ሃይማኖት መሢሐዊት!!!!!!!!!
የካራ ልጅ በአፍ የጦጣ ልጅ በዛፍ የቅብዓት ልጅ በመጽሐፍ!!!!
=================+=================ወዳጃችን እኛ እኮ ትግላችን እንዲሁ አይደለም ፡፡ የካራ ልጅ በአፍ የቅብዓት ልጅ በመጽሐፍ ስንልም እኮ በአሉ ይባላል በተረት ተረት አይደለም ከዚህ በታች እንደምንመለከተው ባለ ዓይነት ሽንጣም መጽሐፍ ነው እንጅ ፡፡ ሲያምኑ ግማሽ ሲተረጉሙ ዳሽ ማለታችንም እኮ ወደን አይደለም እንዲህ ከዚህ በታች እንደምትመለከቱት ግእዙ ከአማርኛው የማይስማማ የተደናበረ ትርጓሜን እየተረጎሙ ጠፍተው የሚያጠፉ የክፉ ልጆችን ግብር በማስረጃ እያቀረብን እንጅ ፡፡ መተርጉማን የሚሏቸው ከንቱ ሰዎች እንዲህ እያወላገዱ ሲተረጉሙት ስንመለከት ሲተረጉሙ ዳሽ አልናቸው ፤ መድኅን ክርስቶስ በመቀባቱ ክርስቶስ የተባለበትን ምሥጢር ትተው አማኑኤል የተባለባትን (ይህችንም ቢሆን ለሊሁ ቀባዒ ወተቀባዒ ወለሊሁ ቅብዕ ብለው ሲደናበሩ ቢያጠፏትም) ብቻ አንጠልጥለው ሲጓዙ ስናያቸው እና አማኑኤል አምላካችን በሰውነቱ የፈጸማቸውን ድንቅ ድንቅ ነገሮችን ለእነሱ የተመቻቸውን ብቻ እየመራረጡ ሲናገሩ ስንሰማቸው ሲያምኑ ግማሽ አልናቸው ፡፡ ታዲያ እንደ አባቶቻቸውና እንደ አያቶቻቸው እንደ አይሁድና ጸሐፍት ፈሪሳውያን ልቡናቸው የደነዘዘ በመሆኑ አሁንም ቢሆን የተሳሳቱ አልመሰላቸውም ፤ መጽሐፉ ግን “በእንተ ቅብዓት ተሰምየ ክርስቶስ” ሲተረጎም ስለ ቅብዓት ክርስቶስ ተባለ ፡፡ “እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ በመንፈስ ቅዱስ” ክርስቶስ ማለት በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ የከበረ ማለት ነውና ይለናል ፡፡ በዘመኑ ትውልዱ ሁሉ ከልሳነ ግእዝ እልም ብሎ ስለራቀላቸው አፈ ቀላጤዎቹ “በእንተ ቅብዓት ተሰምየ ክርስቶስ” የሚለውን ሲተረጉሙ “ሥጋን ስለተዋሐደ ክርስቶስ ተባለ” ብለው የሌለ ፈጠራ የማይገናኝ ልብወለድን ይናገራሉ ፡፡ በግእዙ ላይ ሥጋ የሚል የለም ተዋሕዶም የሚል የለም እነሱ መጨማመር ልማዳቸው ነውና የጨማመሩት ነው ፡፡ ከዚያም በኋላ በምን ተቀባ ብለን ግራ እንዳይገባን “እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ
በመንፈስ ቅዱስ ብሂል(ክርስቶስ ማለት በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ የከበረ ማለት ነውና)” ብሎ ቁልጭ አድርጎ ነገረን ፡፡ እነዚህ የክፉ ልጆች ግን “ክርስቶስ ማለት በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት የከበረ የባሕርይ አምላክ ነውና” ብለው አሽመድምደውታል ፡፡ ቅብዓትን በደንብ ስለሚጾሟት ቅብዓትነት(ክብርነት) የሚለውን ሕይወትነት ብለው ለውጠውታል ፡፡ እነዚህ የሚሽመደመዱ የካራ ልጆች ምሥጢሩን ያመለጥን እየመሰላቸው ቢልወሰወሱ አያመልጡም ጆሮ ግንዳቸውን ሲላቸው ይኖራል እንጅ ፡፡ ምክንያት ክርስቶስ የሚለው የግሪክ ቃል ትርጉሙ በእብራይስጥ ማስያስ ፣ በአረም መሺሕ ፣ በግእዝ ቅቡዕ በአማርኛ የከበረ ንጉሥ ማለት ነውና “ሥጋን ስለተዋሐደ ክርስቶስ ተባለ ቢሉት” እውነትን ላለመቀበል የፈሪ ፍርጠጣ ናትና ጆሮ ግንዳቸውን ሲላቸው ይኖራል ፡፡
እናንት ካሮች እስኪ መልሱልኝ
…..በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት የከበረ የባሕርይ አምላክ ነውና ስትሉ ፤ ለምን ራሱን በራሱ ያዋሐደ አላላችሁትም?ነው ወይስ እናንተ ከተናገራችሁት ችግር የለውም?የባሕርይ አምላክ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስን አዋሐጅነት ለምን ፈለገ?????
No comments:
Post a Comment