በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!!
ሃይማኖት መሢሐዊት ክፍል ሁለት
በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ዉሉደ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዉያን የተሰኛችሁ
ማኅበረ መሢሐውያን እንደምን ሰነበታችሁ እንደምን አላችሁ እንደምንስ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ደረሳችሁ?አሜን እግዚአብሔር ይመሥገን
ብለን ስሙን በኃጢአተኛ አንደበታችን እድንጠራው የወደደና የፈቀደ ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት አንደበት ሁሉ
ስሙ ከአጽናፈ ዓለም እስከ ዓጽናፈ ዓለም ፣ ከአድማስ እስከ አድማስ ፣ ከበርባሮስ እስከ ጽርሐ አርዓያም ድረስ የተመሰገነ ይሁን ፡፡ እሱን ጠርተን እሷን የማንተዋት የንጽኅናችን
መሠረት የጽድቃችን አክሊል ፤ በካሮቹ ዘንድ ያለ ስማችን ስም የተሰጠንባት (ተቀባት ይላሉ እያሉ የሚናሩባት) አምላክን በድንግልና
ጸንሳ በድንግልና የወለደች መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ የሆነች ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሐን ክብርት ድንግል ማርያም አምላክ
በሰጣት ክብር መጠን የተመሠገነች ትሁንልን ፡፡ ጻድቃን ሰማዕታት ፣ ደናግል
መነኮሳት ፣ ነቢያት ሐዋርያት ፣ ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔር አምላክ በሰጣቸው ጸጋ መጠን የተመሰገኑ ይሁኑ ፡፡
የዛሬው መልእክት ሳይማሩ አስተማሪ ነን እያሉ የሚናገሩ “የግቢ ጉባዔ” መደዴዎች ለአእምሯቸው እና ለልቡናቸው ያልተረዱትን እኛ እደተሳሳትን አድርገው የሚናገሯቸውን ጉዳዮች በማንሳት ኦርቶዶክሳዊት መልስን መስጠት ይሆናል ፡፡ በጥሙና ተከታተሉኝ ፡፡