Friday, November 30, 2018

ይድረስ:- በስምህ መጠራት ላፈርከው “ጎጃም ደብረ ማርቆስ” ተብለህ በሀገር ስም ለተሰየምከው ግለሰብ


ብሂል ፩............................ "በእዉነት ማሕበረ ቅዱሳን ማህበረ ሰይጣን ነዉን? " አዎ ነው:: ለምን ቢባል የተወሰነውን ግብሩን በሁለት ክፍል አድርጌ “ስም ሰጥተው ግብር ነሱት” በሚል ርዕስ ስለለጠፍኩልህ ደግመህ ሁለቱንም ክፍል ገለልተኛ ሆነህ አንብበውና ትረዳዋለህ::
ብሂል ፪............................ “ለመሆኑ ይህንን ሁሉ የፍልስፍና ወሬህን ትናገር ዘንድ ምን አነሳሳህ?”............... እንዲህ እናገር ዘንድ የገፋፋኝማ:-
ሀ/ ድርጅቱ[ማቅ] በክርስቶስ ደም የተመሰረተችዋ ኩላዊት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በዘር፣ በቀለም፣ በጎሳ ከፍሎ የዘረኝነትን መርዝ ሲዘራ በማየቴ፣
ለ/ እናቱንና አባቱን የማያከብር ጎረምሳ ሕግ እየጣሰ፣ ሥርዓት እያፋለሰ፣ ሃይማኖት እያጣረሰ፣ ውሸት እያናፈሰ በማየቴ፣ 
ሐ/ ከውሻ ጋር ታግለው ቁራሽ ለምነው ፊደል ቆጠረው ከዲቁና እስከ ጵጵስና የደረሱትን የቤተ ክርስቲያን እንቁ ልጆች ቦታ በመንጠቅ ሳምንት፣ ሁለት ሳምንት በመመላለስ ሁሉን አወቅሁ፣ ሁሉን ደረስኩ በማለት የድርጅቱ አባላት የማይገባቸውን ቦታ ሲይዙ በማየቴ፣ 
መ/ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና በመዳፈርና ሙዳዬ ምጽዋቷ ባዶ ሲቀር በማየቴ፣
ሠ/ የማይደገሙ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲደገሙ ሲያደርግ በማየቴ፣ ዲያቆናትን፣ ካህናትን፣ ጳጳሳትን ሲያሳድድ በማየቴና ከዚህም በላይ መጥፎ መጥፎ ስራዎቹን በማየቴ ከክፉ ሥራው ይመለስ ዘንድ ባለማወቅም የድርጅቱ ተባባሪ የሚሆኑ ምዕመናንም መጥፉ ሥራውን ይረዱት ዘንድ በማህበራዊ ድረ ገጽ ለመልቀቅ ወሰንኩኝ::

ብሂል ፫. ........................... “አየዉህ ተመዘንክ ቀለህም ተገኘህ ".......... ልክ ነህ ሰው በጠላቱ ዘንድ ተመዝኖ መቼም ከብዶ አያውቅምና አይደንቅም:: ዳሩ ግን እውነት መቼም ቢሆን ደስ የምትለው ለእውነተኞች እንጅ ለሀሰተኞች አይደለምና አንተም የአስመሳዮችና የሀሰተኞች ተባባሪ በመሆንህና ለቤተ ክርስቲያን ልዕልና ደንታ ቢስ ስለሆንክ ነው እንዲህ ልትል የደፈርከው::
ብሂል ፬............................”ጭፍን የሆነ ጥላቻህ የቅናት ዉጤት እንደሆነ ያሳብቅብሃል ።ጥቅሙ እንደተነካበት ባለስልጣን ስትክለፈለፍ ታይተሃልና”...... ከድርጅቱም ሆነ ከግለሰብ እኔ ምንም አይነት ጭፍን ጥላቻ የለኝም ነገር ግን የሚሰራውን ሥራ በማየት ነው እንደ አንድ ክርስቲያን የሚመለከተኝን ሥራ እየሰራው ያለው::
ብሂል ፭............................ "እዉነቱን ሐሰት ብርሃኑን ጨለማ ለሚሉ ወዮላቸዉ ፣ ሒድ ይህንን ህዝብ "...ማየትን ታያላችሁ አታስተዉሉም መስመማትን ትሰማላችሁ አታደምጡም በላቸዉ ... " ኢሳ. .......... መጀመሪያ ጥቅሱ ለማን እንደሚነገር ጠንቅቀህ ካወቅኸው እራስህን አዙሮ ይወጋሃልና “ነጽር ወለቡ” ይልሃል መጽሐፍ::
