ለሞተ መነሻዉ ሰዉ ሆነ ማለት እንደሆነ ሁሉ ፤ ለተቀብዐ መነሻዉ ተሰብአ ነዉና ብርሃኑ ሻምበል ፀረ ተዋሕዶ  ሳይሆን ፀረ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ ከበረ ነዉ ፡፡
ምነዉ ወልድ ቅብዕ በተዋሕዶ ከበረን ለምን ይቃወማል?የሚል ቢኖር ፤ በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ የሚሉ መናፍቃን ቃል ከሥጋ ሥጋም ከቃል ጋር በተዋሐደ ጊዜ ከበረ እንጅ ቅብዐተ መንፈስ ቅዱስን አይሻውም ተዋሕዶው በቃው ይላሉ ፡፡ እንደዚህም ማለት ወልድን ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ መለየት ነውና ክሕደት እርምና ነው ፡፡ በዚያውም ላይ በተዋሕዶ ከበረ ማለት ዐራት ኒፋቄያት አሉበት ፡፡ እነርሱም፡-2አካል ማድረግ(ምንታዌ) ፣ ውላጤ ፣ ተድኅሮ ፣ ጥገኛ 4ቱ ኒፋቄያት እነዚህ ናቸው ፡፡
1 . በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ምንታዌን ስለማስከተሉ
ሁለት አካል ማድረግ እንዴት ነው?ቢሉ፤ በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት አካለ ሥጋን አካለ ቃ አከበረው ክብር ሆነው ማለት ነው ፤ አንዱ ወልድ መንፈቁ አክባሪ ፤ መንፈቁ ከባሪ ከሆነ እንደ ልዮን ግብር መለየትን ያመጣል ፤ ግብር ከተለየም አካልና ባሕርይ አይቀርም ፤ ስለዚህም በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ እንደ ንስጥሮስ ፣ እንደ ልዮን ሁለት ፣ አካል ሁለት ባሕርይ አሰኝቶ ምንታዌ የሚያስከትል ነው ፡፡ “ወተሣየጦሙ እግዚአ ይክሕዱ እስመ ¡ክልኤ ወልደ ያስተርእዩ ለነ እለ ኢይርዩ ህላዌ ወበስብሐተ መለኮት ይኬልልዎ ለገብር ወኢይዔሪ ምስሌሁ ክብረ ወዘኢኮነ በአማን ወልደ” እንዳለ ቄር ስጣዌ 43 ፡፡


2. በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ውላጤን ስለማስከተሉ
ውላጤ እንዴት ነው?ቢሉ፤ ሥጋ በርስቱ በተዋሕዶ ከበረ ካሉ ተዋሕዶ አገናዛቢ ነውና ቃልንም በርስቱ ፍጡር ማለት ይሆናል ፡፡ በተዋሕዶ ሥጋ በርስቱ ወልደ አብ ከሆነ ቃልም በርስቱ ወልደ ማርያም ይሆናል ፡፡ ዳግመኛም ሥጋን በርስቱ አካለ ቃል በተዋሕዶ አከበረው ክብር ሆነው ማለት አካለ ቃን አባት ፣ አብን አባት አያት ሥጋን በርስቱ ለአብ የልጅ ልጅ ማድረግ ነው ፤ ይህም ሥላሴን በባሕርያቸውም በግብራቸውም ውላጤ አለባቸው ያሰኛል ፡፡ ማለትም ወልድ የተለየ ግብሩን ተወላዲነቱን ትቶ የአብን ግብር ወላዲነትን የመንፈስ ቅዱስን ግብር ሕይወትነትን ቀምቶ እንደ አብ ወላዲ ፤ እንደ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሆነ ማለት ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የወለደው አከበረው ይላል “ከማሁ ክርስቶስ አኮ ዘወደሰ(ዘንዕደ) ርእሶ ከመ ይኩን ሊቀ ካህናት--እንዲሁ ክርስቶስ ሊቀ ካህን ይሆን ዘንድ ራሱን ያከበረ አይደለም ፤ ዳዕሙ ለሊሁ አክበሬ ዘይቤሎ ወልድየ አንተ ወአነ ዮም ወለድኩከ--አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድኩህ ያለው እሱ አከበረው እንጅ” እንዳለ ጳው ዕብ ምዕ 5 t 5 ፡፡
3. በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ተድኅሮን ስለማምጣቱ
     ተድኅሮ እንዴት ነው?ቢሉ ፤ ሥጋን በርስቱ በተዋሕዶ ከበረ ካሉ በቃል ርስት እምቅድመ ዓለም አልነበረም ዓመተ ምህረትን እንጅ ዓመተ ዓለምን አልገዛም ማለት ተውና ተድኅሮን ያመጣል ፡፡
4. በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ጥገኝነትን ስለማምጣቱ
በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ማለት ጥገኝነትን ያመጣል ማለት እንዴት ነው?ቢሉ ፤ ሥጋን በርስቱ በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ ካሉ ፤ ድኃ ከባዕለ ጸጋ ጥቂት ከብት ተቀብሎ እንዲኖር ፤ እንዲሁ አካለ ሥጋ ከአካለ ቃል ጥቂት ክብር ተቀብሎ ከበረ ፤ አካ ሥጋን ድኃ አካለ ቃልን ባዕለ ጸጋ ያሰኛል ፡፡ ይህም ማለት ሥጋን ለቃል ዜገኛ ማድረግ ነው ፡፡ “ወለምንት ይፈልጡ ወይሬስዩ ለአሐዱ ዘይሁብ ሥልጣነ ወስብሐተ ወይሬስዩ ለካልዕ ዘተውህቦ ሥልጣን ወበጸጋ ረባሕ ዘኮነ ወጥዩቅሰ የሐፅፅ እምዘይሁብ ዘይነሥእ ወይከብር እምዘይሁብ ክብረ” እንዳለ ቄርሎስ ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለት 4ት ኑፋቄያት አሉበት ክሕደት ነው ማለት ስለዚህ ነው ፡፡
ስለዚህ መጻሕፍት የመሠከሩት ፣ ሊቃውንት የተናገሩት ፣ መተርጕማን የተረጐሙት ሃይማኖት ወልደእ ግዚአብሔር ሕያው ወልደ ማርያም ሥግው ስለከዊነ ትስብእት በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የባሕርይ ልጅ የባሕርይ አምላክ ሆነ የሚለዉ ስለሆነ ብርሃኑም የአባቹ ልጅ  ነዉና ፀረ ወልድ ቅብዕ ነዉ እንጅ ፀረ ተዋሕዶ አይደለም ፡፡ 
ብሂል ሁለት
=========================
“……ይህ አነጋገር መልአከ ብርሃ አድማሱ ጀንበሬን  ያለ ማወቅ ዉጤትና  ዛረተም እኛ ቅብዓትን እየተከተልን እናንተም በተዋሕዶ ከበረን እየተከተላችሁ አብረን እንኑር አይነት ጥያቄ ነዉ” ተቻችሎ መኖር  ለሃይማኖት አይቻልም”››››>>>>>>>›››ይህ አስተሳሰብ አእዕምሮዉም ልቡናዉም መላ አካሉ ካተገዘረ ፤ ሀሳም የጠበበ እና ከሙታንም ያልተሻለ ዓይነት ሰዉ የሚያስበዉ ዉዱቅ ሀሳብ ነዉ ፡፡ ምክንያቱም መጻሕፍት “ቢቻላችሁስ ከሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ” የሚሉት ቃል ለሃይማኖት አይሰራም ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን መቃወም ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የክሕደት ጦርነት ማወጅ ነዉና ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ በእምነታቸዉ ጥንተ አብሶን የሚያምኑ እንደሆኑ “መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ ማለት ትስብእትን ከአዳም መርገም አንጽቶ ቀድሶ ለተዋሕዶተ መለኮት የበቃ አደረገዉ ማለት ነዉ” መቅድመ መድሎተ አሚን ገጽ 16 ብለዉ በተናሩት ቃላቸዉ የማዉቃቸዉ ሲሆን ፤ “….ሦስቱም ወገኖች ከካቶሊክ ጋር አንድ አካል ፤ ሁለት አካል ፤ ሁለት ባሕርይ ፤ መንፈስ ቅዱስ ከወልድ ሠረፀ በማለት የሚተባበር የለም ፡፡ እርስ በእርሳቸዉም ሲከራከሩ ይህማ እንደንስጥስ ሁለት አካል ፤ እንደ ልዮን ሁለት ባሕርይ ያሰኝብሃል እየተባባሉ ሁሉም በየበኩላቸዉ  የንስጥሮስንና የልዮንን ተቃራኒዎች መሆናቸዉን ይልጻሉ እንጅ ከዉስጣቸዉ የልዮንን ባህል የሚደግፍ  አይገኝም ፡፡ ስለዚህ አንድ ሁነዉ ራሱን ከሚቃወሙት ከሦስት ወንድማማቾች መካከል በማያገባዉ ጥልቅ ብሎ ገብቶ …….ወንድማማቾችን በከንቱ ዉዳሴ ለያይቶ ረዳትና ወገን ለማግኘት መሞከር አለያይተህ ግዛ የሚለዉን ፖለቲካ የመሰለዉን ሰብቅ ነዉ” መድሎተ አሚን ፤ገጽ 283-84 በማለት የኦርቶዶክሳዉያንን ወንድማማችነትና ተቻችሎ መኖርን የሰበኩ መሆናቸዉን ፤ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መብት ተሟጋች እደነበሩ በደንብ አድርጌ አዉቃቸዋለሁ ፡፡

ይሁን እንጅ እሳቸዉ “በተዋሕዶ ከበረ ወልድ ቅብዕ” የሚል ጽንፍንም የሚደግፉ መሆናቸዉን ኰኵሕ ሃይማኖት በተባለ መጽሐፋቸዉ ላይ ጠቅሰዋል ፡፡ በተዋሕዶ ከበረ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግን አብራርተዉ የተናገሩበት ፤ ከመጻሕፍት ኃይለ ቃል ጠቅሰዉ ያስረዱት ነገር ሳይኖር “በተዋሕዶ ከበረ እናምናለን” ብለዉ ጻፉ እንጅ ፡፡ የዛሬዎቹ የለያይተህ ግዛዉ ርጉማን ግን ምሥራቅ ጎጃምን ቅብዐት ተዋሕዶ ብላችሁ ለሁለት ከፋፍላችሁ “ቅብዓቶች አረማዉያን” “ተዋሕዶዎች ጻድቃን” እያላችሁ ምንም የማያዉቅ ምእመን ስታሰቃዩ ትገኛላችሁ ፡፡ በተለይ ድጋሚ የተጠመቃችሁ አረማዉያንእማ ይህ ተልዕኮ በመድፌ የተሰጣችሁ እስከሚመስል ድረስ ወንድማማች የሆነዉን ደግ ሕዝብ ለመበታተን ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥታችሁ ትሠራላችሁ ፡፡ ስለዚህ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ በትጋታቸዉና በስነ ምግባራቸዉ ከእናንተ እጅግ ይሻላሉ በሃይማኖት ግን ያዉ ምንታዌ ስለሆነ ምንም ልዩነት የላችሁም ፡፡ እኔም እሳቸዉን መጥቀሴ ስለትጋታቸዉና ስለ አብሮነታቸዉ እንጅ ስለሃይማኖታቸዉ አይደለም ፡፡
ስብሐት ለአንዱ አምላክ
ለቅድስት ድንግል
 ወለመስቀሉ ክቡር
ይቀጥላል ፡፡





No comments:

Post a Comment