![]() |
የቆጋ ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ከፊል ገጽታ |
ከእለታት አንድ ቀን የደረቤ አስተዳዳሪ የነበሩት ምንተግዜር ለአደን ግሜ/ጨሞ/ ወደ ተባለ በርሃ ይሄዳሉ፡፡ በአደን ላይ እያሉ አለምን ንቀው ምነና ላይ ያሉ ክፍለ ኪሮስ የተባሉ አባት ያገኛሉ፡፡ ባህታዊውም ሲሶ እነሴ ውስጥ በምስራቅና በምዕራብ የተከበበች ሸጥ ትገኛለች፡፡ መኖሪያህ ከዚያች ቦታ ይሆናልና ወደዚያች ሂድ፡፡ ቦታዋ በደረስክ ጊዜ እቃ ታገኛለህ፡፡ እቃውን በተገቢው ቦታ አስቀምጠው፡፡ አፅሜንም ወደዚያች ቦታ ወስደህ ያስቀመጥክልኝ እንደሆነ እስከ እለተ ምፃት ድረስ ቦታውን በእረዴት አልለየውም ብለውት ባህታዊው ከምንተግዜር ይሰወራሉ፡፡
ምንተግዜርም የባህታዊውን ትዕዛዝ ተቀብለው በባዛ አፋፍ ማጀኔ ጊዮርጊስ እንደደረሱ አፀደ ስላሴን አዩ፡፡ በአካባቢውም እንደሻሽ የነጡ ነገሮችን ሲያስተውሉ ነገሩን ቀርበው ቢያዩት መነኮሳት ሆነው አገኟቸዉ፡፡ ይኸ ቦታ ለእኔ የታዘዘልኝ አይደለም በማለት ሲሄዱ የአሁኑን የቆጋ አንድነት ገዳም የተመሰረተበትን ቦታ አገኙ፡፡ ትክክለኛዋ ማረፊያቸው መሆኗን አውቀው እንደተቀመጡ አባ ብረት ለበሱና አባ ፀጉር ልብሱ የተባሉ ሁለት ባህታውያን የኪዳነ ምህረትን ፅላት ዝግባ ከተባለ ዛፍ ስር ይዘው ያገኟቸዋል፡፡ መነኮሳቱም ፅላቱን ለምንተእግዜር አስረክበዋቸው ከአካባቢው ይሰወራሉ፡፡ ምንተግዜር በክርስትና ስማቸው አባ ወልደ ሃናም በ1524 የአሁንን የቆጋ አንድነት ገዳም መሰረቱት፡፡
በገዳሙ ወንድ ባህታውያን ብቻ የሚስተናገዱበት ለሴቶች የተከለከለ ገዳም ሲሆን የሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን የመሰረቱት ወለተ እስራኤል ከዚህ ህግ ጋር የተያያዘ ታሪክ አላቸው፡፡ ወለተ እስራኤል ከገዳሙ ፀበል ጠጥተው ልጅ በመውለዳቸው ለገዳሙ ስለት ለማስገባት ምንም እንኳን ሴት አይገባም ቢባልም ሱሪ ለብሰው ለመግባት ሲሞክሩ አለቅታሜ ወንዝ ላይ ዘንዶ አላሻግርም ይላቸዋል፡፡
ከዚህ በኋላም ወለተ እስራኤል ገዳሙን ማየት ባይታደሉም በአካባቢው ከተማ ለመመስረት አቅደው ከአባቶች ጋር ይወያያሉ፡፡ የገዳሙ አባቶችም በአካባቢው ከተማ መቆርቆር የገዳሙን ስርዓት ያበላሻል ብለው ወለተ እስራኤል ይቃወሟቸዋል፡፡ ወለተ እስራኤልም የአባቶችን ትዕዛዝ አክብረው አልፈው በመሄድ የአሁኗን ሞጣ ከተማ ይቆረቁራሉ፡፡ የጊዮርጊስን ቤተ-ክርስቲያን ሲመረቅም በወለተ እስራኤል ግብዣ ከቆጋ አንድነት ገዳም አባምኔት እንዲባርከው ተደርጓል፡፡
ለቡራኬ የሄዱት አበምኔትም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን ውስጥ አቡነ መፆረ ድንግል ይከሰቱላቸዋል፡፡ አባምኔቱም አቡነ መፆረ ድንግል የእኔንም ቦታ ጠብቅልኝ ይሏቸዋል፡፡ አቡነ መፆረ ድንግልም በገዳሙ ሰንበት ከተከበረ ፣ ሴት ካልገባ፣ባህታውያን ዘወትር ምሽት “በሀከ ጊዮርጊስ” ብለው ስሜን ከጠሩ እስከ እለተ ምፅዋት ድረስ ቦታዋን አልለያትም፡፡ ጠላትም እንዳይገባባት እጠብቃታለሁ ብለው ቃል ኪዳን ይገቡላቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በገዳሙ ሰንበት እየተከበረበት ፣ ሴት ሳይገባ፣ባህታውያን ዘወትር ምሽት “በሀከ ጊዮርጊስ” እያሉበት እስካሁን ዘልቋል፡፡
በዚህ ገዳም ውስጥ ልዩ ልዩ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን በመዳብ ላይ የተሳሉ የቅዱሣን ስዕሎች፣በአፄ ኃይለ ስላሴ የተበረከተ ከንሃስ የተሰራ ባለሁለት ጀሮ ብረት ድስት ፣ከንግስት ዘውዲቱ የተበረከተ ከነሀስ የተሰራ ጐላ ብረትድስት፣ በ1907 ከደጃች ባልቻ የተሰጠህ ከነሀስ የተሰራ ደወልና አነስተኛ ጐላ ብረት ድስት ይገኛሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በገዳሙ አለማዊ ሰዎች በጥንት ጊዜ ከጦርነት ለመሸሸግ ይጠቀሙባቸዉ የነበሩ ሦስት ዋሻዎች ይገኛሉ፡፡ ዋሻዎችም አገው ዋሻ ፣ቆጋ ዋሻ፣ ኢቶት ዋሻ ተብለው ይጠራሉ፡፡ በአሁ ወቅት ዋሻዎችም የገዳሙ ባህታዊን ሱባኤ ሲይዙ ይጠቀሙባቸዋል፡፡
“በገዳሙ ሰንበት እየተከበረበት ፣ ሴት ሳይገባ፣ባህታውያን ዘወትር ምሽት “በሀከ ጊዮርጊስ” እያሉበት እስካሁን ዘልቋል፡፡”
“በገዳሙ ሰንበት እየተከበረበት ፣ ሴት ሳይገባ፣ባህታውያን ዘወትር ምሽት “በሀከ ጊዮርጊስ” እያሉበት እስካሁን ዘልቋል፡፡”
በአጠቃላይ ቆጋ አድነት ገዳም አመሰራረት በውስጡ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶች ከብዙ በጥቂቱ ይኸን ያህል ካስቃኘናችሁ ገዳሙን ሂደው በመጐብኘት ቀሪውን እንዲያዩ በአክብሮት ጋብዘንወታል፡፡
ጥሩ ነው ነገርግን ያለበትን ቦታ ከሞጣና ከጉምደወይን ምን ያህል እርቀት ላይ እንዳለ ቢገለጽ ጥሩ ነው
ReplyDeleteበርታልን
ReplyDeleteበጣም ነው ዴስ የሚል በርታልን ወንድማችን
ReplyDeleteBetam tiru new
ReplyDeleteእግዚአብሔር ጥበቡን ማስተዋሉን እድሜውን ፀጋውን ያብዛልን
ReplyDelete