ብሂል ፮........................... “ማርያምን አታንሱብኝ የሚል ታሪክ ነገር ጽፈሃል.........”..................... አሁንም እልሃለሁ እኔ በአይኔ ያየሁትንና፣ በጆሮየ የሰማሁትን ከነ ማረጋገጫው ከፊት ከኋላ ከቀኝ ከግራ በማየት ነውና እውነቱን እውነት ሀሰቱን ደግሞ ሀሰት በማለት ለክብር፣ ለዝና ፣ ለሥልጣን ስለማልሳሳና ማስመሰል፣ መሸፋፈን ደግሞ ስለማልወድ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በግልጽ ነውና ያስቀመጥኩልህ ከታሪኩ ላይ ለህግ ተቆርቋሪ ሆኖ “ማርያምን አታንሱብኝ[ማርያም የሚለውን ንባብ]” ያሉት አባት ምሳሌው ለእኛ ነው ፣ ያኛው ደግሞ “ማንቸልቸሌን እንጅ በዘቅዘቁን የት አየሁ ” እንዳለው ሰውዬ የአነባበቡን ህግና ስርዓት የማያውቀውና ዝም ብሎ የሚነገረውን የማይሰማው ብሎም ምዕመኑን በማሳመጽ ማርያምን አንወዳትም፣ እሷን ደግመህ እንዳትጠራት ነው ያለኝ ብሎ በጨዋ አስተሳሰብ በመምህሩ ላይ ያሳመጸው ደግሞ አሁን እንደዚያ ሰውየ ህግና ስርዓት ሳያውቅ በአባቶች ወንበር ላይ መቀመጥ የሚፈልገው፣ አባቶችን የሚያሳድደው የድርጅቱ[ማቅ] ምሳሌ ነው:: 
ብሂል ፯............................ “ዛሬም ማህበረ ቅዱሳን እንዲህ ነዉ እያሉ ያለ ስሙ ስም የሚሰጡ የሰፈር ወሬኞች አልጠፉም ።ጠዋት ማታ ጉድጓድ ይቆፍሩለታል ፤ወጥመድ ያዘጋጁለታል እሱ ግን ዛሬም ስራ ላይ ነዉ ።ትናንት ሲያሳድዱት የነበሩት ደንደስ መነፍቃን ዛሬ የሉም ፤ትናንት ክብሩን ዝቅ አድርገዉ ሲያጣጥሉት የነበሩት ዛሬ ወድቀዋል ።አዎ እርሱ ስራ ላይ ነዉ”............................. ላንተና ለመሰሎችህ የድርጅቱነት የሚያወሳ ከሆነ የሰፈር ወሬ ነው አይደል? ምናለ ዝም ብለህ የጋቱህን ከምትጋት ቆም ብለህ እየመረጥክ ብትበላ፣ አሰስ ከሰሱን፣ ኃጢያቱን፣ ክህደቱንም ሁሉ የምታግበሰብስ ግለሰብ ነህ እንዴ? ምናለ ከበራሪ ወረቀትና ከመጽሔት አለፍ ብለህ የቅዱሳን አበውንም መጽሐፍ ብትመለከት?
ሥራስ አዎ ዛሬም ስራ ላይ ነው ይታወቃል እንደለመደው የአባቶችን ገበና ይሰበስባል፣ ጥምቀትን እያስደገመ፣ አባቶችን እያሳደደ፣ ፖለቲካውን እያራመደ ይገኛልና አንተ ይህን መስራቱ ጽድቅ ነው ካልክ እራስህን ልትፈትሽ ይገባሃል!
ብሂል ፰............................ “የተዘጉ አብያተ ክርስትያናትን ያስከፍታል ፤የተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናትን ያሰራል ፤የደከሙ ገደማትን ያበረታል ፤የጠፉ ወገኖቹን ይሰበስባል ፤ስብከተ ወንጌልና አብነት ትምህርት እንዲስፋፋ ያደርጋል ፤ ዘመኑን ዋጁት እንደ ተባለ ከዘመኑ ጋ እኩል እየተራመደ ቤተክርስትያንን ከተቃጣባት ጥፋት ይታደጋል ፤መናፍቃንና ሐራጥቃዎችን ያጋልጣል ፤መግቢያ መዉጫቸዉን ያሳጣቸዋል ።”...................................... የሚከተሉትን ሲያደርግስ ላንተ አይታይህምን?
ሀ/ የቤተ ክርስቲያንን አባቶችን በእህቶች እንዲፈተኑ ማድረጉ[ለጽድቅ እንቅፋት መሆን]
ለ/ የቤተ ክርስቲያንን ሙዳዬ ምፅዋት ባዶ እያስቀረ የእሱን ካዘና ለመሙላት ደፋ ቀና ማለቱ[ገንዘብ ወዳድነቱ]
ሐ/ የቤተ ክርስቲያን አስራት በኩራት ይሰብሰብም አይሰብሰብም ለእሱ ምንም አይጨንቀውም የእሱ ግን ካልተሰበሰበች ከአገልግሎት ሁሉ እስከ ማገድ መድረሱ[መጽሔት ለማሰራት እንኳ ከ፩ኛ ዓመት ጀምሮ እያንዳንዷን ክፍያ ያስተፋኃል]
መ/ ከላይ ከላይ መንፈሳዊ ሲሆን ውስጡ ግን ሰይጣናው ሥራ መስራቱ፣ ድንግልና ሥጋ ሳይኖራቸው ዲቁና ማሰጠቱ፣ አንዲት ጥምቀትን እንድትደገም ማድረጉ፣ 
ሠ/ አንድ ሰው ከእርምና ወደ ክርስትና ሲመጣ ቢያንስ እስከ ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ትምህርተ ክርስትናንና ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን መማር እንዳለበት መጽሐፍት ይናገራሉ እነሱ ግን በ2፣ በ3 ቀን ሥብከት ዝም ብሎ ምንም ያልተረዳውን ህዝብ ነጠላ እያለበሱ ለቁጥር መሞያ ያደርጋሉ፣ ዘላቂ ህይወቱ አያስጨንቃቸውምን?
በግቢ ጉባኤስ የሚደረገው ሥርዓት አልበኝነት፣ ህገ ቤተ ክርስቲያንን መደፋፈር ከየት የመጣ ነው?
ረ/ በማያገባው መግባቱ፣ ሥራህ ይህ ነው ተብሎ ተሰጥቶ እያለ ሁሉንም ካላየሁ ካልደረስኩ የሚል የጨዋ ስብስብ መሆኑ፣ 
ሰ/ ለይስሙላ ጠረፍ ድረስ ቢሄድ እንኳ የማህሉን ቤተ ክርስቲያን እያተራመሰ መሆኑንና ለፕሮቴስታንት በር ከፋች መሆኑን ልትረዳ ይገባሃል፣ 
ሸ/ እራስ ወዳድ መሆኑ፣ አንድ ሰው ማህበሩ ያለውን የማይቀበል ከሆነ ተሃድሦ፣ መናፍቅ ብሎ ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጣ መንገድ ማመቻቸት
ቀ/ ሁለ ነገሩ እንደ መንፈሳዊ ሳይሆን እንደ ዓለማዊ[ሰይጣናዊ መሆኑ]፣ ሰውን ሲያጠና በድብቅ፣ ደግሞ የሰውን ኃጢያት እየሰበሰበ እንደ ዲያብሎስ ይጽፋል ግሩም ነው [ሐራ ተዋህዶን ማየት ትችላላችሁ ብፁዓን አባቶችን እንዴት እንደሚያብጠለጥላቸው]
በ/ ዘረኛ መሆኑ [ማህበረ ሸዋ] ለሌላው ምንም ደንታ ቢስ መሆኑና ምስራቅ ጎጃሞችን ለብቻ ማጥመዱ
ተ/ የግቢ ጉባኤውን ዳቦ ለቤተ ክርስቲያን ነው ብሎ እየሰበሰበ ለስራ አስፈጻሚዎች ቀለበት መግዣ ማረጉ[ደ/ማርቆስ ግቢ ጉባኤ]
ቸ/ እውነት እሱ መንፈሳዊ ሥራ ቢሰራ ኖሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምዕመናን ብዛት ከ50% በላይ የነበረው ወደ 43% አካባቢ ባልወረደም ነበር:: የድርጅቱ አባላትም ወደ ፖለቲካው ሳይሆን ወደ ገዳም መንነው በሄዱ ነበር::
ብሂል ፱............................ “አልሰሜን ግባ በለዉ አሉ -በሺዎች የሚቆጠሩ በጠረፋማዉ የአገራችን ክፍል የሚገኙ ኢ አማንያንን ወደ ቤተክርስትያን እንዳስገባ አታዉቅምን? በቤተክርስትን ጥላ ስር ተጠልለዉ የሚኖሩ የእናት ጡት ነካሾችን ሴራ በመበጣጠስ እኩይ ተግባራቸዉንም በማስረጃ በማጋለጥ ቤተክርስትያንን እና ህዝቦቿን መታደጉንስ አላየህምን? ምን እሱ ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠር የግቢ ጉባዬ ተማሪዎችን አስተምሮ እንዳስመረቀስ አልነገሩህምን? ምነዉ ዛሬ ጫጫታዉ በዛ?”................................. ወዳጄ መሀሉን ምድረ በዳ እያደረገ፣ ዘመናቸውን ሁሉ በጉባኤ ቤት አሳልፈው ቅኔ ቆጥረው፣ መጽሐፍ ተምረው ቤተ ክርስቲያኗ በወግ በማዕረግ የሾመቻቸውን አባቶች እያሳደደ ጠረፍ ድረስ ሂዶ ቢያሳምን በሰባራ እንስራ ውሃ እንደመቅዳት ያዘው ከላይ ስትጨምር ከታች ይፈሳልና! ሕገ ቤተ ክርስቲያንስ የሚያዝዘው በአንድ ቀን በሁለት ቀን ስብከት ነውን ከሌላ እምነት ወደ ቀጥተኛዋ እምነት የሚመለሰው ያ ሰው ወደ ቀደመ ግብሩ ላለመመለሱ ምን ዋስትና አለው፣ እውነት መሰረቱ ጽኑ ነውን የሚለውን ድርጅቱ ከግምት ውስጥ አስገብቶታልና ነው ወይንስ ነጠላ እየለመነ ቁጥር ለማብዛት ነው የሚሰበስበው?
ወዳጄ ቤተ ክርስቲያንስ ሰላም የነበራት ይህ ዘረኛና አሳዳጅ ድርጅት ከመመስረቱ በፊት ነበር:: የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመረቀ ብለሃል እውነት ነው ግን ፍሬውስ የት አለ? ብዙዎቹ መንፈሳዊነቱን ጥለው ከፖለቲካው ተቀላቅለዋል:: ድርጅቱ ባይኖርስ የማንማር ይመስልሃልን?
ብሂል ፲............................ “ የአባቶችንም ዉሳኔ ያስፈፅማል እንጅ ብቻዉን አይሰራም ።እርሱ አይከፋፍልም ።ለሺህዎች የተከፋፈለዉን የተለያየ የእምነት ድርጅት ወደ አንዲት ሐይማኖት ለማምጣት ጠንክሮ ይሰራል እንጅ”........................... “ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ” ይባል የለ እንኳን የአባቶችን ውሳኔ ሊያስፈጽም ይቅርና በገንዘብ እየደለለ፣ የግል ገመናቸውን በመሰብሰብ የኅሊና እስረኛ ባላደረገ ነበር:: ማሳደዱን፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ላይ ጣልቃ ባልገባም ነበር:: የተሰጠውን የመተዳደሪያ ደንብ ወደ ኋላ በመተው የራሱን አጀንዳ ከፍቶ መጓዙን ባቆመ ነበር::
ብሂል ፲፩............................ “እናንተ ምን ሰራችሁ? የትኛዉን የተቃጠለ ቤተክርስትያን አሰራችሁ? የትኛዉን ኢ አማኒ አሳመናችሁ? የትኛዉን ገዳምስ እረዳችሁ? ከእናቷ ሆድ ወጥታ እናቷን በእርግጫ እንደምትማታዉ የክብሪት እንጨት ሆናችሁ ከመተቸትና አቃቂር ከማዉጣት ዉጭ ሌላ ስራ የላችሁም?”...................... ወዳጄ ድርጅቱም እኮ አገዘ ቢባልም ከእኛ የለመነውን ነው የሰጠው ከየት አመጣው መሰለህ? ከየተማሪው አፍ እየቦጨቀ ቢያንስ እንዲህ ከፍ ያለ ችግር ሲከሰት ለይስሙላም ቢሆን ባይንቀሳቀስ ነበር የሚገርመኝ? ደግሞ ከእኛ ጋር ጥሉ በሌላ እንጅ በሙዳዬ ምጽዋትስ አንድ ነን ምን ትበላላችሁና ነው ከሙዳዬ ምጽዋት የምትለዩት? ከእናቷ ሆድ ወጥታ እናቷን በእርግጫ የሚለው የሚሰራው ለአንተና ለመሰሎችህ ነው ለምን ቢባል ቤተ ክርስቲያን አሳድጋ፣ አስተምራ የቤተ ክርስቲያን ቅንቀን የሆነ ድርጅት ስትገድፍ እንጅ እኛማ ዶግማና ቀኖና ይጠበቅ ባልን ላይ እንዲህ እንባል ዘንድ ምን ምክንያት አለህና?
ብሂል ፲፪............................ “ማህበረ ቅዱሳን የተቋቋመዉ በቅዱሳን ስም ነዉና የቅዱሳንን ስራ ይሰራል”........................................
ቅዱሳን አበው [ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል መነኮሳትና ሌሎችም የክርስቶስ ቤተሰቦች]
የሚከተለውን ሲያደርጉ:-
፩ኛ. ሃይማኖትን ከምንፍቅና፤ ክርስትናን ከእርምና፣ ጽድቅን ከኃጢያት፤ እውነትን ከሀሰት በመለየት ትክክለኛውን መንገድ አሳዩን::
፪ኛ. ፍቅር አንድነትን፣ የዋኃት ትዕግስትን አስተማሩን::
፫ኛ. ስለ ክርስቶስ ሲሉ አንገታቸውን ለስለት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት አሳልፈው ሰጡ:: "ሰማዕታት የዚህን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሡ፤ ደማቸውን ስለ ክርስቶስ ፍቅር አፈሰሱ፡፡" እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም
፬ኛ. “አፌ የሰውን ልጆች ግብር እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ቅዱሳን አበው እኛ ኃጢያተኞች ሆነን ሳለ በሌሎች ሰዎች ላይ እንፈርድ ዘንድ አይገባንም በማለት ያለቅሱ ነበር እንዲያውም ስለኃጢያተኛው ሰው ይጸልዩለትም ነበር::
፭ኛ. አበው የአገልግሎትን ምንነት የሚያውቁት በመማርና በማስተማር ብቻ ሳይሆን በተግባር ነበር:: ለአገልግሎታቸው አንዳችም ነገር ክፍያን አይጠይቁም ነበር እንዲያውም የራሳቸውን ገንዘብና ጉልበት ምጽዋት ያደርጉ ነበር::
ድርጅቱ[የጨዋው ስብስብ = ማኅበረ ሰይጣኑ] ግን
1ኛ. በተቃራኒው ምንፍቅናንና ሃይማኖትን፤ እርምናንና ክርስትናን፤ ኃጢያትንና ጽድቅን፤ ሀሰትንና እውነትን ቀላቅሎ አሳየን::
2ኛ. በእውነተኛ ፍቅር ፋንታ ከንቱ[ሰይጣናዊ፣ ጊዜያዊ፣ የማስመሰል] ፍቅርን ሰበከን:: አበው አንድነትን ሲሰብኩልን ድርጅቱ መለያየትን፣ ዘረኝነትን አስተማረን፤ አበው የዋኅትን፣ ትግስትን ሲያስተምሩን ድርጅቱ ጥላቻን፣ ከንቱ ውዳሴን፣ የማስመሰል ትህትናን[ከዜሮ በታች] ትህትናን አስተማረን::
3ኛ. ስለ ገንዘብ፣ ስለ ዝና፣ ስለ ሥልጣን ሲሉ እራሳቸውን አራቆቱ፣ በሥጋ ከብረው በነፍስ ተሰደዱ:: ለክብራቸው ሲሉ ሰው አሳደዱ፣ ክርስቲያኑን አረመኔ አደረጉ:: “....... ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች. 3፥18-20) እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ የማህበሩ አባላትም ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸውም በነውራቸው ነው፥ አሳባቸውም ምድራዊ ነው:: 
አብ የተከለኝ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ነኝ ይልና የሰይጣንን ስራ ይሰራል፣ 
በአካፋ ይወስድና በማንኪያ ይመልሳል፣
ንዑስ አገልጋይ ነኝ ይልና የጀርባ አጥንት ነኝ ይላል፣
መንፈሳዊ ይመስልና ፖለቲካውን ሲያናፍስ ይውላል፣
የቤተ ክርስቲያንን ሙዳዬ ምፅዋት ባዶ ያስደርግና የእሱን ካዘና ይሞላል::

4ኛ. ድርጅቱ ግን በአባቶች ላይ የሚያደርገው ዘማቻ መጀመሪያ የእሱን[የድርጅቱን] ዓላማ ያሳካ ዘንድ በፀባይ፣ በትህትና በለሰለሰ መንፈሳዊነት[በእግር በራሳቸው ገብቶ ለማሳመን ይሞክራል] ይጠይቃል፤ ነገር ግን ቀድመው የድርጅቱን መጥፎነት፣ እኩይ ተግባራት የማያውቁ ከሆነ በቶሎው ይታለሉና ውስጠ ምስጢሩን ሳያውቁ አብረው ይሮጣሉ:: የሚገርመው ነገር ቢኖር “ጉንዳን የክረምት ምግቧን በበጋ እንደምትሰበስብ” ሁሉ ድርጅቱም በተለያየ አጋጣሚ በፀባይ፣ በትህትና ብቻ ካሳመናቸው አባቶች ጋር ቢጣላ የኅሊና እስረኛ አድርጎ ለማስቀመጥ የግል ገመናቸውን ከልጅነታቸው ጀምሮ ይሰበስብና ያስቀምጣል:: ካልሆነም እንደ ዶክመንተሪ ፊልም[የጤና ምርመራ ይደረግልዎት ይልና] ባለቤቱ በማያውቁት[ባለቤቱ በየዋኃነት፣ ድርጅቱ በሰይጣንነት ዓላማ] መልኩ ይዘጋጅና መረጃው በስውር ይቀመጣል:: ከዚያ በኋላ አሁንም በገሀድ እንደምናየው አንድ ጊዜ ለድርጅቱ[ለማቅ] አንድ ጊዜ ደግሞ ለእውነት እየቆሙ በሕይወተ ሥጋ እያሉ የቁም እስረኛ ሆነው የተቀመጡ እጅግ ብዙ አባቶቻችን አሉ::
ሁለተኛው ደረጃ የመያዣ ዘዴ ደግሞ የሚተገበረው ይብዛም ይነስም ጥቅም በሚፈልጉ አባቶች ላይ ነው:: ይህ አይነቱ ዘዴ “እከከኝ ልከክልህ” አይነት ሆኖ ለጋራ ጥቅም አንዱ የአንዱን ችግር ለመሸፈን ደፋ ቀና የሚልበት መንገድ ነው:: ክርስትናው ከተረሳ ውሎ አድሯል ዳሩ ግን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” እንዲሉ መንፈሳዊ ኃላፊነትንም ለገንዘብ ማግኛ የሚጠቀሙበት ጥቂት አይደሉም::
በመሆኑም ይችም ውለታ ናትና በስውር መዝገብ ተይዛ ትቀመጣለች:: ከዚህ በኋላ በልቶ መሸሽ የሚባል ነገር በድርጅቱ ዘንድ አይሰራምና እያንዳንዱ ጳጳስ ይሁን ካህን፣ ዲያቆን ይሁን ጨዋ ምዕመን፣ መንፈሳዊም ሆነ ፖለቲከኛ በድርጅቱ ሳንባ ካልተነፈሰ መከራ ነው:: እያንዳንዷ እንቅስቃሴው ሁሉ በድርጅቱ ፍቃድ ይሆናል ሳይወድ በግድ ለጥቅም ብቻ ብሎ ከርቸሌ ይገባል::
ሦስተኛው[የመጨረሻ እንዳልለው ሌላም ስለሚኖር] ዘዴው ደግሞ አባቶች የድርጅቱን ዓላማ፣ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ፣ አጀማመሩንና አሁን ያለበትን ደረጃ አንድ በአንድ የሚያውቁ ስለሆነ ከዚህ ድርጅት ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መገናኘት ስለማይፈልጉና ክፉ ሥራውን ስለሚያወጡበት፣ እንደ ፈለገውም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስራውን በማን አለብኝነት ይሰራ ዘንድ ስለማይፈቅዱለት ማጥመድ ይጀምራል:: እንዲህ የሚያደርጉ አባቶች “እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር” የሚል አቋም የያዙና ለማን፣ እንዴት፣ የትና መቼ ማገልገል እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለሆኑና የድርጅቱን ስድ አደግነት የሚረዱ በመሆናቸውና “በጎቼን ጠብቁ” ብሎ መድኅን ዓለም ክርስቶስ የሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዘወትር ጠዋት ማታ ደፋ ቀና የሚሉ ናቸው::
እነዚህን እንቁ አባቶች ደግሞ በእያንዳንዷ እንቅስቃሴያቸው ላይ አሁንም መረጃ ይሰበስብና ድርጅቱ በሚፈልገው መልኩ እንዲዘጋጅ ይደረጋል:: መቁረጥ መቀጠል ሥራቸው ነውና ከስብከት ላይና ከመዝሙር ላይ “እንዲህ አሉ፣ እንዲህ ብለው ተናገሩ” በማለት ከፊትና ከኋላ ያለውን ኃይለ ቃል ያስቀሩና እነሱ የፈለጓትን ብቻ ለይተው በማውጣት ለየዋኃን ምዕመናን ይናገሩና ምዕመኑ ጥርጣሬ እንዲያድርበት፣ ከቤተ ክርስቲያን እንዲርቅ፣ ስለ ሃይማኖቱ እንዳይማር፣ ቅዳሴ እንዳያስቀድስ፣ ኪዳን እንዳያደርስ ጠባሳ ያሳድሩበታል::
በዚህ ምክንያት በእውነት ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ የሆኑ ምዕመናን “ለምን ሃይማኖታችን ተነካ” ይሉና የውስጡን ስውር አጀንዳ ሳይረዱ እንደ በግ የሚነዱ እጅግ ብዙ ናቸው:: እውነታው ግን እንደዚያ ያደረጓቸው አባት ስህተት ሰርተው ሳይሆን ከድርጅቱ ጋር ስላልተስማሙ ነው ዓላማው ያልገባው ምስኪኑ ምዕመን ግን በከንቱ ይደክማል::
በዚህ ምክንያት ያለ አንዳች ምክንያት ከሃገራቸው የተሰደዱ፣ ከየደብሩ የተባረሩ፣ መናፍቅ፣ ተሃድሶ የተባሉ በጣም ብዙ ናቸው::
ስለዚህ ይህ ድርጅት “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው ወይንስ “ማኅበረ ሰይጣን”?
5ኛ. ይህ ድርጅት ግን ዓላማው ሌላ ስለሆነ አገልግሎትን በተግባር ከቶ አያውቀውም:: ስለ ሃይማኖት ምንነት ሳያውቁና ሳይገነዘቡ ጠዋት ጠዋት ብቻ ለኪዳን የሚሄዱ ከሆነ እንደ ታላቅ ሰው በማየት የማይገባውን ክብር ይሰጥና[ከዜሮ በታች ትህትና]፣ የክፍላት ሰብሳቢ፣ የግቢ ጉባኤ ኃላፊ ማድረግ ሥርዓት እንዲጣስ፣ ሃይማኖት እንዲጣረስ በር ከፋች ማድረግ:: የድርጅቱ አባላት በተለይ ደግሞ ግቢ ጉባኤ ላይ “እዩኝ እዩኝ ” ባይ ስለሆኑ ሳይማሩ ለማስተማር መሞከር፣ ምንም ሳያውቁ እራሳቸውን እንደአዋቂ መቁጠር፣ በማያገባቸው መግባት፣ እኔ ካልሰራሁት እኔ ካላየሁት ማለት፣ ከንቱ ውዳሴ መስጠት/ መቀበል ኧረ ስንቱ ጉድ ተዘርዝሮ ያልቃል:: ቤተ ክርስቲያን ስለተመላለሰ ብቻ የቤተሰብ እናት አባት፣ ልጅ በማድረግ ይመድብና እናትና አባት ስልክ በመቀያየር ሌላ አጀንዳ ይዘረጋሉ፤ ልጆችም ይበተናሉ:: በዚያው እንደጠፉ የቀሩም አሉ:: ሰው መጀመሪያ ስለ ክርስትናው ሳያውቅ ስለ ማህበሩ[ድርጅቱ] እንዲያውቅ ማድረግ እና ሁሌም የድርጅቱ ጠበቃ እንዲሆን መጎትጎትና ሌሎችም አንድ መንፈሳዊ ነኝ ከሚል ማኅበር የማይጠበቁ መጥፎ ተግባራት ናቸው:: ይህ ሁሉ ችግር የተፈጠረውም የአገልግሎትን ምንነት ካለማወቅ የመጣ መዘዝ ነው:: ደግሞ የሚገርመው ከሰራተኛው ላይ የሚወስደው ገንዘብ ሳያንስ ከተማሪው ላይ የሚዘርፈው ገንዘብ ነው:: “በልጅ አመኻኝቶ ይበላል አንጉቶ ” እንደሚባለው እስኪሰበሰብ ድረስ ስሙ በቤተ ክርስቲያን ነው ከተሰበሰበ በኋላ ደግሞ የድርጅቱ ነው:: ከዚህ በላይ ዓለም ላይስ ምን ይሰራል?
የገንዘብ ምንጭ ከተማሪዎች:-
ሀ/ ከእለት ጉርሳቸው በመቀነስ ለቤተ ክርስቲያን [ለነፍሳቸው] ሰጠን እያሉ ድርጅቱ ለእራሱ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ያውለዋል:: [ደብረ ማርቆስ ግቢ ጉባኤን መመልከት በቂ ነው የቀለበት መግዣ ሲያደርጉትና 95 ሺህ ብር እንደመለሰ ይታወሳል]::
ለ/ “ወርሐዊ መዋጮ” በማለት “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” የሚለውን ቅዱስ ቃል ለእሱ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሲጠቀምበት ይስተዋላል:: የቤተ ክርስቲያን አስራት በኩራት ይሰብሰብ አይሰብሰብ ለእሱ ምኑም አይደለም:: ዕጣኑ፣ ዘቢቡ፣ ሻማው፣ ጧፉ ..... ይለቅ አይለቅ አይመለከተውም ወርኃዊ ክፍያው ካልተከፈለች ግን መጨረሻ ላይ ቢሆን አይለቅህም:: ሞኞችን የሚያታልልበትና ገንዘብ የሚሰበስብበት “የመመረቂያ መጽሔት” ስላለች ምስኪን ምዕመናንን በዚያ በማጥመድ ያስከፍላቸዋል:: ለመሆኑ መቅደም ያለበት ሰውየው ነው ወይንስ ገንዘቡ?
ሐ/ ሌላው ሳይቀር እንደ ምቀኛ ጎረቤት የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በሙሉ ወደ እሱ ለማድረግ የሚጥር .... የተማሪዎችን ጀሪካን ሳይቀር ከእነሱው ሰብስቦ[ሰኔ ላይ] ለእነሱው ይሸጣል [መስከረም ላይ]::
መ/ የኮርስ ወረቀት ኮፒ፣ አርብን በአንድ ብር፣ የመጽሔት ዕጣ ..... በማለት ለእሱ ገንዘብ ለመሰብሰብ የማይወርደው ቁልቁለት የማይወጣው ዳገት የለም:: ይህ ሁሉ ገንዘብ በራሷው ቅጽር ግቢ ውስጥ ሲሰበሰብ ግን ቤተክርስቲያኗ “የበይ ተመልካች” ነች::
ለዚህ ነው የገንዘብ ጥማት ያለበት፣ ስግብግብ የሆነ ድርጅት ስለሆነ ቅዱሳንን በስም እንጅ በግብር ስለማይመስላቸው ማህበረ እኩያን፣ የጨዋ ስብስብ የምንለው:: ቅዱሳን አበው ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውን ለቤተ ክርስቲያን ሲያውሉ ድርጅቱ ደግሞ ለራሱ ያውላል:: ስለዚህ የዚህ መርዘኛ ድርጅትና የአበው ቅዱሳን ልዩነቱ እንደ ሰማይና መሬት እጅግ ሰፊ ነው::
ታዲያ ይኼ ድርጅት የቅዱሳንን ሥራ ነው የሚሰራው ወይንስ የዲያብሎስን ስራ?
ሥብሐት ለሥሉስ ቅዱስ!
“እውነትን ግዛት አትሽጣትም” ምሳ ፳፫፥፳፫

No comments:

Post a Comment